FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Wednesday, March 20, 2013

ኢትዮጵያ በ21ኛው ክፍለ ዘመን


(ተፈሪ መኮንን)
ethiopia_addis_b


‹‹የሰው ልጆች ሀሉ፣ በነጻነታቸው፣ በከብራቸውና በመብቶቻቸው እኩል ሆነው  የተፈጠሩ ናቸው። የማሰብና የኀሊና ችሎታ ስለ ታደሉ እርስ በርሳቸው፣ በወንድማማችነት፣ መንፈስ ሊተያዩ ይገባል።›› ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች አዋጅ
ለአንድ አፍታ፤ ለትንሽ፤ ደቂቃ፣ እባክችሁን፣ ልባችሁን፣ ሰጡኝ።
„የመጀመሪያው ትውልድ፣ አገር ይገነባል፣አንድነትን ያጠነክራል። ነጻነትንም በጠላት እንዳይነጠቅ፣ይጠብቃል። ሁለተኛው፣ትውልድ፣ ቁጭ ብሎ ይበላል። ተቆጭ፣መካሪና ተቃዋሚ የሌለው ሦሰተኛ ትውልድ ደግሞ እናት አገሩን ይሸጣል። የተቀረው፣ የተወናበደው ትውልድ ደግሞ፣ አባቶች እንደሚሉት፣ የወሬ ቡዋልተኛ ሁኖ፣ አብሮ ተፈቃቅሮ፣ መሥራቱን ጥሎ፣ እርስበራሱ፣ እነደ አውሬ፣ ይቦጫጨቃል። በመጨረሻውም፣ ሁሉም ባሪያ ሁነው ፣ ይጋዛሉ። የትም ቦታ ወድቀውም ይቀራሉ።“ ይህ ብዙ ቦታ፣ከጥንት ጀምሮ፣ የሚታይ፣ የምሁሮች፣ በሽታ፣ ነው። እኛም፣ኢትዮጵያኖቹም፣ ገብተንበታል። ያውም ጊዜ ቢቆጠር ረዘም ይላል። እስቲ ጎበዝ! ትንሽ ረጋ ብለን፣  እንደማመጥ። ጩኸት በዛ፣ ግርግርና፣ ሁካታም፣ በእኛ መካከል፣ ተስፋፋ።
በአንድ ዘመን፣ በሄድኩበት ቦታ ሁሉ፣ሥርዓቱ ተቃውሶ፣  የምሰማው፣ሙዚቃ ይሁን ዘፈን፣ጭፈራ ይሁን ዳንኪራ፣ ድግስ ቤት ይሁን፣ የሰዎች ጨዋታ፣ሁሉም ነገር፣ ተቀያይሮ-  ጩኸት ብቻ፣- የቀለጠ ጩኸት፣ዕብደት የመሰለ-ነገር ብቻ፣ እሰማ ነበር።ያውም፣ አንጎል የሚያዞር!
ያ! ዘመን…..ያ! ሁካታ፣…ያ! ግርግር፣ ረቡሻና….የሙዚቃ መሣሪያዎች፣ ጫጫታ፣ የሰውም ሁሉ፣ ሁኔታ፣ ከካድሬው፣ የቅስቀሳ ማጉዋራት ጋር መጠጡም፤ ተጨምሮ፣ ያ! የቆየው የመደማመጥ ሥርዓት፣ጠፍቶ፣ ጭንቅላት፣ የሚያዞር፣ጆሮም የሚበጥስ፣ ዘመንም፣-ከአልረሳችሁት ነበር።
አሁንም፣ ከስንት አመት፣በሁዋላ፣ እዚያው፣ ዘመን ውስጥ፣  ተመልሼ   የገባሁ ይመሰለኛል። „ፓልቶክ“  የሚባል ነገር ውስጥ፣የሰው ምክር ሰምቼ፣ ሳይቸግረኝ እነሱ ጋ ገብቼ፣ አብጄ እየተባረርኩ፣ከዚያ፣ ፈትለክ ብዬ ወጣሁ። አንዱ ቤትማ ብቻ  ቢሆን ጥሩ ነበር። ምክር ሰምቼ፣ አንድ ሁለት እያልኩ፣ …. አሥሩም፣ አሥራ አምስቱም፣ ሃያውም፣ምንም አልቀርኝም፣ ሥራ ብዬ ፣ እያንኳኳሁ፣ገባሁ። አብዛኛው፣ የቀይ ካርድ -እንደ ኩዋስ ሜዳ እየሰጠኝ፣- ጥያቄ አይወዱም፣እንደምታውቁት፣  ለየት ያለ አስተያየት፣ ማዳመጥ፣ አይችሉም፣ ደርሶባችሁ ከሆነ-  አብዛኛዎቹ፣ ሁሉም፣ሂድ  ከዚህ ጥፋ ብለው፣ አባረሩኝ።
የወንዶቹ ሲገርመኝ፣ የሴቶቹ ቤት፣ የባሰ ሁኖ አገኘሁት። ይሰዳደባሉ። ወንዱንም፣ „አንተ ወስላታ፣…መቼ አጣንህ፤… እናውቃኻለን፣ ዋ…..“እያሉ፣ ሙልጭ እያደረጉ፣ ያዋርዱታል። እሱም በተራው፣ አሳዳጊ እንደበደለው፣ የባለጌ ፣ልጅ፣ አጸያፊ ነገር፣ ይወረውራል። አራት አምስት ሁነው፣ ሴቶቹ፣ ተደጋግፈው፣ ይቦጫጭቁታል። ከት ብሎ ስቆ፣ እሱም፣ -ይገርማል- አፀያፊ ነገሩን፣በተራው፣ ለጥፎባቸው፣ ምን ይታወቃል፣ ቢራውን፣ እየጠጣ፣ ያገሣል።
