FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Saturday, March 9, 2013

በዲላ ከተማ እና በወልቂጤ የሚኖሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አሰሙ


የካቲት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 
ኢሳት ዜና:-ከአንድ አመት በላይ የተካሄደው የድምጻችን ይሰማ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ፣ ዛሬ በአዲስ አበባና በሌሎች ዋና ዋና ከተሞች ረገብ ብሎ የዋለ ቢሆንም፣ በዲላ እና በወልቂጤ ተቃውሞ መደረጉን ማህበራዊ የመገናኛ ብዙሀን ገልጸዋል።
በፌስ ቡክ ላይ በፎቶግራፍ የተደገፉ መረጃዎች  መረጃዎ እንዳማለከቱት፣ ሙስሊም ኢትዮጵያውያኑ መንግስት ድምጻቸውን እንዲሰማ ጠይቀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በትናንት ሌሊት በደሴ ከተማ ከ30 ሺ በላይ በራሪ ወረቀቶች መበተናቸውን ማህበራዊ የመገናና ብዙሀን ዜናውን አሰራጭተዋል።
"መንግሰት የደሴ ሙስሊሞችን ለማዳከም የተለያዩ ሴራዎችን ሲሰራ ቆይቷል" የሚሉት የተቃውሞው አስተባባሪዎች፤ "መስጂዶቻችንን በመቀማት እና ኢማሞቻችንን በማባረር ከመስጂድ እንድንርቅ አድርጎን ቆይቷል፤ በዚህም ሳቢያ በደሴ የነበረው እንቅስቃሴ በተወሰነ መልኩ ተቀዛቀዞ የነበረ ሲሆን ዝምታው ለሊት ተሰብሯል፡፡" ብለዋል አንዳንድ ሙስሊሞች በፌስቡክ ባሰራጩት መልእክት።
ወረቀቶቹ  ፤ በቧንቧ ውሀ ፤ በሮቢት፤ በአሬራ ፤ በሸዋበር ፤ በአራዳ ፤ በሳላይሽ ፤ በሰኞ ገበያ ፤ በአሬራ ፤ በሜጠሮ ፤ በቢለን እና በሌሎች በርካታ የከተማዋ አውራ መንደሮች ነው የተበተኑት።
በወረቀቶቹ ከሰፈሩት መፈክሮች ውስጥ “ኢትዮጵያን እየበጠበጠ ያለው የእስልምና አክራሪነት ሳይሆን የፖለቲካ አክራሪነት ነው፤”ኢቲቪ የውሸት ኢንዱስትሪ ነው!በእምነታችን አንደራደርም! አሚሮቻችንን ማሰር እኛን ማሰር ነው!፤የእምነት መቻቻል እያደፈረሰ ያለው ሙስሊሙ ህብረተሰብ ሳይሆን መንግስት ነው” የሚሉት ይገኙበታል፡፡
በሌላ በኩል  ሌሊት የተበተኑትን በራሪ ወረቀቶች ተከትሎ ፖሊሶች በተለያዩ ሰፈሮች ተበታትነው ሙስሊሞችን በማሰር ላይ እንደሚገኙ አስተባባሪ ኮሚቴው ገልጿል።
በዚሁ አሰሳ ከቄራ መስጂድ አካባቢ ቤት ተከራይተው ቁርዓን ይቀሩ የነበሩ 8 ደረሶች ታፍሰው መወሰዳቸው ተገልጿል።
ዛሬ በደሴ ስልተበተነው ወረቀት መንግስት የሰጠው መግለጫ የለም።
የሙስሊሞች ጥያቄ የኢህአዴግ አባላትን እና አመራሮችን እየከፋፈላቸው መምጣቱን መዘገባችን ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment