FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Sunday, November 25, 2012

የአቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ሐውልት፣ የሚያለማውስ?



ከድሜጥሮስ ብርቁ -ቶሮንቶ
የዳግማዊ ምንሊክ አና የአቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ሃውልቶችን ከስፍራቸው ለማንሳት ዝግጅቱ እንደተጠናቀቀ ስሰማ አሁን በስልጣን ላይ ያለው የህወሃት ቡድን በትክክልም የ”መለስንAbune Petros was born in 1892 in a farmer family in the city of Ficheራዕይ”ለማስፈጸም ደፋ ቀና እያለ እንደሆነ ተረዳሁኝ። ከዚህ በፊት በሌላ ፅሁፍ እንደገለጽኩት የ”መለስ  ራዕይ” የሚባል ነገር እንደሌለ እና የመለስ እየተባለ ለመሸጥ የሚሞክረው “ራዕይ” በትክክል የህወሃት ለመሆኑ አመላክቻለሁ። ጣሊያን ኢትዮጵያን ሲወር የነበረው የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ “ሃገሪቱን አሰለጥናለሁ” የሚል ነበር። አስቡት የኢትዮጵያ ስልጣኔ ጉዳይ ወዝውዞት ከጣልያን ሃገር ድረስ ጦር ሰብቆ ሲመጣ። አቡነ ጴጥሮስ በግፍ ሃውልታቸው የቆመበት ቦታ ላይ የተገደሉትም ዛሬ ህወሃት በሚጠቀመው ቋንቋ ሲመነዘር “ጸረ-ልማት” ናቸው በሚል ነበር።
ሲጀመር “ልማት” የሚለው ‘ዲስኩር’ ከጥርጣሬ ይልቅ የህዝብን አመኔታ እንዲገዛ ማድረግ ያስፈልጋል። መረጃ በማፈን፣ ውዢንብር እንዲነግስ በማድረግ ደሞ የህዝብን ትኩረት ለጊዜው በማስቀየር ሌላ የፓለቲካ ጥፋት ከበስተጀርባ መስራት ይቻል እንደሁ እንጂ የሕዝብን እምነት መግዛት አይቻልም። በዚሁ ሃውልት ጉዳይ እንኳን የሚወራው ዜና የተደበላለቀ ነው። መጀመሪያ ይፈርሳሉ የሚል መረጃ ተለቀቀ። ህዝቡ ሲጯጯህ ደሞ “የለም አይፈርሱም” የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ብቻ ነው ለጊዜው በባለሙያዎች “በክብር” ከቦታው የሚነሳው። ተመልሶም በባለሙያዎች በክብር የነበረበት ቦታ “በክብር” ይቀመጣል” የሚል መረጃ ተለቀቀ። የኋለኛውን መረጃ የምድር ባቡር “ባለስልጣን” (መሆኑ ነው) የተናገረው ተባለ።  የባለስልጣኑን ቃል አንደወረደ ማመን ከተሞክሮ አንጻር ስህተት  ሊሆን ይችላል። ማን ይሆን? ከየት ይሆን ብሎ -ለማወቅ ያህል- መጠየቁ ዘመኑ ከፈጠረው ፖለቲካ አስተሳሰብ ሳይሆን ካለው ነባራዊ የፓለቲካ የሃይል ሚዛን አና አሰላለፍ ነው መታየት ያለበት።  በ “ልማት” ስም መታሰቢያ ሀውልቱን በባለሙያ “በክብር ከማስነሳት” ይልቅ ሃውልቱ በማይነካበት ሁኔታ ባለሙያዎች መስራት የተፈለገውን ግንባታ እንዲሰሩ ስለመቻላቸው ወይንም ስላለመቻልቸው ስለመሞከሩ አና ስላለመሞከሩ የምናውቀው ነገር የለም። የራሳችንን ግምት ግን እንወስዳለን -የአቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ “ለህወሃት ምኑ ነው?” የሚል ጥያቄ ግምት ውስጥ በማስገባት። የህወህትን ተፈጥሮ አና ባህሪ ግምት ውስጥ በማስገባት!