የፖለቲከኞቹም፣ የሓይማኖተኞቹም፣ የነፃ-አጪዎቹም፣….የእነሱም  ከሌሎቹ፣የተለየ አይደለም። ያው ነው። ከአመት አመት፣ የሚያነሱት፣ አርዕስቶች፣ ይደጋገማሉ እንጂ፣ አይቀየሩም። እንደዚያው፣ የዛሬ ስንት አመት፣ የተባለውን ፣ነገሮች፣ መልሰው ያኝካሉ።  የአለፈው አመት በደንብ  የተደቆሰውን ፣ያለቀውን ጉዳይ፣ ዛሬ፣ አዲስ ሁኖ እንደገና ይተረካል።ትላንት የተሰማው፣ ነገ ይደገማል። ከሦሰት አመት፣ በፊት፣ የተባለው፣ ነገር፣ እንደ አዲስ፣ ይወቀጣል።
ሃይማኖተኞቹ ፣አይፈረድባቸውም። መጽሓፉን እየደገሙ፣ እየደጋገሙ፣ መስተማር የግድ፣ አለባቸው።እሱ ነው፣ዋና ሥራቸው።  ሌሎቹ ግን፣ መታረም ይገባቸዋል።… ሁከት፣ግርግር፣ ጩኸት፣ረብሻው፣….. አለመደማመጡ ፣ ሁሉም ቦታ በዛ። ።ግን ፖለቲካ ደግሞ፣ እደምናውቀው፣ ሃይማኖት፣ አይደለም። የሆነባቸው፣ ግን፣ወንድሞቼ፣ ብዙ ናቸው።እርግጥ፣ፓልቶክ ጥሩ የመዝናኛ፣ የሓሰብ መለዋወጫመድረክ ነው።፣ያ መድረክ ግን እንደዚህ መሆን ለበትም።
የጽሁፉንም፣ አለምም፣ራመድ ብለን  ስንመለከተው፣ አብዛኛዎቹ፣ የተለዩ አይደሉም።  እንደዚሁ፣ እኝኝ እያሉ፣ እየተደጋገሙ፣ እያሰለቹ፣ የሚሄዱ ነገሮች ፣ ከጥቂት ገዜ ወዲህ አየሆኑ መጥተዋል።እዚያም የሚናገሩት፣ እዚህም የሚጽፉት፣ አንድ ናቸው።
ሁሉም ጸሃፊ፣… ሰለ ወያኔ ተንኮል፣ ሰለ ተቃዋሚዎች አለመሰባሰብ፣ ሰለ ነጮቹ ፣ ከወያኔ አለመላቀቅ፣…. ስለ ስብሓት ነጋ፣ ስለ በረከት ስምዖን፣ ስለ አዜብ፣ ስለ መለሰ፣ ስለ ሴኩቱሬ፣ ስለ መስፍን፣  ሰለጃመይካ፣ ማነው ሰሙ፣ ሰለ መከላከያው ሚንስቲሩ፣ አዎ፣ ሰለ አለሙዲና ጭፍሮቹ፣ስለ…. እያነሳ፣ ይጽፋል። ኢሳያስ አፈወርቂም፣ አለበት።
ከዚሁ ጋር፣ ሌላው፣እየደጋገመ የሚጽፈው፣ ( እኔ ተማሪውና ነጻ አውጪው ብቻ፣ አገራችንን በመታው የአዕምሮ ቀውስ፣  የአበደ መስሎኝ ነበር፣ ለካስ እብደቱ ዘልቆ ካህናቱም መንደር ገብቶአል) በቤተ ክርስቲያን ፣ ጉዳይ ላይ ነው። በቅርቡ የአነበብኩአቸው፣ ጽኹፎች ፣ ደግሞ፣ ዕውነቱን ለመናገር፣ አንዳዶቹ፣የሚያኮሩ ሳይሆኑ  የሚያሳፍሩ ናቸው። እንዴት ነው፣ለመሆኑ፣ የት ነው? ያለነውም  ያሰኛል። እነሱም፣ -ይገርማል- መሰዳደብ፣ መወቃቀስ፣….እራሻቸው፣ የሃማኖት አባቶች ጀምረዋል።ይህ ያሣፍራል።
ስለ ኢኮኖሚ የሚጽፉ፣ አሉ። … ሰለ ኪነት፣…. ስለ ታሪክ፣… ስለ የግል ግንዛቤና ፣ የሚታያቸውን ጉዳዮች፣ ከዕውቀታቸው ጋር የሚያካፍሉ።….ሰለ ዲሞክራሲ በጽሁፋቸውም  የሚያስተምሩ፣ አሉ። ፍልስፍናም ፣ የሚቃጣቸው፣ ጽሁፎችም፣ አይቼአለሁ።
በአጠቃላይ፣ እንደ ኢትዮጵያ ጋዜጠኞች፣ ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ለነጻና -ዲሞክራቲክ ሥርአት የታገለ፣ የሕብረተሰብ ክፍል የለም፣ ብዬ ብናገር፣ማጋነን አይደለም።እነሱ መመስገን ይገባቸዋል።
አዎ የኢሳትሥርጭትአለ። እሱን ፈጽሞ አልረሣሁም። እሱ ግን ወንድሞቼ፣ እራሱን የቻለ አርዕስት ነው። ….መሻሻል ፣ መሞረድ፣ መስተካከል፣ቅልብጭ፣ ያለች ነገር ሳይንዛዛ ማቅረብ፣….ከስቱዲዮ ወንበርና ጠረጴዛ፣ አንስቶ እስከ የ ወሃ መጠጫ ብርጭቆ….ወዘተ ድረስ…ብዙ የሚያነጋግሩ ነገሮች አሉ። ግን ከእኔ ይልቅ ስለዚህ ጉዳይ ጠለቅ የለ እውቀት ያላቸው፣ ሰዎች ቢናገሩ ደግ ነው፣ብዬ እዚህ ላይ ለግዜው  ማለፉን እመርጣለሁ።
ያም ሁኖ፣…. የሆነው፣ ሁሉ፤ ሁኖ፣ ስለ ወያኔ እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ ነገሮች፣ እንደ አልተዘከሩ ፣ በየጊዜው፣ እንደ አዲስ በየአለበት፣ መነሳቱ ገርሞኛል።እደዚህ አይነቱ፣ አካሄድ አይ በቃም እንዴ!…. በቃ!
