FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Friday, July 19, 2013

ኢትዮጵያዊው ፓይለት የ78 ሰዎችን ህይወት አተረፈ

ኢሳት ዜና :- ባለፈው ረቡዕ 78 ሰዎችን አሳፍሮ ከአዲስ አበባ  ወደ አክሱም ይበር የነበረው ቦምባርዴር ኪው 400 አውሮፕላን ማረፊያ ቦታው ላይ ሊደርስ ደቂቃዎች ሲቀሩት የጭስ መቆጣጠሪያው በመጥፋቱ፣ ፓይለቱ አውሮፕላኑን በአስቸጋሪ ሁኔታ በማሳረፍ የሰዎችን ህይወት እና የአየር መንገዱንም መልካም ስም ታድገዋል።
ሱዳን ትሪቢውን አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ባለስልጣንን ጠቅሶ እንደዘገበው የጭስ መቆጣጠሪያው አውሮፕላኑ ለማረፍ አንድ ደቂቃ ሲቀረው የእሳት አደጋ ምልክት አሳይቷል። የአውሮፕላኑ የግራ ክንፍ እየጨሰ፣ ሞተሩም በስርአት ተግባሩን እያከናወነ አልነበረም ያሉት ባለስልጣኑ፣ ፓይለቱ እሳቱ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት ከመውረጃው ቦታ ቀደም ብሎ በፍጥነት አውሮፕላኑን በማውረድ ህዝቡን ከአሰቃቂ አደጋ አድነውታል።
ከባለቤቱዋና ከአንድ አመት ልጇ ጋር ትጓዝ የነበረችው እርጋት ሀይለገብርኤል ” ከአውሮፕላኑ ክንፍ ጭስ ሲወጣ እንመለከት ነበር፣ ሁላችንም በጣም ፈርተን ነበር ” ስትል ለጋዜጣው ዘጋቢ ገልጻለች።
የአየር መንገዱ ኤክስፐርቶች ጭሱ ከ5 ደቂቃ በፊት ተከስቶ ቢሆን ኖሮ አውሮፕላኑ ሙሉ በሙሉ ይጋይ ነበር በማለት ተናግረው፣ አብራሪው የወሰደውን ፈጣን እና ፕሮፌሽናል እርምጃ  አድንቀዋል። ተሳፋሪዎችም ህይወታቸውን የታደገላቸውን አብራሪ ማመስገናቸውን ጋዜጣው ዘግባል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንድ ሳምንት ውስጥ ተመሳሳይ ችግር ሲገጥመው ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።
በጉዳዩ ዙሪያ አየር መንገዱ ይፋዊ መግለጫ አልሰጠም።

No comments:

Post a Comment