FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Saturday, March 9, 2013

የአዋሽ ባንክ ፕሬዚዳንት ከሃገር እንዳይወጡ ታገዱ

“ዜብራ” ላይ ሰው ገጭተው ሸሽተዋል በመባል ለ10 ቀናት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የቆዩት የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ፀሐይ ሽፈራው በዋስ ተፈቱ፡፡ ወደ ውጭ አገር እንዳይጓዙ ታግደዋል፡፡ 

በትናንቱ የቂርቆስ ምድብ ችሎት፤ ፖሊስ የአንድ ምስክር ማስረጃ ውስብስብ ሁኔታ ፈጥሮብኛል ብሏል፡፡ አቶ ፀሐይ የተጠረጠሩበት ጉዳይ የዋስ መብት የማያሰጥ ቢሆንም በዋስ ከተለቀቁ ግን ከአገር እንዳይወጡ ለሚግሬሽን ትእዛዝ ይሰጥልኝ ብሏል – ፖሊስ፡፡ 

የሥራቸው ፀባይ ከአገር የሚያስወጣ በመሆኑ ከአገር እንዳይወጡ እግድ እንዳይሰጥ የተከራከሩት የአቶ ፀሐይ ጠበቆች በበኩላቸው፤ ሌላ አማራጭ እንዲሰጥ ወይም ለፖሊስ አሳውቀው እንዲወጡ እንዲፈቀድ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ 
ዳኛው የግራ ቀኙን ከሰሙ በኋላ ተጠርጣሪው በ50 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁና ከአገር እንዳይወጡ ለሚግሬሽን እንዲጻፍ አዘዋል፡፡

No comments:

Post a Comment