FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Wednesday, May 15, 2013

ወያኔ እያዘናጋን ነው እየተዘናጋ? ህዝባዊ ጥያቄ መመለስ መፍትሄ ነው!



ምንሊክ ሳልሳዊ
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ህዝባዊ ጥያቄዎች እየበረቱበት የመጣው ወያኔ መላወሻ በማጣቱ የሚያደርገውን እስካለማወቅ ደርሷል:: ከእነዚህም ድንብርብሮች አንዱ ከአባቱ ሻእቢያ እንደወረሰው የፈጠራ ወሬ በአለም አቀፍ ደረጃ ማሰራጨት ነው:: እንዲሁም የህብረተሰቡን ጥያቄዎች ያስረሱልኛል ጭንቅላት ይሰርቃሉ የሚል እደምታ ያለውን ፈጣን ዘገባ ማሰራጨት ስራዬ ብሎ ይዞታል::addis ababa demonstration
ባለፉት 21 አመታት የአገዛዝ ዘመኑ ወያኔ ስልታዊ የሆኑ ያልሰለጠኑ እና ጫካዊ ብልሃቶችን ለመፍጠር እና ሲነቁበትም አለማቀፍ ሽብርን ይፈጥራሉ የሚለውን ወንጀል በዜጎች ላይ በመላከክ የትግል መሪ ሃሳቦችን ወደ አንድ አቅጣጫ ሊነዳቸው ይፈልጋል:: የህዝቦችን የመብት እና የነጻነት ጥያቄ መመለስ ያቃተው ወያኔ በሚፈጥራቸው የፈጠራ ወሬዎች ህዝቡን ለማደንዘዝ እና ለማዘናጋት እየዳከረ ይገኛል::
የፊተኞቹን ጥለን የቅርቦችን ስናስባቸው የሙስሊሙን ጥያቄዎች ተከትሎ የክርስቲያኑን አንድነት ያየው ወያኔ ተደናግጦ በባህር ዳር ደራሲ በኣሉ ግርማ በምንኩስና ተገኛ በማለት የህዝቡን አትኩሮት ለማሳብ ያደረገው ሙከራ ህብረተሰቡ ፊቱን ወደ ባህር ዳር አትኩሮ ትግሉን እንዲያዘናጋ ያደረገው ሙከራ የከሸፈበት ሲሆን ይህንን ተከትሎም ከፍተኛ ውግዘት ያስከተለውን በቤንሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉትን የኣማራ ተወላጆችን ሁኔታ ለመደባበቅ የሻእቢያ እና የወያኔ የእንግሊዝ ወኪሎች እነ ዘርኣይ በምስራቅ አፍሪካ የተነሳባቸውን የአበሻ ትኩሳት ለመፈንገል ይረዳቸው ዘንድ መንግስቱ ሃይለማርያም ሞተ ብለው በቶፒክስ ድህረገጽ እንዲሁም ለእኛ ለሚያውቁን ደሞ በSMS ላኩና ወሬውን እንድያመለስ አድርገን አስፍተን አራገብነው:: ወያኔ ይታወቃት አይታወቃት አላውቅም እንጂ የህዝቡን ጭንቅላት ለመስረቅ የምታደርገው ጥረት እስካሁን አልተሳካላትን ህዝብ ለ 2 እና 3 ቀናት ሊዘናጋ ይችላል እንጂ ለዘላለም አይዘናጋም:: በርግጥ የትግል እረፍት የለውም ለነሱ የስልጣን ማስረዘሚያ ለጫ ደሞ የትግል እረፍት ሊሆን ይችላል::
በዚህ ያላረፉት ወያኔዎች የአባይ ቦንድ በመሸጥ ኪሳቸውን ለማደለብ እና ህገወጥ የኢኮኖሚ አሸባሪነትን በአለም ላይ ለማስፋፋት ፈልገዋል ተብለው በአብዛኛው ዲያስፖራዎች በመወንጀላቸው በየሄዱበት በመዋረዳቸው የሚቀይሱት ነገር ቢያጡ የኢትዮጵያን ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤትን በመወንጀል አትኩሮት ሊያገኙበት ያቀዱትን ነገር ባለማሳካታቸው በተለያ መልኩ ሲመክሩ ውለው እና አድረው ሁኔታዎችን ወደራሳቸው ባለስልጣኖች በማዞር በሙስና ስም ቱባዎችን ወደ እስር ቤት ወረወሩ:: የሚዘናጋ ግን አልነበረም::
ይልቁኑ የራሳቸው ደጋፊዎች እና ተቃዋሚ ዲያስፖራዎች በሃገር ውስጥ ያለው የሰብኣዊ መብት አያያዝ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች….. የኑሩ ውድነት የመዘዋወር መብት
የሃይማኖት እና የህግ ጉዳይ ጥያቄዎችን አንግበው ተነስተውባታል ወያኔ ላይ:: በምንም ነገር ህዝብን በማዘናጋት ትግልን ለማሰልሰል የተደረጉ ሙከራዎች አይሳኩም ህዝባዊ ጥያቄዎች ሲመለሱ የዛን ጊዜ …የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ሲፈቱ ያን ሰአት …ህዝብ ጠግቦ ሲያድር…መልክም አስተዳደር ሲሰፍን ሰው በእውቀት ሲሰራ ጎሳ መቁጠር ሲቆም …እና ተመሳሳይ ጥያቄዎች ሲመለሱ ህዝብ አርፎ ይቀመጣል::
የወያኔ ጁንታ በሙስና ስም የራሱን አብዮት በማካሄድ በዲያስፖራው ዘንድ የአንበሳነት ተሰሚነት ለማግኘት ሲል ይህን ሰሞን በቱባ ባለስልጣኖቹ ላይ ወረራ የጀመረ ሲሆን ይህችን ሰበብ በማድረግ የህዝቡን ጭንቅላት ሰርቆ ለማዘናጋት ያደረገው ሙከራ ስላልተሳካለት ወዲያው ነበር ስብሰባ የተቐመጠው ከውስጥ እና ከውጭ እንዲሁንም ከኣባላቱ የመጣበትን ጫና ያልቻለው ደረቁ ወያኔ ምንም ብልሃት ቢፈጥር ማንም ሊዘናጋ ባለመቻሉ የመጨረሻ እርምጃዎችን ለመውሰድ እያስጠና እንደሆነ ተደርሶበታል::
ህዝብን ያዘናጋ እየመሰለው የተዘናጋው ህዝብን ያፋጀ እየመሰለው ያፋቀረው ወያኔ እንዴት እንደሚሳካለት ባለማወቁ እየዳከረ ነው:: ይህን ሰሞን በባህር ዳር የተከሰተውን የጅምላ ግድያ ተከትሎ ደሞ የስርኣቱን ንዝህላልነት እና እየደከመ ለመውደቅ መንገዳገዱን እንዳያሳብቅበት ይመስላል የተለያየ ዘዴ በመፍጠር እና በማስወራት ራሱን ለትዝብት ዳርጓል:: ወያኔ ራሱ ያሰለጠነው የፖሊስ ሰራዊት በፈጠረው የዲሲፕሊን ግድፈት ተራ በሆኑ ጉዳዮች ምን ያህል የወታደሩ እና የፖሊሱ ክፍል ልፍስፍስ መሆኑን ያመለክታል::
ይህ ጉዳይ መከሰቱ በሙስና ላይ የማደርገው ዘመቻ ብሎ የጀመረው እና በሕወሓት የጦር ጄኔራሎች ተቃውሞ የመጣበት ነገር እንደአዘናጋለት እና በዚሁ ሙስና ያለው ዘመቻ ተድበስብሶ በባህር ዳር ወንጀል ሽፋን እንደቀረለት የተረዳው ወያኔ ምን እና እንዴት ወደ ህዝብ እንደሚዘልቅ ጨንቆታል::ከዚህ ጋር አያይዞ ህዝብን በዘር ለማጋቸት ገዳይ እንዲህ ነው ሟቾች እንዲህ ናቸው በማለት የብሄር ፖለቲካ በማራገብ ህዝብ ወደ ትግል ፊቱን እንዳያዞር እና እርስ በእርሱ እንዲባላ የወጠነው ሴራም ከሽፎበታል::ወያኔ ተዘናጋ::
በሜይ 25 2013 በአፍሪካ ህብረት ደጃፍ ሊካሄድ የታቀደው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ አስደንግጦት መላ እየፈለገ የሚገኘው ወያኔ ካድሬዎቹ ሁላ ነጭ ልብስ ለብሰው ከተማውን እንዲዞሩ በጀት መመደቡ ደሞ ይህን ሰሞን ያደረገው የመዘናጋት በሽታው ነው ህዝብን አዘናጋለሁ ብሎ ራሱ በመዘናጋት በሽታ የተጠቃው ወያኔ ለህዝባዊ ጥያቄዎች መልስ ቢሰጥ የተሻለ ይሆናል:: የዛኔ ህዝብን ማዘናጋት ይቻላል:: ህዝባዊ ጥያቄዎች ታዝለው ግን ረዥም ማንገድ መሄድ አደጋ ስላለው የተዘናጋው ወያኔ በፌዴራል ዱላ ሽባ እናደርግሃለን የሚለው ህዝብ ባባዶ እጆ ወያኔን ሽባ እያደረገው ነው::
ወያኔ አዘናጋለሁ ብሎ የተዘናጋ የአሸባሪዎች ስብስብ መሆኑን በቅርቡ ይመለከቱታል:: ይጠብቁ::

http://ecadforum.com/Amharic/archives/7868

No comments:

Post a Comment