FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Tuesday, November 27, 2012

አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ካቢኔ አያዋቅሩም ተባለ


ህዳር ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭  ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በሟቹ የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር እግር የተተኩት ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አዲስ ካቢኔ እንደማያዋቅሩ
ለኢህአዴግ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቆሙ፡፡
 ምንጮቹ  አዲስ ካቢኔ የማይዋቀረው በምርጫ አሸንፎ የመጣ አዲስ ጠ/ሚኒስትር ባለመኖሩ ነው ብለዋል፡፡
አቶ ኃለማርያም በአቶ መለስ እግር የተተኩ በመሆናቸው አዲስ ካቢኔ ለፓርላማ አቅርበው የሚያጸድቁበት ምንም
ምክንያት የለም ብለዋል  ምንጮቹ፡፡
በዚህም ምክንያት የካቢኔ ሹም ሽር ሊያደርጉ ይችላሉ ተብሎ በአንዳንድ ወገኖች ሲጠበቅ የነበረውን የማይሆን ነው ብለዋል።
አቶ ኃይለማርያም ከተሾሙ በኃላ ባሉት ሁለት ወራት ጊዜያት ውስጥ የሰጡት ሁለት ሹመቶችን ነው፡፡ አንዱ ቃለመሃላ
በፈጸሙበት ዕለት ለፓርላማ አቅርበው ያስጸደቁት የምክትል ጠ/ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን
ሹመት ሲሆን ሌላኛው በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩትን አቶ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ
ተጠባባቂ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አድርገው መሾማቸው ነው፡፡
ይህም ሆኖ ግን የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶ የትዳር አጋራቸው በሽብርተኝነት በመከሰሳቸውና እሱንም
ተከትሎ በኦህዴድ በመገምገማቸው ከመንግስታዊ የሚኒስትርነት ኃላፈነታቸው እንደሚነሱ የሚጠበቅ ሲሆን መቼ ይሆናል
የሚለው ለጊዜው እንደማይታወቅ ተጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም ኦህዴድ በፓርላማ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትርና የኦህዴድ
ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ አስቴር ማሞ ከፌዴራል ኃላፊነታቸው ተነስተው ወደ ክልሉ እንዲዛወሩ መወሰኑን የአገር
ቤት ጋዜጦች መዘገባቸው የሚታወስ ቢሆንም ይህም ክፍተት በሚኒስትር ዴኤታ እየተሸፈነ እንደሚቆይ ምንጫችን
ጠቅሶአል፡፡
አቶ ሀይለማርያም ካቢያቸውን ለመሾም ያልቻሉት በኢህአዴግ ውስጥ በተለይም በኦህዴድ ውስጥ በተፈጠረ ሽኩቻ ነው የሚሉ ዘገባዎች ሲቀርቡ እንደነበር ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment