ባሳለፍነው ሳምንት ሚያዝያ 25 ቀን 2005 ዓ.ም የአለም ፕሬስ ነፃነት ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ተከብሯል፡፡ ይህ አለም አቀፍ የጋዜጠኞት በአል ከመከበሩ አንድ ቀን አስቀድሞ የፌደራሉ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ሌሎች መሰል የህሊና እስረኞች ያቀረቡትን ይግባኝ ውድቅ አድርጎ ነበር፡፡
ከየአቅጣጫው የሚሰነዘሩ ውግዘቶችን “ጆሮ ዳባ ልበስ” ያለው ኢህአዴግ በችሎት በኩል ያንፀባረቀው የማንአለብኝነት ውሳኔ ፣ የፕሬስና ሀሳብን የመግለፅ ነፃነት በአደባባይ ማፈኑን ቀጥሎበታል፡፡ ጋዜጠኞችን በማሸማቀቅ፣ በማሰደድና በማሰር ወደር ያልተገኘለት ኢትዮጵያን የሚገዛው ቡድንም መሰረታዊ የሰብአዊ መብት አካል የሆነው ሀሳብን የመግለፅ ነፃነትን በአደባባይ ደፍጥጧል፡፡ የኢፌዴሪ ህገመንግስት ለመናገርና ለፕሬስ ነፃነቶች እንዲሁም ለሌሎቹም ሰብአዊ መብቶች ዋስትና ቢሰጥም መንግስት በተለያዩ ህገወጥ ህጎች ህገመንግስታዊውን ዋስትና በተግባር አፍኖታል፡፡ ህገመንግስታዊ ዋስትና የተሰጣቸውን የሰብአዊ መብቶች ፖለቲካዊ አንደምታ ባላቸው አዋጆች እየገደበ “ህገመንግስቱን” አስከብራለሁ የሚለው ኢህአዴግ፣ ህገመንግስታዊ መብታቸውን የተጠቀሙ ዜጎችን አስሮ “አሸባሪ” የሚል ታፔላ መለጠፉ ከአሁን በኋላ አያስኬድም፡፡ ምክንያቱም “አሸባሪ” የሚለው ቃል በየስርአቱ መዝገበ ቃላት የአገዛዙ ተቃዋሚ የሆኑትን እንጂ እውነተኞቹን አሸባሪዎች እንደማይመለከት በሀገር ውስጥም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ግንዛቤ ተያዟልና፡፡ ለዚህ አባባል ማረጋገጫው ደግሞ ገዢው ቡድን አሸባሪ ብሎ ታፔላ የለጠፈባቸውን ዜጎች አለም አቀፉ ማህበረሰብ ተራ በተራ መሸለ ነው፡፡
የዘንድሮው የአለም የፕሬስ ቀን ሲከበርም የኢትዮጵያ መንግስት በሽብር ወንጀል የከሰሳቸው ጋዜጠኞች በአለም አቀፍ ተቋማት ተሸልመዋል፡፡ በሽብር ወንጀል ተፈርዶባት በቃሊቲ የምትገኘው ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት ሳይንስና የባህል ተቋም(UNESCO) የዘንድሮውን የጉዋሌርሞ ካኖ የአለም የፕሬስ ቀን ሽልማት ሰጥቷታል፡፡ በተመሳሳይ የሽብር ወንጀል ተከሶ የተፈረደበትና በስደት ሲውዲን ሚገኘው የቀድሞው የአዲስ ነገር ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ፣ በቅርቡ የኢትዮጵያን መንግስት ይቅርታ ጠይቀው ከተፈቱት የሲውዲን ጋዜጠኞች ጋር በጋራ የሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስን (የሲውዲን ቅርንጫፍ) አመታዊ ሽልማት ተቀብሏል፡፡
ይህ ሽልማት የኢትዮጵያ መንግስት ሽብርተኝነትን ተገን በማድረግ በሀገር ውስጥ የሚካሄዱ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን ለማዳፈን እያደረገ ያለው አፈና ያጋለጠ መሆኑን ብናውቅም፣ በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለጉዳዩ በቂ ትኩረት ተሰጥቶታል ብለን አናምንም፡፡
አለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይም ረጂ ሀገራት የኢህአዴግ መንግስት የሚለግሱትን ገንዘብ በምን ላይ እንደሚያውለው በመከታተልና ለአፈና ተግባር እንዳያውለው በመቆጠጠር ረገድ በቂ ስራ አለመስራታቸው ለስርአቱ የልብ ልብ ተጥቶታል፡፡

