ኬንያ፤ በመዲናዋ በናይሮቢ ዌስትጌት በተባለው ግዙፍ የገበያ ህንጻ ውስጥ ፣ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ በሶማልያው አልሸባብ የአሸባሪዎች ቡድን፤ ቢያንስ 72 ሰዎች ከተገደሉ ወዲህ ፣የ 67ቱ ሰለባዎች የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጽሟል ። የ3 ቀን የኀዘን ጊዜም ታውጆ ተግባራዊ በመሆን ላይ ሳለ፣ የዩናይትድ እስቴትስ፤ የብሪታንያ፤ የእስራኤልና የሌሎችም ጠበብት ከኬንያ የምርመራ ጠበብትጋር በመተባበር፤ አደጋው እንዴት ሊሠነዘር እንደቻለ በማጣራት ላይ መሆናቸው ታውቋል። 40 ሚሊዮን ኑዋሪዎች ባሏት ኬንያ የሙስሊሞች ቁጥር 10 ከመቶ ገደማ ሲሆን፣ ተገቢ ቁጥጥር በማይደረግበት ድንበር፤ ሠርገው የሚገቡ የአልሸባብ ታጣቂዎች ከአንዳንድ ኬንያውያን የእምነት ተጋሪዎቻቸው ድጋፍ እንዳልተለያቸው ተነግሯል። አልሸባብ ፤ ሶማሌዎችን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ሃገራት ተወላጆችንም ማሰለፉ ይነገርለታል። ከእነዚህም አንዷ ሳምንታ የተባለችው እንግሊዛዊት መሆኗ ታውቋል። ይህች ሴትዮ እንዴት በሽብር ተግባር ለመሰማራት ተነሳሳች? የለንደኑን ዘጋቢያችንን ድል ነሣ ጌታነህን በስልክ ጠይቄው ነበር።
No comments:
Post a Comment