FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Thursday, November 29, 2012

በጉዲፈቻ ወደ ዴንማርክ የመጣች ህጻን ለከፍተኛ የስነ አዕምሮ ችግር መዳረጓን ከዴንማርክ የደረሰን ዘገባ አመለከተ


ህዳር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የዛሬ አራት አመት ከወላጅ እናቷና አባቷ ተረክበው ህጻኗን ከወንድሟ ጋር የወሰዷት የዴንማር ሰዎች ህጻኗ ለቤተሰቦቿ ያላትን ናፍቆት በየአጋጣሚው በመግለጽ እናቷ ጋር እንዲወስዷት በመጠየቅና ያልተለመደ ባህሪ እያሳየች ደስታ በማጣቷ ለህጻናት ማሳደጊያ እንደሰጧት የኢሳት ምንጮች ከዴንማርክ ገልጣለች::
ከዴንማርክ የደረሰን ይሀው መረጃ እንደሚያመለክተው የህጻኗ ማእሾ ታሪክ በዴንማርክ ከፍተኛ መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን ቤተሰቦቿን ያነጋገረና የህጻኗን ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ጽኑ ፍላጎት ያሳየ ዶክመንተሪ ፊልም ተሰርቶ በቴሌቭዥን መሰራጨቱን ለምንጮቻችን ገልጻለች::
በህጻኗና በወላጆቿ ፍላጎት ወደ ሃገር ቤት መመለስ በሚለውና የለም መመለስ የለባትም በሚለው ላይ የዴንማርክ ህዝብ ድምጽ እንዲሰጥ ተደርጎ 67 ከመቶው ህጻኗ ወደ ሀገሯ ትመለስ በማለት ድምጽ መስጠቱን ምንጮች አረጋግጠዋል::
17 ከመቶ የአፍ መፍቺያ ቋንቋዋን ረስታለችና መመለስ የለባትም ሲሉ 20 ከመቶዎቹ ድምጽ ከመስጠት መቆጠባቸውንም ለማወቅ ተችሏል::
በህጻኗ ህይወት ታሪክ ዙሪያ ተሰርቶ በተሰራጨው ዶክመንተሪ ፊልም የህጻኗ ወላጆች ልጃቸው እንድትመልስ እያለቀሱ ሲለምኑ የሚታይ ሲሆን  የህጻኗ ጤናን ያዛባ የስነ አእምሮ ችግርም ህጻኗ እንዳጋጠማትም ፊልሙን የተመለከተው ምንጫችን ከዴንማርክ በስልክ ገልጻለች::
የዴንማርክ ዜጋ አንድ ህፃን ወደ ሃገሩ ሲያመጣ ከ450 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ እንደሚከፍል የምንጮቻችን ዘገባ ያመለክታል::

No comments:

Post a Comment