ህዳር ፲፭ (አስራ አምት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በሱዳኑ ፕሬዝዳንት ጄነራል ኦማር ሐሰን አልበሽር ላይ የታቀደው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መክሸፉን የሱዳን ባለሥልጣናት ይፋ አደረጉ ። የሱዳኑ የቀድሞ የፀጥታ ሃላፊ ሣላህ ጋሆሽን ጨምሮ 13 ሠዎች ከግልበጣው ሙከራ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውም ታውቋል።
የሱዳን የማስታውቂያ ሚኒስትር አሕመድ ቢላል ኦስማን ለዜና ሰዎች እንደተናገሩት ግልበጣው የታቀደው ላለፈው ሐሙስ እንደነበር አመልክተዋል ከሳምንት በኋላ ትናንት ሐሙስ ህዳር 13/2005 ግልበጣውን ወደ ተግባር ሊለውጡ ሲሉ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አመልክተዋል በሐገሪቱ ቀውስን ለፍጠር መንግስትን ለመጣል የተቀነባበረው ሴራ ከሽፏል ሲሉም አክለዋል።
የሡዳን መንግስት ባልስልጣናት ሑሉን ነገር በቁጥጥር ስር ማድረጋቸውን እየገለፁ ቢሆንም በዋና መዲናዋ ካርቱም ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ታንኮች ጭምር በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን የአይን ምስክሮች ገልፀዋል።
ጀነራል ኡመር ሐሰን አልበሽር የዛሬ 23 ዓመት በመፈንቅለ መንግስት ሥልጣን መያዛቸው ይታወቃል በድርፉር የዘር ፍጅት ዓለም አቀፍ የጦር ፍ/ቤት የእስር ተዕዛዝ እንደቆረጠባቸው ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment