FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Friday, July 12, 2013

መድረክ የሰላማዊ ሰልፍለማድረግ ያቀረበው ጥያቄ በአዲስ አበባ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ።

ኢሳት ዜና :- መስተዳድሩ ለፓርቲው በጻፈው ደብዳቤ- መድረክ ለእሁድ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓመተ ምህረት ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6 ፡00 ሰዓት የሚቆይና ከስድስት ኪሎ ተነስቶ በአራት ኪሎ፣ በፒያሳና በቸርችል ጎዳና በማድረግ  መዳረሻው ድላችን ሐውልት የሚያደርግ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ያቀረበውን ጥያቄ እንደተመለከተው በመጥቀስ ፤ሰላማዊ ሰልፉ የሚደረግበት የጉዞ መስመር  በአሁኑ ጊዜ እየተዘረጋ ባለው የባቡር መስመር የትራፊክ መስመር እየተጨናነቀ ስለሆነ ለሰልፉ እውቅና እንዳልሰጠ ገልጿል።
በደብዳቤው ከምኒልክ አደባባይ እስከ አትክልት ተራ ድረስ ያለው  መንገድ በባቡር መንገድ ሥራ በመዘጋቱ አሁን ያለው ብቸኛ መንገድ የፒያሳና የቸርችል ጎዳና ነው ያለው መስተዳድሩ ፤ እንዲሁም ከመገናኛ ወደ ሜክሲኮ የሚወስደው መንገድ በመዘጋቱና ለሰልፉ የተመረጠው መንገድ ማስተንፈሻ በመሆኑ ፤ ከዚህም በላይ በአካባቢው የመንግስት ተቋማትና ሆስፒታሎች ስለሚገኙና እነዚህም ስፍራዎች በአዋጁ የተከለከሉ በመሆናቸው ለሰላማዊ ሰልፉ እውቅና ለመስጠት አንችልም ብሏል።
የመድረክ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ መንግስት ሰላማዊ ሰልፉን መከልከሉን አረጋግጠዋል።

No comments:

Post a Comment