“ልማት”ን የአስከፊ ጥፋት መጠቅለያ ‘ዲስኩር’  እያደረጉ (አንደጣሊያኖቹ) ዝርዝር መረጃ ሲታፈን እና ነገሮች ከህዝብ ጋር ያለምክክር ሲደረጉ ጥርጣሬ ፣ሁከት፣እና ተቃውሞ አንደሚነሳ መዘንጋት ምን ማለት እንደሆነ አይገባኝም። ዛሬ ወታደራዊ ጉልበት ስላለ አና  የፖለቲካ መዘውር በሃይል ስለተያዘ ብቻም  ህዝቡ አሉኝ የሚላቸውን ከቅርስንትም ያለፈ ትርጉም እና ዋጋ ያላቸውን ታሪካዊም መንፈሳዊም ማህበራዊም ሃብቶቹን አንደፈለጉ መነካካት አሁን ያለውን ትውልድ አና ህዝብ ኢትዮጵያዊ ስነ ልቦና በማድማት የሚያልቅ ጉዳይ አይደለም። የአለመረጋጋትን መሰረት እየጣሉ እንደመሄድ ነው። ተቃውሞው በሌላ መልኩ በሌላ ጊዜ  ሲከሰት  እንዳሁኑ በመጯጯህ እና በሀዘን የሚያልቅ ጉዳይ ላይሆን ይችላል። ከ”ብሶት ተወለድኩ” የሚል ቡድን ብሶት ሊወልድ የሚችለውን ነገር መዘንጋት የለበትም። የትውልዱ ማህበራዊ አስተሳሰብ እና የሃገር ፍቅር ከጥቅም ውጪ ተደርጎአል፤ ስጋት የሚፈጥር ተቃውሞ ሊፈጠር አይችልም( “መቶ አመት እንገዛለን” እንደሚባለው”) የሚመስለው አስተሳሰብ ምናልባት ከትውልዱም የበለጠ የሚናገረው ስለገዢው ቡድን ትምክህትና አላዋቂነት ሊሆን ይችላል። በውጭም በውስጥም ያለውን የጥፋት ትስስር (nexus)ገብቶት እንደ አቡነ ጴጥሮስ ለሃገር ለመሞት የተዘጋጀ ትውልድ ቢነሳስ?
ሕዝቡ “አለማለሁ” የሚለውን ቡድን የሚጠራጠረው ባህሪውን ስለሚይውቅ ብቻ አይደለም።  አንዳንድ “ልማት” የሚባሉ ፕሮጀክቶች በእርግጥም የልማት መሆናቸው አጠራጣሪ ስለሆነም ነው። ገዢውም ፓርቲ ለማወናበድም ዝም ለማለትም የሚሞክረው የኢትዮጵያን ሕዝብ ስለሚያውቀው ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ከመሬት ተነስቶ አይጠራጠርም። ተሞክሮውን ተመርኩዞ እንጂ!  የበፊት የበፊቱን አንኳን ትተን የቅርቡን የጥርጣሬ ምንጭ ለማስታወስ ያህል – የአፍሪካ የውሃ ማማ ናት በምትባለው ፤ ሰፊ የቆዳ ስፋት ዓላቸው ከሚባሉ የአፍሪካ ሃገሮች በምትመደበው ሃገራችን ውሃ አና መሬት የጠፋ ይመስል የስኳር ልማት ዋልድባ ላይ እተክላለሁ ተባለ።  “ልማቱ” በትክክል የህወህት እጅ ብቻ ይሁን ወይንም የውጭ ሃይሎች እጅ ይኑርበት እስካሁን ድረስ የገባኝ ነገር የለም። በትክክል የማውቀው ነገር ቢኖር ግን ዋልድባ ድረስ የተሄደው የኢትዮጵይውያንን እምነት ለመዝረፍ እንጂ ለልማት ጉዳይ ብቻ እንዳልሆነ ከማንም ኢትዮጵያዊ እንደማይሰወር ነው።
