FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Tuesday, September 17, 2013

መስከረም ሲጠባ አደይ ሲፈነዳ …

(ይድነቃቸው ከበደ - የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ኃላፊ)

meskerem


የዘመን መለወጫ ክብረ በዓል በየትኛውም አገር እንደ አገሩ ወግና ልማድ በድቅመት የሚከበር በዓል ነው፤ በእኛ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ደግሞ ልማድና ወጋቻን እጅግ ከመጠንከሩ የተነሳ ለአዲስ ዓመት ወይም ለዘመን መለወጫ ክብረ በዓል ዝግጅታችንም ሆነ አከባበራችን እጅግ በጣም ጠንካራና ደስ የሚል ነው፡፡
አዲስ ዓመት የሁሉ ነገር መጀመሪያ ነው ለዚህም ነው ብዙ እቅዶቻችን ከመስከረም ወር የሚጀምረው፤ ያቀድነው ነገር በዓመቱ መጨረሻ ሊሳካ ወይም ላይሳካ ይችል ይሆናል ቁም ነገሩ ግን በዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ለማሳካት የታሰበ እቅድ መኖሩ ነው፤ ለእቅዱ አለመሳካት ውጫዊና ውስጣዊ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ እነዚህን እንቅፋት የሆኑ ምክንያቶች ለይቶ ማወቅ በራሱ የእቀዱ አንድ አካል በማድረግ እንደገና ለመጪው አዲስ ዓመት ለተሻለ እቅድ ግባት ይሆናል፡፡
የዘንድሮ አዲስ ዓመት ከግለሰባዊ ፋይዳ በላይ አገራዊና ህዝባዊ የለውጥ ፋይዳ የበዛ እንደሚሆን ምልክቶቹ አብዝተው ይታያሉ፤ እነዚህ ምልክቶች ከባለፈው ዓመት ለዘንድሮዎ የተሸጋገሩ የለውጥ ምልክቶች ናቸው፤ በመሆኑም ለለውጥ የተነሳሳው ለውጥ ፈላጊ ለውጡኑ የሚያከሽፍበት አንዳችም ምክንያት ስለመኖሩ እጠራጠራለው ክሽፈት ቢያጋጥም እንኳን ወድቆ ለመነሳት ብዙ ጊዜ የሚባክን አይመስለኝም፡፡
መውደቅ መነሳት ከሚንቀሳቀስ ነገር የሚጠበቅ ክስት ነው መንቀሳቀስ ደግሞ በሀገር ውስጥና በውጪ በሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፣ ፖለቲከኞች፣ በሀይማኖት ተቋመት፣በሲቪክ ማህበራት እና በመሳሰሉት እንቅስቃሴው መሰልቸትና ድካም የማይታይበት ጠንካራ እንቅስቃሴ ነው፤ይህ እንቅስቃሴ ከባለፉት ወድቆ መነሳት እንቅስቃሴ ትምህርት የተቀሰመበት ስለመሆኑ ከምልክቶቹ መካከል አንዱ ነው፡፡
በአገራችን ለለውጥ የሚገፋፉ ብዙ ምክንያቶች መኖራቸው የሚታወቅ ቢሆንም ከብዙ ምክንያቶች በዋንኝነት ትኩረትን የሚስቡት የለውጡን አይቀሪነት አሳበቂ ምክንያቶች ከሆኑት ውስጥ፡-
1ኛ. በዓለም ላይ ካሉ ታላላቅ እምነቶች መካከል ክርስትና እና እስልምና ዋንኞቹ ናቸው፤እነዚህን እምነቶች በመቀበል እኛ ኢትዮጵያዊያን ከቀዳሚዎቹ መካከል እንገኛለን ክርስትናን እና እስልምና እምነትን መቀበላችን ብቻ ሣይሆን የተቀበልነው እምነት ህግና ሥርዓት አክብሮ በማስከበር ወደር አይገኝልንም፡፡ ይሁን እንጂ መንግስት በልማት ስም  የአምልኩ ቦታዎችን በመጋፋት ቤተ ክርስቲያንን ተዳፍሯል፤ ይህ ነገር ተገቢ አይደለም ያሉ የሃይማኖት አባቶች ተደብድበዋል፣ተገለዋል እንዲሁም ከአገር ተሰደዋል፡፡
