FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Saturday, March 16, 2013

ሰራዊት በመድፈር ሙከራ ተከሷል


ሰላም ገረመው
በማስታወቂያና በፊልም ስራ የሚታወቀው አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ፤ በመድፈር ሙከራ አቤቱታ እንደቀረበበት መወራቱን በተመለከተ ተጠይቆ፤ “በሬ ወለደ ወሬ ነው” ሲል አስተባብሏል፡፡ የሠራዊት መልቲ ሚዲያ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ሠራዊት ፍቅሬ ላይ አንዲት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ለፖሊስ አቤቱታ ማቅረቧን የሚናገሩ ምንጮች፣ ባለፈው ቅዳሜ “ለማስታወቂያ ስራ እፈልግሻለሁ” ብሎ ፒያሳ አካባቢ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ ለመሳምና ለማሻሸት ሲሞክር አመለጥኩ” የሚል ነው ብለዋል፡፡
serawit
ምንጮቹ እንደሚሉት፤ የአቤቱታው ሂደት ተቋርጦ፣ ጉዳዩን በሽምግልና እንዲያልቅ መደረጉን ይናገራሉ፡፡ ከፖሊስ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ሳይሳካ የቀረ ሲሆን፤ ሠራዊት በበኩሉ “ወሬው የበሬ ወለደ አሉባልታ ነው፤ ምንም የማውቀው ነገር የለም” ብሏል፡፡ “ካሁን በፊት ከወገቤ በላይ ብዙ ተብያለሁ፤ አሁን ደግሞ ከወገቤ በታች መጡ” በማለት ቀልድ አዘል አስተያየቱን ሠጥቷል – ሠራዊት፡፡

No comments:

Post a Comment