የሰበታ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የነበሩት አቶ የማነ ይገዙ እና የኦሮሚያ ቴሌቪዥንና ሬድዮ ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን ኃይሌ በግምገማ ከኃላፊነት መነሳታቸውን ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፊንፊኔ ዙሪያ፣ኦሮሚያ ልዩ ዞን ሰበታ ከተማ ከንቲባ በመሆን ያስተዳደሩት አቶ የማነ፤ ከሁለት ሳምንት በፊት በሟቹ በአቶ አለማየሁ አቶምሳ በተመራው የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ከመሬት አስተዳደር ጉዳዮች ጋር በተገናኘ በዝምድናና በጎሰኝነት በመስራት ኔትዎርክ ፈጥረዋል በሚል የተገመገሙ ሲሆን ከትናንት በስቲያ ከሃላፊነታቸው መነሳታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ታውቋል፡፡
የከተማው ከንቲባዎች ቶሎ ቶሎ መቀያየር በክልሉ ያለውን የባለስልጣናት ሙሰኝነት ያሳያል ያሉት ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ የከተማው አስተዳደር ፅ/ቤት ሰራተኛ፤ ከ1ሺ በላይ ግለሰቦች ካርታ ይዘው መሬት ሳይረከቡ መቆየታቸው ከዚሁ ጋር የተያያዘ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የዛሬ ዓመት ከመሬት ሽያጭ ሙስና ጋር በተያያዘ በፀረ-ሙስና ኮሚሽን ክስ ተመስርቶባቸው ከአንድ ዓመት በላይ በእስር የቆዩ የቀድሞ የሰበታ ከተማ ከንቲባ አቶ ሽመልስ ሀሰኖን ጨምሮ ከአስራ አምስት በላይ የፊንፊኔ ዙሪያ የአስተዳደር ሠራተኞችና መሃንዲሶች በነፃ መለቀቃቸው ይታወሳል፡፡
በቅርቡ በተካሄደው የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ለዘጠኝ ሰዓታት ያህል የተገመገሙት የኦሮሚያ ቴሌቪዥንና ሬድዮ ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን ሃይሌም ከኃላፊነታቸው እንደተነሱ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ አቶ መስፍን ለአራት ዓመታት የመሩትን ድርጅት በምትካቸው ወክለው እንዲወጡ በተወሰነው መሰረት በኦሮምያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በአስተዳደር ሃላፊነት ሲሰሩ የቆዩትንና በህግ የማስተርስ ምሩቅ የሆኑትን አቶ ተመስገን ባይሳን ወክለው እንደወጡ ተጠቁሟል፡፡
http://addisadmassnews.com/

No comments:
Post a Comment