መንግስት በሃይማኖት ሃይመኖት በመንግስት ጣልቃ አይገባም የሚለውን ህገ-መንግስታዊ ድንጋጌ መንግስት በመጣስ በሙስሊም እምነት ዘው ብሎ በመግባት የእመንቱን መሪዎች እስከመምረጥ ደረጃ ተደርሷል፤ ይህን አይቶ ዝም አለማለት እስላማዊ ግዴታ እንደመወጠት የቆጠሩ እንቢ ለእምነቴ ያሉ በእስር እና በስቃይ ላይ ይገኛሉ፡፡    በእነዚህ ታላላቅ እምነቶች መንግስት እጁን በማስገባት የፖለቲካ ዓላማ ማስፈፀሚያ ለማድረግ ያልፈነቀለው ድንጋይ ምን አለ? በተለይ በሙስሊሞች ላይ እተየፈፀመ ያለው በደል እና በእምነቱ ተከተዮች የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ላይ ያለጥፋታቸው በሐሰት በመወንጀል አሸባሪ ብሎ በእስር ማሰቃየቱ እጅን ጨብጦ ጥርሱን ነክሶ ያልተቆጨ ማነው ?
2ኛ. ኢትዮጵያ አገራችን የብዙ ሺህ ዓመት አኩሪ ታሪክ ያላት እና የተለያዩ –ን–ዎች የሚነገርባት ህዝቧ የቋንቋ ልዩነት ሣይገድበው አንዱ ከሌላው የተዋለደባት እጅግ ውብ እና ማራኪ –ን–፣ ባህል፣ ልምድ፣ ወግ፣ አለባበስ እና አመጋገብ ወዘተ….. የሚታይባት ድንቅ አገራችን ናት፡፡ ይሁን እንጂ የኢህአዴግ መንግስት ይህ ቦታ የናተ አይደለም በማለት ዜጎችን በማፈናቀል ሀብትና ንብረት በማውደም ጎጠኝነትና ዘረኝነት በማስፋፋት ላይ ይገኛል፤ እንዲህ አይነቱ አሳፋሪ ተግባር በአገራችን በአራቱም አቅጣጫ በዘመቻና በእቅድ በመንግስት የተፈፀመ ህገወጥ ተግባር ነው፡፡ በመሆኑም ከኢትዮጵያዊነት በላይ መንደረኝነት እንዲነግስ በመንግስት እየተደረገ ያለው ዘመቻ ያላስቆጨው፣ ያላንገበገበው ማነው? ይህን ቁጭቱን እና በደሉን ለመግለፅ ጊዜና አጋጣሚውን እየጠበቀ ያለው ስንቱ ነው?
እኛ ኢትዮጵያዊያን በእድሜና በውቀታቸው ከፍ ላሉ ሰዎች ያለን ከበሬታ እጅግ የላቀ ነው፤ ለዚህም ነው ለሽምግልና ጉዳይ ቶሎ እጅ የምንሰጠው በሽምግልና ካጣነው ነገር በላይ ያተረፍነው የበዛ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የቆየውና ጠቃሚ የሽምግልና ወገና ሥርዓት በመጠበቅ የአፋር፣ የኦሮሚያ፣ የጋምጎፋ (ቆጫ ወረዳ) እና የሲዳማ የአገር ሽማግሌዎች በአካባቢያቸው ለታየው አስተዳዳሪያዊ ችግር መፍትሔ ለመሻት ከታችኛው የአስተዳደር አካል እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያደረጉት ጥረት ውጤት አልባ ነበር፤ ከምንምንም በላይ የሽምግልና ክብር በመጋፋት መንግስት ጠቃሚ የሆነውን ወግና ሥርዓት ለመናድ የሄደበት መንገድ ሽማግሌዎችንና የተወከሉበትን ማህበረሰብ ምን ያህል ነው ያስከፋው?
