FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Saturday, July 13, 2013

ዜጎች ከስራ አጥነትና ከድህነትን ለማምለጥ ይሰደዳሉ

(ነቢዩ ሲራክ)
unemployed


መብት አስከባሪ አላቸው ለማለት ግን አልደፍርም
“በሽታውን ላልተናገረ መድሃኒቱ አይገኝም!”
አልጀዚራ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ለስደት ስለሚዳረጉ ዜጎች ዙሪያ ያሰራጨው መረጃ ቀልቤን ቢስብው በማለዳ ወጌ ልተነፍስ ብዕሬን አነሳሁ ። የአልጀዚራ ቴሌቪዥን Escaping Ethiopia’s unemployment “በኢትዮጵያ ስራ አጥነትን ለመሸሸ ” ያለው ዘገባ ስለ ስደቱ ከስደተኞች አንደበት፣ ለቀጣዩ ስደት እየተዘጋጁ ስላሉት ፣ ሰለ ህገ ወጥ አሸጋጋሪዎችና ስደቱን ለመገደብ መንግስት እየወሰደ ስላለው ጥረት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እማኝ አድርጎ በዘገባው አሳይቶናል ። በዚሁ ዘገባ ላይ በቀረበው መረጃ ስደትን ለማስቆምና የአዘዋዋሪዎችን ወሽመጥ ለመቁረጥ የተጠና ስራ ላቀረቡ ወጣቶች ስደትን ለመገደብ በመንግስት የተቋቋመው ግብረ ሃይል ወደ 27 ሽህ ዶላር ያበድራል ተብሎ ሰምቻለሁ። የተባለው በእኛ ሃገር ይሆን ? ስልም ጠየቅኩ ! ” ጀሮ ለራሱ ባዳ ነው ” ብየ አላየሁ አልሰማሁም ብየ ልለፈው! አሁን ሰምቻለሁና ይሰጣልም ብየ ለቀበለው ። ግናስ ለብድር አሰጣጥ መስፈርቱ ምንድን ነው? ይህ ግን አልገባኝም ! መስፈርቱ ወሳኝ ሆኖም ይህንንም አድልኦ ሰዎች በፖለቲካ አመለካከት በሃይማኖትና በዘር ሳይለዩ እኩል ታይተው ድጋፉ ይደረጋል በሚል ልቀበለው ። የተባለው ሁሉ እውነት ቢሆን እንኳ የተጠናን ስራ አውርቦ ጠቀም ያለ ብድር የማግኘት እድሉ ተምሮ ስራ ላጣው አለያም ለነቃው እና ለተደራጀው የከተማ ወጣት እንጅ ለቀረው መፍትሄ አይደለም ። ይህ መፍትሄ በዘገባው ቀርበው ላየናቸው በማንኛውምወደ አረብ ሃገራት በኮንትራት ስራ ለመሰደድ ለተዘጋጁት እና ከህጋ የሃገራት ሁለትዮሽ ስምምነት ውጭ ለሰደዱት ከገጠሩ ክፍል የሚጋዙት ቁጥራቸው ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ለሚገመቱት እህቶች የሚፈይደው ነገር የለም ።
በአረብ ሃገር በኮንትራት ስም የሚሰደዱ እህቶችን እንዳይሰደዱ ለማገድ አሸጋጋሪ ደላላዎችን ከመቆጣጠሩ ጎን ለጎን ዜጎችን ከድህነት የሚወጡበትን መንገድ መንደፍ ፣ የዜጎችን ነጻነት ማክበር እና ሁሉንም ዜጎች እኩል በማየት መሰረተ ልማቶችን በማስፋፋት የስራ እድል መክፈት ዋናው መፍትሔ ሊሆን ይገባል። “ኢኮኖሚያችን አደገ ተመነደገ” እየተባለ አቅማችን ይህunemployed 1ን ማድረግ ካልቻለ ብቸኛው መፍትሄው ” አትሰደዱ” ብሎ መለፈፉና እና “ለሚሰሩት እድሉ ” አለ ብሎ መደስኮሩ ከመገናኛ ብዙሃን ፍጆታ ውጭ የሚፈይደው ነገር የለም !