የኢህአዴግ መንግስት ሀሳባቸውን ስለገለፁና በይፋ መንግስትን ስለተቹ ያሰራቸው ጋዜጠኞችና የፖለቲከኞች ካለግብራቸው በሽብርተኝነት መከሰሳቸው የስርአቱን አይን ያወጣ አምባገነንነትና አትንኩኝ ባይነት ያረጋገጠ ነው፡፡ ሆኖም ስርአቱ ሊገባው የሚገባው አንድ ሀቅ ህዝባዊ ተቃውሞንና ብሶትን ታጋዮችን በማሰር እንደማይቆም ነው፡፡
ዛሬም ኢህአዴግ ሀሳብን የመግለፅና የፕሬስ ነፃነትን እንዲያከብር፣ ሀሳባቸውን በመግለፃቸው ብቻ የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ሙሉ ለሙሉ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡
ለመላው ኢትዮጵያዊም ሀሳብን የመግለፅና የፕሬስ ነፃነት ለሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ በመረዳትና መብት በትግል እንደሚገኝ በማመን የፕሬስና ሀሳብን የመግለፅ ነፃነት እስኪረጋገጥ ድረስ በአንድነት እንታገል እንላለን፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት ሚያዝያ 25 ቀን 2005 ዓ.ም የአለም ፕሬስ ነፃነት ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ተከብሯል፡፡ ይህ አለም አቀፍ የጋዜጠኞት በአል ከመከበሩ አንድ ቀን አስቀድሞ የፌደራሉ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ሌሎች መሰል የህሊና እስረኞች ያቀረቡትን ይግባኝ ውድቅ አድርጎ ነበር፡፡
ለመላው ኢትዮጵያዊም ሀሳብን የመግለፅና የፕሬስ ነፃነት ለሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ በመረዳትና መብት በትግል እንደሚገኝ በማመን የፕሬስና ሀሳብን የመግለፅ ነፃነት እስኪረጋገጥ ድረስ በአንድነት እንታገል እንላለን፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት ሚያዝያ 25 ቀን 2005 ዓ.ም የአለም ፕሬስ ነፃነት ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ተከብሯል፡፡ ይህ አለም አቀፍ የጋዜጠኞት በአል ከመከበሩ አንድ ቀን አስቀድሞ የፌደራሉ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ሌሎች መሰል የህሊና እስረኞች ያቀረቡትን ይግባኝ ውድቅ አድርጎ ነበር፡፡
ከየአቅጣጫው የሚሰነዘሩ ውግዘቶችን “ጆሮ ዳባ ልበስ” ያለው ኢህአዴግ በችሎት በኩል ያንፀባረቀው የማንአለብኝነት ውሳኔ ፣ የፕሬስና ሀሳብን የመግለፅ ነፃነት በአደባባይ ማፈኑን ቀጥሎበታል፡፡ ጋዜጠኞችን በማሸማቀቅ፣ በማሰደድና በማሰር ወደር ያልተገኘለት ኢትዮጵያን የሚገዛው ቡድንም መሰረታዊ የሰብአዊ መብት አካል የሆነው ሀሳብን የመግለፅ ነፃነትን በአደባባይ ደፍጥጧል፡፡ የኢፌዴሪ ህገመንግስት ለመናገርና ለፕሬስ ነፃነቶች እንዲሁም ለሌሎቹም ሰብአዊ መብቶች ዋስትና ቢሰጥም መንግስት በተለያዩ ህገወጥ ህጎች ህገመንግስታዊውን ዋስትና በተግባር አፍኖታል፡፡ ህገመንግስታዊ ዋስትና የተሰጣቸውን የሰብአዊ መብቶች ፖለቲካዊ አንደምታ ባላቸው አዋጆች እየገደበ “ህገመንግስቱን” አስከባራለሁ የሚለው ኢህአዴግ፣ ህገመንግስተሰዊ መብታቸውን የተጠቀሙ ዜጎችን አስሮ “አሸባሪ” የሚል ታፕላ መለጠፉ ከአሁን በኋላ አያስኬድም፡፡ ምክንያቱም “አሸባሪ” የሚለው ቃል በየስርአቱ መዝገበቃላት የአገዛዙ ተቃዋሚ የሆኑትን እንጂ እውነተኞቹን አሸባሪዎች እንደማይመለከት በሀገር ውስጥም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ግንዛቤ ተያዟልና፡፡ ለዚህ አባባል ማረጋገጫው ደግሞ ገዢው ቡድን አሸባሪ ብሎ ታፔላ የለጠፈባቸውን ዜጎች አለም አቀፉ ማህበረሰብ ተራ በተራ መሸለ ነው፡፡
