FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Thursday, November 29, 2012

ሞረሽ ወገኔ የአቡነ ጴጥሮስን ሀውልት የማፍረስ እቅድ ተቃወመ


ህዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ሞረሽ ወገኔ የአማራው ድርጅት የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልትን ለማፍረስ መንግስት ማቀዱ የአማራው ታሪክን ለማጥፋት የተያያዘው እርምጃ አካል በመሆኑ እናወግዘዋለን ሲል አስታወቀ።
መላው የኢትዮጵያ ህዝብም ይህንን የመንግስት እቅድ በመቃወም ድምጹን እንዲያሰማ ሞረሽ ወገኔ ጥሪ አቅርቧል።
ሞረሽ ወገኔ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው የአማራው ህዝብ ላይ የማጽዳት እርምጃ ሲወስድ የቆየው ገዥው ፓርቲ ታሪኩንም ሲያጠፋ ቆይቷል ካለ በኋላ የአባቶቻችን የክብር አጽም ያረፈበትን ቦታ አፈረሰ፣ የዋልድባ ገዳምን አረሰ፣ የዝቋላ አቦን አቃጠለ ሲል በአብነት ዘርዝሯል በመግለጫው።
የአማራ ህዝብና በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚያደርገው ታሪክና ቅርስ የማጥፋት እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል ያለው ሞረሽ ወገኔ የአማራው ድርጅት የአቡነ ጴጥሮስ ሀውልት ሳይፈርስ በአንድነት ተነስቶ ቁጣውንና አሻፈረኝ ባይነቱን ሊያሳይ ይገባል በማለት በመግለጫው አሳስቧል።
ድርጊቱን ለኢትዮጵያ ታሪክና አንድነት ተጠብቆ መዝለቅ ጽኑ አላማ  ያላቸውን ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ተነስተው የአቡኑን ሀውልት ለማፍረስ የታቀደውን እቅድ እንዲቃወሙ ጥሪውን አስተላልፏል።

No comments:

Post a Comment