FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Saturday, May 11, 2013

የፌዴራሉ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የ13 ተጠርጣሪዎችን ስም ይፋ አደረገ

የፌዴራሉ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የ13 ተጠርጣሪዎችን ስም ይፋ አደረገ
የፌዴራሉ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፋንታ እንዲሁም ምክትላቸው አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ 13 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን ገለፀ፡፡
የኮሚሽኑ መግለጫ እንዳመለከተው ኮሚሽኑ ከህዝብ የተቀበላቸውን ጥቆማዎች መነሻ በማድረግ ከብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎተ ጋር በመተባበር በጥናት ላይ ተመስርቶ ከቆየ በኃላ በተጠርጣሪዎች ላይ በቂ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ማሰባሰብ ችሏል፡፡
ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት እስኪቀርብ ድርስ ተጠርጣሪዎቹ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲቆዩ ማድረግም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ከሁለቱ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረጉት ግለሰቦች
1.እሸቱ ወልደሰማያት – በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የአቃቤ ህግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
2.አስመላሽ ወልደማሪያም- የቃሊቲ ጉምሩክ ኃላፊ
3.ጥሩነህ በርታ- በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር ቡድን መሪ
4.አምኘ ታገለ- የናዝሬት ጉምሩክ ኃላፊ
5.ሙሉጌታ ጋሻው- በኦሮሚያ ልዩ ዞን መሀንዲስ
6.ከተማ ከበደ- የኬኬ ትሬዲንግ ባለቤት
7.ስማቸው ከበደ- የኢንተርኮንንታል ሆቴል ባለቤት
8.ምህረት አብ አብርሀ- ባለሀብት
9.ነጋ ገብረእግዚአብሄር- የነፃ ትሬዲግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤት
10.ዘሪሁን ዘውዴ -ትራንዚተርና ደላላ
11.ማርሸት ተስፉ – ትራንዚተርና ደላላ ናቸው፡፡

No comments:

Post a Comment