የአቡነ ጴጥሮስ መታስቢያ በ “ክብር” የሚነሳበት ዓላማ በትክክል ልማት ከሆነ ሃውልቱ የሚያስተጋባው መልዕክት በራሱ ልማትም ለልማትም አስፈላጊ የሆነ መሰረታዊ ነገር እንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል። ሃውልቱ ካረፈበት ኩርማን መሬት ይልቅ ሃውልቱ የሚያስተጋባው መልዕክት ዘላቂነት ላለው የልማት ተነሳሽነት አስፈላጊ ነው።  ልማት ለማጣደፍ የሃገር ፍቅር ያስፈልጋል። የዜጎችን ስብዕና እና ህሊና ማልማት ለልማት እንደ መሰረትም እንደ ቅድመ ሁኔታም መታየት አለበት። በስልጣን መባለጉ፣ በሙስና መዝቀጡ፣ የሃገር ጥቅም አሳልፎ መስጠቱ ፣ ሀገርን ለበላየ ሰቦች ጥሎ ወደ ሰው ሃገር ተሰዶ በሰው ሃገር መደላደሉ ሁሉ የሚመጡት ልማት ካላየው -ካልለማ- ስብዕና ነው። የራስን ዜጋ በሆነ ባልሆነው መጨፍጨፍ እና የመሳሰሉት ችግሮች መነሻቸው ያለማ ህሊና እና የሃገር ፍቅር አለመኖር ነው። ሃገሩን የሚወድ ዜጋ ሃገሩን የሚያገለግልበት ዕድል ሲያገኝ ሃገሩን አይዘርፍም። አያዘርፍምም። ሀውልቱ  የሚያነበው እና ጩኽቱን የሚሰማው  የመንግስት አካል ባይኖርም  የሚናገረው እነዚህ የሃገር ጠንቅ የሆኑ ማህበራዊ አና ፓለቲካዊ ተውሳኮች በመቃወም ነው። እንዴት “ባለ ራዕይ” የሚያመልክ ፓርቲ እና መንግስት ይሄን ማየት ተሳነው?
የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት መታሰቢያ  የጠንካራ ስብዕና ፣ የሃገር ፍቅር፣ የቁርጠኝነት እና የነጻነት ተምሳሌትነትን ነው ጧትና ማታ የሚያስተጋባው። በአስቸጋሪ ዘመን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እውነትን አንቆ ለእውነት ስለተሰዋ ክቡር ኢትዮጵያዊ ነው የሚናገረው። የአቡነ ጴጥሮስ የመንፈስ ጽናት ፤ መልዕክት እና መስዋዕትነት  የትግል ስንቅ ሆኗቸው ፋሺስትነትን በጽናት ታግለው ስለሞቱም ኢትዮጵያውያን የሚያስታውሰን መታሰቢያም ነው። ጎበዝ ኢትዮጵያ እኮ በፋሽስት ጦርነት አንድ ሚሊዮን ዜጎቿን አጥታለች። ስልሳ ሺ ታጋዮች ለትግራይ ተሰውላት ተብሎ ትግራይ ላይ ሃውልት የሚሰራ ቡድን በኢትዮጵያን ሃውልት ለምን ይቀለዳል??  በቅርቡ የተሰራው የአባ ጳውሎስ ሃውልትስ ሃይማኖታዊ አይደለም ይፍረስ ሲባል አይፈርስም ሲባል አልነበረ እንዴ? ምነው አቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ላይ ተነቃ?! የአቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ “ለህወሃት ምኑ ነው?” ነዋ ነገሩ! ህወሀት የተዋጋውን ኢትዮጵያዊነት ጧትና ማታ የሚያስተጋባ ነዝናዣቸው ነዋ!
