ከታምሩ ገዳ
ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ የዜና እረፍታቸው ለህዝባቸው እና ለመላው አለም ይፋ የተደረገው የቬንዙዌላው ፕሬዜዳንት ሁጎ ቻቬዝ በብዙዎች ዘንድ አስገራሚ እና አወዛጋቢ ባህሪ የተላበሱ መሪ ነበሩ፡፡ያቺ በላቲን አሜሪካ ውስጥ በተፈጥሮ ጋዝ ሃብቷ ቀዳሚ ስፍራ ያላት ቬንቩዌላን ላለፉት 14 አመታት በሶሻሊስታዊ ርእዮት አለም አካሄድ የመሯት ቻቬዝ ላለፉት ሁለት አመታት ከካንሰር ህመም ጋር ውጊያ ቢያደርጉም በተወለዱ በ58 አመታቸው የሚወዱት ህዝባቸውን እና ከበዙዎች አይምሮ የማይጠፉ አሰገራሚ ትዝታዎቻቸውን ጥለው ወደ ማይቀረው አለም ሄደዋል፡፡
ቻቬዝ በህይወት ዘመናቸው ኑሯቸውን የቀየሩላቸው በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቬንዙዊላዊያን ባለፈው አርብ እለት በተካሄደው የአስክሬን ስንብት ስነ ስርአት ላይ በመገኘት ለታላቁ መሪያቸው ያላቸውን ዘለአለማዊ ክብር እና ፍቅር ለመገለጽ አብዛኞቹ ከ26 ሰአታት በላይ ተሰልፈው ተራቸው እስኪደርስ መጠባበቅ ነበረባቸው፡፡ አነዚያ የአገሪቱ ቤጫ፡ ሰማያዊ እና ቀይ ቀለማትን ያካተተው ብሄራዊ ሰንደቃ አላማን በመልበስ እና በማውለብለብ ወይም የሟቹ ቻቬዝ ምስሎችን በአንገታችው ላይ በማንጠልጠል በዋና መዲናይቱ ካርካካስ ጎዳናዎች ላይ የተሰለፉ የቻቬዝ ደጋፊዎች መሪር ሃዘናቸውን እና እንባቸውን ማፍሰሳቸው አልቀረም፡፡ የታላቁ መሪያቸው (የቻቬዝን ) አሰክሬን መሰናበት ለአብዛኛው ደጋፊዎቻቸው (ቻቬስታስ) ከመሰዋቶች ሁሉ እጅግ ትንሿ መሰዋአት ነበረች ማለት ይቻላል፡፡ ከዚያ በላይ ማድረግ ቢቻል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት እነዚህ የቻቬዝ ደጋፊዎች ሁሉንም ነገር በፍቃደኝነት ባደረጉት ነበር፡፡ አብዛኞቹ የቻቬዝ ደጋፊዎች ለምን ወደ አደባባይ እንደ ወጡ ሲጠየቁ “ ወደዚህ ቦታ ማልደን የመጣነው በፍቅር ነው፡፡ይህ ታላቁ መሪያችንን የመሰናበት እድል ጨርሶ ሊያመልጠን አይገባም፡፡” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚቆጠሩ ቬንዙዌላዊያን ርዝማኔው ከአንድ ኬሎ ሜትር በላይ በሚሆነው የዋና መዲናይቱ ጎዳና ላይ ጸሃይ ፡ብርድ :ረሃብ፡ የውሃ ጥም ሳይሉ በጽሞና ሲጠባበቁ በቴሌቭዥን መስኮት ለተመለከተ “ተወዳጅ መሪ ማለት እንደ ቻቬዝ ነው” ሳያሰኝ አልቀረም፡፡ጁአና ኡካቲጋ ትባላላች የአንደኛ ደረጃ ት\ቤት መምህር ስትሆን አፍቃሪ ቻቬዝ ከሚባሉት ወገኖች መካከል አንዷ ነች፡፡ ጁአና የታላቁ መሪዋን አስክሬንን ለመሰናበት ከተሰላፊው ህዝብ ብዛት የተነሳ ከ15 ሰአት በላይ ወረፋ መጠበቅ ነበረባት ፡፡ መቼም መድረሱ አይቀር ተራዋ ሲደርስ ምን እንደተሰማት ለዜና ሰዎች ስትናገር “ወደአስክሬናቸው ስጠጋ መሪር ሃዘን ተሰምቶኝ ነበር ይሁንና ከአስክሬናቸው አጠገብ ስደርስ ያ ዘወትር