ስለ ሻቢያ ብዙ በሚገባ ፣ ተነግሮአል፣ስለ ኦነግና ስለ ኦጋዴን „ነጻ-አውጪዎች“ ፣በበቂ ተወያይተናል።
ከአንግዲህ፣የወሬ ቋፍ ሁነን መቅረት፣ የማንፈልግ ከሆነ፣ ደግሞ፣ ወደ የማይቀረው፣ የድርጊት፣ እርምጃና ዘመን የግድ ዛሬ፣ መራመድ፣ሁላችንም፣ ይኖርብናል። የቅስቀሳው ዘመን ተገባዶአል። የድርጊት ጊዜ፣አዳምጡኝ ተጀምሮአል። ከእንግዲህ፣ ጡዋት ማታ፣ በዚያው ነገር ላይ መዳረቅ፣ይበቃል። ዜና፣ ማቅረብ ሌላ ነገር ነው። ትንተና፣ መቸክቸክ፣ እንደዚሁ፣ የተለየ ጉዳይ ነው። አዳዲስ ሐሳቦችን ማፍለቅ፣የአዋቂ ሥራ ነው። ቅልብጭ ያለች፣ አጠር መጠን ያለች ሐተታ፣ቆንጆ ነው። ወሬው ግን ወንድሞቼ ይበቃናል።
አጼ ምኒልክ፣ የአደዋ ጦርነት ከመከፈቱ ጥቂት ደቂቃ በፊት፣መቅደስ ገብተው፣ ጸሎታቸውን ከሌሎቹ  በአለሙያዎቻቸው ጋር አድርሰው፣ መስቀሉን ተሳልመው፣ሲወጡ፣ ለአንዱ በፀሎት ተመስጦ፣  ወደ ሁዋላ ለቀረባቸው፣ መሥፍን ፣ ዞር ብለው.፣ እኝሁ ንጉሡ፣“  ጸሎታችን ለአምላካችን በበቂ አድርሰናል፣ አሁን የሚቀረው፣ የእኛ እርምጃ ነው፣ በል ተነስ….“ ብለው፣ የጦር ሜዳ ውስጥ ተያይዘው ገብተው፣ አደዋ ለይ፣  ጣሊያንን፣ድል፣ ከዚያበሁዋላ፣በአንድነት፣  መተዋል።
ለሁሉም ጊዜ አለው። የጸሎት ጊዜ አለ፣ የድርጊት፣ ጊዜም አለ። የጨዋታም፣ የዘፈን ጊዜም አለ። ግን፣ ጨዋታም እራሱም ቢሆን ገደብ አለው።…ሲበዛም፣ ይመራል። ይኸው፣በወሬ፣በዋዛና በፈዛዛ ጉዳዮች ላይ ቢያንስ ሃያ አመት፣ሠላሣ አመት አሳለፍን።
ከዛሬ ጀምሮ፣ ወያኔ ፣ እንደዚህ ናት፣ ወያኔ፣ እንደዚያ ናት፣ እያሉ በቅስቀሳ ላይብቻ፣ ጊዜን በከንቱ ማጥፋት፣ ትርፉ፣ ስበሃት ነጋና፣  በረከት ስምዖን፣ እየተፈራረቁ፣ የሚወረውሩት፣ ቅጀቶች ፣ውስጥ ገብቶ፣ ከእነሱ ጋር አብሮ፣ ያን፣“አረ- አይደለም“ እያሉ፣ መናፈስ፣ ነው። እነሱ ሁለቱ፣ ሥራችን ብለው በእነሱ ቤት፣  የያዙት ነገር፣ ቢኖር፣ በየአሥራ አምሰት ቀኑ፣እንደሚታወቀው፣ ወይም በየወሩ፣ አንድ ነገር፣ እየወረወሩ፣   ሰውን፣ በተለይ፣በ ኢትዮጵያዊነቱና በ ሃይማኖቱ፣ የሚኮራውን ፣ ሕዝብ ማናደድና በእሱ ጉዳይ ላይ ብቻ ተወጥሮ  ቡና እየጠጣ፣ሌላ ነገር ሳያስብ፣ ጊዜውን እንዲገፋ ነው።ይህ መገልበጥ አለበት።
ይህን ግን ገልብጦ መስቀመጥ፣ ያስፈልጋል። ደግሞም ይቻላል። ከእንግዲህ፣ የቤት ሥራ የምንሰጣቸው፣ እነሱ ሳይሆኑ፣ እኛን። ጥያቄው፣ ምን አይነት፣ የቤት ሥራ፣ ለእነሱ አጥንተን፣መክረን እንስጣቸው ?
ዶክተር መረራ ጉዲና፣ በቅርቡ አንድ፣ ትልቅ ቁም ነገር፣ አዲስ አበባ ላይ አንስተዋል።“ „….እኛ የእህዴግን ጥይት እንፈራለን፣ እነሱ ደግሞ፣ የተቃውሞ ማዕበሉን ….“ ብለዋል።
ወይዘሮ ወለተ ማሪያም ደግሞ ፣በተራቸው፣ ቀደም ብለው፣“ „….አምስት ወይም አሥር ሺህ ሰው ብቻውን ከወጣ፣ ወያኔና ሻቢያ ተኩሰው፣ ሕዝቡን በጥይት ከመቁላት አይመለሱም፣….. መቶ ሺህ ወይም ከዚያ በላይ ሕዝብ  ከወጣ ግን- በሌላ ቦታ፣በሌላ አካባቢዎቸ፣ እንደታየው – አይተኩሱም፣…. ተኩሰውስ፣ የት ሊገቡ? ያ ሠልፈኛ፣ ሕዝብ እዚያው፣ ያንቃቸዋል። “ የሚለውን አሰተያየታቸውን፣ ኢትዮ ሚዲያ ላይ አውጥተዋል።
እንግዲህ፣ ጥያቄውም መልሱም፣ አንድ ላይ ተቀምጦአል።
እንደማመጥ ከአልን፣- ሌላም፣ አማራጭ አለ።
በሼክስፒር ድራማ፣ ሁለት ጀግኖች፣ ተፋልመው፣ አንዱ ጎበዙ፣ ብቻውን፣ በሠይፉ ሌላን፣ ጥሎት አሸናፊ ሁኖ ፣መድረኩ ላይ ይወጣል።
በቼኮብ ጨዋታ ደግሞ፣ የተቃራኒውን እናያለን። ሁለቱም ጀግኖች፣ ተዋጥቶላቸው፣ ደክመው መሬት ላይ ወድቀው፣ በደም ተበክለው፣ አንተም፣ ተወኝ፣ እኔም ትቼአለሁ፣ በቃ ከእንግዲህ፣ ወዳጅ ነን፣ ብለው፣ ተቃቅፈው፣ ይቅር ለእግዚአብሔር ብለው፣ አብረው፣ተቃቅፈው ከወደቁበት ተነስተው፣  በሰላም፣ ይኖራሉ።
በኢትዮጵያችን፣ ከሁለተኛው፣መፍትሔ ይልቅ፣ የመጀመሪያው፣ በታሪካችን ውስጥ፣  የተለመደ ነው።ግን፣ የአገራችንን ታሪክ በደንብ ለተከታተለ ሰው ደግሞ ፣የአንቶን ቼኮብ መፍትሔ፣ለእኛ፣ለኢትዮጵያኖች፣ ፈጽሞ አዲስ አይደለም። እንዲያውም የአጼ ምኒልክን የፓለቲካ ጥበብ በደንብ ለተከታተለ ሰው፣ የእሳቸው፣ እርምጃ፣ በዚሁ ላይ የተመሠረተ፣ መሆኑን በቀላሉ ይረዳል። እርግጥም ነው።
ወያኔ ግን ፣…. ለክብ- ጠረጴዛ ንግግር ሆነ፣ከሥልጣኑም ትንሽ ለማጋራት፣….. ወያኔን በነጻ ምርጫ ፣ ወያኔ፣ ሥልጣኑን በሰላም ለማስረከብ፣ ወያኔ፣እራሱ ያወጣውን፣ ሕገ-መንግሥቱን አንኳን ለማክበርና ለማስከበር፣ ጥጋቡ፣ ልቡን ሰለአሳበጠ፣ – ይህ ለማንም አዲስ አይደለም- ምንጊዜም ቢሆን፣ ፈቃደኛ ፣ አይደለም።
ሰለዚህ መፍትሄው፣ አመጽ፣ ብቻ ነው።አመጽ፣ ደግሞ አይነት አለው።  ምን ዓይነት አመጽ?
