ይላችኋል እስክንድር !!!!
———————————-
“በሚመች ሰፊ አልጋ ላይ
ከሚስቶቻችሁ ጎን ብትሆኑም
እንደኔ ተመችቷችሁ
የሰላም እንቅልፍ አታገኙም”
ይላችኋል እስክንድር
ቃሊቲ እስር ቤት ሆኖ
ስትባንኑ ለምትኖሩት
በቁም ለሞታችሁት አዝኖ
ሰብእናችሁ ተሟጦ
አውሬነታችሁ ቢታየውም
ተፈጥሮ ሳይሆን ተመክሮ
እንደሰጣችሁ አላጣውም
ከሽፍታ ፍትሕ መጠበቅ
ሞኝነት እንዳይመስላችሁ
ለሁሉም ጊዜ ስላለው
ለቅሶ ይሆናል ሳቃችሁ
እና
“እኔ እንደሆንኩ በዕምነቴ እንደፀናሁ
በአገሬ እንደኮራሁ … ለዘላለም እኖራለሁ
ምግባራችሁ ለቆሸሸው
ስማችሁ ለተበላሸው
እራሳችሁን ላሳነሳችሁት ግን … እስከወዲያኛው አዝናለሁ”
ይላችኋል እስክንድር (የካናዳው ከበደ)
No comments:
Post a Comment