3ኛ. ‹‹በኑሮ ውድነት የጎበጠው ትከሻችን እረፍት ይሻል›› ኑራችን አላምር ሲል መፈክራችን ማማሩ የሚገርም ነው! ይህ መፈክር ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ ባካሄደው የተቃውሞ ሠልፍ ከፍ ብሎ የተሰማ ጥያቄ ነው፤ እውነትም አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የኑሮ ውድነት ትከሻውን ከማስጉበጥ አልፎ ህይወቱን እየነጠቀወ ነው፡፡ ባለ ሁለት ሃአዝ እድገት በመንግስት ተደጋግሞ የሚነገር አስማታዊ እድገት ምግብም መጠጥም አልሆን ብሎ በመንግስት የሚነገረው እድገትና የምንኖረው ሕይወት ሆድና ጀርባ ሆኖ አልገጥም እያለ ተቸግረናል፡፡
የስራ አጥነት ቁጥሩ በጣም የበዛ ነው፣ሰራተኛም ሰርቶ የሚከፈለው ወራዊ ደሞዝ ወሩን ሙሉ የሚያቆይ አይደልም፣ በኑሮ ውድነቱ ምክንያት 2.5 ሚሊዩን ዜጎች ለጎዳና ተዳዳሪነት መዳረጋቸው የመንግስት መስሪያ ቤት የሆነው የማህበራዊ ዋስትና ድርጅት ባስጠናው ጥናት መሰረት ይፋ አድረጓል፤ ጎዳና ያልወጡ እቤታቸው ጎዳና የሆነባቸው ዜጎች ቤት ይቁጠራቸው፡፡
በመሆኑም እንዲህ አይነቱ ምስቅልቅል የበዛበት የኑሮ ውድነት ዋንኛው መንስሄ ብልሹ የመንግስት አስተዳደር ስለመሆኑ የእኛ መንገስትና ኑራችን ዋንኛ ማስረጃ ነው፤ ስለሆነም እንዲህ አይነቱ ብልሹ የመንግስት አስተዳደር አቅፎና ደግፎ ይዞ የሚሄድ ጉልበትም ሆነ አንጀት ከወዴት ይምጣ?
4ኛ. አሁን ያለው የአምባገነን ሥርዓት የተረጋጋና ጉልበት አልባ መሆኑ ሌላኛው የለውጡን አይቀሪነት አሳበቂ ምክንያት ነው፡፡ ከእሳቸው ሞት በፊት ይታይ የነበረው የአንድ ሰው ፈላጭ ቆራጭነት ከእሳቸው ሞት በኋላ የስርዓቱ ፊት አውራሪዎች ከመብዛታቸውም በላይ በቡድን የተከፈሉና እኛ እናተ መባባላቸው ከጥጋባቸው በላይ የስልጣን ጥማታቸውን የሚያሳይ ነው፤ ግን በሁለት ሆዳሞች መሃል እህል ይደፋል እንጂ ማንም አይበላውም፡፡
ሌላው የስርዓቱ የፊት ሰዎች ከውስጣዊ ሹኩቻ ባለፍ በአደባባይ አንዱ ለሌላው በሙስና እና በስልጣን መባለግ ስም ማሰርና መክሰስ ሌላኛው አገር ጥሎ መሄድ መሳ ለመሳ እየተካሄደ ያለ ውስጣዊ ሹኩቻ ነው፤ በእንዲህ መልኩ በውስጥ የተወጠረው የአባገነን ስርዓት በተጠናከረ እና ሠላማዊ በሆነ ህዝባዊ ግፊት ፈንድቶ ውስጣዊ ሰንኮፉ የማይነቀልበት ምክንያት ምንድነው?
