FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Wednesday, May 15, 2013

"ለምን ገደልከን?” የሚለው የሰማዕታት ድምፅ ይጮሃል



Gudayachn Blog
በባህርዳር አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል በመንግስት ሚድያ 12 ሰዎች በሌሎች ዘገባዎች እስከ 18 ሰው ግንቦት 4/2005 ዓ.ም መፍጀቱ ይታወቃል።የግድያው ምክንያት በደንብ አልተብራራም።”ከፍቅረኛው ጋር በነበረው ጥል ነው” የተባለው ብቻ ምክንያት ነው እንዳይባል በመንገድ ላይ ሲሄድ የነበረን ሰው፣መብራት በርቶበት ያገኘው ቤት ውስጥ ያሉ ነዋሪዎችን፣በአውቶቡስ ከጎንደር አቅጣጫ የመጡ የነበሩ መንገደኞችን አስወርዶ ወዘተ ነው ድርጊቱን የፈፀመው።
Photo Fortune December 4/2011
Photo Fortune: December 4-2011
ይህ ጉዳይ መድበስበስ ያለበት ጉዳይ አይደለም።ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉ።ለምሳሌ=
  • አብረውት የሰሩ የፖሊስ አባላት ስለ ግለሰቡ ምን ይላሉ?
  • ባህሪው እንዴት ነበር?
  • ከእነማን ጋር ያዘወትራል?
  • ፍቅረኛ የተባለችውስ ምን ትላለች?
  • ወላጆቹ እንዴት ነው ያሳደጉት? ምን ይላሉ?
እንደ ክልሉ የፖሊስ ኮሚሽነር አነጋገር (ለኢሳት በግንቦት 6/2005 በሰጡት ቃለ ምልልስ) ግለሰቡ በባህርዳር አካባቢ የሰራው ለ አራት አመታት ነው።አራት አመት ሲኖር ከሕዝቡ ጋር የደስታም ሆነ ክፉ ጊዜ አሳልፏል።
  • በምን ምክንያት ያንን አይነት አረመንያዊ ተግባር ፈፀመ?
  • የፌድራል ፖሊስ የስልጠና ማንዋል ችግር አለው?
  • አንድ የፌድራል ፖሊስ ሲሰለጥን የህዝብ ፍቅር እንዲኖረው ተደርጎ ነው ወይንስ የመንግስትን ትእዛዝ እንዲፈፅም ብቻ ነው የሚሰለጥነው?
  • ፖሊሶቹ ምን እየተባሉ ነው የሚሰለጥኑት?
  • ኢትዮጵያን እንዴት ነው የሚረዷት? ኢትዮጵያ ማለት ለአንድ ፌድራል ፖሊስ የቷ ነች?
  • የህዝብ ፍቅር ማለት ለ ፌድራል ፖሊስ ምን ማለት ነው?
  • ጠላት የሚሉት ማንን ነው?
  • ወዳጅ የሚሉትስ? የሚሉትና ተመሳሳይ ጥያቄዎች መመለስ አለባቸው።
አለበለዝያ ነገስ ቢሆን የህዝቡ ዋስትና ምንድንነው? ግለሰቡ በሽተኛ እንደሆነ የተነገረ ነገር የለም። የኔ ሰው ገብሬ እራሱን ሲያጠፋ በሽተኛ ነው ተባለ። ጤነኛነቱን አረጋግጫለሁ ብሎ ክላሽ መንግስት ያስታጠቀው ገዳይ ፖሊስ ግን ሕዝብ ፈጀ። ለምን? አሰልጣኙም የስልጠና ማንዋሉም አስተማሪውም መፈተሽ አለበት። ጥልቅ ምርመራ ያስፈልገዋል። አሁንም “ለምን ገደልከን?” የሚለው የሰማዕታት ድምፅ ይጮሃልና።
ጌታቸው
ኦስሎ

No comments:

Post a Comment