FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Wednesday, March 13, 2013

መንግስት ታላቁን የአፋር የሀይማኖት መሪ ሊያስር ነው! ይህንንም ምክንያት በማረግ አፋሮች ከኢትዮዽያ ጂቡቲ የሚወስደውን መንገድ ዘግተዋል














አፋሮች ትግሉን መቀላቀላቸው ተከትሎ ታላቁ የሀይማኖት መሪ ሸህ መሀመድ አወል ሃይታንን ለማሰር ፌዴራል ፖሊስ እየተጠራ እንደሆነ ታወቀ::
በአፋር ህዝብ ዘንድ እንደ አባት የሚታዩትን ታላቁን ዐሊም ሸህ መሀመድ አወል ሀይታንን ለማሰር መንግስት እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሆነ ታወቀ፡፡ መንግስት ይህን እርምጃ ሊወስድ ያሰበው ለወትሮውም ቢሆን ለዲኑ ቀናኢ መሆኑ የሚታወቀው የአፋር ህዝብ በአሁን ሰዐት በዲኑ ላይ እየደረሰ ያለውን ጭቆና ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን መቃወም በመጀመሩ ነው፡፡ ሆኖም ግን የአፋር ነዋሪዎች እንደሚሉት የአፋር ህዝብ ስለ ዲኑና ስለ ማንነቱ ጠንቅቆ ያወቀበት ደረጃ ላይ በመድረሱ የትኛውንም አይነት ጭቆና ለመቀበል ፍቃደኛ አይደለም፤ ለዚህም ተቃውሞውን ተቀላቅሏል፡፡  የአፋር ህዝብ ከጊዜ ወደ ጊዜ መንቃቱ ያሰጋው መንግስት በበኩሉ በህዝብ ዘንድ ትልቅ ክብር ያላቸውን ሸህ ለማሰር እንደወሰነ፣ ይህ ደግሞ ትልቅ ዋጋ እንደሚያስከፍለው እየተነገረ ነው፡፡
ሸህ መሀመድ አወል ሀይታን በሎጊያና በሰመራ በአፋርኛ የቁርዐን ተፍሲርና ሃዲስ ህዝቡን ከማስተማራቸውም በላይ ህዝቡ እርስ በእርሱ እንዲቀራረብ ፣ እንዲከባበር፣ እንዲዋደድና ከሌላው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጋርም እንዴት ተቻችሎ መኖር እንደላለበት የሰበኩ ታላቅ የሃይማኖት አባት መሆናቸው ይታወቃል፡፡ የህዝቦች መቀራረብና ሰላም መሆን ምቾት ለማይሰጣቸው የመንግስት አካላት ግን ጉዳዩ ፍርሃት ስለለቀቀባቸው ሸሁን ማሰር አማራጭ አድርገው እንደያዙት ታውቋል፡፡ ሸህ መሀመድ እንዲታሰሩ ለመንግስት ያማከሩ ግለሰቦችና ምክሩንም ተቀብለው ተግባራዊ ያደረጉ ባለስልጣናት የመንግስትን ውድቀት የሚሹ እንደሆኑ የጠቆሙት ምንጮቻችን ቁርዐንና ሃዲስ ለምን አወራህ፣ ህዝብ እንዲከባበርና አንድ እንዲሆን ለምን መከርክ በሚል ሰበብ ሸሁ እዲታሰሩ ሲወስኑ የአፋር ህዝብን በሙሉ ሰብስቦ እስር ቤት እንደማስገባት አድርገው ሊቆጥሩ እንደሚገባና ይህም ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍላቸው እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአፋር ህዝብ ሀይማኖቱን የሚጨቁኑበትንና የሀይማኖት አባቶቹን ወደ እስር ቤት የሚልኩበትን አካላት በሰላማዊ መንገድ ለመቃወም ከምንግዜውም በላይ እንደተዘጋጀ ታውቋል፡፡ መንግስት ሸህ መሀመድ አወል ሀይታንን ለማሰር በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑ እንደታወቀ የአካባቢው ሰዎች እንደገለፁት ‹‹መንግስት ህዝብን ማዳመጥ አለበት፣ ህዝብ ያልፈለገውን ነገር በግድ ለመጫን መሞከር ከመንግስት አይጠበቅም፡፡ መንግስት ለሀገርና ህዝብ ደህንነት ያስባል በሚል አመት ሙሉ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሰላማዊ ጥሪ ላይ ቢገኝም አንዳንድ የመንግስት ፅንፈኛ ባለስልጣናት ከታሪክ መማር ባለቻላቸው ለሀገሪቷ የማይጠቅም ውሳኔ ውስጥ እየገቡ ነው ›› ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ አያይዘውም ‹‹የህዝብ ሙስሊሙ ጥያዌ ምላሽ ያገኛል በሚል ተስፋ ላይ እያለን ጭራሽ በክልላችን እንደ አባት የምናያቸውን ታላቁን ዐሊማችንን ለማሰር መወሰኑ የአፋርን ህዝብ ከምንግዜውም በላይ ድምፁን እንዲያሰማ ያደርገዋል እንጂ ወደ ኋላ አይጎትተውም›› ብለዋል፡፡
The main road that links Ethiopia to Djibouti (Port) has this afternoon been blocked by the Afar youth, De Birhanunderstands. According to De Birhan‘s sources the the main highway between Mille and Adayetu has been blocked and transportation to and from the region has been ceased. The Highway has been blocked when this reported was being posted.
Some parties are stating that the residents have blocked the road after they learnt that the government was to “arrest a prominent Afar Muslim scholar, Sheik Mohammed Awol al Hitani”. The Afar Regional State is one of the nine regional statesof Ethiopia, and is the homeland of the Afar people. It capital is Semera and lies on the paved AwashAsseb highway.
source: De Birhan‘s

No comments:

Post a Comment