FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Wednesday, July 3, 2013

"አፍሪኮም ወደ አገርህ ተመለስ"


አፍሪኮም ከጀርመን ውጣ- ዛሬውኑ! አፍሪኮም ከአፍሪካ ውጣ- ቶሎ ብለህ!
የአፍሪካ አንድነትን 50ኛ ዐመት የመመስረቻ በዓል ቀን ምክንያት በማድረግ የወጣ መግልጫ!
እኛ እዚህ በአዲስ አበባ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ የተሰበሰብነው የአፍሪካ መሪዎችና መንግስታት፣ ማንኛውም አገርና ህዝብ የራሱን ዕድል ወሳኝ መሆኑን እናምናለን፤ በዚህም ምክንያት ነፃነት፣ እኩልነት፣ ትክክለኛ ፍርድና ክብር የአፍሪካ ህዝብ መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎችና የሚገባውም መሆኑን ጠንቅቀን እናውቃለን፤ በመሆኑም የተፈጥሮ ሀብታችን የመጠበቅና፣ ህዝቦቻችንም የተፈጥሮ ሀብታቸውን የመጠቀምና፣ ለሚገባቸው የህብረተሰብና የኢኮኖሚ ዕድገት የማዋል መብታቸው እንደሆነ እናምናለን፤ ለዚህም እንታገላለን።
እ.አ በግንቦት 25 1963 ዓ.ም በሞዲቦ ኪዬታና ሲልቫኖስ ኦሊምፒዮ የረቀቀውና፣ በጊዜው ነፃነታቸውን የተቀዳጁት 33 የእፍሪካ መንግስታት የአፀደቁት ስምምነት መልዕክቱና ዋናው መሰረተ-ሃሳቡ ምንድነው? አንድ ነገር ማለት የሚቻለው በተለይም በቻርተሩ ላይ የሰፈረው ቁም ነገር ተግባራዊ አልሆነም፤ በዚህም ምክንያት የአፍሪካ አንድነት ሊረጋገጥ አልቻለም። ከ50 ዐመት በኋላ የአፍሪካ አንድነት የአፍሪካን አንድነት ድርጅትን ቢተካውም አሁንም ቢሆን ሁሉም የአፍሪካ አገሮች ተፈጥሮ የለገሳቸውን የተትረፈረፈ የጥሬ ሀብት ለመጠቅምና መብታቸውን ለማረጋገጥ በመታገል ላይ ናቸው። በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ላይ በተስፋፋው የስራ ክፍፍል አህጉሪቱ በመበደልና ቁራኛ በመሆን ሙሉ መብቷን እንዳታረጋግጥ የኢምፔሪያሊስት ኃይሎች ከፍተኛ እንቅፋት ሆነዋል። እንዲያውም አልፎ ተርፎ በቅርቡ በፈረንሳይ የመከላከያ ሚኒስተር የወጣው መግላጫ እንደሚያረጋግጠው ፓን አፍርካኒዝም የሚለው አስተሳሰብ ትልቅ እንቅፋት ፈጥሯል በማለት ካለማፈር ይናገራል። ይቀጥላል…

No comments:

Post a Comment