FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Thursday, November 29, 2012

መንግስት በመላ አገሪቱ ሙስሊሞችን እያስገደደ ለተቃውሞ ሰልፍ ሊያስወጣ ነው


ህዳር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከኢህአዴግ ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙና መንግስት በሙስሊሙ ላይ በሚፈጽመው ኢሰብአዊ  ድርጊት የተነሳ ተቃውሞ ያስነሳሉ በተባሉ አካባቢዎች በሙሉ ፣ መንግስትን የሚደግፉ ሰልፎች ይደረጋሉ።
አብዛኛው ህዝብ ተገዶ እንዲወጣ፣ የድርጅት አባላት ከፍተኛ ተልእኮ እንደተሰጣቸው ለማወቅ ተችሎአል።
በዛሬው እለትም በቅርቡ የመንግስት ታጣቂዎች 4 ሰዎችን በገደሉበት ገርባ እና ደጋን መንግስትን የሚደግፉ ሰልፎች ተደርገዋል።
የሰልፉ ዋና አላማ በፍርድ ሂደት ላይ የሚገኙት የድምጻችን ይሰማ የሙስሊም ኮሚቴ አባላት አሸባሪዎች ናቸው የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ነው።
ኢህአዴግ በኮሚቴ አባላቱ ላይ ለፍርድ ቤቱ ጠንካራ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ በዳኞች ላይ ተጽኖ ለመፍጠር ማሰቡን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

No comments:

Post a Comment