መልሱ፣የሼክስፒር ድራማ ነው የምትሉ፣ አትጠፉም። ይህ አመለካከት፣“በሠይፍ የመጣው፣ በሠይፍ ይውርዳል“ የሚባለው፣ ጽሑፍ፣ለይ የተመሠረተ መሆኑን ሁለችንም እናውቃለን። የወያኔና የሻቢያ መሪዎቸም፣ ለምን ወደ ጦር ለመሄድ እንደወደሰኑ አሜሪካ አገር አንዴ   ሲናገሩና ሲያስረዱ፣እንደሰማሁት እነሱ ይህንኑ አላማቸውን፣ እንደዚህ ብለው አስቀምጠዋል“…. እኛ እንደ ክርስቶስ ትምህርት፣ የግራ ጉንጫችችን ለሚመቱት የቀኝ ጉንጫጭችን እንዲደግሙት እንሰጣቸውም፣መልሰን እናጠናግራቸዋለን እንጂ“ የሚለውን ግልጽ የሆነ አቋማቸን፣ለጠያቂዎቻቸው፣እንዲያውቁት አሰምተዋል።
ይህን ለማሳመንም፣ያኔ፣ የነማኦ ሴቱንግን ስም፣ ጠርተዋል። ሆቺሚን ፣ ተጠቅሶአል። ማርክስና ኤንግልስ፣ የነፍስ አባቶቻቸው የሌኒና የስታሊንም ስም ሳይቀር፣ እንደምስክር፣ ቀርቦአል። አብዛኛው፣ የኢትዮጵያም ግራም በዚህ ጦርነት ፣ „ሕዝባዊ ጦር“ በሚባለው ትምህርት፤ “በደፈጣ-ውጊያ“ እንደሚያምንና እንደሚታለልም እነሱ፣ገብቶአቸዋል። ከዚያ በሁዋላ “ዲሞክራሲ“ ብለውም፣ ሰውን  አታለውም ሥልጣኑ ላይ ጉብ ብለው፣ አፍንጫችሁን ላሱ – ወዳጆቻቸውን፣ ጭምር፣ እስከ ማለት ዘልቀዋል። እንደዚህ አይነቱ፣ የጦር መፍትሔ፣ ለአገራችን ሥልጣኔ ከዚያም በሁዋላ፣ አብሮ ተቻችሎ፣ አንደረ ላይ ለመኖር ለምንፈልግ ዜጎች፣ ደም ስለሚፈስ፣ አይጠቅምም።
የእኔ መፍትሔና መንገድ፣ፍጹም ሌላ ነው። እሱም የጋንዲ በሉት፣… የማርቲን ለተር ኪንግ፣ ወይም የሰሜን አፍሪካው፣ የአደባባይ ሠልፍ፣ወይም የምሥራቅ አውሮፓው፣….…ብቻ፣እኔ የምሰጠው ስም፣ „ሰላማዊ ትግል“ ነው።
እንደማንኛውም ሰው፣ አሜሪካዊ ሆነ፣ ፈረንሳይ፣…. እንግሊዝዊ ሆነ ጣሊያን፣…. ጀርመን ሆነ  ሲውደን፣….ኬንያዊ ሆነ ጋና፣ ናይጄሪያዊ ሆነ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ወይም ሕንድ….  በአገራችን  መብታችን ተከብሮ፣  ማንንም ሳንፈራ፣ ሠርተን ኮርተን፣  መኖር  የምንፈልግ ከሆነ፣ ያለን ምርጫ፣ ያንን መብት፣ በኢትዮጵያ፣ ለማምጣትና ለዘለዓለም ፣ ለማሰከበር፣ የግድ ሁለችንም፣በብዛት፣ በሚሊዮን፣ ተነስተን፣ በሰላማዊ መንገድ፣ አደባባይ ለይ፣ወጥተን ፣ መታገል ስንችል ነው። ከምንም ነገር ደግሞ እንደምናውቀው፣ ምንም ነገር ጠብ አይልም። አይመጣም።
ሕገ መንግሥቱም „የተቃውሞ ሠልፍን“  ይፈቅዳል። ጥያቄው፣ በምን አይነት ብልሃትየህን መጠቀም የምንችለው?
ሰላማዊ ትግል ሲባል ጠበንጃ ከአልሆነ ብለው፣  ግራ የሚጋቡ፣ ሰዎች አይጠፉም። ግን በዚህ፣ በሰላማዊው ፣ የትግል መንገድ፣ የሚገኘው ዲሞክራሲ፣ ከጠበንጃው ዓለም፣ ፍጹም የተለየ ነው።
በጠበንጃ የተገኝ ሥልጣን፣ አብዛኛው ቦታ እንደምናየው፣ትርፉም፣ውጤቱ፣ የአምባገነኖች፣ ፈላጭቆራጭ መንግሥት ነው። ይህን ደግሞ፣ሥልጣን፣  አንዴ ፣ እንደ ሻቢያ ና እንደ ወያኔ፣ያሉ ኃይሎች፣ከነከሱ ሥልጣኑን  በምርጫ ተሸንፈው፣ አስረክበው ፣ከቤተ መንግሥቱ፣ በሰላም አይለቁም። አይወጡም።ሌላውም፣ በጠበንጃ ሥልጣንን ከጨበጠ፣ ከላይኞቹ፣ ፈጽሞ አይለይም።አይለቅም። እዚህ ላይ የተባለው:- ልብ አድርጉ- በምርጫ፣ ተሸንፈው፣ ከሥልጣናቸው በገዛ ፈቃዳቸው፣ አይወርዱም!
