FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Friday, November 23, 2012

አቶ በረከት ስምዖን በኢትዮጲያ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸው ሚና እየጎላ መምጣቱ እየተነገረ ነው


ህዳር ፲፭ (አስራ አምት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ በረከት ስምዖን በኢትዮጲያ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸው ሚና እየጎላ መምጣቱ በሕወሐት ሰዎች ዝንድ ቅሬታ መቀስቀሱና በአንዳንዶችም ዝንድ ቁጣ ማስከተሉ እየተሰማ ነው አቶ በረከትም ከጀርባ ሆነው ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ ወጥተው የፊት መስመር ላይ በግልፅ መታየት ጀምረዋል።
በጠ/ሚ/ር ኋ/ማርያም ደሳለኝ የተመራ የልዑካ ቡድን ወደ ኬንያ ናይሮቢ በተጓዘበት ወቅት የልዑኩ 2ኛ ሰው ሆነው ከኬንያው ጠ/ሚ/ር ጋር ሲፈራረሙ የታዩት አቶ በረከት ስምዖን ናቸው።አቶ በረከት ስምዖን ያላቸው ይፋዊ ስልጣን በሚንስትር ማዕረግ የኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ኋላፊ ሲሆን ይህም ከሁሉም የሚንስትር መስሪያ ቤቶች ዝቅ ያል ስፍራ መሆኑም ታውቋል። ሆኖም አቶ በረከት ሥምዖን በሐገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸው ሚና እጅግ እየገዘፈ መጥቷል።
ጠ/ሚ/ር ኋ/ማርያም ደሳለኝ ለተባበሩት መንግስታት ጉባኤ ወደ አሜሪካ ኒውዮርክ ባቀኑበት ወቅት በሐገር ቤት በሁለቱ ሱዳኖች መካከል በተካሄደው ድርድርና ሥምምነት የኢትዮጲያን ምንግስት ወክለው የተገኙት አቶ በረከት ሥምዖን ነበሩ ምክትል ጠ/ሚ/ር ሆነው የተሾሙት አቶ ደመቀ መኮንን በሐገር ቤት የነበሩ ቢሆንም በስፍራው አልታየም።
ሠሞኑን ወደ ኬንያ ከተጓዘው የኢትዮጲያ ልዑካን ቡድኑ ጋር አብረው ናይሮቢ የደረሱት አቶ በረከት ሥምዖን ከኬንያው 2ኛ ሰው ጋር ሲፈራረሙ ታይተዋል።
አቶ ኋ/ማሪያም ደሳልኝ ከሐገሪቱ ፕሬዝዳንት ሞዋይ ኪባኪ ጋር ሲፈራረሙ የኬንያው 2ኛ ሰው ጠ/ሚ/ር ራይላ ኦዲንጋ ከአቶ በረከት ሥምዖን ጋር ተፈራርመዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የሚመሩት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ የገንዘብ ሚንስትሩ አቶ  ሦፍያን አህመድ በስፍራው የነበሩ ቢሆንም የፅ/ቤት ኋላፊው አቶ በረከት ሥምዖን ከፊታቸው ቀድመው ተገኝተዋል።
አቶ በረከት ሥምዖን በኢትዮጲያ ፖለቲካ ውስጥ እየጎሉ መምጣታቸው ከስርአቱ በተለዩትም ሆነ ከስርአቱ ጋር አብረው በዘለቁት የሕወሐት ሰዎች ዝንድ እንዳልተወደደ እየተሰማ ነው የሕወሐት ሠዎች የፊት መስመሩ ላይ በግልፅ ቁጥር አንድ ላይ ባይታዩም በፖለቲካው በኢኮኖሚውም ሆነ በፀጥታውም ያላቸው ጉልህ ሚና መጠቀሱም ታውቋል።

No comments:

Post a Comment