FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Wednesday, July 3, 2013

በአዲስ አበባ የወተት እጥረት እጅግ አሳሳቢ ሆኖዋል

DSCN3499በአዲስ አበባ የወተት እጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ነዋሪዎች ይናገራሉ። አስተያየታቸውን የነገሩን ነዋሪዎች እንዳሉት ፥ በምርቱ ላይ እጥረት ብቻ ሳይሆን የዋጋ መወደድም ይስተዋላል። በካፌዎች የአንድ ስኒ ማኪያቶ ዋጋ እስከ 8 ብር መድረሱን የካፌ ተጠቃሚዎችም ያነሳሉ።የካፌ ባለቤቶች የወተት መጥፋት ለእነሱም ስራ ማነቆ መሆኑን በመግለፅ ፥ ቀደም ሲል ከሚገዙበት ዋጋ በላይ ለመግዛትም አንዳንዴ ጨረታ እንደሚገቡም ጭምር ይናገራሉ። በስድስት ኪሎና በሌሎች አካባቢዎች በተለይ ጠዋት ጠዋት ወተት በማከፋፈያዎች ሱቅ በር ላይ ረጃጅም ሰልፎች ይስተዋላሉ። በእነዚህ ማከፋፈያዎች ውስጥም አንድ ሊትር ወተት እስክ ከ16 እስከ 18 ብር ድረስ ዋጋ ይሸጣል። ወተት የተትረፈረፈባቸው አከባቢዎች ከዚህ በተቃራኒ ከአዲስ አበባ በቅርብ እርቀት ላይ በሚገኘው የሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙ አርሶ አደሮች ወተታችንን የሚገዛን አጣን ፤ ልፋታችንም ውጤት እያስገኘልን አይደለም ይላሉ። የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች በበኩላቸው አልፎ አልፎ ገበያ የማናገኝ በመሆኑ ከአከባቢው የምንሰበስበው ወተት መጠኑ ይቀንሳል ብለዋል። የኢትዮጵያ ስጋና ወተት ቴክኖሎጂ ልማት ኢንስቲቲዩት በበኩሉ በዚህ አካባቢና በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚስተዋሉትን ችግሮች ለመፍታት እየሰራሁ ነው ብሏል። ከሰሜን ሸዋ ዞን አንዱና ዋነኛው የወተት አምራች በሆነው የደገም ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ መብራት ጋረደው ስለ ስራቸውና በአከባቢው ስላለው የገበያ ችግር ሲናገሩ ፤ ካሏቸው ሁለት ላሞች በየቀኑ አጥጋቢ የሆነ የወተት ምርት ያገኛሉ። ይሁን እንጂ የወተቱ ዋጋ በገዢ ድርጅቶች የሚወሰንና መዋዠቅ የሚታይበት ነው ይላሉ። ሌሎች አርሶ አደሮች የነገሩን ከወይዘሮ መብራት ሀሳብ ጋር የሚስማማ ሲሆን ፥ ወተቱን ለማግኘት የሚያወጡት ወጪና ለወተቱ የሚከፈላቸው ክፍያ የማይመጣጠን ሆኗል። በዚህ በሰሜን ሸዋ ዞን ከአርሶ አደሩ ወተት የሚሰበሰቡት ድርጅቶች ማማ ፣ ሾላ ፣ ፋሚሊ፣ ናሂማ ወይም ቢፍቱና የሰላሌ የወተት ህብረት ስራ ዩኒየን ናቸው።
ዩኒየኑ በአርሶ አደሩ ዘንድ የሚታዩትን የገበያ እጥረቶችና የዋጋ ችግሮች ለመቅረፍ የበኩሉን ጥረት እያደረገ እንደሆነ ስራ አስኪያጁ አቶ ሃይሉ ታደሰ ይናገራሉ።
በደብረ ፅጌ ከተማ ላይ ማቀዝቀዣ ያለውና በርካታ ወተት ማከማቸት የሚችል ተቋም ለመገንባት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ጠቁመዋል።
አቶ ሃይሉ የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካን በጫንጮ ከተማ ላይ ዩኒየናቸው እየገነባ እንደሆነና በቅርቡም እንደሚጠናቀቅ ነው የተናገሩት።
ይህንን ፋብሪካን ወደ ስራ ለማስገባትም ቢሆን የመብራት ችግር እንዳለባቸው ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ ስጋና ወተት ቴክኖሎጂ ልማት ኢንስቲቲዩት የአቅም ግንባታ ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ገብረ መድህን ዩኒየኑን የመብራት ችግር ለመፍታት እይተንቀሳቀስን ነው ብለዋል።

No comments:

Post a Comment