FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Sunday, March 10, 2013

የሚከሽፉ መንግስታት Failed-State ምእራባውያን በታዳጊው አለም ላይ የሚሰሩትን ፕሮጀክት በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ ለማስፈፀም እንዲረዳቸው አስቀድመው የዘየዱት መሰሪ ስልት ነው፡፡


 በቅዱስ መፅሀፍ ውስጥ ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም እንዳለው ፈጣሪ ማንኛውም ነገር ዘላለማዊ አይደለምና በእርግጥ እንኳንስ ሀገራትና መንግስታት እራሷ ምድራችንም ከተወሰነላት ጊዜ ገደብ በኋላ አላፊ ነች፡፡ነገር ግን ይህንን የሚከሽፉ መንግስታት Failed-Stateትንበያና ትንተና የሚሰጡት ምእራባውያን በተለይም አሜሪካና እንግሊዝ ይህንን አይንት ትንበያና ትንተና የሚሰጡት አስቀድሞ ሊበሏት ያሰቧትን አሞራ ስሟን ዥግራ ይሏታል አይነት ምእራባውያን በታዳጊው አለም ላይ የሚሰሩትን የዘመነ ግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ ለማስፈፀም እንዲረዳቸው አስቀድመው የዘየዱት መሰሪ ስልት ነው፡፡ስለዚህም ይህ አይነት የሚከሽፉ መንግስታት Failed-State ትንበያና ትንተና ለአንድ ሰው አደገኛ መርዝ ግቶ እከሌ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ይሞታል ብሎ የመተንበይ ያክል ነው፡፡ይህንን ትንበያና ትንተና የሚሰጡት ምእረባውያን አስቀድመው ይህ እንደሚሆን ከተረዱና እራሳቸውንም ለተቀረው ታዳጊው አለም የዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ጠበቃና አርአያ እንደሆኑ አድርገው የሚያስቀምጡ ስለሆነ ለምን ይህ እንዳይሆን አስቀድመው በቀናነት ተገቢውን መልካም ስራ አይሰሩም?ምእራባውያን የእነሱን የውሸት ዲሞክራሲ በአንድ ጀንበር ለታዳጊው አለም ለመጋት ብለው እንደ ሊቢያ አይነት የተረጋጉና በልማት የበለፀጉ ሀገራትን ጭምር የዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ጠበቃና አርአያ እንደሆኑ አድርገው በማራገብ በቀጥታ የኔቶ ወረራ ለምን ፍርስርሳቸው እንዲወጣ አደረጉ?በዘመነ ግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት ትግበራ ለታዳጊው አለም የሚሰበከው ዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ከበስተጀርባ ያለው ቅኔው የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ወይንም ኢምፔሪያሊስታዊ ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ነው፡፡በተባበሩት መንግስታት የኮፊ አናን ዋና ፀሃፊነት ወቅት የረቀቀው የR2P (Responsibility To Protect) ዋና ቅኔውም የምእራቡን አለም አፍሪካንና መላውን ታዳጊውን አለም ነፍስ እንዳላወቀ ህፃን ልጅ በሞግዚት አስተዳደር የማስተዳደርና የመጠበቅ ሃላፊነትን በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ የሚያጎናፅፍ ዘመናዊ የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት ወይንም Neo-Colonialism ነው፡፡እንደሚታወቀው አሜሪካንን የአለም ብቸኛ የበላይ ልእለ ሃያል ሀገር የሚያደርገው PNAC(Plan for New American Century) ወይንም አዲሱ የአለም ስርዓትNew-World Order ከዚህ በፊትና አሁንም ያሉትን ሉአላዊ ሀገራትን Sovereign Nation State ቀስ በቀስ የሚያዳክምና የሚያፈራርስ የግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት አሰራር ነው፡፡
