FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Thursday, November 22, 2012

ኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ተመልሳ ልትመጣ ነው… “የት ሄደሽ ነበር…?” አለ ፋንቱ!



በርዕሱ ጀመር የተደረገው የጋሽ ፋንቱ ማንዶዬ ዜማ ሲቀጥል
“የት ሄደሽ ነበር?”
“አምባ አምባ ተለኬ አምባ…”
“ምነው ዘገየሽ?”
ቢይዘኝ ቢይዘኝ ጎልማሳ…”
እያለ ይቀጥላል።
ኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ጎልማሳም ሳይዘው ማተሚያ ቤትም ሳይዘው መንግስትም ሳይዘው እስከዛሬ የት ነበር!? ብለን እንጠይቃለን!

ከሶስት ነው አራት ወር በፊት ለካስ ቻናል ሆዬ ለሁለት አመታት ያክል የመንግስት ግብር አይከፍልም ነበርና “አሁንስ አበዛከው” ተብሎ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ ለአንድ ቀንም በእስር ቤት አደረ። (መሰለኝ… ነው ወይስ በለሌት እኒያ ዘመዱ አስፈቱት) ብቻ ግን እርሱም ሆነ የማስታወቂያ ድርጅቱ ባለይዞታ ይሆኑት ባለቤቱ እስር ቤቷን ቀመስ አድርገዋት ወጡ።
ጋሽ ሳምሶንም በዚህ ጉዳይ ቶቆጣ! ኢትዮ ቻናል ጋዜጣ መንግስትን አቅፈው ደግፈው ከያዙት ጋዜጦች አንዷ ናት። ታድያ መንግስትን ደግፌ ይዤ እንዴት ግብር ክፈል እባላለሁ ብሎ አኮረፈ! አኮረፈና እንደውም ጋዜጣዋን አላሳትምም ብሎ ጥግ ላይ ቁጭ አለ።
ፍትህ እና ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣዎች ግብርም የማተሚያ ቤት ክፍያም ሳያጓድሉ አትታተሙም ተብለው አንዴ መልካቸውን አንዴ ስማቸውን እየቀያየሩ ለመውጣት ተገደዋል።
ኢትዮ ቻናል ግን ለምን ግብር ክፈል ተባልኩ ተብሎ አኮረፈ ኩርፊያው ሲያልቅም ተመልሶ መጣ “እረኛ ቢያኮርፍ ቁርሱ እራት ይሆነዋል” ያለው ማን ነበር…
ወዳጅ ተስፋለም በፌስቡኩ ላይ “ኢትዮ ቻናል ልትመጣ ነው” ብሎ በለጠፈ ጊዜ ታሪከኛው ዘላለምም አለው “ደሞ መጣች ልታስቀን!” እኛም አልን… ሃሃ…!

No comments:

Post a Comment