FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Friday, May 31, 2013

ESAT Daily News Amsterdam May 31, 2013 Ethiopia


የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን በተጠርጣሪዎች 60 የክስ መዝገቦች መቋረጣቸውን አስታወቀ

court


- የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደለት
- ሁለት ተጠርጣሪዎች በምርመራ ወቅት መደብደባቸውን ተናገሩ
‹‹ተያዘ የተባለው ሰነድ ሁሉ በሀብት ምዝገባ ያስመዘገብኩት ነው›› አቶ ገብረ ዋህድ ወልደ ጊዮርጊስ
የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ምርመራ ቡድን፣ በተለያዩ የሙስና ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር በዋሉ ተጠርጣሪዎች እንዲቋረጡ ከተደረጉት 60 የክስ መዝገቦች ውስጥ 28 ያህሉን መሰብሰቡን ግንቦት 19 ቀን 2005 ዓ.ም. ለፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡
መርማሪ ቡድኑ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ እንዳስረዳው፣ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ባለፉት 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ላይ የሠራውን የምርመራ ሥራ እንዳብራራው፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሥራዎች ጋር ግንኙነት ያላቸውን የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን ሰብስቧል፡፡ ከተለያዩ ባንኮች በተወሰኑ ተጠርጣሪዎች ላይ ከአራጣ ብድር ጋር የተያያዙ ማስረጃዎችን፣ በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ (መኒ ላውንድሪንግ) መጠቀምን የሚያሳዩ ሰነዶችን መሰብሰቡን ገልጿል፡፡
መርማሪ ቡድኑ ጨምሮ እንደገለጸው፣ ተጠርጣሪዎቹ በአራጣ ብድር የተከሰሱ ሰዎችን ክስ ያቋረጡባቸውን የክርክር መዝገቦችን መሰብሰቡንና በኮንትሮባንዲስቶች ላይ በፍርድ ቤት ተጀምረው ከነበሩትና በሕገወጥ ጥቅም ከተቋረጡት 60 የክስ መዝገቦች ውስጥ 28 የሚሆኑት መሰብሰቡንም ገልጿል፡፡
በአንድ የንግድ ድርጅት ላይ ተወስኖ የነበረን ዘጠኝ ሚሊዮን ብር ግብር ወደ ሦስት ሚሊዮን ብር የተቀነሰበትን ሰነድ፣ እንዲሁም 87 ሚሊዮን ብር ግብር እንዲከፍል ተወስኖበት የነበረን ድርጅት፣ በሕገወጥ መንገድ ወደ ስምንት ሚሊዮን ብር ዝቅ የተደረገበትን ሰነድም መሰብሰቡን ቡድኑ ለችሎቱ ተናግሯል፡፡
ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ኦዲት ሊያደርጋቸው የሚገቡ ስምንት ኩባንያዎች መኖራቸውን ማረጋገጡን የገለጸው መርማሪ ቡድኑ፣ ኦዲት የሚደረጉትን ለይቶ መጨረሱንና ለመሥሪያ ቤቱ ደብዳቤ መጻፉን አሳውቋል፡፡ መርማሪ ቡድኑ የምስክሮችን ቃል በከፊል መቀበሉንና የንብረት ጥናትም በከፊል መሥራቱን ገልጾ፣ የቀሩትንም የምርመራ ሥራዎች ጠቁሟል፡፡
ያላግባብ ክሳቸው የተቋረጡ 40 የክስ መዝገቦችን መሰብሰብ፣ በሕገወጥ መንገድ ግብር እንዲቀነስ የተደረገባቸውን ሰነዶች፣ ሕጋዊ በማስመሰል ሕገወጥ ገንዘብን ለመጠቀም የተዘጋጁ ሰነዶችን መሰብሰብ፣ የስምንት ኩባንያዎችን ግብር ማጣራት፣ የኦዲተሮችን ቃልና የቀሪ ምስክሮችን ቃል መቀበል እንደሚቀረው በመግለጽ፣ ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡
መርማሪ ቡድኑ ላለፉት 14 ቀናት በተጠርጣሪዎቹ ላይ የሠራቸውንና የሚቀሩትን ሥራዎች ለችሎቱ ካሳወቀ በኋላ፣ በጠየቀው ተጨማሪ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜን በሚመለከት አስተያየታቸውን እንዲሰጡ በችሎቱ የተፈቀደላቸው፣ በኢትዮጵያ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ማስከበር ኃላፊ የምርመራ መዝገብ ሥር ያሉ 12 ተጠርጣሪዎች ናቸው፡፡
መርማሪ ቡድኑ በጥቅል ከመግለጽ ባለፈ እያንዳንዱ ተጠርጣሪ ምን እንደሠራ፣ ተጠርጣሪው ከሠራው ወይም ካጠፋው ነገር አንድም እንኳን እንዳልተነገረው፣ ምን ሠርቶ ምን እንደቀረው እስካሁን የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ለፍርድ ቤቱ ያስረዱት፣ የአቶ ነጋ ገብረ እግዚአብሔር ጠበቃ ናቸው፡፡ ደንበኛቸው ተጠርጥረው የታሰሩት ክስ በማቋረጥና ባልተፈቀደ የፍራንኮቫሉታ ፈቃድ ሲሚንቶ ማስገባት እንደነበር ያስታወሱት ጠበቃው፣ መርማሪ ቡድኑ 14 ቀናት የምርመራ ተጨማሪ ጊዜ ሲጠይቅ ያልተናገራቸውና ለደንበኛቸው ያልተገለጹላቸው ሰነዶችን ማሸሽ፣ ንብረት ከተገቢው በላይ ማፍራትና ከባለሥልጣናት ጋር መመሳጠር፣ ሕገወጥ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ መጠቀም፣ አራጣ ማበደርና ግብር ያላግባብ መቀነስ የሚሉት የሕገ መንግሥቱን ድንጋጌ የሚጥስና ያላግባብ መሆኑን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡
በሕገ መንግሥቱ ድንጋጌ መሠረት ስለተጠረጠሩበት ወንጀል በተያዙበት ወቅት ሊነገራቸው ይገባ እንደነበር የገለጹት ጠበቃው፣ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ መርማሪ ቡድኑ የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ሲጠይቅ ያስመዘገባቸው፣ ‹‹የሲሚንቶው ጉዳይ ምን ሆነ? ሰነድ ጠፋ ወይስ ምን ሆነ? ሊገለጽልን ይገባል፤›› ካሉ በኋላ፣ በወቅቱ ያልተገለጹና እንደ አዲስ ክስ የቀረቡት ጉዳዮች ተገቢ ጥያቄዎች ባለመሆናቸው የ14 ቀናት ተጨማሪው የጊዜ ጥያቄው ውድቅ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡
አቶ ገብረ እግዚአብሔር እንዲናገሩ ችሎቱን ጠይቀው ሲፈቀድላቸው እንደተናገሩት፣ በምን ተጠርጥረው እንደታሰሩ አያውቁም፡፡ ለምርመራ ሲቀርቡ በተደጋጋሚ የሚቀርብላቸው ጥያቄ ስለንብረታቸው ነው፡፡ የልብ ሕመምተኛ መሆናቸውንና ንብረታቸውም የተመዘገበ መሆኑን በመግለጽ፣ ማወቅ የሚፈልገው አካል በፈለገ ጊዜ ሊያውቅ እንደሚችል ገልጸው፣ እሳቸው ግን በአንድ በተዘጋ ክፍል ውስጥ መሆናቸው አግባብ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡
እምባና ሳግ እየተናነቃቸው ዝቅ ባለ ድምፅ መናገር የቀጠሉት አቶ ነጋ፣ በታሰሩበት ክፍል ውስጥ ሁለት ጊዜ ራሳቸውን ስተው ወድቀው እንደነበርና መደብደባቸውንም ገልጸዋል፡፡
ነጋዴ በመሆናቸው ሀብት ማፍራት እንደሚችሉ የተናገሩት ተጠርጣሪው፣ ምርጥ ታክስ ከፋይ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ መሆናቸውን፣ ለአገራቸው 33 ሚሊዮን ብር መድበው በ23 ሚሊዮን ብር ያስገነቧቸውን ፖሊ ቴክኒክ ትምህርት ቤቶችን ለሕዝብና ለመንግሥት ማስረከባቸውን ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡
‹‹አገሬን ያወቅኋት አሁን ነው፤ ዜጋ ነኝ ለማለት አይቻልም፤›› ያሉት አቶ ነጋ፣ ሲደበደቡ ራሳቸውን ስተው እንደሚወድቁ አስታውቀው፣ ኢሰብዓዊ ድርጊት እንደተፈጸመባቸው ጠቁመዋል፡፡ የደም ግፊትና የስኳር ሕመምተኛ መሆናቸውንና የልብ ቱቦ ተገጥሞላቸው ያሉ ታማሚ በመሆናቸው ክትትል ካልተደረገላቸው ለሕይወታቸው አስጊ መሆኑን ጠበቃቸው አክለዋል፡፡
የመርማሪ ቡድኑን በጥቅል የመግለጽ ሁኔታ እንደ አቶ ነጋ እሳቸውም እንደሚቃወሙት የተናገሩት የባለሥልጣኑ ሠራተኛ አቶ ጥሩነህ በርታ ሲሆኑ፣ መርማሪዎች ወደ ምርመራ ክፍል በመውሰድ የሚጠይቋቸው ከሥራቸው ጋር የማይገናኝ፣ መረጃ እንደሚያውቁ ተደጋጋሚ ጥያቄ እንደሚቀርብላቸውና በማያውቁት ጉዳይ ላይ መረጃ ሰብስበው ክስ ለመፍጠር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እሳቸው ተጠርጥረዋል በተባሉበት ክስ የማቋረጥ ወንጀል መጠየቅ ያለባቸው እሳቸው ሳይሆኑ ከእሳቸው በላይ ያሉ ኃላፊዎች እንደሆኑ የተናገሩት ተጠርጣሪው፣ እነሱ ሳይጠረጠሩ እሳቸውን አስሮ ማሰቃየት ኢሰብዓዊ ድርጊት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ሱሪያቸውን ከፍ በማድረግ እግራቸውን ለችሎቱ እያሳዩ መደብደባቸውን የገለጹት ተጠርጣሪው፣ ውኃ እየተደፋባቸው እንደተገረፉ ለበላይ ኃላፊ ቢያመለክቱም፣ መርማሪዎቹ በድጋሚ ሲያገኟቸው ‹‹እንኳን ለኃላፊ ለማንም ብትናገር አንተውህም›› እንዳሏቸው ሲገልጹ መርማሪ ቡድኑ አቤቱታቸውን ተቃውሟል፡፡ የተቃወመበትን ምክንያት እንዲያስረዳ ፍር ቤቱ ሲፈቅድለት፣ ተጠርጠሪው የሚያነሱት ጉዳይ አስተዳደራዊ መሆኑን በመጠቆም፣ ፍርድ ቤት ሊቀርብ እንደማይገባ አመልክቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ምላሽ፣ ‹‹አስተያየታቸው ሊደመጥ ይገባል፡፡ ኮሚሽኑ ከሰብዓዊ መብቶች ጋር በተያያዘ የሚነሱ አቤቱታዎችን እንዲያስተካክል በተደጋጋሚ ቢታዘዝም ሊታረም አልቻለም፤›› በማለት ተጠርጣሪው አቤቱታቸውን እንዲቀጥሉ አዟል፡፡
ተጠርጣሪው ቃላቸውን እስካሁን የተቀበላቸው እንደሌለ በመግለጽ፣ ቢሮአቸውንም ሆነ ቤታቸውን ቡድኑ በርብሮ ምንም አለማግኘቱን፣ እያንገላታቸው ያለው አዲስ ማስረጃ ለማሰባሰብ እንጂ በእሳቸው ላይ ምንም ዓይነት ጭብጥ እንደሌለው ፍርድ ቤቱ እንዲገነዘብላቸው አመልክተዋል፡፡
የባለሥልጣኑ ኦዲተር መሆናቸውንና ደመወዛቸው ከአሥር ሺሕ ብር በላይ መሆኑን፣ የተጣራ 5,600 ብር አካባቢ እንደሚያገኙና ሥራ የሌላቸውን ባለቤታቸውን ጨምሮ፣ ልጆቻቸውንና የእህታቸውን ልጅ ጭምር የሚያስተዳድሩት እሳቸው መሆኑን የተናገሩት አቶ በላቸው በየነ ሲሆኑ፣ መርማሪ ቡድኑ የልጃቸው ላፕቶፕ ጨምሮ በመሥሪያ ቤታቸውና በቤታቸው ያለውን ሁሉንም ሰነድ ስለወሰደ በዋስ እንዲለቃቸው ጠይቀዋል፡፡
የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን በጥቅሉ ሳይሆን እያንዳንዱ ተጠርጣሪ የተጠረጠረበትን ወንጀል ለይቶ ማቅረብ እንደሚገባው የገለጹት ተጠርጣሪው፣ መንግሥት በመደባቸው በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ ለ27 ዓመታት መሥራታቸውን፣ አብዛኛው ሥራዎቻቸውን የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ጭምር ያውቁት እንደነበር፣ ቤተሰብንም ሆነ ሌላ አካል ወይም ማንንም ለመጥቀም በሚል ሕገወጥ ሥራ ሠርተው እንደማያውቁ አስረድተዋል፡፡
በቅርቡ ለዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ኃላፊዎች ሥልጠና ለመስጠት እሳቸውና ሌላ አንድ ሰው ተመርጠው እንደነበር የተናገሩት ተጠርጣሪው፣ መርማሪ ቡድኑ ኩባንያዎችን ኦዲት እንዲያደርጉለት ለዋና ኦዲተሩ ደብዳቤ መጻፉን አስታውሰው፣ ‹‹ኦዲት የሚያደርጉት ሠልጥነው ነው ወይስ?›› ሲሉ ፍርድ ቤቱ ‹‹ይኼ በማስረጃ ጊዜ የሚታይ ነው፤›› በማለት አስቁሟቸዋል፡፡
አቶ ገብረ ዋህድ ወልደጊዮርጊስ ሁለት ሕፃናት ልጆቻቸው እስካሁን ድረስ የት እንዳሉ እንደማያውቁ፣ የሚረዳቸው ወይም የሚቀልባቸው ሰው ባለመኖሩ ሥጋት ላይ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ በማስረዳት፣ ባለቤታቸው ኮሎኔል ሃይማኖት ተስፋይና እህታቸው ወ/ሮ ንግስቲ ተስፋይ፣ እንዲሁም በውጭ አገር ለሰባት ዓመታት ቆይቶ ከመጣ አራት ወራት ብቻ የሆነው የወ/ሮ ንግስቲ ልጅ አቶ ሀብቶም ገብረመድኅን በዋስ እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡
እሳቸው የተጠረጠሩበትን የወንጀል ሰነድ አሽሽተዋል በሚል ቤተሰቦቻቸው መታሰራቸው አግባብ አለመሆኑን የገለጹት አቶ ገብረ ዋህድ፣ ሸሽቷል የተባለው ሰነድ ኮሚሽኑ ባወጣው የሀብት ማስመዝገብ አዋጅ የተመዘገበና ኮሚሽኑ የሚያውቀው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የባለቤታቸው እህት የ60 ዓመታት አዛውንት መሆናቸውን፣ ከአቅም በላይ በሆነ ውፍረት ክብደታቸው ከፍተኛ በመሆኑ ዕርዳታ እንደሚፈልጉና የደም ብዛትና የስኳር ሕመምተኛም ስለሆኑ ከተቻለ በነፃ ካልሆነም በዋስ አንዲለቀቁ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡
ኮሚሽኑ የቀረው መደበኛ ሥራው መሆኑን የገለጹት አቶ ገብረ ዋህድ፣ ከእሳቸውና ከቤተሰባቸው ጋር የሚያገናኘው ነገር ስለሌለ በዋስ እንዲለቀቁ ወይም የምርመራ ጊዜው አንዲያጥር አመልክተዋል፡፡
የአቶ ስዬ አብርሃ ወንድም አቶ ምሕረተ አብ አብርሃ ባቀረቡት አቤቱታ እንደገለጹት፣ የሚተዳደሩት በንግድ ነው፡፡ ከ1993 ዓ.ም. እስከ 1999 ዓ.ም. ድረስ በታሰሩበት ወቅት ንብረታቸውን ያስተዳድር የነበረው ኮሜት የሚባል ድርጅት ነበር፡፡ ንብረታቸውን በሚመለከት ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ጋር አለመግባባት ላይ ደርሰው፣ መብታቸውን ያስከበሩት በፍርድ ቤት ነው፡፡ በመሆኑም አሁን ‹‹ተጠርጥረሃል›› ከተባሉበት ክስ ማቋረጥ፣ ኮንትሮባንድ፣ አራጣና ሌሎች ጉዳዮች ጋር እንደማይገናኙ ተናግረዋል፡፡ ከነበሯቸው ከ15 በላይ ተሽከርካሪዎች ልጆቻቸውን እያስተዳደሩ ያሉት በሁለት ተሽከርካሪዎች በሚያገኙት ገቢ ብቻ መሆኑን የገለጹት አቶ ምህረተ አብ፣ ባለሥልጣኑ ከፍተኛ ግብር ጭኖባቸው ከ1999 ዓ.ም. እስከ 2003 ዓ.ም. ድረስ በፍርድ ቤት ባደረጉት ክርክር መብታቸውን ማስከበራቸውን ገልጸው፣ አሁን የተጠረጠሩበትን ምክንያት ስለማያውቁት ዋስትና እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል፡፡
ሁሉም ተጠርጣሪዎች በአጠቃላይ መርማሪ ቡድኑ ያቀረበው የምርመራ ውጤት ወንጀሉ ጥቅል መሆኑን፣ በተያዙበት ወቅት ያልተነገራቸው የወንጀል ክስተት እየቀረበባቸው መሆኑን፣ ማስረጃ ተሰብስቦ ቢያልቅም መብታቸው አለመከበሩን፣ ጥርጣሬዎቹ ከሰነድ ጋር የተገናኙ በመሆናቸው ታስረው ሊቆዩ እንደማይገባና ዋስትና ሊፈቀድላቸው እንደሚገባ፣ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንደማያስፈልግ የሚሉትን ሐሳቦች ሁሉም ያነሱ ሲሆን፣ በተናጠል ደግሞ የቤተሰብ ኃላፊ መሆናቸውን፣ የጤና ችግር እንዳለባቸው፣ የመብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው መሆኑን፣ ከተያዙ ጀምሮ ቃላቸውን አለመስጠታቸውን ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል፡፡ በምርመራ መዝገቡ የቀረቡት 12 ተጠርጣሪዎች ናቸው፡፡
የኮሚሽኑ መርማሪ ቡድን ተጠርጣሪዎቹ ላነሷቸው ጥያቄዎች በሰጠው ምላሽ፣ የተጠረጠሩበት ወንጀል የተፈጸመው በተናጠል ሳይሆን በቡድንና ውስብስብ በሆነ መንገድ መሆኑን ገልጿል፡፡ ጉዳዩ አገራዊ በመሆኑ በቀላሉ የሚታይ አለመሆኑንም አስገንዝቧል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከፍተኛ ኃላፊዎችና ባለሀብቶች መሆናቸውን በመጠቆም፣ ሥልጣንንና ገንዘብን ተገን በማድረግ ውስብስብ በሆነና በጥቅም በመመሳጠር በአገር ገቢ ላይና በሌሎች የሕዝብ ጥቅሞች ላይ የተፈጸመ ወንጀል መሆኑን አስረድቷል፡፡ ክስ እንዲቋረጥና ከውጭ የሚገቡ የንግድ ዕቃዎች ቀረጥ እንዳይከፈልባቸው ሲደረግ፣ ለጠቋሚዎች የሚከፈል አበል ለራስ ጥቅም ሲደረግ፣ አንድ ተጠርጣሪ ብቻ የሚሠራው ሳይሆን በቡድንና በመመሳጠር የሚሠራ መሆኑን መርማሪ ቡድኑ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡ ድርጊቱ በአጠቃላይ በትብብር የተሠራ መሆኑንና ለቀሪ የምርመራ ጊዜ ተጨማሪ 14 ቀናት ጊዜ እንዲፈቀድለት በድጋሚ አመልክቷል፡፡
ቃል አልሰጠንም ያሉት ተጠርጣሪዎች ቃላቸውን መስጠታቸውን በተለያየ መንገድ መግለጻቸውን፣ ሰብዓዊ የመብት ረገጣ ደርሶብናል ያሉት ተጠርጣሪዎችም በማስረጃ የቀረበ ባለመሆኑ ሊታመን እንደማይችል መርማሪ ቡድኑ ገልጾ፣ ዋስትና ቢፈቀድ የሰነድና የምስክሮች ቃል ሊያጠፉበት እንደሚችሉ በመናገር ዋስትናውን ተቃውሟል፡፡
መርማሪ ቡድኑ በተሰጠው ጊዜ በማን ላይ ምን እንደተሠራ፣ በማን ላይ ምን እንደቀረው በግልጽ አለማስቀመጡን፣ ይኼም ለክርክር በር መክፈቱን፣ በርካታ ምስክሮች የቀሩት በማን ላይ እንደሆነና ሰነድም ሆነ ሌላ መረጃ ለማጣራት የተፈለገው በማን ላይ እንደሆነ ግልጽ አለመደረጉ አግባብ አለመሆኑን ፍርድ ቤቱ ገልጾ፣ በቀጣይ ቀጠሮ በእያንዳንዱ ተጠርጣሪ ላይ በተናጠል የተሠራው ተዘርዝሮ እንዲቀርብ አዟል፡፡
በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ ከድርጊቱ ውስብስብነት አንፃር የተጠርጣሪዎች ዋስትና ጥያቄን አለመቀበሉን፣ የመርማሪ ቡድኑን 14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜያት መፍቀዱን አስታውቆ፣ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ዙሪያ ተጠርጣሪዎች ያቀረቡትን አቤቱታ ኮሚሽኑ አጣርቶ እንዲያቀርብ በማዘዝ ለሰኔ 3 ቀን 2005 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በዕለቱ መቅረብ የነበረበት የእነ አቶ መላኩ ፈንታ የምርመራ መዝገብና የእነ አቶ መሐመድ ኢሳ የምርመራ መዝገብ በመሆኑ፣ መዝገቡ የቀረበ ቢሆንም ቀኑ በመምሸቱ ለግንቦት 21 ቀን 2005 ዓ.ም. በይደር ተቀጥሯል፡፡ በእነ መሐመድ ኢሳ የምርመራ መዝገብ ፍሬሕይወት ጌታቸው የተባሉ ተጠርጣሪ በመካተታቸው ጠቅላላ የተጠርጣሪዎች ቁጥር 55 ደርሷል፡፡
ግንቦት 19 ቀን 2005 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሹማምንት፣ ታዋቂ ነጋዴዎችና ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ችሎት ለመታደም በፍርድ ቤት የተገኙ ታዳሚዎች ከችሎቱ አቅም በላይ ስለነበሩ በርካቶች ችሎቱን መከታተል አልቻሉም፡፡ (ምንጭ: ሪፖርተር)