በዚህ እቅድ አሰራርና አካሄድ የተነሳ ደግሞ በሂደት ቀስ በቀስ የማይፈራርስ ሉአላዊ ሀገር አይኖርም ማለት ነው፡፡በምእራቡ አለምና በእኛም ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን ጥራዝ-ነጠቅ ምሁራን የሚኮነነው ዘመነ ኮሚኒዝምና ቀዝቃዛው ጠርነት አሁን ካለው የማስመሰልና የውሸት ዘመነ ዲሞክራሲ(Fantasy of The Day) ነገር ግን በተቃራኒው በተግባር ካለው የዘመነ ግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት(Order Of The Day) በአንፃራዊነት የተሻለ የአለም ሰላምና መረጋጋት የሰፈነበት ነበር፡፡ጋዳፊ በምእራባውያን የጦር ወረራ በአሳዛኝና አሳፋሪ ሁኔታ የተወገደው AFRICOM የተባለውን የአሜሪካንን አፍሪካዊ የወታደራዊ ግብረ ሃይል ስለተቃወመ ነበር እንጂ ምእረባውያን የውሸት ዲሞክራሲ ባያገኝም ቅሉ ግን የተረጋጋ ሰላማዊ ህይወት የሚኖረውን የሊቢያ ህዝብ የተሻለ ዲሞክራሲ መልካም አስተደዳርና ልማት ሊሰጡት አስበው አልነበረም፡፡አሁን በማሊ አሸባሪነትን ሽፋን አድርጎ እየተፈጠረ ያለውም የቅኝ ግዛት ወረራ የሊቢያን ቀውስ ተከትሎ ጭምር የተፈጠረ ነው፡፡አሁን ባለው የአለማችን ሁኔታ የሚከሽፉ መንግስታት Failed-State(Not Failed Governments or Regimes) እንዲፈጠሩ የሚሆነውም አሸባሪነት የተባለውን በቦታና በጊዜ ወሰን የሌለውን(Open Ended and Omnipresent) መናፍስት(Ghost) እንደ ሽፋን በመጠቀም መላውን ታዳጊውን አለም አጠቃላይ አለመረጋጋትና ቀውስ ውስጥ በመክተት እንደሆነ ብዙዎቻችን አልተረዳንም፡፡እረ ለመሆኑ አንድ ወሳኝና ምክንያታዊ ሎጂካል ጥያቄ እናንሳ::እንዴት ነው በአንድ በስልጣኔ ብዙም ያልገፋ ነው ከሚባለው የአረቡ አለም ከወጣው ኦሳማ ቢላደን ከተባለ አንድ እስላም ግለሰብ አማካኝነት የሚመራው አልቃይዳ የተባለ አሸባሪ ቡድን ለዘመናት የሰለጠነና ሃያል የሚባለውን አሜሪካንንና የምእራቡን አለም ይህንን ያህል በትሪሊዮን ዶላር የሚያስወጣ አለም አቀፍ ጦርነትና ፈተና ሊከት የቻለው?ይህ ሁል ጊዜ አእምሮዬን የሚኮረኩረኝ ቅኔ ነው፡፡በሀገራችን ያለው አገዛዝም አስቀድሞ ሊያጠቃ የሚፈልገውን ተቃዋሚ ግለሰብና ቡድን ሁሉ አሸባሪ እያለ ነው የሚፈርጀው፡፡
ከታሪክ እንደምንረዳው በአለም ላይ ያሉ ብዙ መሰሪ አገዛዞችና ልሂቃን ስልጣናቸውን (Power) በዚህም አማካኝነት ህልውናቸውን ጥቅማቸውን ፍላጎታቸውን በዘላቂነትና በአስተማማኝ ለማስጠበቅና ለማስቀጠል ሲሉ አንድን ሀገርና ህዝብ በራስ የመተማመን መንፈሱ ተኮላሽቶ ሁልጊዜ እንደ ህፃን ልጅ በፍርሃት እየራደና እየተረበሸ የእነሱን ተገቢና ጤናማ ያልሆነ ጥበቃ በመሻት ዘላለም የእነሱ ጥገኛ እያደረጉት እንደፈለጋቸው በቁጥጥራቸው ስር ለማድረግ የግድ አንድ የሆነ ጠላት (External Enemy) እንደሚፈጥሩ የታወቀ ነው፡፡ እነዚህ አገዛዞችና ልሂቃን ይህንን አይነት መሰሪ ስራና ስልት ተግባራዊ የሚያደርጉበት ዋና ስልት ደግሞ State-Terrorism በመጠቀም ነው፡፡እንደዚሁም እነዚህ መሰሪ አገዛዞችና ልሂቃን ሌላውን ለፍላጎታቸው የማይመቻቸውን ደካማ ሀገር ለማጥቃትና ለመውረር የግድ ይህንን ተመሳሳይ ሁኔታ በመጠቀም የሚገዙትን የሀገራቸውን ህዝብ አሳምነው ወደ ጦርነት ውስጥ ለመግባት የግድ አንድ የሆነ ሰበብ (Casus-belli) በተጠቂው ሀገርና መንግስት ላይ መሸረብ አለባቸው፡፡እነዚህ መሰሪ አገዛዞችና ልሂቃን ይህንን አይነት መሰሪ ስራና ስልት ተግባራዊ የሚያደርጉበት ቅድመ ሁኔታና ስልት ደግሞ አስቀድመው Mainstream ሚዲያውን በመጠቀም ሊያጠቁት የሚፈልጉትን ሀገርና አገዛዝ ሃጢያት የተጋነነና የተዛባ እውነታ በመፍጠር ሰለባ የሚሆነውን ሀገርና አገዛዝ የተወገዘና የተረገመ (Demonize) እንዲሆን በማድረግ ነው፡፡The first casualty of war is truth የሚባለውም ለዚህ ነው፡፡ጋዳፊ የምእራባውያን ሰለባ ከመሆኑ በፊት አስቀድሞ 42 አመት ያስተዳደረውን የገዛ እራሱን ህዝብ እንደ ጭራቅ የሚበላ ፍጡር ተደርጎ ነበር በMainstream ሚዲያው የተሳለው፡፡ከዚያ ግን ምን ተፈጠረ?አዎ ምእራባውያን በኔቶ አማካኝነት የሊቢያን በተለይም የጋዳፊን የትወልድ አካባቢ ነው የሚባለውን መሰረተ ልማት በቦምብ እንዳልነበረ አድርገው አፈራረሱት እንደዚሁም ጣልቃ-ገብነታችን ለሰብዓዊነት(Humanitarian Mission) ነው እንዳልተባለ ጋዳፊንም ለርፍድ እንኳን ሳይቀርብና አጠፋ የተባለው ጥፋትና ወንጀል ለአለም ህዝብ ይፋ ሳይሆንና ሳይረጋጋጥ አሳዛኝና አሳፋሪ በሆነ ኢ-ሰብዓዊ በሆነ ሁኔታ ገደሉት እንደዚሁም ይህንን ወረራ ተከትሎ ብዙ ወዘተ ወዘተ ሁኔታ ተፈጠረ፡፡ነገሩን መዘርዘር ስለሚከብድ ነገር ግን ቢያንስ አንድ ወሳኝ ነገር ላንሳ፡፡ለመሆኑ ጋዳፊ በውጪ በምእራቡ አለም ባንኮች አስቀመጠው የተባለውና በጦርነቱ ወቅት እንዳይንቀሳቀስ የተደረገ የነበረው በመቶ ቢሊዮነች ዶላር የሊቢያ ህዝብ ገንዘብ እጣ ፈንታው ምን ሆነ?ነው ወይነስ ይህ ገንዘብ ምእራባውያን ለሊቢያ ወራራ ላወጡት ገንዝብ ካሳ የሚከፈልና የሊቢያንም መሰረተ ልማት በቦምብ ስላፈራረሱት መልሰው ለመገንባት የእነሱ ሀገራት አለም አቀፍ ኩባንያዎች ለሚወስዱት ውድ የፕሮጀክት ኮንትራት እንደ ማካካሻ የሚከፈል የጦር ካሳ ማለት ነው?አዎ በዘመነ ግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት አሰራር ስንሄድ ደካማ ተዳጊ ሀገራትን በጠርነት መውርርና የተፈጥሮ ሀብታቸውንና ኢኮኖሚያቸውን መቆጣጠር ነፃ-ገበያ ተብሎ ይጠራል፡፡ብዙ የአለም ጦርነቶችን ታሪክ ስናጠና አንዱ ዋናው የስር መሰረቱ መነሻ መንስኤ እራሱ ግሎባል ካፒታሊዝም ሆኖ እናገኘዋለን፡፡አንዳንድ የፖለቲካ ጠበብት እንደሚናገሩት ከሆነም በማሊ ያለው የእርስ በርስ ግጭትና ይህንንም አሸባሪነት የተባለ መናፍስት ሰብብ አድርጎ እየተፈፀመ ያለው የውጪ ወረራ ዋናው መንስኤ በራሱ በምእራቡ አለም ካለው የግሎባል ካፒታሊዝም የፋይናንስ ቀውስ ጋር በተያያዘ በማሊ ያለውን የተፈጥሮ ሀብት በተለይም ወርቅ ፍለጋ ነው፡፡እንግዲህ ይህች ናት የግሎባል ካፒታሊዝም ዲሞክራሲና ነፃ-ገበያ ሰምና ወርቅ ቅኔ፡፡የሚከሽፉ መንግስታት Failed-State ትንበያና ትንተናም ከዚህ የታዳጊውን አለም የተፈጥሮ ሀብትና ኢኮኖሚ ያለማንም ሃይ ባይ እንደፈለጉ ለመቀራመትና ለመዝረፍ ከታለመ የረቀቀና የተቀነባበረ መሰሪ ስልት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ምክንያቱም የሚከሽፉ መንግስታት Failed-State ሉአላዊ ሀገር(Sovereign Nation State) ስላልሆኑ የገዛ ህዝባቸውንና ሀብታቸውን ከውጪ ሃይል ለመከላከልና ለመቆጣጠር አይችሉም ማለት ነው፡፡ስለዚህም ለምሳሌ አፍሪካውያን ቀስ በቀስ AFRICOM በሚባለው የአሜሪካ ወታደራዊ የውጪ ባእድ የሞግዚት አስተዳደርና ጥበቃ ስር ሆነው ነገር ግን ከውስጥ ባሉ እንደ ጠንካራ መንግስት በማይታዩ ሀገር በቀልና ሃላፊነት በማይሰማቸው ቅጥረኛ የሆኑ ወሮበላና ሆዳም ልሂቃንና አገዛዞች ነው የመተዳደሩት ማለት ነው፡፡የR2P(Responsibility To Protect) ቅኔው ይህ ነው፡፡Yes the civilized West has the responsibility to protect and rule the rest uncivilized world.አዎ R2P ተግባራዊ እንዲሆን ደግሞ የግድ ሃላፊነት የማይሰማቸውና ሀገራቸውና ህዝባቸውን የማያከብሩ የማይወዱ የማይታመኑ አድርባይና ሆዳም ወሮበላ የሆኑ ቅጥረኛ ሀገር በቀል ልሂቃንና አገዛዞች በራሳቸው በምእራባውያን እየተደገፉ በረቀቀና በተቀነባበረ መንገድ ስልጣን ላይ እንዲወጡ ይደረጋል፡፡ሀገርና ህዝብ በእነዚህ ቅጠረኞች በአለቆቻቸው እርዳታ ጭምር አበሳውን እያየ የእርስ በረስ ጦርነት እልቂትና መበታተን(የከሽፈ መንግስት Failed-State) ውስጥ ሲገባ ምእራባውያን ደግሞ እንደ አዳኝ መሲህ(Holly Savior) ሆነው ነፃ ሊያወጡንና ሊጠብቁን ይመጣሉ ማለት ነው፡፡