የገዢው ቡድን በተለይም የህወሀት ጽንፈኛ ደጋፊዎች  የሚመስሉኝን ሰዎች (አንዳንዶቹ በብዕር ስም የሚጽፉ የአመራር አባላትም ይመስሉኛል) በዌብሳይቶች ላይ የሚጽፉአቸውን ጽሁፎች እከታተላለሁ። በዋነኛነት ከማነባቸው ውስጥ የሳይበር ኢትዮጵያን የፓለቲካ አምድ(click here) አንዱ ነው። በኦፊሲየል ሲነገር የማይሰማውን የህወሃትን የፓለቲካ እሳቤ -በተለይም ከትምክህትና የበላይነት ስለ ልቦና ግንባታ ጋር የተያያዙትን ሀሳቦች ብዙ ሳይነካኩ (አንዳንዴ ምንም ሳይነካኩም) እንደወረደ የሚያቀርቡ ግለሰቦች አይጠፉም።
እንደወረዱ የሚቀርቡትን ትቼ ትንሽ እየተነካኩ አንዳንዴ የስነ-ጽሁፍም ገጽታ እየተሰጣቸው የሚሰነዘሩ ሃሳቦችን ለአብነት አቀርባለሁ። እንደዚህ አይነት ሃሳቦችን ያንጸባርቃሉ ያልኳቸውን ጽሁፎች ለማየት በቅንፍ ውስጥ ያለውን ማጣቀሻ ይጫኑት( click here) ። ሃሳቡ የህወሃት ለመሆኑ ሁነኛ ማስረጃ ይሆናል ብየ ከማስበው ነገር እንዲህ ያለውን ጽሁፍ ብዙ ጊዜ የሚያሞካሿቸው (በዚያው መድረክ ላይ ማለቴ ነው) ህወሃት ባደረገው የትጥቅ ትግል ተሳትፈናል የሚሉ ስልጣን ከያዙ በኋላም ተምረው  በዲፕሎማሲ ስራ ላይ (ካያያዛቸው ይመስላል) የተመደቡ ይገኙበታል። ጉዳዩን እዚህ ያነሳሁበትም ምክንያት ህወሃት የሚከተላቸውን “የልማት” ይሁን ሌሎች የኢኮኖሚ ፓሊሲዎች  ዓላማቸው ህወሃት የበላይነት ስነ-ልቦን መገንባት እና የበላይነቱን ያስጠበቀበትን የስልጣን ተዋረድ ጠብቆ ለማቆየት የሚያስችለው ከመሆን ውጪ ሌላ ሊሆኑ እንደማይችሉ ለማመላከት ነው። እንዲህ አይነቶቹን ፓሊሲዎች ህወሃት በቀጥታ የሚያስትላልፋቸው አይደሉም ማለት ህወሀት የውሳኔው አድራጊ እና ፈጣሪ አይደለም ማለትም አይደለም (በነገራችን ላይ የህወሀት አመራር ‘ሜንተሮችን’ እነማን ነበሩ? ናቸው?)።
ቅጥ ባጣ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እና የነጻው ፕሬስ ላይ የዘመተው ህወሃት መራሽ መንግስት ከዚሁ ጎን ለጎን በስፋት የተያያዘው ነገር የህዝብን ስነ-ልቦና የሚዘርፍበት ፣ ማህበራዊ አስተሳሰባችን ርባና ቢስ የሚያደርግበት ዘመቻ ነው (ለአስተሳሰቦቹ ሃውልት የተሰራላቸው አንገበዋቸው የኖሩ አና አንግበዋቸው የሞቱ ኢትዮጵያውያንን በመዘከር እንደሆነ እንዳይረሳ)። ማህብራዊ ስነ-ልቦና የሚዘረፍብት ምክንያት በዘራፊነት አና በግፍ ላይ የተመሰረተ የስልጣን ተዋረድ የማይቀርለትን ተቃውሞ በመገንዘብ  የተቃውሞውን ምንጭ እና ለስልጣን የበላይነቱ ችግር ይፈጥሩብኛል የሚላቸውን ጉዳዮች ከምንጫቸው ለማድረቅ ከሚደረግ ጥረት አካል ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ።
የመሃል ሃገሩን ታሪካዊውን – ዓለም ጭምር ያወቀውን የነጻነት ትግል የሚያስታውሱ መታሰቢያዎችን በ “ልማት” ሰበብ  “መልስን በክብር እንደነበረ እናደርገዋለን” እየተባለ እየሰወርን በነበረው የርስ በርስ ጦርነት  “ተሰው” የሚባሉ የህወሃትን ታጋዮች የሚያስታውስ መታሰቢያ ትግራይ ላይ ለቱሪስት ማስጎብኘት እና “በክልሉ” የሚያድጉ ህጻናትን ጭምር በዚህ መልክ ማነጹ አሁንም ትምክህት ከተሞላበት የፓለቲካ ስራ  ውጪ ከ”ልማት”ጋር የተያያዘ ነው ለማለት ያስቸግራል።  በነገራችን ትግራይ ላይ ያለው ሃውልት ስለ ርስበርስ ጦርነቱ ሙሉ ገጽታ ይሰጣል? ለትግራይ ህጻናት ከ”ትግራዋይነት” እኩል ኢትዮጵያዊነት ስሜት እንዲፈጥሩ ያግዛል? የመሃል ሃገሩስ ታዳጊ ወጣት በራሱ እንኳን አነሳሺነት (መንግስት እንደማያደርገው እርግጠኛ ስለሆነኩ ነው) የሃገሩን ታሪክ እንዲጠይቅ የሚያስታውሰው መታሰቢያ እንዳያይ የሚደረግበት ምክንያት ስልታዊ የስነ ልቦና ዘረፋ ካልሆነ በስተቀር ምን ሊሆን ይችላል??
