FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Saturday, November 24, 2012

ኢትዮጵያ አደጋ ውስጥ ከገቡ አገሮች ተርታ ተመደበች


ፎሬን ፖሊሲ መጋዚን ባወጣው የፌልድ ሰቴትስ ኢንዴክስ ኢትዮጵያን ከአለም አገሮች በ17ኛ ደረጃ በማስቀመጥ፣ለአደጋ የተጋለጠች አገር ሲል ፈርጇታል። ለኢትዮጵያ ህልውና አስጊ ሆነው ከቀረቡ ችግሮች መካከል የህዝብ ቁጥር መጨመር፣ የስደተኞች መብዛት፣ የህዝብ ብሶቶች መጨመር፣ ዜጎች አገራቸውን ጥለው መሰደድ፣ የፖለቲካ መሪዎች ልዩነት እና የጸጥታ ሀይሎች ጣልቃ ገብነት የሚሉት ይገኙበታል።
ከሁለት አመት በፊት ኢትዮጵያ እንደ ዘንድሮው ሁሉ በ17 ኛ ደረጃ ላይ ትገኝ የነበረ ሲሆን፣ አምና ግን ደረጃዋን በማሻሻል ወደ 20ኛ ዝቅ ብላ ነበር።
 በዚህ አመትም በአገሪቱ ውስጥ የሚፈጸመው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መክፋቱን መረጃው ያሳያል። ከአንድ እሰከ 20 ባለው ዝርዝር ውስጥ የሚገኙ አገሮች የመፈራረስ አደጋ ያንዣበበባቸው አገሮች ናቸው። ሶማሊያ አሁንም በቀዳሚነት ትመራለች። ኤርትራ ከአንድ እስከ 20 ካሉት አገሮች ተርታ በመውጣት በ23 ደረጃ ላይ ትገኛለች።
አዲሱ መረጃ የኢትዮጵያን ማህበራዊ እና ኢኮሚያዊ ችግሮች እያሻሻልኩ፣ አገሪቱን ወደ መካከለኛ ገቢ ለማሳደግ ግስጋሴ ላይ ነኝ ለሚለው የመለስ መንግስት የሚያቀርበውን ተደጋጋሚ ፕሮፓጋንዳ የሚቃረን ነው። የኢትዮጵያ ህልውና ከጊዜ ወደ ጊዜ አደጋ ውስጥ መውደቁን አለምአቀፉ የግጭቶች አስወጋጅ ድርጅት ባወጣው ሪፖርት መግለጹ ይታወሳል። በቅርቡ የአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንትም ለኢትዮጵያ ህልውና አደገኛ የሆኑ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና እና የጎሳ ግጭቶችን በዝርዝር አቅርቧል።

No comments:

Post a Comment