የዘንድሮው የአለም የፕሬስ ቀን ሲከበርም የኢትዮጵያ መንግስት በሽብር ወንጀል የከሰሳቸው ጋዜጠኞች በአለም አቀፍ ተቋማት ተሸልመዋል፡፡ በሽብር ወንጀል ተፈርዶባት በቃሊቲ የምትገኘው ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት ሳይንስና የባህል ተቋም(UNESCO) የዘንድሮውን የጉዋሌርሞ ካኖ የአለም የፕሬስ ቀን ሽልማት ሰጥቷታል፡፡ በተመሳሳይ የሽብር ወንጀል ተከሶ የተፈረደበትና በስደት ሲውዲን ሚገኘው የቀድሞው የአዲስ ነገር ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ፣ በቅርቡ የኢትዮጵያን መንግስት ይቅርታ ጠይቀው ከተፈቱት የሲውዲን ጋዜጠኞች ጋር በጋራ የሪፖርተርስ ዊዝ አውት ቦርደርስን (የሲውዲን ቅርንጫፍ) አመታዊ ሽልማት ተቀብሏል፡፡
ይህ ሽልማት የኢትዮጵያ መንግስት ሽብርተኝነትን ተገን በማድረግ በሀገር ውስጥ የሚካሄዱ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን ለማዳፈን እያደረገ ያለው አፈና ያጋለጠ መሆኑን ብናውቅም፣ በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለጉዳዩ በቂ ትኩረት ተሰጥቶታል ብለን አናምንም፡፡
አለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይም ረጂ ሀገራት የኢህአዴግ መንግስት የሚለግሱትን ገንዘብ በምን ላይ እንደሚያውለው በመከታተልና ለአፈና ተግባር እንዳያውለው በመቆጠጠር ረገድ በቂ ስራ አለመስራታቸው ለስርአቱ የልብ ልብ ተጥቶታል፡፡
አለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይም ረጂ ሀገራት የኢህአዴግ መንግስት የሚለግሱትን ገንዘብ በምን ላይ እንደሚያውለው በመከታተልና ለአፈና ተግባር እንዳያውለው በመቆጠጠር ረገድ በቂ ስራ አለመስራታቸው ለስርአቱ የልብ ልብ ተጥቶታል፡፡
የኢህአዴግ መንግስት ሀሳባቸውን ስለገለፁና በይፋ መንግስትን ስለተቹ ያሰራቸው ጋዜጠኞችና የፖለቲከኞች ካለግብራቸው በሽብርተኝነት መከሰሳቸው የስርአቱን አይን ያወጣ አምባገነንነትና አትንኩኝ ባይነት ያረጋገጠ ነው፡፡ ሆኖም ስርአቱ ሊገባው የሚገባው አንድ ሀቅ ህዝባዊ ተቃውሞንና ብሶትን ታጋዮችን በማሰር እንደማይቆም ነው፡፡
ዛሬም ኢህአዴግ ሀሳብን የመግለፅና የፕሬስ ነፃነትን እንዲያከብር፣ ሀሳባቸውን በመግለፃቸው ብቻ የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ሙሉ ለሙሉ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡
ለመላው ኢትዮጵያዊም ሀሳብን የመግለፅና የፕሬስ ነፃነት ለሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ በመረዳትና መብት በትግል እንደሚገኝ በማመን የፕሬስና ሀሳብን የመግለፅ ነፃነት እስኪረጋገጥ ድረስ በአንድነት እንታገል እንላለን፡

No comments:
Post a Comment