አዎ የታዳጊው አለም ህዝብ በሁለት ጨካኞች(ሀገር በቀል እና ውጪ) መካከል ዘላለም አበሳውን ያያል ማለት ነው፡፡ኢትዮጵያም ሆነች አፍሪካ እንዲሁም መላው ታዳጊው አለም በዚህ በዘመነ ግሎባል ካፒታሊዝም ኒዎ-ሊበራል እና ኒዎ-ኮሎኒያሊዝም ኢምፔሪያሊስታዊ ፕሮጀክት የተነሳ አበሳቸውን እያዩ ሳለ ስለግለሰቦች ዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብት ብቻም ሳይሆን እንደ ሉአላዊ ሀገር(Sovereign Nation-State)አንድ ሀገርና ህዝብ እንዴት ተከብሮና ታፍሮ የጋራ ህልውናውና ደህንነቱ(Collective Security and Common goods) ተጠብቆ ለመቀጠል እንደሚቻል እጅግ ፈታኝ እየሆነ ነው፡፡የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች እንዲሁም ሰዶ ማሳደድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ እንዲሉ ደርሶ በዘመነ ወያኔ ኢትዮጵያችን የጋሪና የፈረሱ ቅድም ተከተል ተምታቶብን ያለአካሄዱ ስለ ግለሰብ ነፃነትና ዲሞክራሲ ያን ያህል በከንቱ ተጨነቅን እንጂ ከዚህ በባሰ ግን እንደ ሀገር የመቀጠል ትልቅ አደጋው ግን ብዙ የታየን አልሆነም፡፡
በዘመነ ቅኝ ግዛት አበሳውን ሲያይ የነበረውና አሁንም በዚያው ተመሳሳይ ዘመናዊ ቅኝ ግዛት ውስጥ ለሚዛብቀውና እንደ ህፃን ልጅ ዳዴ የሚለው ታዳጊው አለም የጋራ ህልውናውና ደህንነቱ (Collective Security and Common goods) ተጠብቆ እንደ ሉአላዊ ሀገር(Sovereign Nation-State) ለመቀጠል የሚችለው ይበልጥ በጋራ ጉዳዩ (Socialistic) ላይ በማተኮር እንጂ የምእራቡን አለም አይነት የግለሰብ ነፃነትን(ሊበራል ዲሞክራሲ) በማቀንቀን አይደለም፡፡በታዳጊው አለም ውስጥ የግለሰብ ነፃነት(ሊበራል ዲሞክራሲ) በዘላቂነትና በአስተማማኝ ተግባራዊና ውጤታማ ሊሆን የሚችለው ታዳጊው አለም ቅድሚያ የጋራ ህልውናውና ደህንነቱ (Collective Security and Common goods) ተጠብቆ እንደ ሉአላዊ ሀገር(Sovereign Nation-State) ለመቀጠል ሲችል ነው፡፡ዛሬ ወደ ልእለ ሃያልነት ደረጃ የደረሰችው ቻይናም ለዚህ የበቃችው ዋና ምክንያት ይህንን የጋራ ህልውናና ደህንነት (Collective Security and Common goods) ተጠብቆ የምእራቡን አለምና የጃፓንን ቅኝ ግዛት ጫና በመቋቋም እንደ ሉአላዊ ሀገር(Sovereign Nation-State) ለመቀጠል ስለቻለች ነው፡፡ታዳጊው አለም ይህንን እንዲያደርግ የተፈጥሮ ህግም ጭምር ያስገድደዋል፡፡ምክንያቱም የግለሰብ ነፃነትን በተገቢው ሁኔታ በመቀነስና ይህንንም በጋራ ህልውናውና ደህንነት (Collective Security and Common goods) ላይ በማዋል ነው የውጪውን ጫናና ወረራ ለመመከት የሚቻለውና በዚህም የከሽፈ መንግስት Failed-State ከመሆን መታደግ የሚቻለው ፡፡We have to be so wise so that we achieve such a viable and working stable and balanced equilibrium point where we can survive both as an individual as