ህወሀት የአርበኛውን የአቡነ ጴጥሮስን መታሰቢያ ሀውልት አነሳለሁ በሚልበት ሰዓት ጣሊያኖቹ በኢትዮጵያ ብዙ እልቂት ላደረሰው የጦር መኮንናቸው (ግራዚያኒ) የመታሰቢያ ሃውልት ሊያቆሙ ነው። የህወሀት ድርጊት ሳይታሰብ በአጋጣሚ የተደረገ ነው ማለት ያስቸግራል። ምናልባትም የአማካሪ  ሃሳብም ያለበት ድርጊት ሳይሆን አይቀርም(ከላይ nexus ያልኩበትም የጥርጣሬ መሰረት ይሄው ነው)። የህዝብ ስነ-ልቦና ዘረፋ የመጨረሻው ደረጃ መሆኑ ነው። ይሄ ጉዳይ በቸልታ የታለፈ እንደሆነ አንድ ሰው ገስግሶ ዓይናችንን ሊያጠፋው ወደዓይናችን ሲጠጋ አይቶ እንዳላየ እንደመሆን ነው። በድርጊቱ ቀጥሎበት ዓይናችን ከተዛቀ የሚደርሰው ነገር ከአካል ጉዳትኝነት  ያልፋል።
የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ሃይማኖታዊ የሆነ እና የነፍጠኞች ነው ተብሎ የሚታሰበው( በህወሃቶች ዘንድ) የኦርቶዶክስ ሃይማኖት የሃይማኖት ቅርስ አይደለም። ክርስቲያን ላልሆነውም ኢትዮጵያዊ ቅርስ ነው። ታሪኩ የሃይማኖት ሳይሆን የነጻነት ትግል ታሪክ ነው። ስለሆነም አሁን ባለው ነብራዊ ሁኔታ በተሻለ ሁኔታ ተደራጅተው እየታገሉ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችም እንደ ኢትዮጵያዊነታቸው በጽናት ሊቃወሙት እና ሊያወግዙት  የሚገባ ድርጊት ነው።
የነጻነትን ትርጉም እየጠየቀ “ሊበራሊዝምን” ከእምነት በማይተናነስ መልኩ ተቀብሎ  ስለ ውጭ ሰዎች የነጻነት እሳቤ እና ትግል የሚነግሩን የፖለቲካ ሰዎች (“አደፍርሶች”) ፤ የአቡነ  ጴጥሮስ አይነት ክቡር ዜጋ  ስለ ነጻነት በተግባር የከፈለውን መስዋዕትነት የመነጋገሪያ ርዕስ አድርገው ቢያወሩን ኖሮ ዛሬ እንዲህ አይነት ነገር ሲሰማ የሚሰማው ቁጣ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል በሆነ። የነ አባ ጳውሎስ ሃውልት ተጎልቶ የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት በ”ክብር ከቦታው ይነሳል” እየተባለ ሲላገጥ ከመስማት የበለጠ ውርደት ለዚህ ትውልድ መቸም አይመጣም።
ጸሃፊውን በኢሜይል dbirku@hotmail.com  ወይንም  twitter- @dimetros  ላይ ማግኘት ይቻላል።

No comments:

Post a Comment