የግንቦት 7 ንቅናቄ 4ኛ ጉባኤ ህዝቡ ወደ ትግሉ እንዲቀላቀል ጥሪ አቀረበ

Weekly_Editorial_Tumbnail
የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነት፣ የዲሞክራሲ ንቅናቄ 4ኛ ጉባኤ ከግንቦት 11 – 19/2005 አ/ም በበርካታ ወቅታዊ፣ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየት እና የድርጅቱን አዲስ ም/ቤት በመምረጥ ወያኔን በማስወገድ ረገድ ሊከተል የሚገባውን ጠቋሚ አቅጣጫዎችንና ውሳኔዎችን ከተሳታፊው በመውሰድ ወሳኝ የሆነ ውይይት አድርጓል።
ንቅናቄው ከተለያዩ አለማት በአባላት የተወከሉ ጉባኤተኞች እና በተለያዩ የስራ ክፍል የሚገኙትን የድርጅቱን አባላት ያሳተፈ፤ ከዚህ በፊት ከተደረጉትም ጉባኤዎች እጅግ የላቀ አባላት የተገኙበት ነበር።
ጉባኤው የነበረውን የም/ቤት ሪፖርት፣ የስራ አስፈጻሚ እንዲሁም የኦዲትና ማናጅመንት ኮሚሽን፣ የግልግልና ዳኝነት ኮሚቴን እና የፋይናንስ ሪፖርቶችን በማዳመጥ ጥልቅ የሆነ ወይይቶች አደርጓል።
የግንቦት 7 ንቅናቄ ጠቅላላ ጉባኤ ተሳታፊዎች፤ ደርጅቱ የጀመረውን ወያኔን የማስወገድ ትግል በየትኛውም አቅጣጫ አስፈላጊ ሆኖ የታመነበትን ማናቸውም መንገድ ሁሉ በመጠቀም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የዘረኝነትን ስርአት ድባቅ መምታት፤ አልፎም ዘላቂ የሆነ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት አስቸኳይና ማንም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ግዴታው አድርጎ መውሰድ ያለበት አጣዳፊ ስራ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጧል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ የሰላም አየርና የዲሞክራሲ ጮራ ሁሌም የሚፈነጥቅባት፣ ህዝብ ካለፍርሃትና ሰቀቀን ወጥቶ የሚገባባት፣ ህዝብ በነጻነት የፈለገውን ፓርቲ የሚመርጥበት፣ የሚያወርድበት፣ ስልጣን የህዝብ መሆኑን የሚረጋገጥበት፣ የመንግስት አካላት ለህዝብ ተጠያቂ የሚሆኑበት፣ ነጻ ሚዲያ ለመልካም አስተዳደር ግንባታ የሚያገለግልበት፣ ፍትህ ለሁሉም በእኩል የሚሰጥበት፣ ዜጎች በየትኛውም የሀገሪቱ ክልሎች የመኖር፣ ሀብት የማፍራት፣ ቤተሰብ የመመስረት፤ ከቦታ ወደ ቦታ ያለምንም ገደብ የሚንቀሳቀሱበት መብት እንዲኖራቸው፣ እና የሃይማኖት ነጻነት ይኖረን ዘንድ የድርጅቱ ጉባኤተኞች ሙሉ መሰዋእት ለመክፈል ዝግጁዎች ነን ሲሉ በድጋሚ ቃል በመግባት መራራ የሆነውን ትግል እጅ ለእጅ ተያይዞ ተራራውን ለመውጣት እና ለማቋረጥ ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይተዋል።
ከ4ኛ ጉባኤ ጋር በተያያዘ ጉባኤተኛው የግንቦት 7ን 5ኛ አመት ምስረታ ታሪካዊ ቀን አስቦ ውሏል። በዚህ በግንቦት 7, 1997 ቀን የኢትዮጵያ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር ተሳትፎ ፍትህ፣ ነጻነትና ዲሞክራሲ በሀገሪቱ ይሰፍን ዘንድ ለዘመናት ተጭኖት የነበረውን ጫና ተቋቁሞ የወያኔን ስርአት በድምጹ የጣለበት ልዩ ቀን ነበር። ግንቦት 7, ሁሌም በታሪክ የሚዘከር ልዩ እለት ነው።
ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያዊ ትውልድ በግንቦት 7 ያሳየውን ልበሙሉነት፣ ጀግንነት፣ መሰዋእትነት፣ አንድነትና ወንድማማችነት ለዘለአለም ሲታወስ ይኖራል። ይህንኑ በ97 የተጀመረው የትግል ፍሬ፤ ውጤት ያፈራ ዘንድ አስፈላጊ ያላቸውን ትግሎችን እያደረገ እንደሆነ ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነት፣ የዲሞክራሲ ንቅናቄ 5ኛ አመቱን ከአባላቱ ጋር ሆኖ ሲዘክር ተወያይቷል። ይህም ታሪካዊ የህዝብ ድል ቀን፤ በጠመንጃ ሃይል የነጠቀውን ወያኔን ለማስወገድ እና የህዝብን ድምጽ ለማስመለስ ድርጅታችን ማናቸውንም መንገድ በመጠቀም የሚያደርገውን የትግል ጅማሮ ግብ ለመምታት አሁን ከአለንበት በተሻለ በመጠናከር መሆኑንም ስምምነት ተደርሷል። ድርጅታችን ካለፈው ጉባኤ ጀምሮ ድርጅቱ ያደረገውን እንቅስቃሴ በስፋት ገምግሞ፤ በስራ ሂደት የታዩ ድክመቶችን አፍረጥርጦ ተወያይቶ፤ የታዩትን ጠንካራ ጎኖች ይበልጥ የሚጎለብቱበትን ሁኔታ ተመልክቶ፤ በድርጅቱ የእስትራቴጂ አካሄድ ላይ የተወሰኑ ማሻሻያዎችን አድርጎ፤ እነኝህን የእስትራቴጂ አቅጣጫዎች በተቀላጠፈ መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ወሳኝ የመዋቅር ለውጦችን አጽድቆና ይህን አዲስ መዋቅር የሚያስፈጽሙ ያመራር አባላትን መርጦ፤ በከፍተኛ የጓዳዊ መንፈስና ልዩ በሆነ የትግል ወኔ ጉባኤውን በድል አጠናቋል::
በመሆኑም ግንቦት 7፣ በግንቦት 7 የገባውን ቃል ኪዳን ዛሬም ህያው መሆኑን ሲያረጋግጥና ትግሉ ከመቼውም በበለጠ ጽናትና ቁርጠኛነት እንደሚገፋበት ቃል ሲገባ፣ የሀገራችን ህዝብ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ; አዛውንት፣ ወጣት፣ ጾታ፣ ሃይማኖት፣ ዘር ቀለም ሳይለያችሁ በግንቦት 7/ 1997 የተሰረቀውን፣ የተነጠቅነውን የህዝብ መንበረ-ድምጽ ስልጣን ወደ ትክክለኛ ባለቤቱ እንዲመለስ የምናደረግውን የትግል ጉዞ ትቀላቀሉ ዘንድ ጥሪያችን ይድረሳችሁ!
የሀገራችን ወጣቶች ሆይ፡ ለነጻነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ቱርፋቶች መሰዋእት ሆናችሁ መሰዋእትነታችሁ በጥቁር ህዝብ የኢትዮጵያ ታሪክ ገድል ውስጥ ለዘላለም ተከትቦ ይቀመጥ ዘንድ ኢትዮጵያዊ የሞራል ግዴታ አለባችሁ፡፡ ግንቦት 7 ትግሉን ጀምሯል። ኑ ተቀላቀሉ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

"አፍንጫ ሲመታ፥ ዓይን አያገባውም"! (በ አገኘሁ አሰግድ)


