ሰማያዊ ፓርቲ ኢትዮጵያ
የሰማያዊ ፓርቲ የአደረጃጀት መዋቅር ውስጥ አንዱ የሆነው የድሬዳዋ አስተዳደር የሰማያዊ ፓርቲ መዋቅር የስራ-እንቅስቃሴ ከሀምሌ 6-7/2005 ዓ.ም. ባሉት ቀናት የፓርቲው የስራ-አስፈጻሚ አባላት ተዘዋውረው ተመለከቱ፡፡
የስራ-እንቅስቃሴውን ለመጎብኘት የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ጌታነህ ባልቻ እና የጥናትና ስትራቴጂ ኃላፊ አቶ ወረታው ዋሴ ተገኝተዋል፡፡ ከጉብኝቱም በኃላ በድሬዳዋ አስተዳደር የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ጋር አጠቃላይ በፓርቲውና በድሬዳዋ አስተዳደር መዋቅር ላይ ሰፊ ውይይትና ግምገማ በማድረግ የወደፊቱን የፓርቲውን ስራ በማጠናከር ሰላማዊ ትግሉን በሚያስቀጥሉበት ስራዎች ዙሪያ ተመካክረው የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
በመጨረሻም ሁሉም አካላት የተጀመረውን ትግል እንደሚያጠናክሩ ይህንንም ለሌሎች በድሬዳዋ ለሚገኙ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች እንደሚያሳውቁ በመግለጽ የዕለቱ ውይይታቸውን አጠናቀዋል፡፡
No comments:
Post a Comment