FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Tuesday, March 25, 2014

ለዜጎች ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ አፈናና እስራት ምላሽ አይሆንም! (ሰማያዊ ፓርቲ)

ከሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት የወጣ የአቋም መግለጫ

የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት መጋቢት 14 ቀን 2006 ዓ.ም ባካሄደው ሁለተኛ ዓመት አራተኛ መደበኛ ስብሰባው የካቲት 30 ቀን 2006 ዓ.ም የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው ሩጫ ላይ በተገኙ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት አባላት ላይ ፖሊስና ፍርድ ቤት በመተባበር የፈጸሙትን ሕገ መንግስት የጣሰ ተግባር፣ እንዲሁም ከአሜሪካ መንግስት በደረሳቸው ግብዣ መጋቢት 12 ቀን 2006 ዓም ምሽት ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ቦሌ አውሮፕላን ማረፈያ በተገኙት የፓርቲያችን ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ላይ ራሳቸውን ከህግ በላይ ያደረጉ የደህንነት ኋይሎች የፈጸሙትን አሳፋሪና ሕገ ወጥ ተግባር በመመርመር የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡፡Statement from Semayawi party of Ethiopia, regarding Nile issue.
1. የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው ሩጫ ላይ የተገኙ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት አባላት በሩጫው ከተሳተፉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች የሚለዩት የነጻነትን ቀን ሊያከብሩ በተገኙበት ቦታ ስለ ነጻነት፣ስለ ፍትህ፣ስለዴሞክራሲ፣ስለ ሰብአዊ መብት ወዘተ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በማሰማታቸው ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 29/2 «ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሀሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው» ተብሎ የተደነገገውን ከምንም ያልቆጠረውና ሕጉን ሳይሆን ጠመንጃውን ተማምኖ፣ የሙያውን ሥነ ምግባር ሳይሆን የአለቆቹን ትዕዛዝ አክብሮ እንደሚሰራ በተግባሩ ያረጋገጠው ፖሊስ እነዚህን የሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣቶች አፍሶ ሲያስር አንዳችም ህጋዊ ምክንያት አልነበረውም፣ የፖሊስ ሕገ ወጥ ተግባር በዚህ ሳያቆም የታሰሩ የትግል አጋሮቻቸው የሚገኙበትን ቦታና ሁኔታ ለማወቅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሄዱ የፓርቲው አመራር አባላትንም አሰረ፡፡ ዋስትና ለማስከልከል አይደለም ለክስ የሚያበቃ ምንም ምክንያት ሳይኖረው ለፍ/ቤት ምርመራየን አልጨረስኩም የግዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ በማለት አባላቱ ለአስር ቀናት በጣቢያ እስር እንዲጉላሉ በማድረግ ሕግን ለማስከበር ሳይሆን የፖለቲከኞችን ፍላጎት ለማስፈጸም የቆመ መሆኑን በተግባር አረጋግጠ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ይህንን ሕገ መንግሥቱን በግልጽ የጣሰ የፖሊስ ተግባር በጽኑ እያወገዘ፣ፖሊስ የግለሰቦች ሥልጣን ጠባቂ ሳይሆን ሕግ አስከባሪ መሆኑን በተግባር እንዲያሳይ ይጠይቃል፡፡
2. የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 19/4 «የያዛቸው የፖሊስ መኮንን ወይም ህግ አስከባሪ በጊዜው ገደብ ፍርድ ቤት በማቅረብ የተያዙበትን ምክንያት ካላስረዳ ፍርድ ቤቱ የአካል ነጻነታቸውን እንዲያስከብርላቸው የመጠየቅ ሊጣስ የማይችል መብት አላቸው፡፡» ተብሎ የተደነገገውንእንዲያቀርቡ አዟል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምር ፍርድ ቤቱ ለህግ የበላይነት የሚሰራና በመተላለፍ ታሳሪዎቹን የዋስትና መብት ከልክሎ ለሁለት ግዜ ለፖሊስ የግዜ ቀጠሮ የፈቀደው ፍርድ ቤት፣ የእኔ ሥልጣን አይደለም መደበኛ ፍርድ ቤት አቅርቡዋቸው በማለት ካሰናበት በኋላ የምርመራ መዝገቡ ለክስ አይበቃም ተብሎ በአቃቤ ሕግ ውድቅ የተደረገበት ፖሊስ መልሶ እዛው ፍርድ ቤት ሲያቀርባቸው እያንዳንዳቸው 1300 ብርና የሰው ዋስ በጣምራ ለፍትህ መከበር የቆመ አለመሆኑን በተግባር ያረጋገጠበትን ይህን ተግባር እያወገዘ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 79/2 «በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ የዳኝነት አካል ከማንኛውም የመንግሥት አካል፣ከማንኛውም ባለሥልጣን ሆነ ከማንኛውም ሌላ ተጽዕኖ ነጻ ነው» እንዲሁም በአንቀጽ 79/3 ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸውን በሙሉ ነጻነት ያከናውናሉ፣ከሕግ በስተቀር በሌላ ሁኔታ አይመሩም »ተብሎ የተደነገገው በተግባር እንዲገለጽ አጥብቆ ይጠይቃል፡፡
3. የፓርቲያችን ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ወደ አሜሪካ የሚያደርሳቸውን አስፈላጊ የጉዞ ሰነድ አሟልተው ሻንጣቸው አውሮፕላን ላይ ካስጫኑ በኋላ ፓስፖርታቸው በደህንንት ኋይሎች ተቀዶ ጉዞአቸው እንዲስተጓጎል ተደርጓል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ይህን ሕገ ወጥ ብቻ ሳይሆን እጅግ አሳፋሪ የሆነና የደህንነት ክፍሉን ብቻ ሳይሆን የአየር መንገዱንም ስም የሚያጎድፍ ተግባር በጽኑ እያወገዘ ድርጊቱን በፈጸሙት ማን አለብኝ ባዮች ላይ ከሕግ በላይ ሊሆኑ እንደማይችሉ የሚያሳይ ሕጋዊ ርምጃ አንዲወሰድ እንጠይቃለን፡፡ 
4. መንግሥት ለዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብት ጥያቄ እስራት አፈናና ማስፈራራት ምላሽ እንደማይሆን ከታሪክ በመማር ለዜጎች የመብት ጥያቄ ትክክለኛውን ምላሽ እንዲሰጥና ትግሉ ሰላማዊ፣ ዓላማው ሕዝባዊ ግቡ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እውን ማድረግ ከሆነው ሰማያዊ ፓርቲ ላይ የጥፋት እጁን እንዲያነሳ አጥበቀን እንጠይቃለን ፡፡
መጋቢት 14/2006 ዓም አዲስ አበባ
http://ecadforum.com/Amharic/archives/11523/

No comments:

Post a Comment