well as a society in our nation-statehood. Failed-State becomes inevitable whenever such viable and working stable and balanced equilibrium point is destabilized. So here it is very important to properly discern the nature of our social fabric and class structure in our nation-state so that we shall not become failed-state.
So as long as it has the power to destabilize the equilibrium point of our social fabric and class structure not only savage dictatorship that has the power to render failed-state but also externally imposed westernized bogus democracy has also similar tantamount role to cause same effect of failed-state. Because we have live witnessed bogus democracy becoming the very source of conflict, violence and ensuing chaos that has been destabilizing 3rd world nations. And that is why Bogus democracy and humanitarian mission is serving as a Joker card by West in order to systematically destabilize 3rd world nations. Any way be it trough direct and blatant dictatorship (as is in Monarchical Arabic GCC Nations) or be it through bogus democracy (as is in Ethiopia and many other 3rd world nations) however what Global Capitalism aspires and thrives is to have installed stooge client-regimes who serve its Neo-Liberal and Neo-colonialism Imperialistic projects. And hence neither Dictatorship nor Democracy is its agenda (and never ever will it be) as long as its interest are maintained.
So the irony behind Failed-State hype is like the irony behind terrorism hype.
Because both happen mainly because it is systematically and insidiously maneuvered by global master elites to happen likewise.So when we are doomed by others to become failed-State in prediction, we have to be aware that they also want us to be like that and it is also their wish so for it not to happen on us as a reality we have to work hard. One of the great means is to honestly and audaciously expose both the lies and the truth to the public for public awareness and enlightenment.
God Bless Ethiopia!!!
Save-Ethiopia says: www.goolgule.com

No comments:

Post a Comment