ስደት ክፉ ነገር ነው ፣ እጅግ በጣም ጥቂት ከሆኑት እያላቸው ካላቸው ለመጨመር ከሚሹ ስግንግቦች ውጭ ብዙው ስደተኛ ለመሰደዱ የስራ ማጣት ፣ የድህነትና የኑሮ ውድነት በቂ ምክንያት እናዳለው በስደቱ አለም ስኖር ካገኘኋቸው ስደተኛ ወገኖቸ የተረዳሁት ሃቅ ነው ። የኑሮ ውድነት ሳያንገሸግሽ ፣ ሳያጨናንቀው ስደትን የሚፈልግ የለም ፣ በሃገሩ ተምሮና ሰርቶ እሱንና ቤተሰቡን መደገፍ እየቻለ ስደትን የሚመርጥ የለም! የመንግስት ሃላፊዎች ለገጽታ ግንባታ የሚለቋቸውን መረጃዎች ገታ አድርገው በስደተኛው ችግር ላይ ቢያንስ ትክክለኛ መረጃ ቢሰጡን መልካም ነበር ።
ከሁሉም በላይ ወደ አረብ ሃገራት በኮንተራት ስራ ስም የሚላኩ ዜጎችን ጉዳይ ቆም ብለው ሊመረምሩት ይገባል። ሰው ” በሃገሬ ተቸገርኩ ፣ ተምሬ ስራ አጣሁ !” እያለ ስደቱን ማቆም ይከብዳል። ያም ሆኖ በህገ ወጥ ደላላ ተታልለው በህገ ወጥ መንገድ የሚሰደዱትን ለማስቆም መንግስት በስራ አገናኝ ኤጀንሲዎችን ስም እየተሰራ ያለውን ህገ ወጥ የበከተ ድለላ በሰውር የሚሰራውን ስራ ሰንሰለቱን ከቁንጮው ሊበጣጥሰው ይገባል ። ስደትን ማሰወቆም ካልቻልን አማራጩ ዜጎች ስለሚሄዱበት ሃገር እና ሊሰሩት ስለሚችሉት ስራ ትክክለኛ መረጃ እና ቅድም ዝግጅቶችን በትክክል አሟልቶ ማቅረብ አማራጭ ሊታይ ይገባል። ከዚህ ሁሉ አስቀድሞ ግን ዜጎችን በሃገራት መካከል በሚደረግ የሰራተኛ ውል መሰረት በህጋዊ ኮንትራት ስራ ዜጎችን መላክ እና ከተላኩም በኋላ በመብት ማስከበሩ ዙሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስረትር መስሪያ ቤት በፖለቲካ ታማኝነት ሳይሆን ዲፕሎማሲው ጥብብ የተካኑትን ከሃላፊዎች በበቂ ሁኔታ በአረብ ሃገራት ሊመድብ ይገባል!
ያለንት የስልጣኔ ዘመን ነውና መረጃን በመደባበቅ እውነትን ማጥፋት አይቻልም። ትክክለኛ ያልሆነ መረጃን ማቀበል ያዋርዳል እንጂ አያስከብርም ፣ ከሃቅ የራቀ መረጃ ገጽታን ያጨለማል እንጅ ፈካ አድርጎ ቀይሮ አያሳይም ! በአልጀዚራ ዘገባ እንደተነገሩት አንዳንድ መረጃዎች አጋጣሚውን ገጽታ መገንቢያ አድርገን እውነቱን የምንሸፋፍን ከሆነ ትልቅ ስህተት ተሳስተናል ! እውነትን በውሸት ለመድፈን ስንቆፍር ነገም እንደ የትናንቱ ከመከራ መውጣት አይቻለንም ! ዛሬም ጉዟችን ቅጥፈት ከሆነ በምናየው የወገን ሮሮ ፣ የሰቆቃ ድግግሞሽ ስናለቅስ እንደኖርን ስናለቅስ እንኖራለን ! አባቶች “በሽታውን ላልተናገረ መድሃኒቱ አይገኝም! ” እኛው ራሳችን በሽታችን ስንነግራቸሁ ስሙን ፣ መድሃኒቱንም ፈልጉልን ! የማለዳ ወጌን አበቃሁ !
በሽታችን ተረድቶ መድሃኒት ጀባ የሚል የህዝብ አገልጋይ ይስጠን!

No comments:

Post a Comment