አዎ! ዛሬ ዛሬ አፍንጫ ሲመታ ዓይን አያለቅስም፡፡ አፍንጫ ሲመታ አፍንጫ ብቻ ነው የተመታው፡፡ የአፍንጫ መመታት ለዓይን ጉዳዩ አይደለም፡፡ አንተ ቤት ሲንኳኳም እኔ ቤት አይሰማም፡፡ እኔ ጋር የሚሰማ እኔ ጋር የተንኳኳ እንደሆን ብቻ ነው፡፡ ባለቤት ሲጮህ ጎረቤት አይሰማም፡፡ ጩኸቱ ጩኸት ብቻ ነው፡፡ እሪ በከንቱ! አዎ ይህ ዓይነት ዝመት የሕዝባችን እውነት እየሆነ መጥቷል፡፡ በየጥጋጥጉ ለራስ ብቻ የመሮጥ ግዴለሽነትና ምን አገባኝ ባይነት መንፈስ አድፍጧል፡፡ አንዳንድ ዘመን የራሱ መንፈስ አለው፡፡ ከሌላው ጊዜ የተለየ በጎም ይሁን ጥሩ የራሱ ቀለም ይኖረዋል፡፡ ይሄንንም ዘመን አስተውሎ ለተመለከተ ሰው የኅብረተሰባችንን በምን አገባኝነትና በግድ የለሽነት ድቅድቅ ውስጥ እየተዋጡ መሄድ መለየት አይሳነውም፡፡ ግለሰቦች፣ ድርጅቶች፣ መንግሥት፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሁሉም በዚህ ምን አገባኝ መንፈስ ዋግ ተመትተዋል፡፡ ለትንሽ ትልቁ የኑሮ ፈሊጡ ሆኗል፡፡ እዚህ ጋር ይህንን መንፈስ አድምቆ ሊያሳይ የሚችለውን የኑረዲን ኢሳን ግጥም እንውጣው፡፡
ZONE 9
‹‹እኔን ምን አገባኝ የምትሉት ሐረግ
እሱ ነው ሀገሬን ያረዳት እንደ በግ
የተሰኘ ግጥም ልጽፍ አሰብኩና
ምን አገባኝ ብዬ ቁጭ አልኩ እንደገና፡፡››
ይህ ግጥም የዚህ ዘመን ስዕል ነው ፡፡ የግጥሙ ተናጋሪ ሕዝቡን ቀፍድዶ የያዘውን ሕፀጽ ለመተቸት ነበር አነሳሱ ነገር ግን በምን አገባኝነት ባይነቱ ስፋትና ጥልቀት የተነሳ እሱንም እዛ መንፈስ ውስጥ ዳግም ሲቀላቀል እና ተደላድሎ ሲቀመጥ እናየዋለን፡፡
ኢትዮጵያዊነት ሲነሳ መተጋገዝ መተያየት አለሁ ባይነት—- እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አብረው የሚነሱ እሴቶች ነበሩ፡፡ ደቦ፣ ጂጊ፣ ወንፈል፣ የሚባሉ በኅብረት የመተጋገዝና የመሥራት ማኅበራዊ ተቋማት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ዛሬ እነኚህ ምን ደረጃ ላይ ላይ ናቸው? ምን ያህል እድሮች ሰው ሲሞት ከመቅበር የዘለለ ሥራ ይሠራሉ? ምን ያህሉ አጠገባቸው በቁም ለሞተው ይገዳቸዋል – ግለሰቦችስ ቢሆኑ “የያዙትን አንጠልጥሎ ያልቻሉትን ጥሎ” ከማለፍ ውጪ እርስ በእርስ ይተያያሉ? የያዙትን ይዘው ለማለፍ ሲሞክሩ የጣሉትን ዞሬው ያያሉ — ዝቅ ብለው ያነሳሉ? ይሄን የሚያደርጉ የሉም እያልኩ አይደለም! ብዙው ግን እንዲህ አይደለም፡፡ ሰፊው ክፍል በምን አገባኝ ባይነቱና በግድየለሽነት መንፈስ የተዋጠ ነው፡፡ ነገ ያሉትን ጥቂቶች ምን አገባኝ አስብሎ ስላለማስቀመጡ እርግጠኛ አይደለንም፡፡ ማኅበራዊነት፣ አብሮነት፣መረዳዳት ችግር መካፈል — ወደ መቃብር እየተጓዙ ያሉ ያለፈው ዘመን ዘይቤዎች ወደ መሆን ደርሰዋል፡፡ —– የራሳችንን ቆሻሻ ማራቃችን እንጂ ሌላውን ማቆሸሻችንን ከቁብ አንቆጥረውም፡፡ የኛ መቆም እንጂ የሌላው መውደቅ ግድ አይሰጠንም፡፡ በድጋፋችን መቆም የሚችሉ ብዙዎች እያሉ እጃችንን ነፍገናቸዋል፡፡ በኅብረት ያልቆምንባት የመጀመርያዋ ቅጽበት፤ ያልተጋገዝንበት የመጀመርያዋ ሰዐት የስብራታችንና የውድቀታችን አዋጅ መሆኗን አርቆ ማየት ተስኖናል፡፡
“ነግ በኔ” ነው…
በአንድ ወቅት፣ ሦስት በሬዎች ከለምለም መስክ ላይ ሳር ይግጣሉ፡፡ በመሀል አንበሳ ወደነሱ መጣ፡፡ የአንበሳውን መምጣት ሲያዩ እራሳቸውን ለማዳን አጠገብ ለአጠገብ በመቆም እራሳቸውን ለመከላከል ተዘጋጁ፡፡ አንበሳው ሁለቱን በሬዎች እንዲህ አላቸው” እንድትበሉ ሚያደርጋችሁ ቀዩ በሬ ነውና እሱን አሳልፋችሁ ስጡኝ እናንተን አልነካችሁም” አላቸው፡፡ ተስማሙ፡፡ አንበሳው ቀዩን በሬ ወሰደ፡፡ እንዲሁ በሁለተኛው ቀን ተመልሶ መጣ፡፡ ሁለቱ በሬዎች እራሳቸውን ለመከላከል ቀንዳቸውን አሹለው ጎን ለጎን ቆሙ፡፡ አንበሳ “ነጩን በሬ አሳልፈህ ከሰጠኸኝ አንተን አልነካም” አለው፣ ለጥቁሩ በሬ፡፡ ተስማማ፡፡ ነጩን በሬ ወሰደው፡፡ በሦስተኛው ቀን ጥቁሩ በሬ አገር አማን ብሎ ሳር ሲግጥ አንበሳው መጣ፡፡ በሬው በድንጋጤ የሚገባበት ጠፋው፡፡ “ሁለት ጓደኞቼን አሳልፌ ሰጥቼህ ልትበላኝ?” ጠየቀ በፍርሃት፡፡ አንበሳውም “አንተን የበላሁህ እኮ ቀዩን በሬ እንድወስድ በፈቀድክባት ቅጽበት ነው፡፡” ብሎ ቀጨም አድርጎ አጣጣመው፡፡
ለጊዜያዊ ራስን ማዳን ሌላውን ማጋፈጥ ነገ ራስን ማጥፋት ነው፡፡ የነገን ችግር ተካፋይ ለዛሬ ጊዜያዊ ችግር መገበር አይወጡት ችግር በገጠመ ጊዜ ችግር ተካፋይን ማጣት ነው፡፡ በምን አገባኝና በግድለሽነት ውስጥ ያለው ትልቁ ትርፍ ይኸው ነው፡፡ አንገትን እንደሰጎን አሸዋ ውስጥ መቅበር አያዋጣም፡፡ መሰበራችን ከራስ ለራስ በላይ አሻግሮ ማየት በተሳነን ቅጽበት ነው፡፡
መንግሥት ስለዜጎቹ ግድ የለውም፡፡ ሲነኩት ለመኮርኮም የሚሮጥበትን ያህል ፍጥነት ዜጎቹ ሲቸገሩ ለመድረስ ጊዜ የለውም፡፡ የሕዝቡን ጩኸት ለመስማት ጊዜ ያለው አይመስልም፡፡ አሁን አሁን እንደውም ከነጻው ፕሬስ ነጻ የሆነች ሀገር ለመፍጠር የሚፈልግ ይመስላል፡፡ ለምን ለሕዝቡ ለቅሶ ግድ የለውማ! የግል ሚዲያዎች የሕዝቡን ብሶት ከማሰማት በላይ ምን ፋይዳ አላቸው? በማን አፍንጫ መመታት የማን ዓይን ያለቅሳል? እስከመቼ “ሁለትም ሦስትም ሆናችሁ በስሜ ስትሰበሰቡ ብቻ በመሐከላችሁ እገኛለሁ” እያለ እንደሚዘልቅ መልስ የለም፡፡ የሚቃወሙትን ከሚደግፉት ዕኩል በአንድ ዓይን የሚያይበት፣ ስለእነሱ ይገደኛል የሚልበት ቀን ይናፍቃል፡፡ ግለሰቦች ስለሀገር ግድ የላቸውም፡፡ ከቤት ውስጥ ልጅ ያገባኛል ቢል “አንተ ምን አገባህ አርፈህ ተቀመጥ” እያሉ ቤተሰቦቹ የመንፈሳቸው እስረኛ ያደርጉታል፡፡ “ጎመን በጤና”ን ይነግሩታል፡፡ “ፈሪ የእናቱ ልጅ ነው”ን ያሰርጹበታል፡፡ “ከራስ በላይ ንፋስ፣ ንፋስ” ሲሉ ያጠምቁታል፡፡ እሱም የምን አገባኛቸው አቀንቃኝ ይሆናል፡፡ ጨለማውን አብሮአቸው ብርሃን ይላል፡፡ ነጋዴው የሸማቹ ጩኸት አይሰማውም፡፡ አከራዩ የተከራዩ እሮሮ አይቆረቁረውም፡፡ ነግ በኔ የለም፡፡ ኅብረት የለም፡፡ ኅብረት የሌለው ጩኸት ተራ የድምፅ ብክነት መሆኑን መገንዘብ አቅቶናል፡፡ መንግሥት በራሱ ሚዲያዎች ላይ ከዕውቀትም ሆነ ከጋዜጠኝነት ስነምግባር የፀዱ ጋዜጠኞች በሚያቀርቧቸው ፕሮግራሞች የሚፈጠረው ማኅበራዊ ቀውስ አያሳስበውም፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ነን ባዮች የምርጫ ሰሞን ብቅ ብለው ከመጥፋት ውጪ እርስበርሳቸው እንኳን ኅብረት ኖሯቸው አያውቅም፡፡ የተንሸዋረረ ፖለቲካቸውን ከማውራት አልፈው ዝቅ ብለው ሕዝቡን አይመለከቱም፡፡ ለሕዝባችን ይላሉ እንጂ ሕዝቡን በቅጡ አያውቁትም፡፡ ጩኸቱን አይጮሁለትም፡፡ የራሱን ጩኸት እራሱ ይጩህ ይመስላል! በማን አፍንጫ መመታት የማን ዓይን ያለቅሳል?
የምናገባኝ መንፈስ የሰፈነበት ሕዝብ ታላላቅ ሰዎች አይኖሩትም፡፡ የታላላቅ ሰዎች ታላቅ መንገድ ለሌሎች ግድ ማለት ነው፡፡ ለራስ ብቻ ኑሮ ለራስ መሞት ደመነፍሳዊ የእንስሳት ባሕሪ እንጂ ሰብኣዊ አይደለም፡፡ አንስታይን “ትክክለኛው ሕይወት ለራሳችን ብቻ ሳይሆን ለሌሎች የኖርነው ነው፡፡ አልያ ግን ኖርን አይባልም” የሚል እምነት ነበረው፡፡ የታላቅነቱም ሚስጢር ይሄው ነው፡፡ ዛሬ ዛሬ እየወረረን ባለው ለራስ ብቻ ኑሮ ለቁሳዊ ነገሮች ተቅበዝብዞ የማለፍ አባዜ በአንድ ኮንዶሚንየም (የጋራ ቤት) ውስጥ አንድ ግድግዳ እየተጋሩ በዓይን የማይተዋወቁ ሶዎችን እስከመታዘብ አድርሶናል፡፡ ይህን የተረዱ የቀን ሌቦች የተዘጋ ቤት ከፍተው እየገቡ የቤት እቃ ጭነው እስከ መሄድ ደርሰዋል፡፡ ሰው ቁሳዊ ብቻ አይደለም መንፈሳዊም ነው፡፡ ስጋዊ ምቾት ሁሉ መንፈሳዊ እርካታን አያተርፍም፡፡ የዚህ ሁሉ ግድየለሽነታችን ምንጩ ቁሳዊ አስተሳሰብ ነው፡፡ የብዙ አሜሪካውያን ሕይወት እንዲህ ነው፡፡ መሮጥ… መሮጥ… ብቻ ለራስ ጊዜ የሌለበት! ሩጫ፣ ነገ አዲስ ቴሌቪዢን፣ አዲስ መኪና፣ አዲስ ኮምፒውተር፣ ለመግዛት መሮጥ …መሮጥ …ሞት! መሥራት መልካም ነው፡፡ ሀብትም መልካም ነው፡፡ እዛ ውስጥ ጠፍቶ መቅረት ግን የሰውን ልጅ መንፈሳዊነት አድቅቆ “ለቁስ ስለቁስ” የሚኖር እንስሳ ያደርገዋል፡፡
አዎ! ያገባኛል ባይነታችን እየሞተ ነው፡፡ አንዳንዴ እኔ ያገባኛል ማለት “ሌላው አያገባውም” ማለት የሚመስላቸውም ብዙዎች ናቸው፡፡ ይህም ቢሆን ምን ያገባኛል ከሚለው አስተሳሰብ ያልተለየ ጠማማ ዕይታ ነው፡፡ በተለይ መሪዎቻችን የዚህ ስሜት ተጠቂዎች ናቸው፡፡ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ “ኢትዮጵያ ያለ እኔ ምንም አይደለችም፡፡ ዕድሏ ከእኔ ጋር የተሳሰረ ነው፡፡ እኔ ነኝ የማደርሳት፡፡ ካለኔ ትኖራለች ብለህ አታስብ፡፡” እስከማለት መድረሳቸው ኦቶባዮግራፊ (ሕይወቴ ታሪክ) በሚለው የተክለ ሀዋርያት ተክለ ማርያም መጽሐፍ ላይ ተጠቅሶአል፡፡ መንግሥቱ ኃ/ማርያምም ቢሆን “ከእኔ በላይ ሀገር ወዳድ” የሚል ነበር፡፡
ዛሬም ቢሆን ኢሕአዴግ “ከኢሕአዴግ ውጪ አማራጭ የለም” እያለን ነው፡፡ የብዙኃኑን ከማልቀስ ውጪ ያልሆነ ሕይወት ወርዶ ያየ ይመስል! ኢትዮጵያዊ ኅብረት እየሞተ ነው፡፡ ወደ ነበር እያደገ ነው፡፡ የገዛ አፍንጫችን በተመታ ዓይናችን እንባ የለውም፡፡ ዓይናችን እስኪመታ እንጠብቃለን፡፡ መረን የለቀቀ ግላዊነታችን በዚሁ ከቀጠለ ማጣፊያው ያጠረ የከፋ ጦስ ነው ይዞብን የሚመጣው፡፡ ኅብረት በሌለበት ተሰባሪው ብዙ ነው፡፡ ኅብረት በሌለበት ወዳቂው እልፍ ነው፡፡ ኅብረት በሌለበት ጉዞ ሁሉ፥




ነው፡፡ ቁልቁለት ሲወርዱት ቀላል ነው፡፡ ዳግም ሊወጡት በፈለጉ ጊዜ ነው ክብደቱ!…. እናም በአያያዛችን ዘልቀን አንወጣውን ከፍታ በራሳችን ላይ ከምንፈጥር እንተያይ! በኅብረት እንቁም! ለአንተ አፍንጫን መመታት የእኔ ዓይን እንባ ይኑረው! የቤትህ መንኳኳት ለቤቴ ይሰማ! የጎረቤቴን ጩኸት ጆሮዬን ይስማው! እንዲሁም ጩኸቴ ላንተ ይሰማ!
የዚህ ጽሑፍ ዋና ቅጂ በኢትዮጵያ እንዳይነበብ በታገደው በዞን ዘጠኝ ጦማርላይይገኛል፡፡

ሰላማዊ ሰልፉን ከበካዮች (Contaminants) እንጠብቀው!

ግርማ ሞገስ (girmamoges1@gmail.com)

ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ እሁድ ግንቦት 25 ቀን 2005 ይደረጋል የሚል ዜና ዘሃበሻ ድረ ገጽ ላይ ሐሙስ ምሽት ተመለከትኩት። አንድነት ፓርቲ እና መኢአድም ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በአንድነት መቆማቸውን እና መንግስት ሰላማዊ ሰልፉን መፍቀዱን ጨምሮ ይገልጻል ጽሑፉ። ወዲያውኑ ሰላማዊ ሰልፉ እንከን የለሽ እንዲሆን እጅጉን ተመኘሁኝ። የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ እንደ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ተቃውሞ በድስፕሊን የታነጸ እና ክብርን ከመንግስት ሳይቀር የሚጎናጸፍ እንዲሆን እጅጉን ተመኘሁ። የበኩሌንስ ምን አስተዋጽኦ ላድርግ ብዬ ተጨነቅኩ። ይኽን ጽሑፍ በችኮላ እንዳዘጋጅ የገፋፋኝ እሱ ነው።Addis Ababa, Ethiopia a call for demonstration
የሰላም ትግልን ሊበክሉና ለአደጋ ሊያጋልጡት ከሚችሉ ተግባሮች፣ አሰራሮች እና ሁኔታዎች ውስጥ ጥቂቶቹን አንስቼ በአጭር በጭሩ ልበልና ልሰናበት።
(1ኛ) ሰላማዊ ሰልፍ ሲደረግ በመንግስት ወይንም በመንግስት ደጋፊዎች አማካኝነት የሚፈጸምበትን የሽብር ጥቃት ለመመከት ሲል የሚፈጽመው ማንኛውም አይነት የኃይል እርምጃ ሰላማዊ ሰልፉን ሊበክል እና ውድቀት ሊያስከትልበት ይችላል። ስለዚህ የዲሞክራሲ አራማጅ የሆነው ወገን ለሽብር መልሱ ሽብር ነው ከሚለው ፍልስፍና መራቅ አለበት። ሰላማዊ ትግል ወደ ኃይል እርምጃዎች ከተንሸራተተ በሰላማዊ መንገድ ለነፃነት መታገል የጀመረው ህዝብ እምነት ሊተን ይችላል። ህዝብ ሁከት አይወድም። ለሽብር መልሱ አለመሸበር መሆን አለበት።
(2ኛ) የሰላም ትግል አመራር የወጣቶች እንዲሁም በእድሜና በተመክሮ የበሰሉ ሰዎች ቅይጥ ቢሆን ለበካዮች ቀዳዳ ላይከፍት ይችላል። በድስፕሊን የታነጸ ግራና ቀኙን የሚያይ እና ሰላማዊ ሰልፈኛው ውስጥ ጸብ ጫሪ ተግባር እንዳይፈጸም የሚጠብቅ በሰላም ትግል መርሆዎች የሰለጠነ ኃይል መሰማራት አለበት።
(3ኛ) በድርጅቶች ህብረት-አመራር ዘንድ የሚታይ ክፍፍል የሰላም ትግልን ይበክላል። ገዢው ቡድን ደጋፊዎቹን በመላክ ወይንም ከሰላም ትግል አመራር ውስጥ ህሊና ደካሞችን በጥቅም በመግዛት ወሬ እንዲያቀብሉት (informants) ሊያደርግ እንደሚችል ቀደም ተብሎ ሊታሰብበት ይገባል። እነዚህ የመንግስት ወሬ አቀባዮች ለውይይት በሚነሱ ጉዳዮች ላይ ሆን ብለው ስምምነት እንዳይኖር እያደረጉ ዞር ብለው ደግሞ ለሰላማዊ ታጋዩ ህዝቡ ስምምነት ጠፋ ይሉታል። ህዝብ በክፍፍሉ የተነሳ በትግሉ እምነት እንዲያጣ ለማድረግ። ከፍራቻ መውጣት እና መታገል እንዲሳነው ለማድረግ። ስለዚህ የዲሞክራሲ ኃይሎች ህብረትን ማጠናከር እንዳይሳናቸው እና ጸብ ጫሪ ሰርጎ ገቦች (agent provocateurs) ምኞታቸው እንዳይሳካ መደረግ አለበት።
(4ኛ) የሲቪክ ድርጅቶች አመራሮች በአምባገነኖች ቁጥጥር ስር ከሆኑ የሰላም ትግል በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ተበክሏል ማለት ይቻላል። ለምሳሌ የመምህራን፣ የሰራተኛ፣ የወጣቶች ማህበራት አመራሮች በገዢው ቡድን ቁጥጥር ስር ከሆኑ እነዚህ ተቋሞች የመጨቆኛ አጋዥ ምሶሶዎች ሆነዋል ማለት ነው። ነፃ ማውጣት አሊያም ሊላ
ትዩዩ (Parallel) ድርጅቶች መመስረት ያስፈልጋል። እነዚህ ተቋሞች የነፃነት ትግልን ኃላፊነት ለእያንዳንዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ለመበትንም ይጠቅማሉ። ወጣቱ ብቻ የሁሉም ህብርተሰብ ነፃ አውጪ ሊሆን አይችልም።
(5ኛ) በሰላም ትግል ኃይሎች የሚሰጡ መግለጫዎች አግላይነት ከታየባቸው የተገለለው ወገን ወደ ጸበኛነት እንዲሄድ በማድረግ የሰላም ትግል ሊበከል ይችላል። ለምሳሌ የአንድ ተቃዋሚ ድርጅት አባል ሲታሰር የሁሉም ድርጅቶች ጉዳይ ሊሆን ይገባል። መንግስት ሁሉንም በወዳጅ አይን እንደማያያቸው እና ቢቻል ሁሉም ቢጠፉለት እንደሚፈልግ መዘንጋት የለብንም። ጥቃቱ ተራ ጠብቆ የሚመጣ መሆኑ ታውቆ አንዱ ሲጠቃ ሁሉም እንደተጠቃ በመውሰድ በአንድነት መቆም ጠቃሚ ነው።
(6ኛ) የመንግስት ወሬ አቀባዮች (informers) ካሉበት የሰላም ትግል የመንግስት መልክተኛ ቆስቋሾች (agent provocateurs) ሰርገው የገቡበት የሰላም ትግል ይበልጥ ተበክሏል (Contaminated) ሊባል ይችላል። የመንግስት ወሬ አቀባዮች (informers) የሰላም ትግልን አቅምን እና እቅዶችን ለመንግስት ይዘግባሉ። የመንግስት መልክተኛ ቆስቋሾች (agent provocateurs) ግን ሆን ብለው የኃይል እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋሉ ወይንም እራሳቸው ድንጋይ ይወረውሩ እና ህግ አክባሪው ሰላማዊ ሰልፈኛ እንዲመታ ያደርጋሉ። በሰላም ትግል ኃይል ውስጥ ብጥብጥ ያነሳሳሉ። ለኃይል መልሱ ኃይል ነው የሚል አዝማሚያ በማራመድ የሰላም ትግል መንግስትን በደካማ ጎኖቹ እንዳይገጥመው ያደርጋሉ።
(7ኛ) ፖሊሶች ከከተማው ህዝብ ጋር ተቀላቅለው ስለሚኖሩ ጥሩዎቹን ልናርቃቸው አይገባም። ለምሳሌ ጎረቤቴ የሆነ ፖሊስ እኔ ፍጹም የሰላም ትግል አማኝ መሆኔን እንዲያውቅ አድርጌው ሳለ ድንገት ከፖሊስ ጣቢያ እከሌ ሽብርተኛ ነው እና ይዘህ አምጣ የሚል ትዕዛዝ ቢሰጠው ለአለቃው ሽብርተኛ አለመሆኔን ሊናገር ይችላል።
ለራሳችን ጊዜ ሰጥተን ቁጭ ብለን ብናሰላስል ሌሎች በርካታ ብክለት ሊጋብዙ የሚችሉ ሁኔታዎችን ማግኘት እና እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል ማስላት እንችላለን።
ፍጹም ሰላማዊ እና እንከን የለሽ እንዲሆን ምኞቴ ነው!

Thursday, May 30, 2013

ESAT Daily News Amsterdam May 30, 2013 Ethiopia


የተቃውሞ ሠልፉ ቅስቀሳ እየተካሄደ ነው! ሠማያዊ ፓርቲ


ሠማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም ለሚካሄደው የተቃውሞ ሠልፍ ዝግጅቱን በታቀደው መሠረት በአመርቂ ሁኔታ እያካሄደ ነው፡፡ በዛሬው ዕለት 5ሺህ የድምጽ መልዕክቶች እና 10 ሺህ የጽሁፍ መልዕክቶች በእጅ ስልክ(በሞባይል) የተላለፈ ሲሆን፣30 ሺህ በራሪ ወረቀቶች እና 2 ሺህ ፖስተሮች ተሰራጭቷል፡፡ ሰው ለሰው የሚደረገው ቅስቀሳ በተቀላጠፈ ሁኔታ እየተካሄደ ነው፤በሚቀጥሉት ቀናትም ቅስቀሳው በልዩ ልዩ ዘዴዎች ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
የእሁድ ሰው ይበለን!
Addis Ababa, Ethiopia a call for demonstration

ጋዜጠኛ ተመስገን ደስአለኝ ለሃምሌ ሁለት ተቀጠረ : የፍርድ ቤት ውሎ

394711_184013551696255_1365830121_nፍርድ ቤቱ የተከሳሽን  ቃል ሲሰማ እና ጠበቆች ስለምስክሮቹ መግለጫ ሲሰጡ ሰዓቱ ስላለቀ ሃምሌ 2 የምስክሮቹን የምስክርነት ቃል ለመስማት ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ የተመስገን ጠበቃ ምስክሮቹ በምን ጉዳይ ላይ ምስክርነታቸውን እንደሚሰጡ ከተናገረ በኋላ አቃቢ ህግ የሁለቱ መስካሪዎች እንዳይመሰክሩ በምክንያት አስደግፈው ተቃውመው ነበር::  በዚህም መሰረት አንደኛው ምስክር ዶ/ር ያሬድ ከህገ መንግስቱ እና ኢትዮጵያ ከፈረመቻቸው ሃሳብን የመግለፅ መብቶች ከሚደነግጉ ህጎች አንፃር ተመስገን የተከሰሰባቸው ፅሁፎች ከህግ ውጪ እንዳልሆኑ ያስረዳሉ ::  ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም ደሞ ኢሰመጉ ይሰሩባቸው በነበሩበት ወቅት በኢሰመጉ ሪፖርት የቀረቡ በኢትዮጵያ መንግስት ስለተጣሱ ሰብአዊ መብቶች ያቀርባሉ:: አቶ እንዳልካቸው ሃ/ሚካኤል ክስ የቀረበባቸውን ፅሁፎች ከጋዜጠኝነት ስነምግባር እና አሰራር ከሙያ አንፃር እንዴት መታየት እንዳለበት ያቀርባሉ:: አቃቤ ህጎች የሁለቱ ምስክርነት ቃል እንዳይሰማ ብለው ተቃሟቸውን አቅርበው ነበር በ1ኛ እና 2ኛ ምስክሮች ላይ::
ጠበቆቹ ስለምስክሮቹ መግለጫ ካቀረቡ በኋላ አቃቤ ህጎቹ በ1ኛ እና 2ኛ ምስክር ላይ ተቃሞ እንዳላቸው ተቃሟቸውን አቀረቡ:: 1ኛ ምስክር ዶ/ር ያሬድ የህግ ባለሙያ ቢሆኑም ህገመንግስቱን የመተርጎም ስልጣን የላቸውም :  ህገመንግስቱን የመተርጎም ስልጣን ያለው የፌዴሬሽን ም/ቤት ብቻ ነው ስለዚ የሳቸው ምስክርነት አያስፈልግም:: 2ኛ ምስክር ፕ/ር መስፍን ኢሰመጉ ሊቀመንበር ሆነው የሰሩ ቢሆንም ከ97 በኋላ ባላቸው የፖለቲካ እንቅስቃሴ እና አቋም ገለልተኛ ሆነው መመስከራቸው ያጠራጥረናል ስለዚህ የሁለቱን ምስክር ሆኖ መቅረብ ፍ/ቤቱ ውድቅ እንዲያደርግ ጠይቀዋል::
የተከሳሽ ጠበቆችም ምላሽ ሲሰጡ : 1ኛ ምስክር ዶ/ር ያሬድ ህገመንግስቱን እንዲተረጉሙ ሳይሆን ደንበኛቸው የተከከሰሰባቸው ፅሁፎች ከህገመንግስቱ እና ኢትዬጵያ ከፈረመቻቸው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ከሚደነግጉ አለም አቀፍ ህጎች አንፃር እንዴት ትክክል እንደሆኑ ለማስረዳት መሆኑን 2ኛ ምስክር ፕ/ር መስፍን ደግሞ የሚያቀርቡት ኢሰመጉ ሲሰሩ በነበሩባቸው ጊዜያቶች ያዩትን የሰሙትንና ድርጅቱም በሪፖርቱ ያካተታቸውን ጉዳዮች እንጂ ሌላ ነገር አለመሆኑም..የገለልተኝነታቸው ጉዳይ በተመለከተ ደግሞ በህጉ ምስክሮች ገለልተኛ መሆን አለባቸው የሚል እንዳልተጠቀሰ ..አቀረቡ:: ዳኛውም ግራ ቀኙን ካዳመጡ በኋላ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላለፉ:: በአቃቤ ህግ ተቃሞ የቀረበባቸው ምስክሮች 1ኛ ምስክር ዶ/ር ያሬድ ህገመንግስቱን መተርጎም እንደማይችል ነገር ግን ከዛ ውጪ ባለው እውቀት ክስ የቀረበባቸውን ፅሁፎች ከህገመነግስቱ እና ሌሎች ህጎች አንፃር እንደማያስከስሱ ብቻ ማቅረብ እንዳለባቸው 2ኛ ፕ/ር መስፍንም ኢሰመጉ ሲሰሩ በነበሩበት ወቅት የሚያቁትን ብቻ እንዲያቀርቡ፡፡ ገለልተኛ ለተባለው…መስካሪዎች ገለልተኛ እንዲሆኑ የሚል ደንብ ስለሌለ ማንኛውም ሰው ያለምንም ልዩነት የምስክርነት ቃል መስጠት ይችላል::
በፍትሕ ጋዜጣ ላይ፣ የተዘገቡ ”የካቲት 23 2004 ዓ.ም በተሰራጨው የፍትህ ጋዜጣ ቅጽ 05 ቁጥር 177 እትም የፈራ ይመለስ በሚል” : ”በቅጽ 5 ቁጥር 179 መጋቢት 7 2004 ዓ.ም ዕትም መጅሊሱና ሲኖዶሱ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ማጥመቂያ” እና “ ሐምሌ 22 ቀን 2003 ዓ.ም የሁለተኛ ዜግነት ህይወት በኢትዮጵያ እስከመቼ?”  በሚሉ ርእሶች በወጡ መጣጥፎችን ተከትሎ ”የሕዝብን ሐሳብ ማናወጥ፣ሕዝቡን በሕገ-መንግስቱ ላይ ማነሳሳትና የመንግስትን ስም በማጥፋት” በሚሉ ሶስት ክሶች ነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የተከሰሰው::

ጎንደር ታምሷል፤ አዲስ አበባ ህዝቡ ተነሳስቷል!

EMF – በመተማ ገንዳውሃ ከተማ ግንቦት 20 ቀን 2005 ዓ. ም የእርሻ መሬታቸው የተነጠቁ በርካታ ሰዎች በተገኙበት ስብሰባ ተካሄደ፡፡ በስብሰባው የ‹ክልሉ› ም/ አስተዳደር እንደሚገኝ ቢነገርምsemayawi-party-ethiopia የተገኙት የሰ/ ጎንደር አስተዳደር ሀላፊ አቶ ግዛት አብዩ ናቸው፡፡
ስብሰባው የእርሻ መሬታቸውን በተነጠቁት አርሶ አደሮች ጉዳይ ሲሆን ከፍተኛ ክርክር ተካሂዶ ስምምነት ያልተደረሰ ሲሆን አቶ ግዛት ‹‹ መሬቱን መልቀቅ አለባችሁ..›› ሲሉ ተሰብሳቢዎች ተቃውሞ አድርገዋል፡፡አያይዘውም አቶ ግዛት ‹‹…እስከ አፍንጫው የታጠቀ መከላከያ ሰራዊት ነው ያለን ሜዳው ያውላችሁ….›› በማለት ዛቻ አሰምተዋል፡፡ አርሶ አደሮችም ‹‹ መሬቱን አንለቅም መከላከያ እገላለሁ ካለም ይግደለን፡፡›› በሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ከስብሰባው በኋላ የኢህአዴግ አባላትን ይዘው እስከ ምሽቱ 6፡00 በመሰብሰብ ችግር ይፈጥራሉ ባሏቸው ሰዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ዶልተው ሂደዋል፡፡
በተመሳሳይ በጎንደር ከተማ የሚገኙ ባለኀብቶችና ነጋዴዎችን የቀበሌ ሹማምንት ‹‹የመለስ ራእይ›› የሚለው ‹‹መፃህፍን›› ከ2000.00- 5000.00 ብር ግዙ በማለት ከፍተኛ ጫና እየፈጠሩ መሆኑን ነጋዴዎች በምሬት ገለፁ፡፡ እያንዳንዱ ቀበሌ ‹‹መፅሀፉን›› ሽጦ ከ400.000.00- 500.000.00 ብር ገቢ እንዲያደርግ ታዟል፡፡
በሌላ መልኩ ቁጥቸው 500 የሚደርሱ ሚሊሻዎች ከደባርቅ ወረዳ በመሰብሰብ ለልዩ ስልጠና ከ21/ 09/ 2005 ዓ. ም ጀምሮ በድብ ባህር ልምምድ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ የስልጠናው ምክንያት በአካባቢው ባሉ የታጠቁ ኃይሎች ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይነገራል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰማያዊ ፓርቲ አዲስ አበባ ላይ የጠራው ህዝባዊ ስብሰባ የሰሞኑ የአገር ቤት አቢይ ዜና መሆኑ ተገልጿል። ከዚሁ ጋር የደረሰን መእክት እንዳስተላለፈው፤ የህዝባዊ ስብሰባው አጀንዳ ሀገራዊ በመሆኑ ቀደም ሲል ሁሉም ኅብረተሰብ ‹‹ተቃዋሚ የለም፣ ማን ያስተባብረን፣ ሚጠራን የለም፣…ወዘተ. ›› ጉንጭ አልፋ ወሬዎችን የሰበረ ነው፡፡ ይኸው ‹‹ና›› ተነስ ተቃውሞህን ግለጽ ተብለናል፡፡ በየጓዳው፣ በየካፌው፣ በየባንኮኒው፣ በየወረቀቱ፣ በየ…፣በየ…፣ መትመክመክ ዋጋ የለውም፡፡
ስለዚህ በዚህ ምቹ አጋጣሚ ሁላችንም ተነስተን ‹‹ሆ›› ብለን ተቃውሟችን እንግለፅ፡፡
በስብሰባው መገኘት የግድ የሰማያዊ ፓርቲ አባል መሆን አይደለም፣
ስብሰባው ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ይጋብዛል፣
ሁሉንም ተቃዋሚዎች ይጋብዛል፣
ሁሉንም እምነቶች ያካትታል፣
ከቤት ውጭ በመሆኑ በጣም አመችና ገላጭ ነው፣
መፈክር ይዞ ለመውጣት ያመቻል፣
ለረዥም ቀናት/ድል ለመጨበጥ/ ያመቻል፣
ከሁሉም በላይ ወሩ ግንቦት ነው፣
ጥንካሬ፣ ድፍረት፣ ቆራጥነት፣ ፅናት፣ ….ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡
የዘገባው መጨረሻ፤ ራሳችን ነፃ ወጥተን ሀገራችንን ነፃ እናውጣ!!!
…..ቱኒዝያ፣ ግብፅ፣ ሊብያ፣ የመኒያ፣……ኢትዮጵያ፣……” ብሏል ርእየ- ሁለንተና – አዲስ አበባ- ኢትዮጵያ

የአሜሪካ የህግ ባለሙያዎችና አኢጋን በኅብረት ስራ ጀመሩ!

