FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Monday, March 18, 2013

"ወገኖቻችንን ጥለን አንወጣም" ሰልፈኞቹ (ከእሥር ቤት የተገኘው ጥቂት መረጃ )


(በጽዮን ግርማ)
የታሠሩት ሰልፈኞች ተራ በተራ ከተጠየቁ በኋላ የተወሰኑትን ‹‹ውጡና ሂዱ›› አሏቸው ፡፡ ‹‹ሁላችንም ካልተፈታን ብቻችንን አንወጣም›› የሚል መልስ ሰጡ ፡፡ ከውጭ ያሉ ወዳጆቻቸው ማምሻውን ምግብ እና መኝታ አቀበሏቸው፡፡ ‹‹የአባቶቻችንን መስዋትነት ለፋሽት ሐውልት በመገንባት ማራከስ አይቻልም›› በሚል ለጣሊያን መንግሥት ተቃውሟቸውን ለማሰማት የወጡ 34 ሰዎች ዛሬ እስር ቤት ያድራሉ፡፡
ቁጥራቸው ወደ 100 የሚገመት ሰልፈኞቹ ስድስት ኪሎ አካባቢ መድረስ የጀመሩት ሰዓቱ ሦስት ሳይሞላ ነበር፡፡ በቦታው የተገኙትም፤ ‹‹በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ጭፍጨፋና ግፍ ላደረሰው ፋሽስቱ ማርሻል ግራዚያኒ በጣሊያኗ አፊል ከተማ ሙዚየምና ሐውልት በስሙ መገንባቱ ለእርሱ ክብር የሚሰጥ የአባቶቻችን መስዋዕትነት ደግሞ የሚያራክስ ነው›› በሚል የኢትዮጵያ ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ማኅበር፤ ሰማያዊ ፓርቲ እና ባለራዕይ ወጣቶች ማኅበር በጋራ በመሆን ለጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ ድጋፍ ለመስጠት ነበር፡፡
ሰላማዊ ሰልፉ የሚጀመረው ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ በመኾኑ በቦታው ቀድመው የተገኙት አስተባባሪዎች፤ ከፊት ለፊቱ ስድስት ኪሎ የሚገኘውን የሰማዕታት ሐውልት ምስል ከኋላው ደግሞ ‹‹የአባቶቻችንን መስዋትነት ለፋሽት ሐውልት በመገንባት ማራከስ አይቻልም›› የሚል መልዕክት የያዘ ቲሸርት ለመልበስ በመዘጋጀት ላይ እያሉ ፌደራል ፖሊሶች በአንድ መኪና መጥተው፤‹‹ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የተሰጣችሁ ፍቃድ የታለ?›› ብለው ይጠይቃሉ፡፡ አስተባባሪዎቹም ፤ሕጉ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ማሳወቅ እንጅ ማስፈቀድ እንደማይል በዚህም መሰረት በተገቢው መንገድ ማሳወቃቸውን ክልከላ ቢኖር ኖሮ በደብዳቤ ሊገለጽላቸው እንደሚገባ ጠቅሰው ነገር ግን እስከዛች ሰዓት ድረስ ምንም የደረሳቸው ነገር ስለሌ ሊከለከሉ እንደማይገባ በመንገር ምላሽ ይሰጣሉ፡፡
ፌደራል ፖሊሶቹም ለደቂቃዎች የስልክ እና የሬዲዮ ልውውጥ ካደረጉ በኋላ ‹‹በሉ ተበተኑ ፍቃድ የላችሁም›› ይላሉ ሰልፈኞቹ ሁኔታውን ደግመው ለማስረዳት ይሞክራሉ በምላሹ ያልተበገሩት ፖሊሶች ሬዲዮ አድርገው ተጨማሪ ኃይል እንዲመጣላቸው ይጠይቃሉ፡፡
መጀመሪያ ላይ ከዳር ቆመው የነበሩት ዶ/ር ያዕቆብ ቀረብ ብለው ሁኔታውን ለማስረዳት ሲሞክሩ ‹‹እርሶን እንፈልጎታለን›› በሚል ወደ መኪናው እንዲገቡ ያዟቸዋል፡፡ ቀስ እያለም ሁኔታዎች ይቀየራሉ ዶ/ር ያቆብ ኃይለማሪያም፣ የሰማያዊው ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት፣ አቶ ታዲዮስ ታንቱ እና ጥቂቶቹ እየተገፈተሩ ወደ መኪና እንዲገቡ ይደረጋሉ፡፡ ቀሪዎቹ አስተባባሪዎች ነገሩን አብርደው ወጣቶቹ መሳሪያ ከጨበጠ ሰው ጋር ትግል እንዳይገጥሙ በሰላማዊ መንገድ እንዲበተኑ አድርገው መኪና የያዙት የተወሰዱትን ሁኔታ ለመከታተል እና ሁኔታውን ለማሳወቅ መግለጫ ለመስጠት ተነጋርረው ከቦታው ይሄዳሉ፡፡ ሰልፈኞቹም ከስድስት ኪሎ በእግራቸው የአራት ኪሎን መንገድ ይዘው መሄድ ይጀምራሉ፡፡ አምስት ኪሎ አካባቢ ሲደርሱ በድንገት ፌደራል ፖሊስ መጥቶ ይከባቸዋል ‹‹የለበሳችሁትን ቲሸርት አውልቁ›› በሚል በተፈጠረ ግብግብ በዱላ እየተደበደቡ ቀደም ሲል ከታሰሩት ጋር የእስረኞቹ ቁጥር 34 ይኾናል፡፡

No comments:

Post a Comment