በሰላማዊ ትግል ግን እንደሌሎቹ፣- እንደ ሙባራክና እንደ ቤን አሊ፣ እንደ ሆኔከርና እንደ እገሌና አገሊት……ወደው ሳይሆን ተገደው  ቤተመንግሥቱን  ጥለው፣እያለቀሱ ፣ የወያኔና ሻዕብያ መሪዎች ይወጣሉ። የማይወጡበት፣ ምንም ምክንያት፣የላቸውም።
በሰላማዊ ትግል፣እንደሚታወቀው፣  እላይ የተጠቀሱትና ሌሎቹ፣ ብዙ ሕዝቦች ነፃ ወጥተው፣የ ዲሞክራሲን አየር፣ ተንፍሰው፣  አዲስ ሥርዓት መሥርተው፣ መሪዎቻቸውን፣ በምርጫ፣ እያወጡም፣መልሰው፣ አያወረዱም በሰላም ለጓዙ፣ ሊኖሩ ችለዋል። የኢትዮጵያም ጉዞ ወደፊት ከዚህ የተለየ  ሊሆን አይቸልም።  እዚያ ላይ ለመድረሰ፣ ግን ፣ ቢያንስ አንድ አርምጃ በመጀመሪያ፣በየፊናችን „ መንጫጨቱን ትተን“፣  መራመድ፣ይኖርብናል። ደግሞም፣ አለብን። አለበለዚያ ፣ኢትዮጵያ  – በተጀመረው ጉዞ- ነገ አትኖርም።የመኖሩዋም፣ ጉዳይ፣የሚያጠራር ነው።
አለበለዚያ፣ ወያኔና ሻዕቢያ ነገ ታርቀው፣ ጉድም፣ ሊፈላብን፣ ይችላል። ይህ ሁለተኛው፣ምክንያት ነው። ሌላው፣ሦስተኛው ምክንያት፣ በኢትዮጵያ ላይ ወያኔና ሻዕብያ እንዲቀልዱብን ፣ ድጋፍ እየሰጡ፣ ሰበአዊ መብት ሲረገጥ፣ ዝም ብለው፣ (አምኒስቲ ኢንተርናሸናል በየጊዜው ይከሳል) በመንግሥት ደረጃ ግን እነዚህ መንግሥታት እያዩ፣ ለይስሙላ ፣ በዝቀትኛ ባለሥልጣን እያስተቹ፣ የሚያሾፉብንን፣ትላልቅ መንግሥታት፣ ሳንፈራ፣ በአደባባይ፣እነሱን፣እነሱ አንድ ቀን ተነስተው፣ ሳይሸጡንና ሳይለውጡን፣    በሕዝባቸው ፊት የግድ መክሰስ ይኖርብናል።
እኔ አልረሳውም፣ ማንም ሰው፣ አይረሳውም፣ የሞስኮ ኮምኒስቶች፣ ለእኛ፣ እነ፣ ኮነሬል መንግሥቱ ኃይለማርያም ና ጭፍሮቹ፣እነሱ ያሻሉላችሁዋል ብለው መርጠውልን፣ አሥራሰባት ወርቅማ ዘመናችንን፣በከንቱ አሳልፈናል። አሁን ደግሞ፣ ይህ አልበቃ ተብሎ፣ይኸው፣ ሃያ አንዱን አመት፣ አሜርካኖቹና እንግሊዞቹ አዲስአበባን፣ ለሕዝባዊ ወያኔ፣ አሥመራን፣ ለሻብዕያ ሰጥተው፣ ያው እነሱ፣ በሌላ አነጋገር፣ መርጠውልን፣ እንደገና መከራችንን እናያለን።
ይህ መቆም አለበት። ይህም ሥራ፣ መታረም አለበት። እኛ ነን፣እንጂ፣አገሪቱን፣ ሊያገለግሉ፣ የሚችሉ ሰዎች፣በየአራት አመቱ መምረጥ ያለብን፣ አነሱ አይደሉም።እኛ ነን መጪው፣ ጠቅላይ ሚንስትር ማን ይሁን ብለን ድምጻችንን፣አደባባይ ወጥተን፣ የምንሰጠው አንጂ እነሱ አይደለም። ይህን ደግሞ፣ ዛሬ ከአልተናገርን፣ ነገ እኛን ከመሸጥ በምንም አይነት አይመለሱም። ያደርጉታል።
ስለዚህ፣  በአሜሪካን አገር፣ በዋሽንግተን ከተማ፣ ልክ፣ ዶከተር ማርቲን ሉተር ኪንግ ከ አንድ መቶ ሺህ ሰው በለይ አሰልፎ ለጥቁር ሕዝብ ነጻነት፣ ያኔ እንደወጣው፣ ከዚያ የሚበልጥ ኢትዮጵያዊ፣ ዋሽንግተን ላይ ወጥቶ፣ የአሜሪካን መንግሥት፣ ወቅሶ ፣ለአሜሪካ ሕዝብና  ለአለም አቤቱታውን አሰምቶ፣ የአበባ ጉንጉን፣ የሊንከንና የክንግ፣ ሐውልት ሥር አሰቀምጦ፣ ፊቱን ወደ አዲስ አበባ፣ ሰው ሁሉ፣ ማዞር ከእንግዲህ፣  ይኖርበታል። ዘራዕይ ደረስ እኮ፣ ሮም ላይ በፋሺሽቱ ሞሱሌን ላይ፣  -ያውም ነጻነት በሌለበት፣ አገር፣ ጎራዴውን፣ መዞ፣ለነጻነቱ፣ ለእናት አገሩ ለኢትዮጵያ፣ ሮም ላይ ወድቆአል። አሜሪካን አገር እንደምናውቀው፣ ሠልፍ ይፈቀዳል። አሜሪካን አገር፣ ሰው ሐሳቡን መግለጽም፣ ይችላል።
