FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Monday, September 16, 2013

የፖለቲካ ኃይል ምንጮች

ክፍል አንድ/2፡ የዝንጀሮዎቹ ጌታ ሞተ - ለምን እና እንዴት?

monkeys


የዝንጀሮዎቹ ጌታ አጭር ታሪክ የተወሰደው ቻይናዊው ሊዩ ጂ/ Liu-Ji (1311-1375) ከጻፈው የሞራል ማስተማሪያ መጽሐፍ ነው። ይኽ አጭር ታሪክ የአምባገነን ገዢዎች የፖለቲካ ኃይል ከየት እንደሚፈስላቸው (ምንጩ ምን እንደሆነ) እና እንዴት ምንጩን በመቆጣጠር የአምባገነኖችን አቅም መቆጣጠር አልፎም ምንጩን በማድረቅ አምባገነኖችን ማስራብ እንደሚቻል በምሳሌ አድርጎ ግልጽ ያደርጋል። ሰለዚኽ የሰላማዊ ትግል ተመራማሪው እና ዘመናዊ የፖለቲካ ሳይንስ ጠበብቱ ሲድኒ ታይ (Sidney Tai) ከቻይንኛ ወደ እንግሊዘኛ ቋንቋ ተረጎመው። የእንግሊዘኛ ትርጉሙን “በማጭበርበር መግዛት” (“Rule by Tricks”) የሚል ርዕስ ሰጠው እና ሰላማዊ ቅጣቶች (Nonviolent Sanctions) በሚል ርዕስ የአልበርት አነስታይን ሰላማዊ ትግል ምርምር ተቋም በሚያትማት ጋዜጣ ላይ አሳተመው ሲድኒ ታይ (Sidney Tai)። የዝንጀሮዎቹ ቅጣት ሰላማዊ ቅጣት እንደነበር እና የዝንጀሮዎቹ ጌታ ቅጣት ግን የኃይል ቅጣት (Violent Sanction) እንደነበር ወደፊት ከቦታው ስንደርስ እናስተውላለን። በቅርብ ደግሞ ጂን ሻርፕ (Gene Sharp) የተባለው ሌላው የዘመናችን የሰላማዊ ትግል ተመራማሪ እና በካምብሪጅ ዩንቨርስቲ መምህር ይኽን አጭር ታሪክ ከአምባገነን ወደ ዲሞክራሲ በሚለው መጽሐፉ ገጽ 17-18 ላይ ሰላማዊ ትብብር የመንፈግ ትግል (Nonviolent Non-cooperation Struggle) የሚለውን የሰላማዊ ትግል ጽንሰ አሳብ ለማብራራት ተጠቅሞበታል። የዚህ ጽሑፍ ግብ በዚህ አጭር ታሪክ አንባቢዎች እየተዝናኑ እንዲመራመሩ ማድረግ ነው። ይኽ ምርምር በቅርብ ለንባብ ለማቀርበው ጽሑፍ መሰረት ይጥላል የሚል እምነት አለኝ። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)

No comments:

Post a Comment