FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Saturday, May 18, 2013

የ’ልማታዊው አርቲስት’ ሠራዊት ፍቅሬ የኢቲቪ ፕሮግራም ታገደ


serawit-fikre
በሕዝብ ዘንድ “ልማታዊ አርቲስት” በሚል የመሽሟጠጫ ስያሜ ከሚጠሩት አርቲስቶች መካከል የቀድሞው የደርግ ወታደርና የአሁኑ የወያኔ ስርዓት ዋነኛ አቀንቃኝ አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ፤ ለመንግስት በሚያደርጋቸው የአጎብዳጅነት ተግባራት በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ላይ የቶክ ሾው ፕሮግራም እንዲያዘጋጅ የዓየር ሰዓት ተፈቅዶለት ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል። ከአዲስ አበባ የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደጠቆሙት አርቲስቱ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ላይ ያቀርበው የነበረው ቶክ ሾው ውለታው ተዘንግቶ እንዲታገድ ተደርጓል።
“ግራና ቀኝ” የሚል ቶክ ሾው ከሌላኛው ‘ልማታዊ’አርቲስት ሽመልስ በቀለ ጋር ላለፉት 6 ወራት ሲያቀርብ የቆየው የደርጉ ወታደር ሰራዊት ፍቅሬ ይህን የዓየር ሰዓት ያገኘው ለመንግስት ባለው ታማኝነት እንደሆነ የሚታወቅ ቢሆንም ድንገት ያቀርበው የነበረው ፕሮግራም በወያኔ ካድሬዎች በሚመራው ኢቲቪ እንዲታገድ መደረጉ አስተተያየት ሰጪዎችን “ፍቅር አለቀ ወይ?” የሚሉ ግምቶችን እንዲሰጡ በር ከፍቶላቸዋል።
የአቶ መለስ ዜናዊ ሕልፈት ከተሰማ በኋላ አርቲስቶች ጥቁር በጥቁር ለብሰው “ባለ ራዕዩን መሪ” እንዲቀብሩ በማስተባበር እንዲሁም ጥቁር በጥቁር አንለብስም ያሉና ለቅሶ አንደርስም ያሉ አርቲስቶችን “ሲያስጠቁር” (ለመንግስት በማቃጠር) ነበር እየተባለ የሚተቸው አርቲስቱ 6 ወር በቴሌቭዥን ያቀረበው “ግራና ቀኝ” ቶክ ሾው እንዲታገድ የተደረገው “አዝናኝ ፕሮግራም” አይደለም በሚል ምክንያት ነው ተብሏል። ይህ እገዳ እስከመቼ ሊቀጥል እንደሚችል እንደማያውቁ የሚገልጹት የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከባለፈው እሁድ ጀምሮ መታየት አቁሟል ብለዋል።
ኢቲቪ ወትሮም አዝናኝ ፕሮግራም አቅርቦ የት ያውቅና ሲሉ የሚተቹ አስተያየት ሰጪዎች አዝናኝ ፕሮግራም አይደለም በሚል ቶክ ሾው እንዲታገድ መደረጉ በቂ ምክንያት አይደለም በሚል ከእገዳው በስተጀርባ አንድ ነገር እንዳለ ይገምታሉ። በተለይም እንደሪፖርተርን ያሉ አፍቃሬ ሕወሓት/ኢሕአዴግ ያሉ ጋዜጦች “በአቶ መለስ ስም መነገድ ይቁም” በሚል በረዥሙ ሲተቹ የከረሙት እንደሠራዊት ያሉትን ሆዳም አርቲስቶች ነው የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች የኢቲቪ ካድሬ መሬዎች የሰራዊትን ማንነት በግልጽ ተረድተው ይሆናል ያገዱት ሲሉ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።
በዚህ ዜና ዙሪያ ዘ-ሐበሻ አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬን ለማነጋገር ያደረገችው ጥረት አልተሳካም።
አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ በቅርቡም አንዲትን ልጃገርድ የማስታወቂያ ሥራ አሰራሻለሁ በሚል የወሲብ ተንኮሳ አድርጓል በሚል በጋዜጣ ላይ መከሰሱ መዘገቡ ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment