FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Thursday, November 22, 2012

እነ እስክንድር ነጋ በዛሬው ዕለት ፍ/ቤት ቀርበው ያለምንም ውጤት ተመለሱ


ህዳር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የአንድነት ፓርቲ ም/ሊቀመንበር ወጣቱ ፖለቲከኛ አቶ አንዱዓለም አራጌን ጨምሮ በአሸባሪነት የተከሰሱ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች በዛሬው ዕለት ፍ/ቤት ቀርበዋል፣ ያለምንም ውጤትም ወደ እስር ቤት ተመልሰዋል።
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ፣ አቶ አንዱዓለም አራጌ ፣ አቶ ናትናኤል መኮንን እንዲሁም አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ እና ሌሎች በአሸባሪነት ተከሰው እስራት የተፈረደባቸው ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ፍ/ቤት የቀረቡት የፍ/ቤቱን ውሰኔ ተቃውመው ለጠቅላይ ፍ/ቤት ባቀረቡት ይግባኝ ነው።
ከፍተኛ ፍ/ቤት በወጣቱ ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌ ላይ የእድሜ ልክ እስራት ሲወስን ፣ በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ የ18 ዓመት እስራት ፣ እንዲሁም በሌሎች ላይ በየደረጃው የእስራት ውሳኔ መስተላለፉ ይታወሳል።
በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ፍ/ቤት ለይግባኝ የቀረቡት እነ እስክንድር ነጋ ፍ/በቱ መዝገቡን ለመመርመር በቂ ግዜ ያስፈልገኛል በማለቱ በቀጠሮ ወደ እስር ቤት ተመልሰዋል ፣ ለታህሳስ 10/2005 ቀጠሮ መሰጠቱንም ለማወቅ ተችሎዋል።

    No comments:

    Post a Comment