ዓርብ የፖለቲካና የሙስሊም እስረኛ ጠበቆችን ያነጋግራሉ
aba nsmne


በኢትዮጵያ በግፍ የታሰሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን በተመለከተ የአሜሪካን የህግ ባለሙያዎች ማህበር (ABA – American Bar Association) ሙሉ በሙሉ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችለውን ስራ አርብ እንደሚጀምር ተገለጸ። አዲስ አበባ ካሉ የፖለቲካና የሙስሊም ወገን እስረኞች ጠበቆች ጋር የመጀመሪያ ስብሰባ አርብ ግንቦት 23፤2005ዓም ያደርጋሉ። አቶ ኦባንግ ሜቶ የተረሱ እስረኞች ጉዳይም እንደሚካተት ጠቅሰው በፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ለታሰሩ ዜጎች ጥብቅና የቆሙ ካሉ የአዲሲቷን ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ በቀጥታ እንዲገናኙ ጥሪ አቅርበዋል።
(ABA) በሚል ስያሜ የሚታወቀውና ከተቋቋመ 135ዓመታትን ያስቆጠረው የአሜሪካ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ከ400 ሺህ በላይ የህግ ባለሙያ አባላት አሉት። ይህ በአሜሪካ ትልቅ የተባለ ማህበር በግፍ ለሚሰቃዩ ኢትዮጵያዊያን እስረኞች ድጋፍ ለማድረግ የወሰነው የአኢጋን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ በይፋ የድጋፍ ጥያቄ ባቀረቡ በቀናት ውስጥ ሲሆን፣ በጋራ በተከናወኑ ንግግሮችና የሰነድ ውይይቶች በወር ጊዜ ውስጥ ወደ እንቅስቃሴ ለመግባት እንደተቻለ ለማወቅ ተችሏል።
ከወር በፊት በተካሄደ የማህበሩ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ንግግር እንዲያደርጉላቸው በተጋበዙት መሰረት አቶ ኦባንግ ህግን abaእየተንተራሰ ዜጎችን በቁም እስርና በወህኒ ቤት እያሰቃየ ስላለው የኢህአዴግ አገዛዝ በስፋት ባስረዱበት ወቅት ማህበሩ እሳቸው ከሚመሩት ድርጅት ጋር በትብብር ለመስራት ፈቃዱን አሳይቶ እንደ ነበር አቶ ኦባንግ ለጎልጉል ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ፣ ኢህአዴግ ህግን ከለላ በማድረግ በዜጎች ላይ የሚፈጽመውን ግፍና ወንጀል፣ ለአፈና ተግባሩ ማስፈጸሚያም የጸረ ሽብርተኝነትን፣ የመያዶችን፣ ወዘተ ህጎችን በማውጣት ዜጎችን ለወህኒ ቤትና ለቁም እስር፣ ለስደት፣ ለስቃይ መዳረጉን፣ የፍትህ አካላቱን ህግን በሚያከብሩና ፍትህ በሚያስፈጽሙ ገለልተኛ አካሎች ሳይሆን ራሱ በመሠረተው ተቋም እያመረተ የሚጠቀምባቸው የፖለቲካው መሳሪያዎቹ ስለመሆናቸው፣ በመዘርዘርና ማስረጃ በማጣቀስ አቶ ኦባንግ ለጉባኤው መናገራቸውን አመልክተዋል።
ቀደም ሲል ጀምሮ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የስራ አስፈጻሚዎች የሚታወቁትም ሆነ ሚዲያው የዘነጋቸው ዜጎች ጉዳያቸው ዓለም ዓቀፍ ትኩረት እንዲያገኝ በያቅጣጫው እየተደረገ ካለው የተለያየ  ጥረት በተጨማሪ ሲመክርበት የነበረው ጉዳይ እንደሆነ በመግለጽ አስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ኦባንግ “ተጽዕኖ ሊፈጥሩ የሚችሉት አካላት በራሳቸው ሰዎች በቂ መረጃ እንዲያገኙ ማድረግ ታላቅ ተግባር ነው። ድርጅታችን እንደ ስኬት ይቆጥረዋል። ዓርብ በዝርዝራችን ካገኘናቸው የታዋቂ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪ ጠበቆች ጋር የስካይፕ ስብሰባ ይካሄዳል። በቀጣይ አገር ቤት በመሄድ ባመቻቸው መንገድ ስራቸውን ያከናውናሉ” ብለዋል።
በአሁኑ ጊዜ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የሙስሊሙን ህብረተሰብ ጥያቄ በማንሳታቸው የታሰሩት ወገኖች፣ ወዘተ ጠበቆች ጋር በስካይፕ ንግግር እንደሚደረግ አቶ ኦባንግ አስታውቀዋል። እስከዛሬ ጆሮ ያልተሰጣቸው ወገኖች ጉዳይ አደባባይ ከማውጣት በተጨማሪ የጋራ ንቅናቄው ባቋቋማቸው ግብረኃይሎች አማካይነት ወደ ህግ የሚሄዱ፣ ሌሎች አብረው መስራት የሚፈልጉ አካላት የሚያቀርቧቸውን አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን ጉዳዮች በአገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ክስ መስርቶ ለመሟገት ማህበሩ ዝግጁ መሆኑንን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “አስፈላጊውን የህግ ድጋፍ የሚፈልጉ ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች ጥያቄያቸውን ለጋራ ንቅናቄው ማቅረብ ይችላሉ” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ማህበሩ መንግስትን የሚያማክሩ፣ የሚመክሩ፣ ፖሊሲ በማርቀቅ ስራ ላይ የተሰማሩ ታዋቂ የህግ ባለሙያዎች፣ ለዓለም ዓቀፍ ሚዲያና ኔትወርኮች ቅርበት ያላቸውና ተሰሚነታቸው የጎላ በመሆኑ እንዲህ ካሉ አካላት ጋር በጨዋነት መስራት በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ለማስተጋባት መልካም አጋጣሚ ማመቻቸት እንደሆነም አቶ ኦባንግ አመልክተዋል።
“… ኢህአዴግ በስደተኛነት ስም ደጋፊዎቹን በስርዓቱ የተገፉ በማስመሰል የሃሰት ማስረጃ እያስጨበጠ በአሜሪካ፣ በካናዳና በተለያዩ የምዕራብ አገራት ያሰማራቸውና በተቀነባበረላቸው መረጃ የስደት መኖሪያ ፈቃድ ካገኙ በኋላ ስደተኛውን እንዲሰልሉና ለሥርዓቱ እንዲሰሩ እያደረገ መሆኑ፤ በተለያዩ አገራት በገቢር የተያዙ መረጃዎችና ዋቢ ክስተቶች መኖራቸውን የተረዳው የባለሙያዎቹ ማኅበር ጉዳዩን በጥልቀት እንደሚያየውና ያለውን ከፍተኛ የሰው ኃይል በመጠቀም ከአኢጋን ጋር እንደሚሰራ ከሌሎች ማኀበራት ጋር በመሆንም በተለይ በምዕራቡ ዓለም የተሰገሰጉትን አስመሳይ ስደተኞች ወደ ፍትህ የማምጣቱ ጉዳይ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን ለድርጅታቸው አረጋግጠዋል” በማለት ከዚህ ቀደም ለጎልጉል ስለተናገሩት አስተያየት እንዲሰጡ አቶ ኦባንግ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።
“ኢህአዴግን የሚደግፉ ዜጎችም ቢሆኑ ለጋራ ንቅናቄያችን ልጆቹ ናቸው” በማለት አስተያየታቸውን የጀመሩት አቶ ኦባንግ “ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ጉዳይ ላይ ምስጢረኛ ለመሆን እገደዳለሁ። አንድ ነገር ለማስታወስ ያህል ግን ምዕራባውያን አሠራራቸው መጭበርበሩን ካረጋገጡ ምህረት የላቸውም። ከሰብአዊነትም አንጻር ቢሆን አገሩ መኖር ያልቻለን ዜጋ ስደት አገር ድረስ እየተከታተሉ ማሳደድ በየትኛውም መስፈርት ተቀባይነት የለውም። በህግም አይፈቀድም። እንደዚህ ካሉት ጋር የሚተባበሩ አገሮችን ህግ ፊት በማቆም በህግ ስለፍትህ እንከራከራል” የሚል መልስ ሰጥተዋል።
ABA የሚባለው የህግ ባለሙያዎች ማህበር ዓመታዊ ጉባኤ ላይ ከሁለት ሳምንት በፊት ሲያከብር ንግግር እንዲያደርጉ የተጋበዙት አቶ ኦባንግ ሜቶ በርካታ ጉዳዮችን በማንሳት ድጋፍ ጠይቀው አዎንታዊ ምላሽ እንዳገኙ፣ ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። አቶ ኦባንግ እንደሚሉት አርብ የሚደረገው ንግግር የድጋፉና አብሮ የመስራቱ ሂደት መጀመሪያ ነው። ሥራው ጊዜ የሚወስድና እልህ የሚያስጨርስ መሆኑን ሁሉም እንዲያስተውለውና ፈጣን ውጤት በመጠበቅ ቶሎ ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ ሁሉም ዜጋ አለኝ የሚለውን መረጃ ለጋራ ንቅናቄው በመላክ ትብብሩን እንዲቀጥል ጨምረው ገልጸዋል፡፡

Wednesday, May 29, 2013

የኢትዮጵያ ትንሣኤ! (ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም)


ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
H.I.M. Haile Selassie and bronze statue of Ghanaian President Kwame Nkrumah
ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ: ፕሬዚደንት ንኩሩማ ሃዉልት
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (ኦ ኤ ዩ) የአፍሪካ ሕብረት (ኤ ዩ በየአፍሪካ አንድነትን የተካው) ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ከተማ  የወርቅ ኢዩቤልዩውን በማክበር ላይ ነው፡፡ በሜይ 1963 አፍሪካ አንድነት ሲመሰረት፤የጋናው ፕሬዜዳንት ክዋሚ ንኩርማ የመዝጊያ ንግግሩን የደመደመበት በተለይ በእድገት ላይ ያለችውንና ተቀኚ የነበሩትን የአፍሪካ ሃገራት ወደ ነጻነት ለመራችው ኢትዮጵያ ለክብሯ በመረጠውና ባዘጋጀው ግጥሙ ነበር፡፡ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን አስመልክቶ ንኩሩማ  ሲናገር: ‹‹ግርማዊ ሆይ! በጓደኞቼና በራሴ ስም የሚቀረኝ ለኢትዮጵያና ለሕዝቦቿ በተለይም ለግረማዊነትዎ ያለኝን አክብሮት በመግለጽ በዚህች ታሪካዊ ሃገር ባደረግነው ቆይታ የተቸረንን አቀባበልና መስተንግዶ ሳላመሰግን ማለፍ አይቻለኝም፡፡ ንኩሩማህ ዘወትር ባነበብኩት ጊዜ ትውስታ የሚያጭርብኝን ይህን የግጥሙን ስንኝ አሰማ፡፡  የራሱ የንኩሩማህ ቃላት እነዚህ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ ትነሳለች!
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ብሩህ አንቁ
ከለምለሞቹ ተራሮች መሃል
የጨለመባቸውን በነጻነት ጎዳና ስታጓጉዝ
የአባይ ወንዝ አናት
ኢትዮጵያ ትነሳለች!
ኢትዮጵያ የብልሆች ምድር
ኢትዮጵያ፤ የቀደምት አፍሪካ ሕግጋት ማሕደር
ለምለም የእውቀት ገበታ
የእኛ አፍሪካ የባህሏችን  አለኝታ
ብልኋ ኢትዮጵያ ትነሳለች፤ ገና
ደምቃ በሙሉ ክብር
አቤት የአፍሪካ ተስፋ
መዳረሻዋ  እድል
በ2011 በአፍሪካ ሕብረት ግቢውስጥ የግ ቀ.ኃ.ሥ. ሃውልት እንዲቆም ሃሳቡ ሲቀርብ፤የኢትዮጵያ ‹‹ታላቁና ባለራዕዩ መሪ›› በመቃወምና ኢትዮጵያዊነቱን በመርሳትና በመካድ  ሲናገር ምንጊዜም ስለ ፓን አፍሪካኒዝም ስናነሳ የሚታወሰን ክዋሚ ንኩሩማ ነው፡፡ ይህን ለመቀበል መቸገር አሳፋሪ ነው የሚሆነው›› በማለት የራሱን አሳፋሪ ክህደት ፈጸመ፡፡የከሰለ ልብ ባለቤት መሆን እንዴት ያሳፍራል! ሃፍረተ ቢስነት እንዴት ያሳፍራል! ቀደምት የአፍሪካ እንድነትን ምስረታና ተግባራዊነት ያረጋገጠን መሃንዲስ እውነታ መካድስ እንዴት ያለ አሳፋሪ ተግባር ነው፡፡የማይቻለውንና የማይሞከረውን የሁለት ጎራ ፍጥጫ፤ የ “ሞኖሮቪያ”ንና የ “ካዛ ብላንካን” ቡድናዊ መራራቅን አቀራርቦና አስማምቶ፤ አስታርቆና አዋህዶ የአፍሪካ አንድነትን ምስረታ እውን ስለመደረጉ ታሪክ የግርማዊ ቀ ኃ ሥን ውታ ጨርሶ የማይዘነጋው ነው፡፡ የአፍሪካ እንድነትን እውን ለማድረግ ያለመሰልቸት በትጋት ጥረዋል፡፡የአፍሪካ አንድነትን ለመመስረትም ስለ ፓን አፍሪካኖዝምም ለአፍሪካ ምሉእ ነጻነትም ታላቅ አስተዋጽኦ ያደረጉና አሁን ለደረሰበትም ደረጃ ተጠቃሽና ባለውለታነታቸው የማይዘነጋ ነው፡፡
….የወደፊቷን የአፍሪካን ራዕይ ከነጻነት አኳያ ብቻ ሳይሆን በአንድነታችንም አኳያ ነው የምናየው፡፡ይህን አዲስ ትግል በማወቅ ካለፈው ባገኘነው ውጤት መበረታታትና ጥንካሬ ተስፋ እናደርጋለን፡፡በመሃላችን ልዩነት እንዳለ እንገነዘባለን፡፡ አፍሪካውያን የተለያየ ባህል ባለሃብቶች ነን፤ልዩ ተሰጥኦና ልምዶች ያሉን ነን፡፡ ያም ሆኖ ሰዎች በበርካታ የሚያለያያቸው ሁኔታ ቢኖረንም በመግባባትና በመተሳሰብ አንድነት ማምጣትም እንደምንችል እንገነዘባለን፡፡… ታሪክ እንደሚያስተምረንና እንደሚያስታውሰን አንድነት ሃይል መሆኑን፤በመገንዘብ ግባችንን በማስቀደም፤ለጣምራ ግባችን የተባበረ ሃይላችንን ለዚሁ በማዋል ለዕውነተኛው የአፍሪካ ወንድማማችነት አንድነት ልንቆም ግድ ነው፡፡ …እንደ ነጻ ሰብአዊ ፍጡራን ጥረታችን አዲስ ግንኙነት ለመፍጠር መቆም ይገባናል፡፡በራሳችን መተማመንን፤ግባችን በማድረግ እኩልነትን ከሌሎች በእኩልነት ላይ መሰረት ካደረጉ ጋር ሁሉ አንድ ልንሆን ተገቢ ነው………
በግንባር ቀደም የአፍሪካ አንድነት አመሰራረት ላይ የምስረታውን አባቶች በምቃኝበት ወቅት፤ ለግላቸው የመዳብ ሃውልት ይቁምላቸው በሚል ሙግት ለመግጠም አይደለም፡፡እኔን አጅግ ያሳዘነኝ፤እራሳቸውን በከለላ ውስጥ እሰገብተው፤ እራሳቸውን መሆን ስለሚቸግራቸው፤ አጋጣሚውን በመጠቀም፤ታሪክን በማወላገድና መሰረቱን በማሳት፤ጭፍን ‹‹ራዕይ›› አለን የሚሉት በአፍሪካ መስራች አባቶች ስምና ተግባር ተከልለው፤(ይልቁንስ በራሳቸው ስምና ማንነት መቆም ባለመቻላቸው) የኢትዮጵያን የኖረና የዘመናት መታወቂያ ለማፈራረስ የቆመውንና የቆሙለትን ትልማቸውን ለማሳካት መጣራቸው ነው፡፡ ታሪክ ስለሥልጣንና ማንነት ቢሆን ኖሮ ቀ ኃ ሥን ማንም ቀድሞ አይገኝም፡፡ ቀ ኃ ሥ ከማንም የአፍሪካ መሪ የላቀ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በዘመኑ የአፍሪካ አንድነትን ከመሰረቱት አቻ መሪዎች ‹‹የአፍሪካ አንድነት አባት›› ተብለው በ1972 ዓም በተካሄደው 9ኛው የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ በይፋ ተመርጠዋል፡፡ ቀደም ሲል በምስረታው ወቅት በ1963 ዓም የመጀመርያው የአፍሪካ አንድነት ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ዳግመኛም በ1966 ድጋሚ ሊቀመንበር ሆነው እንዲመሩ ዳግም ተመርጠው በሁለት ዘመናት በሊቀመንበርነት ተመርጠዋል ፡፡ የአፍሪካን ኮሎኒያሊዝም ቅስም ለመስበርና ከአፍሪካ ምድር ጨርሶ እንዲጠፋ ለማድረግ ግንባር ቀደሙ ናቸው፡፡ከኋላ የመጣ አይን አወጣ እንዲሉ የማንም ጭራ ነስናሽ ጥብቅና የሚሹ አይደሉም ይሄው ጭራ ነስናሽ የራሱን ሃውልት ለማቆም የነግ ድጋፍ ለማግኘት የተደረገችው ይቺ በንኩሩማህ ስም የተቸረች ሙስናዊ አካሄድ የትም አታደርስም፡፡
ታሪክ በርካታ እንቆቅልሾች አሉት፡፡ምናልባት በሃውልቱ መቆም ወቅት ንከሩማህ ወይ ሞት በማለት አጥበቀው ሲሞግቱ የነበሩ ስለፓን አፍሪካኒዝም በተነሳ ቁጥር መታወሱን ብቻ ያቀነቀኑት ንክሩማህ ስለ ኢትዮጵያ ያለውን ስር የሰደደ ፍቅርና አክብሮት ቢያውቁ ኖሮ በመቃብራቸው ውስጥ መንደፋደፋቸው አይቀርም፡፡ንክሩማህ በልቡ ውስጥ ለኢትዮጵያ የተለያ ጓዳ ነበረው፡፡ምንም እንኳን ስለ ፓን አፍሪካኒዝም ቀደምት ቢሆንም ኢትዮጵያን ደግሞ እንደ አፍሪካ አንጸባራቂ የጸረ ኮሎኒያሊዝም ብርሃን በመመሰል ከቅኝ ገዢዎች ጋር ሲያደርጉ በነበረው ትግል ወቅት የዚህች የነጻ ኢትዮጵያ ኮከብነት መሪያቸው እንደነበረ ያስታውሳሉ፡፡ከዚሁ አኳያ የኢትዮጵያን የጸረ ኮሎኒያሊዝምን ጥቃት በመታገል ነጻነቷን ጠብቃ መቆየቷ የሚያኮራ መሆኑን በማስገንዘብ፤የአፍሪካ አንድነት አሽከርካሪ መሆኗንም አረጋግጠዋል፡፡
እርግጥ ንክሩማህ ስለ ፓን አፍሪካኒዝም ንቁ ተሟጋች መሆናቸው ባይካድም፤ ለፓን አፍሪካኒዝም ግን አንድም ግጥም አላበረከተም፡፡ አፍሪካ ስለአፍሪካ ብሩህ እሳቤ ያለው ቢሆንም ለአፍሪካ ግጥም አላሰፈረም፡፡ ንክሩማህ ፓን አፍሪካኒዝምንና አፍሪካ ይወድ ነበር፤ለኢትዮጵያ ግን የበረታ ፍቅር ነበረው፡፡ለዚህም ነው በምስረታው ወቅት በመዝጊያው ላይ ባደረገው ንግግሩ ላይ ስለኢትዮጵያ ግጥም ጀባ አለ፡፡ ከዓለም መሪዎች መሃል ለኢትዮጵያ ታሪካዊነትና ግንባር ቀደምትነት፤ ስለ ሕዝቦቿ መስተንግዶ የጻፈ ብቸኛ መሪ ንክሩማ ነው፡፡
ቀ ኃ ሥ ወቅቱ ሲመጣ ሃውልታቸው እንደሚገነባ አያጠራርም ምክንያቱም ‹‹እውነት በርብራብ ስር ወድቃ አትቀርም፤ ቅጥፈትም በዙፋን ላይ ተኮፍሶ አይኖርምና››::
ወደኋላ መለስ ብለን ስናስታውስ፤ ንክሩማህ የበረታ ፓን አፍሪካኒስት ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ‹‹ትንቢተኛም›› ነበር፡፡ ንክሩማህ ማየት የተሳናቸው ባለራዕዮች ኢትዮጵያን ወደ ዘር ፖለቲካ አረንቋ ውስጥ ከመድፈቃቸው አስቀድሞ ኢትዮጵያ ገና እንደምትልቅ ያወቀ ነበር፡፡ንክሩማሕ የኢትዮጵያን ገኖ መዝለቅ ሃፍረት ለባሾች ‹‹የአፍሪካ ትንሳኤ …. ከማለታቸው በፊትና ከመቀላመዳቸው አስቀድሞ ያውቅ ነበር፡፡ንክሩማህ ባለጊዜ አስመሳዮች ለራሳቸው ስም ለመገንባት ጉብ ቂጥ ከማለታቸውና ‹‹ኒዮሊቤራሊዝም›› ከመዝፈናቸውና ደሟን ጨርሰው እንባዋን ከመምጠታቸው አስቀድሞ ስለማንኛውም በዝባዢና አስመሳይ ለቀስተኛ ጠንቅቆ ያውቅ ነበር፡፡
በእርግጥም የንክሩማህ ግጥም ‹‹ትንቢት›› ነበር፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ትነሳለች እንደ ንጋት ጸሃይ በርታ እንደ ውድቅት ጨረቃ ደምቃ ኢትዮጵያ ትነሳለች! ከምር ገና በላይዋ ላይ ያጠላውን ጥቀርሻ ዲክታተርሺፕ አስወግዳ ት ትነሳለች፡፡ኢዮጵያ ካጠመዳት ክፉ ደዌ ተላቃ እንደገና እንደ ብርቅዬ አልማዝ ታበራለች! ከዘረኝነትና ሃይማኖት ክፍያ ትላቀቃለች፡፡ ኢትዮጵያ ከወረራት የመከራ ከበባ ተላቃ፤ ልጆችዋን ካስመረራቸው ክፉ አሳቢና እኩይ ምርጊት አላቃ እጆችዋን ከተበተባት የዘርና የጎሳ ፖለቲካ፤ ከችግርና ከመከራ፤ ከእልቂትና ከደዌ ነጻ አድርጋ ልጆችዋን በአንድነት ታቅፋለች፡፡  ኣምላክም መልሶ ያቅፋታል::
ንክሩማህ እውነተኛው የኢትዮጵያ ልጅ ነው፡፡መጤዎቹ ኢትዮጵያ የ100 ዓመት ታሪክ ነው ያላት ቢሉም ንክሩማ ግና አስቀድሞ ሃሰት በማለት ኢትዮጵያማ የሰው ዘር መገኛ ማዕከል ነች ብሏቸዋል፡፡ ኢትዮጵያን በፈላጭ ቆራጭነት ሊገዙና ሕዝቦቿንም ለመራና ሰቆቃ ሲዳርጉ ንክሩማ ግን አስቀድሞ ‹‹እምቢኝ! ኢትዮጵያማ የአፍሪካ አንጸባራቂ ሉል ናት፡፡ ማንጸባረቅ ማብራት አለባት! ልቀቋት ትግነንና ታብራ ብሏል፡ ንክሩማ ‹‹ ኢተዮጵያ የብልሆች ሃገር ናት፤አባይን የጦር መንስኤ ሊያደርጉ ሲዶልቱ ንክሩማ እምቢኝ! ‹‹ኢትዮጵያ የአባይ መመንጫ ናት›› አባይ ደሞ የህይወትን ስጦታ ለአፍሪካ ያድላል ብሏቸዋል፡፡ መንፈሳችንን ለማጉደፍና ለማጣጣል ሲሸርቡና ለመከራና ለስቃይ ሲያዘጋጁን፤ ንክሩማ እምቢኝ!‹‹ኢትዮጵያማ የአፍሪካ ራዕይ ተስፋ ነች›› አላቸው፡፡ ንክሩማ የጋና ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያም ልጅ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በተስፋ አስቆራጭ ትቢያዎች ልንቆሽሽ መስሎ ሲሰማን በንክሩማ ትንቢታዊ አባባል ብርታት እናግኝ፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ገና ትትነሳለች›› ስለዚህም በግርማዊ ቀ ኃ ሥላሴና በንክሩማ  መሃል ውድድር የለም፡፡ ሁለቱም የኢትዮጵያ የተከበሩ ልጆች ናቸውና:: ንክሩማን ማክበር ማለት ቀ ኃ ሥላሴን ማክበር ነው፡፡ የሜይ 1963ቱን የንክሩማን ግጥም ሳነብ፤ ቀ ኃ ሥላሴ በኦክቶበር 1963 በተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ ያደረጉት ንግግር ትዝ ይለኛል፡፡ በዚያ ንግግራቸው ቀ ኃ ሥላሴ ለአፍሪካን ፓን አፍሪካኒዝም ጥብቅና ከመቆማቸውም ባሻገር የአፍሪካን  ነጻነት ጠብቆና አክብሮ ለማቆየት የሚያስፈልገውን አይዲዮሎጂ በሚገባ አስገንዝበው ነበር፡፡
…አንዱን ዘር ከፍተኛ ሌላውን ዝቅተኛ አድርጎ የሚያሳየው ፍልስፍና ጨርሶ እስካልተወገደ ድረስ፤ አንደኛ ዜጋና ሁለተኛ ዜጋ የሚለው ደረጃ እስካልፈረሰ ድረስ፤ የአንድ ፍጡር ቀለም ከዓይኖቻችን ቀለም የተለየ ትርጉም እንደሌለው እስካልተረጋገጠ ድረስ፤ሁሉም ሰብአዊ መብቶች ከዘርና ከጎሳ ከቀለም ልዩነት ባሻገር ለሁሉም እኩል እስካልሆኑ ድረስ፤ በተስፋነት ብቻ የሚታሰቡ እንጂ አንዳችም እርባና አይኖራቸውም… እኛ አፍሪካዊያን አህጉራችን ከዳር እስከዳር ሰላም እስክትሆን ድረስ አስፈላጊ ከሆነ ትግላችንን አናቆምም፡፡ ደግሞም ድልን በእጃችን እንደምናደርግ ጥርጥር የለንም፡፡ መልካምነት እኩይነትን እንደሚረታው ስለምንገነዘብ ድል እንደማይርቀን እርግጠኞች ነን፡፡
ቦብ ማረሊም እነዚህን ቃላቶች ለዜማው ‹‹ዋር›› (ጦርነት) ለሚለው የአፍሪካ የትግል ዜማ የሆነውን  ሙዚቃውን አጅቦበታል፡፡(ምናለ አንድ ባለሙያስ የንክሩማን ግጥም ወደ ዜማ ቢለውጠው… ኢትዮጵያ ትትነሳለች፤ ትገናለች…  ታበራለች…. ወደ ላይ ትወጣለች::)
በምትገነዋ ኢትዮጵያ አንድን ጎሳ፤ ሃይማኖት፤ቋንቋ፤ጾታ ከሌላው አብልጦ የሚያጎላ፤ ፍልስፍና አይኖርም፡፡ በኢትዮጵያ አንደኛ ደረጃ ዜጋና ሁለ፤ተኛ ደረጃ ዜጋ አይኖርም፡፡በነገዋ ገናና ኢትዮጵያ ዘር ጎሳ፤ ሃይሞኖት፤ወረዳ፤ጾታ፤ሁሉ ከዐይኖቻችን ቀለሞች መለያየት ያለፈ ትረጉም አይኖራቸውም፡፡ በምትገነዋ ኢትዮጵያ ሁሉም እኩል የሰብአዊ መበት ባለቤት ይሆናል፡፡
ወይ ጉድየአፍሪካ አንድነት ድርጅትየአፍሪካ  ሕብረት
ወይ ጉድ! የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/ የአፍሪካ ሕብረት ስለ አፍሪካ አንድነት/አፍሪካ ሕብረት አስተያየት ማስፈር ልብ ሰባሪ ጉዳይ ነው፡፡ በ2013 በዓለም ካሉት 47ሃገራት እድገት ከማያሳዩት ሃገራት መሃል 36ቱ በአፍሪካ ይገኛሉ፡፡ በአንድ ወቅት የታንዛኒያ መሪ የነበሩት ጁሊየስ ኔሬሬ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ‹‹የመሪዎች የወሬ ማሕበር›› በማለት ጠቅሰውት ነበር፡፡ ሌሎች ደግሞ‹‹የፈላጭ ቆራጭ ጋጠወጥ ራስ ወዳድ መሪዎች ክበብ›› ይሉታል፡፡ጋናዊው ታዋቂ ኢኮኖሚስት ጆርጅ አይቴ ‹‹እባካችሁ ስለ አፍሪካ አንድነት ድርጅት ማውራት ይብቃን፡፡ በአህጉራችን ካሉት ድርጅቶች ሁሉ አዘቅዝቆ የሚሄድና እርባና ቢስ የሆነ ድርጅት ነው፡፡‹‹ዴሞክራሲን›› እንኳን በሚገባ ሊተረጉም ያልቻለ ድርጅት ነው፡፡ የራሱ የሆነ ወጥነት ያለው ተግባር ጨርሶ የሌለው ነው›› ይለዋል፡፡
የአፍሪካ ሕበረት ዋና መስሪያ ቤት በቻይና መንግሥት ምጽዋት በ200 ሚሊዮን ዶላር ተሰራ በተባለና የቻይና ስጦታ “ለታዳጊዋ” አፍሪካ በተበረከተ ጊዜ ቅሬታዬን አስቀምጬ ነበር፡፡ የቻይና የግንባታ ኩባንያ ስራውን በአጠቃላይ ከቻይና በተገኘ ቁሳቁስና ቻይናዊያን ዜጎች ሰራተኞች ገነባው ሲባልና አስፈላጊውን ቁሳቁስ ሁሉ ያሟላውም ያው ቻይና ኩባንያ ነው ሲባልና ወንበርና ጠረጴዛም ሳይቀር ከቻይና ተጓጓዘ መባሉም ክፉኛ አሳዝኖኝእንደነበር ገልጫለሁ፡፡ በስጦታው ርክክብ ወቅትም የአፍሪካ ‹‹ሃፍረተ ቢስ መሪዎች›› ተርታ ገብተው እንደ ውሃ ወረፍተኛ ለቻይና የምስጋና ውርጅብኝ ሲያጎርፉ  ‹‹የአፍሪካ ትንሳኤ… የአፍሪካ ሬኔሳንስ ተጀመረ ለማስቀጠልም መንገዱን አግኝተናል በማለት አሸሸ ገዳሜ ሲሉ ነበር፡፡››
አፍሪካ አልተነሳችም አልኩ፡፡ አፍሪካ ለልመና ተዳርጋለች፡፡‹‹የቻይና ትንሳኤ በአፍሪካ ተጀምሯል›› በአዲስ አበባ የተገተረው አዲሱ የአፍሪካ ሕብረት ግንብ የአፍሪካ የሃፈረት ግንብ  እንጂ የአፍሪካ ኩራት ግንብ አይደለም፡፡ የአፍሪካ መሪዎች በአንድነት ለአፍሪካ ሚሆን ቋሚ ቢሮ ለመገንባት አቅሙን ካጡ፤ ለአፍሪካ ትንሳኤ የሚሆነውን መስራት ከተሳናቸው ያሁኑን ግንብ ‹‹የአፍሪካ ምጽዋተኞች አንድነት አዳራሽ›› ከማለት አላልፍም:: የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/ የአፍሪካ ሕብረት እና ሰብአዊ መብት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/የአፍሪካ ሕብረት በአፍሪካ የፖለቲካ፤ የኤኮኖሚ እና የሶሻል ግንኚነቶችንና ነጻነትን ከማጠናከርና ተግባራዊ በማድረግ ወደ ልማት አቅጣጫውን ከማራመዱ አስቀድሞ ማከናወን ያለበት ሰብአዊ መብትን ነው፡፡ የአፍሪካን  ልማት  ለማከናወንም ሆነ አቅዶ ወደ ግብ ለማድረስ የሰብአዊ መብት መከበር ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው፡፡ ሕዝቦች በነጋ በጠባ ለመከራና ስቃይ እየተዳረጉና የግፍ ኑሮ፤ የባርነት ቀንበር ተሸክመውጀርባቸው በተደራራቢ ችግር ጎብጦ ልማትን አመጣለሁ ብሎ ሩጫ ለመውደቅና ለከፋ መከራ ለመዳረግ መጣር ብቻ ነው፡፡
የአፍሪካ አንድነት ጸረ ኮሎኒያሊዝም፤ኒዮ ኮሎኒያሊዝም ጸረ ጸረ ጸረ ብሎ የሚደረድራቸው ማለቂያ የሌላቸው ጸረዎች በችግርና በመከራ ላሉ ሕዝቦች አንዳችም ጠቀሜታ የሌላቸው ልፈፋዎች ብቻ ናቸው፡፡ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/ የአፍሪካ ሕብረት ጤት አልባ ከዚያም አልፎ ዋጋ ቢስ መሆኑን ለሰብአዊ መብት ካለው አመለካከትና ከከወነው ተግባር ነው፡፡ በበርካታ የአፍሪካ ሃገራት ክፍሎች ጦርነት የየቀናት ክስተት ነው፡፡ሰዎች በየቦታው ሲተላለቁ የአፍሪካ አንድነት እጁን አጣጥፎ ከመመልከት ውጪ አንዳችም እርምጃ አልወሰደም፡፡ የአፍሪካ ጉልበተኛና ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ከውጪ ወራሪ በከፋ መልኩ ሕዝቦችን ሲጨፈጭፉ ለስደት ሲዳርጉ በግፍ ከመኖሪያቸው ሲያፈናቅሉ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አይኑን ጨፍኖ፤ ጆሮውን ደፍኖ፤አፉን ለጉሞ የድርጊቱ ተባባሪ መሆንን የመረጠ ነው፡፡ ለሕዝቦች እልቂት ደንታ የሌ፤ልው ድርጅት/ ሕብረት፡፡ የሩዋንዳ እልቂት በሚሊን የሚቆጠሩትን ንጹሃን ዜጎች በሞት ሲቀጥፍ የአፍሪካ አንድነት ቢሮውን ዘግቶ አርቲ ቡርቲ ከማራገብ ውጪ ምንም ያደረገው አልነበረም፡፡ ሌላው ቀርቶ የአፍሪካ አንድነት ግድያውን ‹‹ጄኖሳይድ›› ለማለት እንኳን ድፍረቱና ወኔው አልነበረውም፡፡!
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/ የአፍሪካ ሕብረት ሶማልያ ለሁለት አሰርት ዓመታት በመበታተን ላይ ሳለች፤ የጎሳ መሪዎች ተቀራምተዋት ለጥፋት ሲዳርጓት እንኳን መድረስ ቀርቶ ከሩቅ ሆኖም ማስጠንቀቂያም ሆነ ማስፈራሪያ አልሰነዘረም፡፡ ለተፈጠረው ችግር ሌሎች ሃገራት ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ በሚያመቻቸው መንገድ ጣልቃ ገብተው ሲያማትሩ የአፍሪካ አንድነት በቂ ጦር እንኳን ለመላክና ሕዝቡን ከመከራ ለመታደግ አልሞከረም፡፡ በኮት ዲቭዋር የተፈጠረውን ችግር የፈረንሳይ ወታደሮች ገብተው ሲፈነጩበት የአፍሪካ እንደነት በስፋራው ቀርቶ በአካባቢውም አልደረሰም፡፡ በማሊም የተፈጠረውን ሽብር ለማስታገስና ስርአት ላመስያዝ የፈረንሳይ 5000 ወታደሮች ሲዘልቁ የአፍሪካ አንድነት ከጠቅላይ ቢሮው ንቅንቅም አላለም፡፡ በኢትዮጵያም የምርጫ  በጠራራ ጸሃይ ሲሰረቅና ተሸናፊው አሸናፊ ሆኖ ሲወጣ በዝምባብዌ፤በኬንያ፤ በዩጋንዳ ተመሳሳይ የምርጫ ውጤት ዘረፋ ሲካሄድ የአፍሪካ አንድነት በገለልተኛነት ከዳር ቆሞ ከተመልካችነት አላለፈም፡፡
የአፍሪካ ሕብረት የሰብአዊ መብትን ጥሰት በተመለከተ፤ ወንጀለኞችን መደገፍን  ሙያ ብሎ ይዞታል፡፡ የሱዳኑ ኦማር አል በሺር በሰብአዊ መብት ጥሰትና በጦር ወንጀለኛነት በግፍ ጭፍጨፋ በዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተከሰው መያዣ ሰነድ ሲተላለፍባቸው ‹‹የአፍሪካ ሕብረት አባል ሃገራት በሮም የተፈረመውን የፍርድ ቤቱን ስምምነት አናከብርም በማለት የሱዳኑን አልበሺርን አሳልፈን አንሰጥም አቋም ያዙ›› ይህ ደግሞ ነግ በኔ በሚል ስጋትና አስቀድሞ መንገድ ለመዝጋት ሲሉ ተመሳሳይ ወንጀለኛ መሪዎች የወሰዱት አቋም ነበር፡፡ በዚህም የአፍሪካ ሕብረት ተግባሩን መወጣት ባለመቻሉና ፍላጎትም በማጣቱ አይ ሲ ሲ ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ጣልቃ መግባቱ አስፈላጊ ሆነ፡፡ ከ2011 አንስቶ በሰባት የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ ይሄው ፍርድ ቤት የማጣርያ ምርመራውን በማካሄድ ላይ ነው፡፡
የአፍሪካ ሕብረት የሌለው ቢሮ ያላቋቋመው የመብት ማስከበርያ ጽ/ቤት የለም ግን አንዳቸውም ለተግባር አልበቁም፡፡ የአፍረካ ሕብረት የሰብአዊ መብት ቢሮ፤ የአፍሪካ ሕብረት የልጆች መብት፤ የሴቶች መብት፤ በማለት በርካታ ኣዋጅ አውጥቷል ቢሮም አቋቁሟል፡፡ የአፍሪካ ሕብረት የፖለቲካ ቢሮም አለው፡፡ የዚህም ቢሮ ተግባሩ ሰብአዊ መብትን ማስከበር፤ የዴሞክራሲ ስርአትን ትግበራ ማረጋገጥ፤ምርጫዎችን በአግባቡ ተካሂደው የህዝብ ፍላጎት ማሟላት ቢሆኑም አንዱንም አላከናወነም፡፡ በአባል ሃገራት ምርጫ ወቅት ዳጎስ ያለ ወጪ በመመደብ ታዛቢዎች ቢሊክም ታዛቢዎቹ ሆቴላቸውን ሳይለቁና ምርጫ ጣቢያዎችም ቢሆን እንደነገሩ ደረስ መለስ ከማለት አልፎ አንዳችም ውጤት ያለው ትዝብት አላከናወኑም፡፡ በየሄዱበት ሃገር ያለው ገዢ ፓርቲ የሚሰጠውን መግለጫ ደግፈው ተጋብዘውና ተሸልመው ከመመለስ ውጪ ምንም አላደረጉም:: በ2010 ነፍሳቸውን በተገቢው ቦታ ያኑረውና መለስ ዜናዊ 99.6 በመቶ ምርጫ አሸነፍኩ ሲል፤በቀድሞው የቦትስዋና ፐሬዜዳንት ማሲሬ ለታዛቢነት የተሰማራው ቡድን ምርጫው ፍትሃዊና ሰላማዊ ነበር፤ የምንግስት መዋቅርን መጠቀምና ሕገ ወጥ የሆነ ሂደትም መራጩንም ማስፈራራትና መስገደድም ያልነበረበት ምርጫ ነበር በማለት ማሲሬ ቀልማዳ ትዝብቱን ተፈራረመ፡፡ ሲደመድምም ምርጫው የአፍሪካን አንድነት የምርጫ ደንብና ስርአት ያሟላ፤ የመራጩን ሕዝብ ፍላጎት ያካተተ፤… የአፍሪካ ሕብረት ተቃዋሚዎች ከምርጫው አስቀድሞ ያሰሙትን ቅሬታ የሚያረጋገጥ አንዳችም ሁኔታ አልታየም፡፡ ክሱን ወይም ውንጀላውን የሚረጋግጥ አንዳችም ሁኔታ አላየንም በማለት ነበር፡፡
አፍሪካ ከመቼውም በከፋ መልኩ አሁን ተበታትናለች፡፡ፓን አፍሪካኒዝም አፈር ዲቤ በልቷል፤ እድሜ ለአፍሪካሕብረት፡፡አሁን በአፍሪካ ላይ በማንዣበብ ላይ ያለው አዲስ አየዲዮሎጂ ነው፡፡ የአፍሪካ ጨቋኝ ገዢዎች በድፍረትናበማን አለብኝነት የዘር ብሔርተኝነትን በስልጣን ለመቆየት አመቺ ስለሆናቸው በመንዛት ላይ ናቸው፡፡ የዘርማንነት፤ የዘር ጥራት፤የዘር መኖርያ፤ በሚል ሰበብ ሕዝብን መጨፍጨፍና ከራሳቸው ከገዢዎች ውጪ ያለውን ዘር በሚልያስቀመጡትን ሁሉ ለማጥፋትና ብቸኛ ዘር ሆነው ለመኖር እየገሰገሱ ነው፡፡
በኢትዮጵያም ‹‹የብሔር ፌዴራሊዝም›› በሚል ቆንጆ መጠቅለያ የተጀቦነ ፖለቲካዊ ሂደት እየተንደረደረነው፡፡ኢትዮጵያዊያን በማንነታቸው በትውልዳቸው በቀያቸው መገለልና መገፋት መፈናቀል እየደረሰባቸው ነው፡፡በክልልተደልድለው ያለፍላጎታቸው ስም ወጥቶላቸው ለጥቃት ተዘጋጅተዋል፡፡ ጥቂት የገዢው መደብ አባላት በድሎት እንዲኖሩናያለሃሳብ እንዲንደላቀቁ 80 ሚሊዮን ሕዝብ ለግፍ ተዳርጓል፡፡እንዳይናገር በሆዳም ካድሬዎችና ለጊዜው ገዢዎችእራሳቸውን በሸጡ አጎብዳጆች ተወጥሮ መከራ እየወረደበት ነው፡፡ ሆዳሙ ያዜማል ሆዳሙ ይገጥማል፤ ሆዳሙ ይጨፍራል፤ሆዳሙ ቅኔ ያፈሳል ሆዳሙ ያጨበጭባል ሆዳሙ ይደሰኩራል፤ ሆዳሙ ሆዱን ይሞላል ሕዝቡ ግን ለመከራና ስቃይተዳርጓል፡፡
ታላቁ የአፍሪካ ደራሲ ቺኒዋ አቼቤ  (Things Fall Apart) ለምንድን ነው በአፍሪካ ሁሉም ነገርየሚፈራርሰው በሚል መነሾ ጻፈ፡፡የኔ መለስ አጭር ነው፡፡ባለፈው የግናሽ ምእተ አመት ነጻነት የአፍሪካን ግፈኛገዢዎች ተጠያቂ የሚያደርግ ድርጅት ለመፍጠር ባለመቻሉ ነው እላለሁ፡፡ላለፉት 50 ዓመታት የአፍሪካ መሪዎችተጠያቂነትን አሻፈረን ብለዋል፡፡ የዚህ ተጠያቂ ሕዘቡ እንደሆነ ለማሳመን ጠረታቸው መጠን የለውም፡፡አፍሪካ ከቅኝገዢዎች በተተወለት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው፡፡ሰበብ እየተደረገ ዘወትር በማያልቅ ጥሪ የሚጠቆመው፤ ነጮች፤ የቅኝገዢዎች ቅሪት፤ ካፒታሊዝም፤ ኢምፕሪያሊዝም፤ ኒዮ ሊቤራሊዝም፤ ግሎባላይዜሽን ነው መሸሻው፡፡ ….. የዓለምየገንዘብ ተቋም ነው፤የዓለም ባንክ ነው፤……የአህጉሩ ያለማደግና ያለመልማት ሰበቡ  የመኑስናው፤ የመልካምአስተዳደር እጦት ሁሉም በመጥፎና እርኩስ መንፈስ የመጡ እንጂ የአህጉሩ አይደሉም ማለት ይዳዳቸዋል፡፡ነገሮች ሁሉ በአፍሪካ ፍርስርሳቸው የሚወጣበት ሰበብ የአፍሪካ ‹‹መሪዎች›› የሕዝቦቻቸውን ሰብአዊ መብትባለማክበራቸው ነው፡፡የአቼቤን አባባል ለማጠናከር፤ አፍሪካ አሁን ያለችበት ሁኔታ ውስጥ ያለችበት መንስኤየአፍሪካ መሪዎች እንደመሪ ሊሆኑና ሊያደርጉ የሚገባቸውን የመሪነት ሚና መጫወት ባለመቻላቸው ነው፡፡ ‹‹ጥቂትየአፍሪካ መሪዎች የሕዝቦቻቸውን ክብርና ሰብአዊ መብት በአግባቡ ያከብራሉ፡፡ አፍሪካ መሪዎች ናቸው በሚባሉትገዢዎቿ እያደናቀፉ እየጣሏት እንዴትስ መነሳትና መግነን ትችላለች? ለመነሳት በሞከረች ቁጥር ያንን የመርገምትቦት ጫማቸውን ማጅራቷ ላይ አሳርፈው እንዳትነሳ፤ እንዳታድግ፤ እንዳትለማ ረግጠው ይዘዋት እንዴት ብላ ነውየምታድጋው? ያም ሆኖ ጊዜው ሲደርስ አፍሪካ ፍርስርሳቸው የወጡባት አፍሪካ ተሰባስበው አንድ የገነነች አፍሪካሆና ትነሳለች!ስለዚህም ለአፍሪካ አንድነት/ አፍሪካ ሕብረት 50ኛው ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ ለግ ቀ ኃ ሥላሴና ለክዋሚህንክሩማህ የማበረክተው ስንኝ
ኢትዮጵያ ከፍ በይ! የኢትዮጵያ ትንሳኤ! የአፍሪካ ትንሳኤ
ኢትዮጵያ የአፍሪካ አንጸባራቂ ማዕድ ትነሳለች ትገናለች
ከፈላጭ ቆራጭ ስርአት ተላቃ
የግድበ አፍሪካ ምድር እንደሚበራው የበጋ የንጋት ፍንጣቂ
በአፍሪካ ምሽት ሰማይ እንደምትበራው የጨረቃ
ብርሃን አንቂ ኢትዮጵያ ትንሳኤዋ ያበራል ትገናለች::
ኢትዮጵያ ከራስ ደጀን ጉብታ ጫፍ ትንሳኤዋ ይታያል
እስከ ኪሊማንጃሮ ዘልቆ ይጠራል
ከፖለቲካው አረንቋ መታወቂያነት
እስከ ሀገራዊ ኩራት በልዩነት
ኢትዮጵያ አስከብራ የሁሉንም ማንነት ትነሳለች::
በአፍሪካ ምድር የነጻነት ብርሃኗን ትረጫለች
የሊቃውንት ሃገር ኢትዮጵያ ከመንደርተኛ አዋቂዎች በላይ ተንብያ
ህዝቦቿ ተሰባስበው ተዋህደው ተፋቅረውና ተግባብተው
ሰብአዊነትን ወግነው አንድነትን መቻቻልን አንግበው
ኢትዮጵያ ትነሳለች ትገናለች::
ኢትዮጵያ የነግህ የአፍሪካ ተስፋ
በትንሳኤዋ የረገጧትን የጨፈለቋትን  አልፋ
ቅጥፈታቸውን ጭካኔያቸውን ሙስናቸውን
ያን ያለፈ ዘመናቸውን ከነምኞታቸው ገንዛ በብረት ሳጥን
የሕግ የበላይነትን አስከብራ፤ኢትዮጵያ እንደ ጸሃይ ታበራለች::
በምድሯም ሰላም እስከ ዘልዓለሙ እንዲሰፍን ታደርጋለች
የኢትዮጵያ ትንሳኤ በማይደፈሩት ሃቀኛ ወጣቶቿ
ከፍ ትላለች ተደግፋና ተሞሽራ በልጆቿ
ኢትዮጵያ እስከማዕዜኑ ትገናለች
ለወጣቱ ትውልድም  የዘልአለም ቤቱ ትሆናለች::
*የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from):
(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::) ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

