Kaleb
ያልገባኝ ነገር ሌጋሲ ሚሳከው በሰላማዊ ሰልፍ ነው እንዴ ፤ ተማሪው ትምህርቱን ትቶ ፎቶ አንጠልጥሎ በየቦታው ሲዞር ፤ ሰራተኛው ስራውን ትቶ ሲከተል፤ በሰልፈኛው ምክንያት መንገድ ሲዘጋጋ፤ ቢሮ አርፍደን ስንገባ ‹‹ወይ አይሰሩ ወይ አያሰሩ››ን ማንጎራጎር ግድ ሲሆንብን፤ በዚህ ክፉ አየር (የሰሞኑ አስደማሚ ጉንፋን) መነፃ ሲሸመትና መነጻ ሲከፋፈል በየቤታችን ምንም ባላደረግነው ላይ ሲቸረቸር ፤ ከስራ ስንቀር ……ይቺናት ሌጋሲ…… እኔምለው ግን ታክሳችን በቃ የሚውለው እዚህ ላይ ሆነ ማለት ነው ፤ መንግስት ገንዘብ እንደሌለው እናውቃለን (ቢኖረው ኖሮ ምክርቤቶችና ጠቅላያችን 6000 ባልተከፈላቸው ነበር ..ሎል) ታዲያ ከየት አምጥቶ ነው ይሔንን ሁላ ህዝብ ውሎ አበል ከፍሎ፤ የትራንስፖርት ችሎ፤ ወዘተ ….. ወዝቶ የሚችለው…..
የምሬን ነው ምላችሁ ተወዳጁ (አንዳንዴም ‹አናዳጁ› የሚሉ አሽሟጣጮች አሉ) የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴራችን ጓድ መለስ ዜናዊ ሞተዋል ባለ ራዕዩ መሪያችን ተለይተውናል የሳቸውን ራዕይ እናሳካለን ሲሉ የራሳቸው እንደሌላቸው ያሳበቀባቸው ሰዎች (ስጠረጥር የእሳቻውም ራዕይ የጠፋባቸው መሰለኝ) ራዕያቸውን ጎግል አድርገው የሆነ አገር ተሞክሮ እስኪያገኙ ድረስ……. ሰላማዊ ሰልፍ አማረኝ ያለቻቸው ሰትዎ ያለች አስመሰሉት፡፡
ደግሞ ደግሞ አዲስ አበባ ለካ 125 አመት ሞላት እናም ጀግና አይሞትም ፉከራ(ፉገራ አላልኩም) ለቀድሞው ጠቅላያችን እየተ ሞሸላቸው ነው ግን ማን ይሙት አዲስ አበባን ወልደው ያሳደጓት ሚኒሊክ ከነ ስም አጠራራቸው አርፈው ከተቀመጡበት ቦታ ለማጥፋት ትንቅንቅ ሰዎች ሲዪዙ እንደው ጠቅላያችን ቀና ብለው አረ ሼም ነው ቢሏቸው ምን አለበት (…እንደው ፈጣሪ ካላጣኽው ጥበብ….)
ደግሞ…….ልቁ (እንደ አለማየሁ ገላጋይ አነጋገር ‹‹ጨዋው›› ) በውቀቱ ስዩም ምንበረ ያለው ‹‹አዲስ አበባ ከምድር ወገብ ወደ ምድር ብብት ከፍ ብላለች…ነው .. some thing like that ብቻ ያለው ነገር ትዝ አለኝ ፤ እናም አዲስ አበባ ገጣባ አህያ መስላ ከ አበባነት ወደ ገንዳነት ተለውጣ 125 ዓመቷን በሙሾ ታከብራለች ….. (ልደት የመኖር ተስፋን አሳይቶኝ አያውቅም እንደውም ከተሰጠን ላይ የቀነስነውን እንጂ፤ የመጨመር ሳይሆን የመቀነስን ስሌት ነው ሚያስታውሰኝ ፤ እናም አዲስ ከተሰጣት ላይ 125ቱን ቀነሰች ስንት ቀራት ይሆን ……..)
No comments:
Post a Comment