FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Thursday, May 16, 2013

የሰማያዊ ፓርቲ ለጠራው ሰልፍ ዝግጅት እያደረገ ነው



የሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት ፅ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጥሪ ባስተላለፈው መሰረት አመራሮቹ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሆኑ ገለጹ።Ethiopian blue party, semayawi party
ፓርቲው “በመንግስት ምላሽ የተነፈጓቸው ጥያቄዎቻችን የዓለም ዓቀፍ ማሕበረሰብን ትኩረት የሚያገኙበትን መንገድ ለመፈለግ…” በሚል ባስተላለፈው የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚከበረውን የአፍሪካ ሕብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ሐገራትና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መሪዎች በሚገኙበት ድምፃችንን ለማሰማት ከግንቦት 15 – 17 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ጥቁር ልብስ በመልበስና ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም ደግሞ በአፍሪካ ህብረት ፅ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ያነሳናቸው ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ የሚፈልግ የፖለቲካ ፓርቲ፣ የሲቪክ ማህበራትና ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በእነዚህ ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ” ሲል አሳስቧል።
ይህ በዚህ እንዳለ በፌስቡክ፣ ፓልቶክና ሌሎችም የማህበራዊ መገናኛ መረብ (social media) ተጠቃሚ ኢትዮጵያውያን ለተጠራው የሰላማዊ ሰልፍ ድጋፋቸውን እየገለጹ ነው። በርካታ ኢትዮጵያውያን የፌስቡክ ፎቶዎቻቸውን በጥቁር የሰው ምስል በመቀየር ድጋፋቸውን እያሳዩ ሲሆን የፓልቶክ መወያያ መድረክ ታዳሚዎች ደግሞ ጽሁፎቻቸውን በጥቁር ቀለም በመቀየር ሰማያዊ ፓርቲ ጥቁር ልበሱ ሲል ያስተላለፈውን መልዕክት ተግባራዊ እያደረጉ ነው።
እስካሁን ከገዢው ፓርቲ አካባቢ የተጠራውን የሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ የተባለ ነገር የለም።
የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት ሰላማዊ ሰልፈኞች ቀደም ብለው ስለ ሰላማዊ ሰልፋቸው እንዲያሳውቁ የሚደነግግ ሲሆን። የግድ ፈቃድ መጠየቅ እና ማስፈቀድ አለባቸው አይልም።

No comments:

Post a Comment