የፍትህ ሚኒስትሩ አቶ ብርሃነ ኋይሉ ከሃላፊነት ቦታቸው ተነሱ፡፡ ሚኒስትሩ አቶ ብርሃነ ኃይሉ ትናንተ ከሰአት በኋላ በጠቅላይ ሚኒስቴር ኋይለማርያም ደሳለኝ በተጻፈ ደብዳቤ መሰናበታቸው እውን መሆኑ ታውቋል፡፡ በህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ክስ የመሰረቱት አቃብያን ሕጎች እና የችሎቱን ድራማ የሚዘውሩት ግለሰቦች አቶ ብርሃነ ኋይሉ በሚመሩት የፍትህ ሚኒስቴር ውስጥ የሚገኙ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ግለሰቡ ከ1997 ጀምሮ በዚሁ ቦታቸው ላይ የነበሩ ሲሆን ከዚያ ቀደም ብሎ በቀድሞ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ውስጥ ሰርተዋል፡፡ አቶ ብርሃነ ኃይሉ የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) አባልና ከፍተኛ አመራር ሲሆኑ የኮሚቴዎቻችንን እና የሌሎች ግለሰቦችን ክስ አስመለክቶ ተደጋጋሚ መግለጫ ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ በዚህ ላይ ተጨማሪ መረጃ ካገኘን ለማቅረብ ጥረት እናደርጋለን፡፡ አላሁ አክበር
No comments:
Post a Comment