ኢህአዴግ ያወጣው የአመራር መተካካት ከመፈክር ባለፈ እየተተገበረ አለመሆኑን ለግንባሩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ የግንባሩ ከፍተኛ አመራሮች ከ17 ዓመታት በላይ በጫካ ትግል ላይ ዕድሜያቸውን ያሳለፉ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በአሁኑ ወቅት በተለይ ከዕድሜና ሕመም ጋር ተያይዞ ብዙዎቹ የያዙትን ከፍተኛ ኃላፊነት መወጣት የማይችሉበት ደረጃ ላይ እየደረሱ በመሆናቸው በሌላ አመራር የመተካታቸው ጉዳይ ታምኖበት የአፈጻጸም ፕሮግራም ወጥቶለት እንደነበር ይታወሳል፡፡
በዚሁ ፕሮግራም መሰረት እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ነባሩ አመራር በአዲስ ኃይል እንዲተካ በሟቹ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ የተነደፈ ዕቅድ ቢኖርም በአሁን ወቅት አፈጻጸሙ ከመፈክር በዘለለ እየተተገበረ አለመሆኑ ታውቋል፡፡ ለዚህ ዋነኛው ምክንያት ከፍተኛ አመራሩ ስልጣን ለማስረከብ ፈቃደኛ ካለመሆኑ ጋር የተያያዘ ነው፡፡
ከመስከረም 5 እሰከ 7/2003 ዓ.ም በአዳማ በአባገዳ አዳራሽ የተካሄደውን የግንባሩን 8ኛ ጉባዔ ተከትሎ በዚሁ የመተካካት መርህ መሰረት ከህወሃት አቶ ስዩም መስፍን፣አቶ አባይ ጸሐዩ፣አቶ አርከበ ዕቁባይ፣ከብአዴን አቶ አዲሱ ለገሰ ፣አቶ ተፈራ ዋልዋ፣አቶ ታደሰ ካሳ ከፓርቲ የአመራር ቦታቸው እንዲገለሉ ተደርገዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በስራ ላይ ያሉት እነአቶ አባይ ወልዱ፣ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል፣አቶ ጸጋዩ በርሄ፣አቶ በረከት ስምኦን፣የመሳሰሉ ነባር አባላት ስልጣናቸውን ለተተኪዎች ከማስተላለፍ ይልቅ ማጠናከር ላይ ተደምጠው መታየታቸው ዕቅዱ መክሸፉን ማሳይ ጥሩ ምልክት ነው ብለዋል ምንጮች።
የአቶ መለስን ራዕይ አስፈጽማለሁ በሚል ጠዋት ማታ የሚምሉት በስልጣን ላይ ያሉ ወገኖች ፣ የመተካካቱን ጉዳይ ከወሬና ከወረቀት በዘለለ መተግበር አለመቻላቸው ብዙዎችን የድርጅቱን አባላት ጭምር እያነጋገረ ነው። ከሁለት ዓመት በፊት በአዳማ የተካሄደው 8ኛ የኢህአዴግ ጉባዔ መተካካትን በተመለከተ ሲገልጽ፡ “በጉባኤያችን ማግስት በድርጅታችን የአመራር መተካካት ስርአትን ለመቅረፅና በተግባር ላይ ለማዋል ሰፋ ያለ
እንቅስቃሴ ተካሂዷል፡፡ ድርጅታችን አላማውን ከዳር ለማድረስ ትግሉ ከሚያልፍባቸው መድረኮች ጋር ራሱን እያጣጣመና የመምራት ብቃቱን እያዳበረ መጓዝ እንዳለበት በማመን ቀጣይ የአመራር ትውልድ የመፍጠር ስራው በስርአት እንዲመራ ጥረት ተደርጓል፡፡ በዚህ መሰረት ነባሩ የአመራር ሃይል በስራ ብዛትና በእድሜ መግፋት መስራት የማይችልበት ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት ደረጃ በደረጃ በአዳዲስ የአመራር ሃይሎች እየተተካ እንዲሄድ ማድረግ የሚያስችል አቅጣጫ ሊቀየስ ችሏል፡፡ በዚህ አቅጣጫ መሰረት ነባሩ አመራር ከፊት መስመር ለቆ በአዲሱ እንዲተካና በድርጅት አመራርነት ግን አስተዋፅኦውን እያበረከተ የሚቀጥልበት ሁኔታ እንዲፈጠር ተወስኖ ተግባራዊ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በዚህ አቅጣጫ መሰረት ነባሩ አመራር በሶስት ምዕራፎች ተከፋፍሎ በሚቀጥሉት አምስት አመታት ከፊት መስመር የሚለቅና ሚናውን እየተጫወተ የሚቀጥልበት ሁኔታ ተመቻችቷል፡፡ ” ብሎአል።

ይህ መግለጫ አያይዞም “በተመሳሳይ መልኩ የአብዮታዊ ዴሞከራሲያዊ አላማዎቻችንን ቀጣይ ተፈፃሚነት ለማረጋገጥ የአመራር መተካካት ስርአታችን መካከለኛ አመራሩንም የሚያካትት እንዲሆን ለማድረግ የሚያስችል አቅጣጫ አስቀምጠን ተንቀሳቅሰናል፡፡ከዚህ አኳያ ቀደም ሲል የተጀመረውን ሰፊ የመካከለኛ አመራር ሃይል የመፍጠርና በየስራው መድቦ በማጠናከር ሰፊ የመካከለኛ አመራር ሃይል እንዲኖረን ተደርጓል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በሁሉም እርከኖች የመተካካት ስራው አፈፃፀም በየደረጃው ያሉ የአመራር አባላት ከአንድ እርከን ወደ ቀጣዩ እርከን ወይም ወደ ትምህርት እድል የሚሸጋገሩበት አሰራር በዝርዝር ተጠንቶ እንዲፀድቅና ይህም መተካካቱ የሚፈፀምበት ተጨማሪ አቅጣጫ እንዲሆን ተወስኗል፡፡ በአጠቃላይ ከመተካካት አኳያ የተከተልነው አቅጣጫ በአንድ በኩል የአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ሃይላችንና የስርአቱን ተጠናክሮ መቀጠል የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ህዝቡ ከመተካካት አኳያ ያነሳቸው ለነበሩ ጥያቄዎች ትክክለኛ ምላሽ የሰጠ እንደሆነ በተግባር ከተገኘው ግብረ መልስ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ” ብሎአል።
በአሁኑ ወቅት አንዳንድ ነባር፣ ከፍተኛና መካከለኛ አመራር ላይ የሚገኙ ሰዎች ከትግል በሁዋላ ተምረን ብቃታችንን አሳድገን ሕዝባችንን ለማገልገል በተዘጋጀንበት ሰዓት መተካካት በሚል መገፍተራችን ተገቢ አይደለም በሚል በግልጽ ተቃውሞአቸውን እየገለጹ ነው። አመራሮቹ በሙስና ያፈሩትን ሀብትና ንብረት ስልጣን ከለቀቅን እናጣዋለን ብለው ይሰጋሉ።
የፊታችን ቅዳሜ በባህርዳር ከተማ በሚጀምረው የግንባሩ 9ኛ ጉባዔ ላይ ከመተካካት አኳያ ብዙም የሚጠበቅ አዲስ
ነገር እንደማይኖር ይታመናል፡፡
ነገር እንደማይኖር ይታመናል፡፡
ደኢህዴን ዛሬ ባካሄደው ጉባኤ እንደተጠበቀው አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን የድርጅቱ ሊቀመንበር፣ አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ደግሞ ም/ል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል። በሌሎችም ድርጅቶችም ተመሳሳይ ምርጫዎች ሲካሄዱ ውሎአል።
ESATTV.COM
No comments:
Post a Comment