FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Wednesday, July 3, 2013

ሳውዲ ከ40 ሺ በላይ ለሚሆኑ ኢትጵያውያን ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ ልትሰጥ ነው

43cb3b26768b82a0e3ec1fb837718565_Mከሰኔ 25/2005 ጀምሮ በሳውዲ አረቢያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ሚገኙት የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከሳውዲ አረቢያ አቻቸው ሳውድ አል ፋይሰል በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ዶ/ር ቴዎድሮስ ኢትዮጵያ ነብዩ ሙሀመድና ተከታዮቹን ተቀብላ ያስተናገደችበትን የሁለቱን ሀገራት ጥንታዊ የታሪክ ግንኙነት፣ በሃገሪቱ ስላለው የኢኮኖሚያ እድገትና የኢንቨስትመንት አማራጮች ለሳውዲ አረቢያው አቻቸው አብራርተዋል፡፡
ውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ በሳውዲ አረቢያ ለሚገኙ ከ40ሺ በላይ የኢትዮጵያ ስደተኞች ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ ለመስጠት በመፍቀዷ አመስግነው፣ህጋዊ ፈቃድ ለማገኘት ያልቻሉ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በመኖራቸው የተሰጠው ህጋዊ የመሆኛ ቀነ ገደብ እንዲራዘምም ለሳወዲው አቻቸው ጥያቄ አቅረበዋል፡፡
የሳውዲ አረቢያው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሳውድ አል ፋይሳል በበኩላቸው በህገወጥ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵዊያን እድሉን እነዲጠቀሙበት መንግስታቸው ቀነ ገደቡን ለ4 ተጨማሪ ወራት እንደሚያራዝም ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለችውን እድገት ሚንስትሩ አድንቀው፣ በኢኮኖኖሚ ልማት፣ እርዳታና ኢንቨስትመንት መስኮች ሁለቱን ሀገራት ትብብር ለማጠናከር ተስማምተዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮቹ በቀጠናው ባሉ ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል፡፡የኢትጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለሳውድ አረቢያው አቻቸው ሳውድ አል ፈይሰል የጉብኝት ግብዣ አቅርበውላቸዋል፡፡
ምንጭ፡- የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጠቅሶ ኢዜአ

No comments:

Post a Comment