————————-
የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ እና ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሺበሺ ደህንነታቸው አደጋ ላይ ነው፡፡
የሟቹን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊ ምስል ያለበት ቲሸርት የለበሱ ከ10 የሚልቁ የመንግስት ካድሬዎች በወላይታ ሶዶ እየተደረገ የነበረውን አንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን ምክር ቤት ስብሰባን በሀይል ማደናቀፋቸውን ከስፍራው ለፍኖተ ነጻነት የደረሰው ዘገባ አመለከተ፡፡
ካድሬዎቹ የስብሰባ አዳራሹን በሃይል በመስበር ከተሰብሳቢዎቹ ላይ የተለያዩ ሰነዶችን የቀሙ ሲሆን ድብደባ በመፈፀም ላይ ናቸው፡፡ በስብሰባ አዳራሹ ውስጥ የነበሩት የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ እና ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሺበሺ ደህንነታቸው አደጋላይ መሆኑን ለፍኖተ ነፃነት ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፣ ፍኖተ ነጻነት
ከታሰሩት የአንድነት አመራሮች መካከል፣
http://ecadforum.com/Amharic/archives/11517/
No comments:
Post a Comment