ህዳር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- በዛሬው እለት በቦሌ ቡልቡላ ከ1ሺ በላይ በላይ ቤቶች መፍረሳቸውን አካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት የአካባቢውን ነዋሪዎች ሲያንገላቱ መዋላቸውንም ነዋሪዎች ተናግረዋል። አንድ ቤታቸው የፈረሰባቸው ሰው ለኢሳት እንደተናገሩት በአሁኑ ጊዜ ህጻናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ቤት አልባ ሆነዋል።
በእሳከሁኑ የመንግስት እርምጃ ከ30 ሺ በላይ ቤቶች እንደፈረሱ ይታመናል። በጉዳዩ ዙሪያ የመስተዳድሩን ባለስልጣናት ለማናገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም።
No comments:
Post a Comment