FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Saturday, March 9, 2013

ኡሁሩ ኬንያታ የኬንያን ምርጫ አሸነፉ


የካቲት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 
ኢሳት ዜና:-የኬንያን ምርጫ የጆሞ ኬንያታ ልጅ እና የወቅቱ የሀገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኡሁሩ ኬንያታ ማሸነፋቸው ተገለጸ።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከየክልሎቹ የምርጫ ጣቢያዎች የተሰባሰቡት ውጤቶች ኡሁሩ ኬንያታ በጠባብ ልዩነት ማሸነፋቸውን የሚያመለክቱ ናቸው።
እስካሁን በተደረገው ቆጠራ ኡሁሩ ኬንያታ 50 ነጥብ 3 በመቶ ማግኘታቸው ተመልክቷል።
ምርጫውን ያሸንፋሉ ተብለው በስፋት ሲጠበቁ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ፤ተቀናቃኛቸውን ራይላ ኦዲንጋን አሸናፊ የሚያደርግን ውጤት ፈጽሞ እንደማይቀበሉት ተናግረዋል።
የ አገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን  በ ኦፊሴል ደረጃ ውጤቱን ይፋ ለማድረግ በተዘጋጀበት  ሰዓት፤የኦሬንጅ ዲሞክራቲክ ንቅናቄ መሪ የሆኑት ራይላ ኦዲንጋ በምርጫው አሸናፊ ካልሆኑ ክስ እንደሚመሰርቱ አስጠንቅቀዋል።
ሳሊም ሎን የተባሉት  ለኔሽን ጋዜጣ ስለጉዳዩ በሰጡት አስተያየት፦<<ራይላ ኦዲንጋ መሸነፋቸውን የሚያመለክትን ውጤት ተዓማኒ ነው ብሎ ለመቀበከል ያስቸግራል>>ብለዋል።
ሁለቱም ዕጩዎች ካለፈው ሰኞ ጀምሮ በድምጽ ቆጠራ ሂደቱ ላይ በታዩ ችግሮች አቤቱታ ሲያቀርቡ መቆየታቸው ይታወሳል።
አሸናፊ ለመሆን የሚያስፈልገው ድምጽ 5 ሚሊዮን 340ሺህ 546 ሲሆን፤እስካሁን በተደረገው ቆጠራ ከአጠቃላይ 12ነጥብ 3 ሚሊዮን ድምጽ መካከል ኡሁሩ ኬንያታ  6ሚሊዮን 173ሺህ 433 ድምጽ ማግኘታቸው እየተገለጸ ነው።

No comments:

Post a Comment