ታዲያ፣ ወደ 50 ሺህ የሚጠጋ ሰው ቢያንስ፣ ለእግር ኳስ ውድድር፣ አሜሪካን አገር የሚወጣ ከሆነ፣ለእናት አገሩ ለኢትዮጵያ፣ መቶ ሽህ፣ ከዚያም በላይ ሰው፣ ሠልፍ የማይወጣበት፣ምንም ምክንያት የለም። ደግሞ አንደዚህ አይነቱ እርምጃ በፕሬዜዳንት ኦባማ የግዛት ዘመን፣ በእሻቸው ሥር መሆኑ፣ትልቅ ትርጉም በታሪክም ፊት፣… በሚዲያም፣…በአፍሪካም፣…በጥቁሮችም ዘንድ፣ ትልቅ ቦታ አለው።
መሰብሰብ ፣ መናገር፣ መጻፍ፣ መቃወምና ሠላማዊ ሠልፍ በሕግ በተፈቀደባቸው፣ አገሮች፣ ኢትዮጵያኖች ተሰብስበው፣ በሁለት ምላስ የሚናገሩትን፣ የአሜሪካንና የአውሮጳን መንግሥታትን፣በሰላማዊ ሠልፍ እበተከታታይ፣ በለነደንና በፓሪስ፣ በስዊዲና በፍራንክፈርት፣በኬንያና በደቡብ አፍሪካ…. ነሱን  መጠየቅ፣  በሕዝቦቻቸውም ፊት፣ ማዋከብ- መብታችን ነው- ይገባል። መሆንም አለበት።
ለሮበርት ሙጋቤ፣ ለጄነራል  አልባሽር፣ ለአህመድ ነጅዳድን….ለበርማ ጄኔራሎችን፣ ….. ለኣሳድ ፣…. ወዘተ ፣ወዘተ፣ መውደቅ፣ ጡዋት ማታ የሚሰሩ፣  ለመተችት እነሱን  የማይደክሙ፣ ዲሞክራሲ ለነዚያ ሕዝቦች፣ በቶሎ  መምጣት አለበት በአደባባይ የሚሉ፣ የምዕራብ መንግሥታት፣ ለምን በወያኔና ሸብዕያ ላይ እንደማይበረቱ፣ አደባባይ ላይ እነሱ፣ በሕዝባቸው ፊት፣ መከሰስና  መጠየቅ፣የግድ፣ ያስፈልጋል። መልሳቸውንም፣ ማዳመጥ፣ ትምህርት ነው።
ከዝያ በኹላ እንግዲህ፣ አዲስ አበባን፣ እህአዴግ የራሱን ሕገ-መንግሥት እንዲያከብር፣  በሠልፍ ማጥለቅለቅ ይቻላል።
እንዴት?
ዝርዝር ጉዳዮች ውስጥ ሳልገባ፣ ሁለት ነገሮች ብቻ ላንሳ። በምንገበያይበት፣ በአሜሪካን ዶላር ላይ፣ አንድ ጥሩ ምን የመሰለ፣ አረፍተ ነገር አለ። „We trust in God“ ይላል። እኛም፣እኮ ገና ዱሮ፣ በእግዚአብሔር፣ እናምናለን፣በእሱም እንመካለን። ስለዚህ፣ ለእኛም፣ መጽሓፍ ቅዱስና ቅዱስ ቁራን በእጃችን ይዘን አደባባይ መውጣት፣- አሜሪካን አገር እንደሚደረገው- ወንጀል፣ አይደለም። ወንጄለኛም፣ አያደርገንም።  ይህን ይዘን- ይህ ነው የእኔ ምክር-   መጽሓፍ ቅዱስና ቅዱስ ቁራን በእጃችን ይዘን አደባባይ፣…  የገብርኤል ቀን እንውጣ! በአርጀንቲና- ምሳሌ ለመጥቀስ- እናቶች፣ የብረት ድስታቸውን፣ ይዘው ወጥተው፣ የወታደሩን መንግሥት ጥለዋል።
ግን ለምን የገብርኤል ቀን ብቻ?
…..በማሪያም፣ ዕለት፣ይቻላል። በሚካኤልም ፣ በጊዮርጉስም፣…..ዓርብም ቀን ቅዱሳን መጻኅፍትን፣ ቅዱስ ቁራንና መጽሓፍ ቅዱስን  ይዘን እንውጣ!