የሚያጠልቁት ቀዩ የወታደራዊ ኮፍያችውን ፡የደምብ ልብሳቸውን ለብሰው የክብር ሜዳሊያቸውን አጥልቀው ስምለከታቸው ከፍተኛ ደስታ ተስምቶኛል ፡፡ቀረብ ብዮ ስመለከታቸው ቻቬዝ እጅግ ውብ ነበሩ “ብላለች፡፡የሰላሳ አመቷ ኬምብሬይ ጋርሼያ ሌላኛዋ የቻቬዝ ደጋፊ ስትሆን በቆራጡ መሪዋ መሞት የተሰማትን ሃዘን የገለጸችው” ቻቬዝ ጸሃያችን ናቸው ፡ቻቬዝ ሰማያችን ናቸው ፡፡እርሶን ለመግለጽ ቃላት ያጥረኛል እንዲያው በደፈናው ዛሬ አገር እንዲኖረን ስላደረጉን እናመሰግንወታለን፡፡” በማለት አፍቃሪ ቻቬዝነቷን
ስሜቷን መቆጣጠር እስኪሳናት ድረስ በማልቀስ ገልጻለች፡፡ ሁጎ ቻቬዝ በተለያዩ የአሜሪካ እና የአውሮፓ ባንኮች ውስጥ የሚገኙ ዋጋቸው በ ብዙ ቤሊዮኖች የአሜሪካ ዶላር የሚገመቱ የቬንዙዌላ ተቀማጭ ወርቆች ከባንኮቹ ውጥተው ወደ አገሪቱ ብሄራዊ ባንክ እንዲቀመጡ ውሳኔ በማስተላለፍ የብሄርተኛነት (ናሽናሊስት) ስሜት በማንጸባረቃቸው ፡በአገሪቱ የሚገኙ የነዳጅ ማማረቻዎች ለደሃው የአገሪው ህዝብ መሰረታዊ ፍጆታዎች ማሙያዎች እንዲያበረክቱ በማድርግ ፡ደሃው ዜጋ ተመጣጣኝ እና አንስተኛ ዋጋ የሚጠይቁ መኖሪያ ቤቶች እንዲኖራቸው በማድረግ የአብዛኛው ደሃው ማህብረሰብ አባት ተብለው ሲጠሩ በምትኩ ቱጃር ቬንዙላዊያኖች ከተስፋ ምኞት ውጪ ለሃብታሞች ያልጠቀሙ የአገሪቱን አንጡራ ሃብት ለፖለቲካ ፍጆታችው ያደረጉ ፡ኤኮኖሚውን ወደ ተሳሳተ መንገድ እንዲሄድ ያደረጉ ፡ተቃዋሚዎችን የሚደፈጥጡ (አምባገንን )መሪ . ናቸው ሲሉ ይወነጅሏቸዋል፡፡ እኝህ በህይወት ዘመናቸው ብዙ ወዳጆች (ከዝቅተኛው ማህበረሰብ) እና መጠነኛ ተቃዋሚዎችን ያፈሩት ሁጎ ቻቬዝ የቀድሞው የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆርጅ ቡሽን “ሰይጣን” በማለት በአደባባይ በመጥራት ለሃያሏ አገር አሜሪካ ያላቸውን ንቀት ያስመሰከሩ ሶሻሌስታዊ መሪ ነበሩ፡፡ በተቃራኔው ቻቬዝ የቀድሞው የኩባ ፕሬዜዳንት ፊደል ካስትሮን “መምህሬ እና አባቴ” በማለት ለዚያች ትንሽ አገር የነበራቸውን ልዩ ፍቅር እና ቀረቤታ ከማሳየታቸው በተጨማሪ ኩባ በቀላሉ ከማይነጥፈው የቬንዙዌላ የተፈጥሮ ጋዝ በረካሽ ዋጋ እንዲፈስላት አድርገዋል፡፡
ሌሎቹ ጎረቤት አገሮች ኔኳራጓ እና ቦሊቬያ ተመሳሳይ የቻቬዝ ምጽዋተኞች አድርገው የሚቆጥሯቸው ተቃዋሚዎቻቸው የቦሊቬያው ፕሬዜዳንት ኤቮ ሞዳሌ ካለፈው እሮብ አንስቶ ከቻቬዝ እስክሬን አጠገብ ባለመለየት የማልቀሳቸው ነገር “እንደ ጨቅላ ህጻን ልጅ ገንዘብ ተከፍላቸው ያለቀሱ ፕሬዜዳንት” የሚል ስላቅ ተሰልቆባቸዋል፡፡ በረካታ አገሮች በቻቬዝ መሞት የተሰማቸውን ሃዝን ለመግለጽ ሲሉ በአገራቸው ብሄራዊ የሃዘን ቀን እስከ ማወጅ ደርሰዋል፡፡በሌላ በኩል ከቻቬዝ ጋር ምንም አይነት የጥቅም ግንኙነት ሳይኖራችው የአላማ ቁርኝት ብቻ ያላቸው በርካታ የአለም መሪዎች እና ታዋቂ ሰዎች የቻቬዝ አስክሬንን ለመሰናበት ባለፈው አርብ እለት ቬንዚዌላ ውስጥ የገቡ ሲሆን ከቻቬዝ ጋር የተለየ ቅርርቦሽ የነበራቸው የኤራኑ ፕሬዜዳንት አህመዲን ናጃት የቻቬዝን መሞት ገና እንደሰሙ በግል ድህረ ገጻቸው ላይ “ቻቬዝ እንደ እየሱስ ክርስቶስ እና አንደ ሼያቱ ሙስሊም ኤማሙ መሃዲን ሞትን ድል አደርገው በመነሳት ስለ ሰላም እና ፍትህ መስፈን ይሰብካሉ “ማለታቸው በአገር ቤት (ኤራን) ውስጥ ከፈተኛ የህዝብ ቁጣ ያስነሳባችው ቢሆንም “ጽረ- ኤምፔሪያሌስቱ” አህመድ ነጃት በቬንዙዊላ ቆይታቻው የቻቬዝ አስክሬን በአጃቸው በመዳሰስ እና የራሳቸው የቀኝ እጅ ወደ ላይ ከፍ በማድርግ እርሳቸው ሆኑ አገራቸው ኤራን ቻቬዝን ለዘላለም የማትረሳ መሆኗን ለታዳሚው ለማሳይት ሞክረዋል፡፡የኤራኑ መሪ አቀራረብ ምንም እንኳን የፕሮቶኮል ሄደትን የጣሰ ቢሆንም በረካታ እንግዶች ድጋፋቸውን ለአህመድ ነጃት ከመስጠት አለተቆጠቡም፡፡ የቻቬዝን ወንበር በጊዜያዊነት በቃለ መሃላ የተረከቡት ምክትላቸው ኔኮላስ ማደሮ በበኩላቸው ሲቃ እየትናነቃቸው “ ጓድ ቻቬዝ ዛሬ አልተሸነፉም፡፡ለዘለአለም ይኖራሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ሀዘንተኛውም በበኩሉ” ቻቬዝ ለዘላለም ይኑሩ ትግሉም ይቀጥላል “ በማለት ጠንካራ ሶሻሊስታዊ አቋሙን ገልጿል፡፡ በነገራችን ላይ የኤራኑ መሪ እና ከፍተኛ የቬንዙዌላ ባለሰልጣናትን ጨምሮ በረካታ አፍቃሪ ቻቬዞች በቆራጥ እና ብሄርተኝነት አቋሟቸው ከምእራባዊያኖች አካባቤ ጠላት እንዳተረፉ የሚነገርላቸው ቻቬዝ ለሞታቸው መንስኤው የተፈጥሮ ህመም ብቻ ሳይሆን የአሜሪካኑ የስልላ ድርጅት የሆነው (ሴ አይ ኤ) እና የአስራኤሉ አቻው (ሞሳድ )እጆች ሳይኖርበት አይቀርም ከሚል ጥርጣሬ ላይ የደረሱ ሲሆን ለዚህ አባባላቸው አንደማስረጃ የሚያቀርቡት የቀድሞው የኩባ ፕሬዜዳንት ፊደል ካስትሮን ለመግደል ተሞክረው የከሸፉትን በርካታ የግድያ ሙከራዎችን ይጠቅሳሉ፡፡ሁኔታውም እንዲጣራ ቬንዙዌላ ውስጥ ምርምር ተጀምሯል፡፡
የቬንዙዌላ መንግስት የቻቬዝ አስክሬንን እንደ ቀድሞው የራሺያው ቭላዲሜር ሌኒን እና ጆሴፍ ስታሊን እንዲሁም ፡ እንደ ቻይናው ኮሚኒስት መሪ ማኦ ዘእይቱንግ ሳይፈራርስ በመሰታወት ውስጥ በማድረግ ህዝቡ እና ቱሪስቶች እየመጡ በክብር እንዲጎበኙት ውሳኔ አስተላልፋል፡፡የላቲን አሜሪካ ፖለቲካን በብዙ መልኩ የቀየሩት ሁጎ ቻቬዝ አገራቸው ድህረ ቻቬዝ ምን አይነት የፖለቲካ እና የኤኮኖሚ ፖሊሲን ትከተል ይሆን የሚለው ጥያቄ ዛሬም ነገም በጥያቄነቱ የሚዘልቅ ይመስላል፡፡ ቬንዙዌላ አዲስ ፕሬዜዳንት ለመምርጥ በመጬው ወር ሜያዚያ 14 2013 እ ኤአ የቀን ቀጠሮ የዘዋል :: ምርጫው ምን ሆነ ምን አንድ ነገርን በቅድሜያ በርግጠኝነት መናገር ይቻላል እርሱም ቻቬዝን የሚተካ ደፋር፡ ከግል ጥቅሙ ስለህዝቡ ኑሮ መሻሻል የሜጨነቅ እና በፈገግታው እና በአነጋገሩ የብዙሃኑን ቀልብ የሚስብ መሪ ማግኘት እጅግ ከባድ መሆኑን ነው፡፡
No comments:
Post a Comment