FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Wednesday, March 6, 2013

ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ

frankfurt
- ”የህሊና እስረኞች ይፈቱ!”
- ”የፕሬስ ነጻነት ይከበር!”
- ”ሃሳብን በነጻነት የመግለፅ መብት ይከበር!”
- ”ጅሃዳዊ ሐረካት የወያኔ ፈጠራ ነው!”
- ”የሃይማኖት ነፃነት ይከበር!”
-  ”በአለም ዙሪያ ያሉ የወያኔ ቆንስላ ፅ/ቤቶች የኢትዮጵያን ህዝብ አይወክሉም!”
- ”የአውሮፓ ህብረት ለአፋኙ የወያኔ አገዛዝ የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፍ ያቁም!”
- ”ከአባይ በፊት ሙስናና ዘረኝነት ይገደብ!” የሚሉ መፈክሮች በሰፊው የተደመጡ ሲሆን
ከአንድ ሰዓት ተኩል የእግር ጉዞ በኋላ ተሰላፊው የወያኔ ቆንስላ ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሲደርስ በከፍተኛ ጩኸት እና ፉጨት ተቃውሞውን ማሰማት ችሏል። በዚህም የተደናገጡት የወያኔ ቆንስላ ሠራተኞች የህንፃውን መስኮት በፍጥነት በመዝጋት ከፊሎቹ ህንፃውን እየለቀቁ የወጡ ሲሆን ቁጥራቸው ከአራት የማይበልጥ የቆንስላው ራተኞችም ከውስጥ በመሆን ሠልፈኞችን ለማስፈራራት በሚመስል መልኩ ፎቶ ሲያነሱ ተስተውለዋል። ሰልፈኛውም ተቃውሞውን ይበልጥ በማጠናከር ለአንድ ሰዓት ያህል መፈክሮችን በማሰማት፣ የሀገር ፍቅር ዜማዎችን በማዜም እንዲሁም ይህንን ሰልፍ በቅርብ ርቀት ይመለከቱ ለነበሩ የሀገሬው ዜጎች በጀርመን፣በእንግሊዝኛና በአማርኛ ቋንቋዎች የተዘጋጁ በራሪ ወረቀቶችን በማደል የኢትዮጵያ ህዝብ በዘረኛው የወያኔ አገዛዝ እየደረሰበት ያለውን ግፍና መከራ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ይፋ አድርገዋል።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ተወካይ፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች እና የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተወካዮች በአካል ተገኝተው አጠር ያለ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎም ከኔዘርላንድ የላከው ደብዳቤ ተነቧል።
ይህ ከሶስት ሰዓት በላይ የፈጀው የተቃውሞ ሠልፍም በሠላምና በታላቅ ድምቀት መጠናቀቅ ችሏል።
By: Dawit Fanta /Engineer/

http://www.goolgule.com/demo-in-frankfurt-germany/

No comments:

Post a Comment