እመኑኝ፣ ውንድሞቼና እህቶቼ! ከዚህ አይነቱ፣የሰላማዊ ትግል  በኁላ፣ ድብልቅልቁ፣ ይወጣል።
እመኑኝ፣ እህቶቼና ወንድሞቼ!  የሚፈራው፣ የሻሪያ ሕግ በኢትዮጵያ፣ ፈጽሞ፣ አይመጣም። እመኑኝ የአገሬ ሰዎች፣ በዚህ እርምጃ ተአምር ይሰራል።መርሳት የለብንም። የዘውድ አገዛዝን ቀምሰናል።፣ የወታደር መንግሥትን አይተናል ።፣የወያኔና የሻቢያ በዘር ላይ የተመሠረተ፣ ያው! እንደ ደርግ፣  የኮሚንስቶችን አምባገነን መንግሥት ቀምሰን፣ጠጥተን፣ሁላችንንም ባልሳሳት፣ አሽሮናል ።
አሁን ማን ይሙት፣ ከዚህ ሁሉ የመከራ ዘመን በሁዋላ፣ የሻሪያን መንግሥት፣ ወይም የአንዱን ጎሣ መንግሥት፣ በኢትዮጵያ፣ ለማምጣት፣ የሚደፍረው? ቢመጣስ የሚቀበለው ሰው ማነው? አትፍሩ፣ እባካችሁ። አትደናገጡ ሻሪያ ይመጣል ብላችሁ።
እንኳን በኢትዮጵያ፣ብዙ ክርስቲያኖች በአሉበት አገር፣ ቀርቶ፣ (ልንገራችሁ) በግብጽም በሱዳንም፣ በሱማሊያም፣ የሻሪያ፣ መንግሥት አልተቋቋመም።ሕዝቡም ወጣቱም፣ ይህን ሥርዓት፣ አይፈልግም። ሰዎች በኢትዮጵያ የሚፈልጉት፣በአጭሩ ለማስቀመጥ፣ ሦስት ነገሮች ናቸው። አንደኛው፣ ሕዝብ የሚፈልገው፣ ሥራና ዳቦ ነው። ሁለተኛው፣የኢትዮጵያን አንድነት ነው። ከዚያም በላይ፣ሦስተኛው ማንንም ሣይፈሩ፣ አመላካቸውን አመስግነው፣ የዲሞክራሲን አየር እየተነፈሱ፣በሰላም፣አብሮ  መኖርን ነው። ወያኔን ዛሬ የሚበትነው፣ሊበትነውም የሚችለው፣ እነዚህ መሠረታዊ ጥያቄዎች ነቸው።
ታዲያ ሕልም ተፈርቶ፣ ….የለም!  ሻሪያ የሚባል ነገር ፤  ተፈርቶ፣ በወያኔ ሥር፣ ተገዝቶ፣ በባዕድ አገር ተንከራቶ፣ መሞት፣ወይም፣ በረሃብ ማለቅ፣….አያሳፍርም ወይ! ነጻነትና እና የኢትዮጵያ፣ አንድነት ደግሞ፣  ከባርነት፣እጅግ አድርጎ፣ ይበልጣል። አልተረዳነውም እንጂ፣ ባርነት ከኢትዮጵያ፣ ጠፍቶአል ይባላል። ግን አሁንም አለ። የኃያላን መንግሥታት  ጣልቃ-ገብነት፣ የለም  ይባላል። እሱም፣በደንብ አለ። ለእኛ ዛሬ „ገዢዎቻችንን ያውም ፣ ለሠላሣና ….ከዚያ በላይ“ የሚመርጡልን፣ እነሱ ናቸው። ይህ መቆም አለበት። ይህ መነገር አለበት። እነዚህ ነገሮች የሚቆሙትም፣እላይ በተዘረዘሩት፣ መንገዶች፣ብቻ፣ ነው። አልገባንም ፣እንጂ፣ሁላችንም፣ የቁም ምርኮኞች፣ ሁላችንም የቁም እሥረኞች ነን። ይህ ከሆንም በቀላሉ፣ቢያንስ አርባ አመት፣ ያልፈዋል።
ሲያሰኛቸው፣ በሌለህበት የሞት፣ፍርድ ይፈርዱብሃል። አለፍርድና ጥፋት፣ ይዞህ፣ እሥር ቤት፣ያስረሃል። ንብረትህን፣ ሊወርስ ይችላል። „የዓይን ቀለምህ አላማረኝም“፣ ብሎ፣ አቶመለሰ አንዴ እንዳሉት፣ ከአይሮፕላን ጣቢያም፣ወይም ከመኖሪያ ቤትህ ማጅራትህን ይዞ ሊያባርህ ይችላል።
ታዲያ ይህ ባርነት ነው ወይስ ነጻነት? … 18ተኛው ክፍለ ዘመን፣ ወይስ  21 ኛው፣ ክፍለዘመን?…..የት ነው ለመሆኑ ዛሬ እኛ ያለነው? የቆምነው? ማነው ይህን ሁሉ በርታ ብሎ ከጀርባ ሁኖ የሚያበረታታው?
ዝም ብለን፣ እንደተለመደው፣ተሳስቀን ፣ዳቦአችንን እየገምጠን ፣ ቢራችንን ተጎጭተን የምናልፈው፣ ጉዳይ አይደለም።  ኢትዮጵያ ከእንግዲህ አትሸጠም፣ኢትዮጵያ አትለወጥም። የሃይማኖትና ሌሎች ነጻነቶቻችን መከበር ይነኖርባቸዋል፣ ዳቦና ሥራ፣ ወጣቱና ጎልማሳው፣ ይፈልጋል። በዚህ ብቻ፣ በእነዚህ ጥያቄዎች ብቻ ውያኔን መበተን ይቻላል።
ከተቀበርንበት የዛጎል ቤታችን እንውጣ። ነገሮችን ሰፋ አድርገን እንመልከት።
ተፈሪ መኮንን

http://www.goolgule.com/ethiopia-in-21st-c/

No comments:

Post a Comment