ኢህአዴግ የሚያሸንፈው መቼ ነው?

ጌታቸው ሽፈራው

መቼም ይህን ጥያቄ ስጠይቅ የግንቦት 20ን ‹‹ድል››፣ የ2002ና የባለፈውን ሚያዚያ 2005 ዓ/ም የቀበሌ፣ የወረዳ……ምርጫም ጨምሮ በመከራከሪያነት በማንሳት ምን ነካው ኢህአዴግ እኮ እያሸነፈ ነው የሚሉ አይጠፋም፡፡ ለእኔ ማሸነፍ ማለት የህዝብን ልብና አዕምሮ (hearts and minds) መያዝ ሲቻል ነው፡፡ በሀይልማ ከሆነ ጣሊያን፣ ጀርመን፣ እንግሊዝ በአጠቃላይ ቀኝ ገዥዎቹ አፍሪካውያንን በወታደራዊ ሀይልና በሌሎች አቅሞቻቸው በመብለጣቸው እስከ መቶ አመት ድረስ ገዝተዋል፡፡ በኤሲያን ደቡብ አሜሪካ ደግሞ ከ200 እስከ 800 አመትም የተገዙ ህዝቦች ነበሩ፡፡ ለጊዜው አሸናፊ የመሰሉት ቅኝ ገዥዎች የእነዚህን ህዝቦች ልብ መግዛት ባለመቻላቸው ጊዜ ጠብቀውም ቢሆን ተሸናፊዎች ሆነዋል፡፡ ኢህአዴግ አሸነፍኩት የሚለውን የመንግስቱ ሀይለማሪያም ደርግ ጨምሮ ህዝባቸውን በሀይል ጨምድደው የኖሩ ስርዓቶች የኋላ ኋላ ተሸንፈዋል፡፡ እነዚህ አካላት የተሸነፉት ህዝብን በሀይል እንጂ በሀሳብ ማሳመን ባለመቻላቸው ነው፡፡ ሰውን በሆዱ አሊያም በግድ ለዘላለም መግዛት አይቻልም፡፡ አንድም የሚፈልገው ነገር በየጊዜው ስለሚጨምር ይህን በየጊዜው የሚጨምርን ነገር ማሟላት አይቻልም፡፡ ማሟላት ቢቻል እንኳ ሰው የመጨረሻ ፍላጎቱ ነጻነት ነውና ዳቦ ጠግቦም ሆነ ሳይጠግብ ነጻነቱን መጠየቁን አያቆምም፡፡
ኢህአዴግም እስካሁን የኢትዮጵያውያንን ልብ በሀሳብ መግዛት አልተቻለውም፡፡ በብሄር፣ በስራና ጥቅማጥቅም፣ በማሳፈራራት፣ የሌሎቹ አስተሳሰብ እንዳይደርስ በማገድ ስልጣኑን ለማራዘም ቀና ደፋ እያለ ነው፡፡ ኢህአዴግ በዋነኝነት አሸንፍበታለሁ ብሎ የጀመረው የብሄርን ፖለቲካ ቢሆንም ይህ ቀመር የኢትዮጵያውያንን ልብ ሊገዛለት አልቻለም፡፡ ይህ እንደማያዋጣው ያሰበው ኢህአዴግ ኢትዮጵያውያን ሊሸነፉበት የሚችሉትን አስተሳሰቦች ለይስሙላህም ቢሆን ከጀመረ ጥቂት አመታት ተቆጥረዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል የሚሊኒየም በዓልና የሰንደቅ አላማ ቀን የመሳሰሉትን አገራዊ እሴቶች ማንሳት ጀምሯል፡፡ ይሁንና እነዚህንም ቢሆን ከልብ ሳይሆን ለመቀስቀሻነት ብቻ እየተጠቀመባቸው በመሆኑ ሊያሸንፍባቸው አልቻለም፡፡ በመሆኑም ኢህአዴግ  እስካሁን ኢትዮጵያውያንን ማሸነፍ አልቻለም፡፡
ኢትዮጵያውያን የሚሸነፉት መቼ ነው?
ኢህአዴግ ለጊዜው ኢትዮጵያውያንን በበላይነት መራ እንጂ አላሸነፋቸው እያልን ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በአንድ አካል በሀይል ቁጥጥር ስር የወደቀ ሰው በዚህ አካል ሀይል ቁጥጥር ስር እንዲገባ ያደረገውን እምነቱን ጣል እርግፍ አድርጎ እስካልጣለ ድረስ ተሸናፊ ሊባይ አይቻልም፡፡ በመሆኑም ለእኔ እነ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት አለሙ፣ ውብሸት ታዬ፣ በቀለ ገርባ የመሳሰሉት ዜጎች በኢህአዴግ ቁጥጥር ስር ቢሆኑም ከአካላቸው ውጭ እምነታቸውን መቆጣጠር እስካልቻለ ድረስ ተሸናፊዎች አይደሉም፡፡ በተቃራኒው ትናንት  ‹‹ዜሮ ዜሮን›› ዘፍነው ዛሬ ‹‹ይቀጥል!›› ያሉት እነ ሰለሞን፤ ትንንት ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድ ድምጽ የነበሩትና አሁን በክብ ጠረጴዛ ለስርዓቱ ድምጽ የሆኑት እነ ሚሚ እንደልባቸው ቤተመንግስት መግባት ቢችሉም ኢህአዴግ ከልብና አዕምሯቸው በላይ ገዝቷቸዋል አሳዛኝ ተሸናፊዎች ናቸው፡፡ አሳዛኝ ተሸናፊ መጀመሪያ የተነሳበትን አያውቅም አሊያም ሲሸነፍም ድሮ ከነበረው አመለካከት በተቃራኒ ሁለመናውን የሚማረክ ነው፡፡ የእነዚህ ኢትዮጵያውያን ሽንፈት ጠንካራ ወታደር እያለው እራሱን ለጠላት በምርኮ እንዳቀረበ ጀኔራል እቆጥራቸዋለሁ፡፡ በተቃራኒው እነ እስክንድር ምንም ወታደር በሌለበት ብቻውን ከጠላት ጋር የሚፋለም ሲፋለም ተይዞ ስለ ክብሩ ሞትን ከሚጠባበቅ ጀግና ጀኔራል ጋር ቢመሰሉ አያንስባቸውም፡፡ ሽንፈት እንዲህ ለእየቅል ነው፡፡ ለአብዛኛዎቹ በተለይም ለታዋቂዎቹ መሸነፍ ጥቅም፣ ዝና ቀዳሚው ሲሆን በርካታዎቹ ኢትዮጵያውያን እንዳይሸነፉ ያደረጋቸው ኢትጵያውይነት ነው፡፡
አንድ ሰው በራሱ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ፣ ጉራጌ.. መሆኑን በማመኑ አሊያም ሌሎች በዚህ ምድብ ውስጥ ስላስገቡት ብቻ በብሄር ስም ሊጠራ ይችላል፡፡ አምኖም ሆነ ተወናብዶ በብሄር ማመኑ በራሱ ችግር ላይኖረውም ይችላል፡፡ ብሄር ችግር የሚያመጣው የመከፋፈያ መንገድና ለፖለቲከኞች መጠቀሚያ በሚያመች መልኩ ሲመነዘር ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ብሄር ለመከፋፈያና ለፖለቲከኞች መጠቀሚያ በሚያገለግል መልኩ ቢመነዘርም አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን በዚህ ደስተኛ ባለመሆናቸው ኢህአዴግም ለማስመሰያነት  የሚጠቀምበት የአንድነት አጀንዳ ለማንሳት ፈራሁ ተባሁ እያለ ይመስላል፡፡ ኢትዮጵያውያን በዚህ በኩል ከመሸነፍ ይልቅ ማሸነፍ ወደሚችሉበት መንገድ ተቃርበዋል ማለት ይቻላል፡፡
በተቃራኒው ግን ብሄርን በዋነኛ መሳሪያነት የሚጠቀመው ኢህአዴግ ያሸነፈ የመሰላቸው ‹‹እሳትን በእሳት›› በሚል ይህን ቀመር የመረጡ አልጠፉም፡፡ ኢህአዴግ ያደርጋቸውን እያንዳንዱን እንቅስቃሴዎች ከብሄር አይን ብቻ በማየት በብሄር ቀመር ለመፍታት መጣር እስካሁንም ተቃውሞው ጎራ ውስጥ አልጠፉም፡፡ ይህ አንድ ስልት አይደለም ማለት አይቻልም፡፡ ሆኖም በተለይ በኢትዮጵያውይነት እናምናለን የሚሉትም አጀንዳ ሲያደርጉት ፖለቲካውን መርህ አልባ ያደርገዋል፡፡ ለአብነት ያህል ከየክልሉ የሚባረሩ ኢትዮጵያውያንን በኢትዮጵያውይነታቸው ሳይሆን በአማራነታቸው ብቻ መመንዘር እየተበራከ ነው፡፡ በእርግጥ ኢህአዴግ በተወሰነ ማህበረሰብ ላይ የሚያደርገው ይህ እርምጃ ተቃዋሚዎችን ወደዚህ የኢህአዴግ መስመር ሊጎትት ይችል ይሆናል፡፡ ኢህአዴግ የሚፈልገውም እያንዳንዱ ጉዳይ በአገር ማዕቀፍ ሳይሆን በብሄር አይን እንዲመነዘር ነው፡፡ ለተቃዋሚዎች ውድቀቱ የሚሆነውም ኢህአዴግም ይህን አንድ ማህበረሰብ ላይ የሚያደርገው እርምጃ የብሄር ፖለቲካውን እንዳይበርድና ኢትዮጵያውያን በአንድ ማዕቀፍ ይልቅ በቋንቋ የሚከፋፈሉበትን ‹‹የእኛ›› እና ‹‹እነርሱ›› ፖለቲካ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማድረግ  ስለሆነ በእሱ መስመር መግባታቸው ነው፡፡ በዚህ የኢህአዴግ ቀመር መሰረት ‹‹አማራ›› በመሆናቸው ‹‹ከቤንሻንጉል››፣ ከደቡብ ብሄራዊ ክልሎች ተባረሩ የሚል ክርክር አሸናፊ ሊሆን አይችልም፡፡ እነዚህን ህዝቦች በብሄር አምኖ የመደበ ተቃዋሚ ‹‹ውጡልን›› ያላቸው ፖለቲከኞች ወክለነዋል የሚሉትን ብሄር መብት ኢህአዴጋዊ በሆነው በዚሁ ቀመር ሊያምን ነው ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ጉዳዩ መታየት ያለበት በኢትዮጵያዊ መዕቀፍ እንጂ በብሄር ማዕቀፍ አይደለም፡፡ ተቃውሞው በብሄር ማዕቀፍ ሳይሆን በኢትዮጵያውይነት ከዚያም አለፍ ሲል በሰብአዊነት ሲሆን የትግል አንድነቱ በመርህ ላይ የተመሰረተ ያደርገዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያውያን ተቃዋሚዎችም ወደውም ሆነ በግድ ወደ ኢህአዴግ ቀመር እየተንፏቀቁ በመሆኑ ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ በደል ሲደርስበት ይህን ህዝብ እንወክላለን የሚሉት አካላት ብቻ በቀዳሚነት ድምጻቸውን ያሰማሉ፡፡ አማርኛ ተናጋሪው ላይ በደል ሲደርስ በብሄርና አንድነት መካከል ግራ የተጋቡት ተቃዋሚዎች ድምጽ ሲያሰሙ ‹‹ሌላውን›› ህዝብ የሚወክሉት አካላት ድምጻቸው እምብዛም አይሰማም፡፡ በትግራይ ህዝብ ላይ በደል እንደሚደርስ የሚያምኑ ኢትዮጵያውያን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሱ ነው፡፡ በዚህ በኩል ህውሃት/ኢህአዴግ ባያሸንፍም ለጊዜው የተሳካለት ይመስላል፡፡ በቅርቡ ወደ ተቃውሞ ጎራው ለመቅረብ እየሞከሩ ያሉት ትግርኛ ተናጋሪዎች የትግራይን ህዝብ በደል ብቻቸውን የሚናገሩ ሆነዋል፡፡
ኢላማውን ያልለየ ተቃውሞ
አንድ ትግል እንደ ትግል ውጤታማ ለመሆን ኢላማውን መለየት ይገባዋል፡፡ ካልሆነ ከእንሰሳ መንጋ ውስጥ ገብቶ ያየውን ሁሉ ለመያዝ የሚቋምጥና ሁሉን ሲያሯሩጥ ውሉ ደክሞ የሚመለስ አዳኝ እንሰሳ መሆን ነው፡፡ የሚይዘውን ታዳኝ ቀድሞ ያልለየ አዳኝ ትርፉ ድካምና ታዳኙ ማንቃት ብቻ ነው፡፡ በፖለቲካ ስልትም ቢሆን ተለይተው መቀመጥ ያለባቸው ኢላማዎች ይኖራሉ፡፡ ከአንድ በላይ መለየት ያለባቸው እንኳ ቢኖሩ በቅደም ተከተል መቀመጥ የግድ ይላቸዋል፡፡ ይህ ገንዘብን፣ የሰው ሀይልንና ጊዜን ለመቆጠብም ሆነ በአጭር ጊዜ ውጤት ለማምጣት አይነተኛ መንገድ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የሚከተለው ተስፋ መቁረጥና መጀመሪያ ከተመረጠው የትግል ስልት ማፈንገጥ ሲብስም ከተቃውሞው ጎራ መውጣትና እንዋጋዋለን በሚሉት ሀይል መዋጥ ወይንም መሸነፍ ነው፡፡
ይህ ችግር በአገራችን የተቃውሞ ጎራም ተከስቷል፡፡ በተለይ ብሄር ለዚህ አላማውን ያልለየ የፖለቲካ ኪሳራ የሚዳርግ የመጀመሪያው ምክንያት ነው፡፡ ብሄር ስስ፣ የፖለቲከኞች መጠቀሚያና እንደፈለገው የሚጠመዘዝ በመሆኑ ኢላማን ለመለየት እንዳይቻል ያደርጋል፡፡ በኢትዮጵያ ብሄርን  በቀዳሚነት የጀመሩ ሀይሎች  ተሸንፈዋል፡፡ ተሸንፈዋል ስንል ሀሳባቸውም ማለታችን ነው፡፡ ለብነት ያህል ለመጀመሪያ ጊዜ ብሄርን ወደ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ይዞ ብቅ ያለው ጀብሃ አስከፊ ሽንፈት ከገጠማቸው ፓርቲዎች መካከል ቀዳሚው ነው፡፡ ይህ ፓርቲ በኤርትራና ኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ብቻ ሳይሆን ትግርኛ ተናጋሪውን የኤርትራ ህዝብ ሲከፋፍል ኖሯል፡፡ ለኤርትራ ችግር የገዥዎችን ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን ህዝቦች ራሱ ባስቀመጠው የብሄር ቁና እየሰፈረ ሁሉም ላይ ለመዝመት ሞክሯል፡፡ በአሁኑ ወቅት መሳሪያና ስንቅ ሲያስታጥቀው ከነበረው ህውሃት በታች የሆነው ሻቢያም በኢትዮጵያ ገዥዎች ብቻ ሳይሆን በአማርኛ ተናጋሪው ህዝብ ላይ የመረረ ጥላቻ የነበረውና  ኢላማውን መለየት ያልቻለ ፓርቲ ነው፡፡ ምንም ያህል ስልጣን ላይ ቢወጣም ሻቢያ ያኔ ‹‹ከአማራ ነጻነት አወጣችኋለሁ›› ብሎ ያታለላቸው ህዝቦችን ልብ መግዛት ባለመቻሉ አሁን በመሸነፍ ላይ ይገኛል፡፡ ከ30 በመቶው በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ስም የተቋቋመው ኦነግ ከነገስታቱም ይሁን በጊዜው ከነበሩት ልሂቃን ይልቅ ‹‹አማራ›› መባሉን በማያውቀው ኢትዮጵያዊ ላይ ሁሉ በመዝመት ጊዜ፣ ጉልበቱንና አቅሙን አዳክሟል፡፡ ከምንም በላይ ወክየዋለሁ ከሚለው ኦሮምኛ ህዝብ ሳይቀር ይህ ህዝብን በጅምላ የማስጠላት ፖለሲው ላይ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ በየትኛውም አለም ሰፊ ህዝብ እወክላለሁ የሚል ፓርቲ አንድነትን በማጠናከር እንጂ በጠባብነት ሁሉ ላይ በመዝመት አይታወቅም፡፡ በጠባብ ብሄርተኝነት ተራው ህዝብ ላይ ሲዘምት የነበረው ኦነግም ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ለመውጣት ተገዷል፡፡ በቅርቡ ይህን ስህተቱን ያመነ የሚመስለው ኦነግ ህዝብ ላይ ሳይሆን አላማውን ልሂቃን ላይ በማድረግ በኢትዮጵያውይነት ማዕቀፍ ወደፖለቲካ መድረኩ እንደገና መመለሱ እየተነገረለት ነው፡፡
በብሄር ላይ የተመሰረቱ ፓርቲዎች የጊዜ ጉዳይ እንጂ መሸነፋቸው የግድ መሆኑን  ታሪክ ያስረዳል፡፡ ሶቬት ህብረትና ዩጎዝላቪያ በአንድ ወቅት ታላቅ ቢመስሉም በዚህ ኢላማውን በማይለይ የፖለቲካ ቀመር ምክንያት ተበታትነዋል፡፡ ሶቬት ህብረት በወቅቱ  አሜሪካን የምትገዳደር አገር ለመሆን ብትበቃም የኋላ ኋላ ተፈረካክሳ ግዛቶቿ ከአሜሪካ ስር ሆነዋል፡፡ ተከፋፍላ የነበረችው ጀርመን አውሮፓን መግዛት የቻለችው አንድ በመሆኗ ነው፡፡ የፋሽስትና ናዚ ፓርቲዎች  ኢላማ ለይተው ሳይሆን  በአለማቀፋዊ ‹‹የእኛ›› እና ‹‹እነርሱ›› ዘረኝነት ፖለቲካ ህዝብን ለጥቂት ጊዜ ማንቀሳቀስ የቻሉ ቢሆንም ሲሸነፉ ይከተሉት የነበረው ስርዓት የሚወገዝ፣ የሚናቅና የሚያስቀጣ ሆኗል፡፡ ጀብሃ፣ ሻቢያ፣ ኦነግ፣ ኦብነግ በብሄር ፖለቲካቸው ምክንያት ተሸንፈዋል፡፡ ህውሃት እስካሁን በሀይል ቢገዛም የሻቢያ መስራች ጀብሃ፣ ከዚያም የህውሃት አጋዥ ሻቢያ ክስረት ሽንፈቱ ወደማን እየመጣ ለመሆኑ ጠቋሚ ነው፡፡ ምን አልባት እነሻቢያ ብቻ ሳይሆን እነኢህአፓ፣ መኢሶንና የመሳሰሉትን አልተሸነፉም? የሚል ጥያቄ ሊቀርብ ይችል ይሆናል፡፡ ለእኔ የእነዚህ ፓርቲዎች ሀሳብ ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል ማለት አልችልም፡፡ ከአሁን በኋላ ኢትዮጵያ እንጀብሃ፣ ሻቢያ፣ ህውሃት፣ ኦነግና ኦብነግ ያሉ ተገንጣይ ፓርቲዎችን ጸረ ኢትዮጵያዊ አቋም የምታስተናግድበት ቦታ ያላት አይመስልም፡፡ ለዚህም ህውሃት ለይስሙላህም ቢሆን የጀመረው የአገራዊ አንድነት፣ የኦነግ የስልት ለውጥ እና የአብዛኛዎቹ ሽንፈት ዋነኛ ማስረጃ ነው፡፡ ምንም እንኳ እነ መኢሶንና ኢህአፓ በፓርቲነት ባይኖሩም ጀምረውት የመነረውን ኢትዮጵያን ለክፉ የማይሰጥ ‹‹የብሄር›› ፖለቲካቸውን የአሁኑ ኢህአዴግ እንኳን አውን ሊያደርገው አልቻለም፡፡ ምን አልባት ከቀደም ፓርቲዎች ስህተት መማር ከቻሉ ተቃዋሚዎች የኢህአፓንና መኢሶንን አንዳንድ መስመሮች መፍታት የሚችሉ ይመስለኛል፡፡ በተለይ እነዚህ ቀደም ፓርቲዎች ብሄርን ከጠባብ ብሄርተኝነት ይልቅ ለአገር አንድነት  በሚጠቅም መልኩ  ለማዋል ጥረት  ማድረጋቸው የሚታወቅ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት ባለው ፖለቲካችንም አላማን ያልለየ ፖለቲካ ይስተዋላል፡፡ በእርግጥ ለዚህ ዋነኛ ምንጩ ህውሃት/ኢህአዴግ ነው፡፡ ህውሃት ትግርኛ ተናጋሪውን ህዝብ ከቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ በመነጠል ለመያዣነት እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡ ይህም በብሄር ስም በተወናበደው ህዝብና በአንዳንድ ተቃዋሚዎች ዘንድ ትግርኛ ተናጋሪው ህዝብ ተጠቃሚ እንደሆነ ተደርጎ እየቀረበ ነው፡፡ ይህን ህውሃት ይፈልገዋል፡፡ ምክንያቱም ትግርኛ ተናጋሪውን ህዝብ ልብ ለማግኘትም ሆነ ሌላውን ለማሸነፍ የሚጠቅመው ይህ ስልት በመሆኑ ነው፡፡  የሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝቦችም ይወክሉናል በሚሉት ስር ከመስራት ውጭ በኢትዮጵያውነት ማዕቀፍ ለመታገል አማራጭ እንደሌላቸው ያምናሉ፡፡ ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ውጭ ሌሎች ተቃዋሚዎች  በአገር ማዕቀፍ የሚታገሉ በመሆኑ በብሄር ስም የሚታገሉትም በመዳከማቸው የኢትዮጵያ ህዝብ ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶችም ጎን ተስልፎ የአገሪቱን ኬክ ለመካፈል፣ ራሱን ለመከላከልና ለጥቅም እንዲቋምጥ ያደርገዋል፡፡ ማህበራዊ ድህረገጾችን ጨምሮ በአገር ውስጥ በሚደረገው ተቃውሞ ጠባብ ብሄርተኝነት የወለደውን እሳት በሌላ ጠባብ ብሄርተኛ እሳት ለመዋጋት የሚደረግ ጥላቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በንጉሳዊያኑ ዘመን  አማርኛ ተናጋሪ ህዝብ አልተጠቀመም ብለው የሚከራከሩ ሀይሎች በኢህአዴግ ዘመን ትግርኛ ተናጋሪው ህዝብ ተጠቅሟል ወደሚል መርህ አልባ ፖለቲካ እያዘነበሉ ነው፡፡ ህወሓት ከሌሎቹ ‹‹የኢህአዴግ አባል›› ድርጅቶች በላቀ መከላከያውን፣ ደህንነት፣ የውጭ ጉዳይ፣ ፍርድ ቤት በአጠቃላይም የኢትዮጵያን ተቋማ ይዟል፡፡ በእርግጥ ቅጥር በዘመድ አዝማድ፣ በጓድነት፣ በፖለቲካዊ ቅርርብ ነውና እነዚህ ሰዎች በርካታ ሰዎችን (የህወሓት አባላትን) ስበዋል፡፡ ይህ ከህወሓት የበላይነት እንጅ ትግርኛ ተናጋሪው ኢትዮጵያዊ እንደ ህዝብ ገዥ በመሆኑ የተፈጠረ አይመለኝም፡፡ በአሁኑ ወቅት ከህውሃት ጎን ባለመሆናቸው እንደሌሎች ኢትዮጵያውያን ጥቃት እየደረሰባቸው የሚገኙ ትግርኛ ተናጋሪዎች  የብሄር ፖለቲካ ለመጠቀሚያነት ብቻ እያገለገለ የሚገኝ ቀመር መሆኑ እየተዘነጋ ይመስላል፡፡ ይህ የኢህአዴግን ቀመር መጠቀም ኢህአዴግን እቃወማለሁ የሚል አካል ሁሉ ኢትዮጵያውያንን ወደ ብሄር ፖለቲካ በመግፋት የራሱን ሽንፈትና የኢህአዴግን ድል ማፋጠኑ የግድ ነው፡፡ በአንድ ወቅት በብሄር ሳይሆን በኢትዮጰያውነት ማዕቀፍ ይህን ብልሹ ፖለቲካ ሲታገል የነበረው የአውራምባው ዳዊት  ሌሎች ባደረጉበት ግፊት (የራሱ ጽናት ማጣትም ተጨምሮበት) የብሄር ፖለቲካውን እየታከከ ነው፡፡ ይህ የኢህአዴግ ቀመር ነው፡፡ ይህ ብሄርን መሰረት ያደረገና አላማውን ያልለየው ‹‹የእኛ›› እና ‹‹እነርሱ›› ፖለቲካ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጥረው ሽንፈትን ብቻ ነው፡፡ የኢህአዴግ የብሄር ፖለቲካም የሚያሸንፈው ያኔ ነው፡፡