5ኛ. ሐሳብን በነጻ የመያዝና የመግለጽ እንዲሁም የመደራጀት መብት ዓለም አቀፍ  እንዲሁም ሕገ መንግስታዊ መብት ነው፡፡ በመሆኑም አንዱአለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን፣ በቀለ ገራባ፣ ኦልባና ለሊሳ እና ሌሎችም የፖለቲካ እስረኞች እንደማንም ኢትዮጵያዊ የራሳቸው ኑሮ እና ህይወት ያላቸው ናቸው፤ ይሁን እንጂ ነፃነት እና ፍትህ ለነሱ ሁለተኛ ጉዳይ አይደለም የመጀመሪያ ጥያቄያቸው ነው! ከራስ ወዳድነት አልፈው ይህ ጥያቄ የኛ ብቻ ሣይሆን የኢትዮጵያዊያን ጥያቄ ነው በማለት በአደባባይ ስለነፃነት እና ፍትህ የዘመሩ በዚህም አኩሪ ተግባራቸው በእኛ የኢትዮጵያዊያን ዘንድ ልዩ ቦታ የምንሰጣቸው ነን፡፡ የታሰሩበት እና የሚሰቃዩበት ጉዳይ የኛም ጉዳይ ነው የሚሉ ቁጥራቸው መብዛቱ ሠላማዊ ትግሉ አባገነን ስርዓቱን የሚበላ እሳት መሆኑ ማሳያ ነው፡፡
ይህ በእንዲ እንዳለ  በአገር እና በህዝብ ላይ የሚፈፀም በደል ማቆም አለበት መንግስት እየወሰዳቸው ያለው እርምጃ የዜጎች ሰብአዊ እና ዲሞክራሳዊ መብቶችን የጣሱ ናቸው፤ በማለት ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብታቸውን ተጠቅመው ከምንም በላይ የጋዜጠኝነት ስነ-ምግባር ጠብቀው ሚዛናዊ መረጃ ለእዝብ ያደረሱ ዓለም ዓቀፍ ተሸላሚ የሆኑ ጋዜጠኖች በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ እርዮት ዓለሙ እና ውብሸት ታዬ በስራቸው ዓለም ያደነቃቸው አድናቆቱም በሽልማት የታጀበ መሆኑ ለማናችንም ግልፅ ነው፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ የዓለም ህዝብ ቆሞ ያጨበጨበላቸው ጋዜጠኞች አባገነኑ መንግስት በሽብርተኝነት ወንጅሎ በማሰር እያሰቃያቸው ይገኛል፡፡ ይህ ስቃያቸው ያልተሰማው ማነው? ከዚህ ስቃይ እንዲወጡ ምን ባደርግ ይሻላል እያልን እራሳችንን ያልጠየቅን ስንቶቻችን ነን? በሆነውስ ነገር ያልተቆጨ ማነው?
6ኛ. በውጪ የሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተፅኖ ሌላው ለአምባገነኑ ሥርዓት የእግር እሳታ መሆን ነው፤ በውጪ የሚገኙ ዜጎች በአገር ውስጥ ለታየው ብልሹ አስተዳደር ፊት ከመንሳት ባለፈ በተደራጀና በሚያስደንቅ ሁኔታ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ነው፡፡ እንቅስቃሴውም ከሌላው ጊዜ በተሸለ በኢኮኖሚ እና በፖለቲካው ስኬታማ መሆኑ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ በተለያየ ወቅት በሰጡት ቃለ ምልልስ እና መንግስት በሰጠው መግለጫ በውጪ በሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን መንግስት መሸነፉን የሚያሳብቅ ነው፡፡
በመሆኑም ከላይ በማሳያነት የቀረቡ የለውጡ ግፊት ሃይል ከሆኑ ምክንያቶች ውስጥ የተጨለፈ ቢሆንም  በመንግስት የአስተዳደር ብሉሹነት ምክንያት ይህ አስተዳደር በቃኝ ለማለት ምክንያቱ ብዙ ነው፡፡ ስለሆነም መስከረም ሲጠባ አደይ ሲፈናድ ለውጥ ፈላጊ የፈለገውን ለውጥ ላለማጣት ከባለፈው ዓመታት ትምህርት በመውሰድ በዘንድሮ አዲስ ዓመት ከግለሰባዊ ፋይዳ በላይ አገራዊና ህዝባዊ ለውጦች የምናይበት ዓመት ይሆናል፡፡ (ፎቶ: bernos.com)

No comments:

Post a Comment