FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Monday, December 31, 2012

ከዚህም ከዚያም


ፍቅር ቁመት አይወስነውም
የዓለማችን ረጅም ወጣት የከንፈር ወዳጅ የሆነው የ22ዓመቱ ብራዚላዊ ከፍቅረኛው ጋር ያለው ግንኙነት እጅግ አስደሳች እንደሆነ ገለጸ፡፡ ዕድሜዋ 17ዓመትና ቁመትዋ 6ጫማ ከ8ኢንች (2.1ሜትር) የምትረዝመው ኤሊሳኒ ሲልቫ ዕድገቷን የሚቆጣጠረው ዕጢ ላይ ባጋጠማት ችግር ምክንያት እንደዚህ ቁመቷ ሊረዝም እንደቻለና በሽታዋ ከታወቀ በኋላ ሐኪሞች ዕብጠቱን እንዳስወገዱት ተገልጾዋል፡፡
ወደፊት ሞዴሊስት ለመሆን የምታስበው የከንፈው ወዳጅዋ መልካም ስብዕና ያለውና ለእርሷም ድንቅ አመለካከት እንዳለው ገልጻለች፡፡ ሆኖም ችግሯን ከመግለጽ አልተቆጠበችም፤ “ያለኝ ዋና ችግር እጅ ለእጅ ተያይዘን ስንሄድ ትንሹን ወንድሜን ወይም ልጄን ይዤ የምሄድ ይመስለኛል” ብላለች፡፡
የዓመቱ ሰው
ቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ታህሳስ 4፤ 1928ዓም (ጃኑዋሪ 6፤1936 አውሮጳውያኑ ቆጣጠር) ዕትሙ የዓመቱ ሰው በማለት የሰየማቸውና በየዓመቱ ይህንኑ ሲያደርግ የቆየው ታይም መጽሔት ባራክ ኦባማን የ2012 የዓመቱ ሰው በማለት ሰይሟቸዋል፡፡ ለስያሜው ምክንያት አድርጎ የጠቀሰውም ባራክ ኦባማ የአሜሪካንን ኅብረት ወደ ተሻለ ደረጃ በማድረስና በዚህ አስቸጋሪ ዘመን ደካማነትን ወደ ዕድል (ብርታት) በመቀየር ቀዳሚውን ቦታ በመያዛቸው የዓመቱ ሰው ለመባል መቻላቸውን ይጠቅሳል፡፡
በተቃራኒው የፕሬዚዳንቱን መመረጥ የሚቃወሙ ድርጊቱን አጥብቀው የኮነኑ ሲሆን ባራክ ኦባማ ለዚህ የዓመቱ ሰው ክብር መብቃት የቻሉት “ደደቦች ስለሚወዷቸው እና የመረጃ እጦት ያላቸው ስለሚደግፏቸው” መሆኑን በመጥቀስ ምርጫውን ያጥላሉም አሉ፡፡
የግብረሰዶማውያን መጽሐፍ ቅዱስ
ራሱን “የግብረሰዶማውያን መጽሐፍቅዱስ” በማለት የሚጠራ መጽሐፍ መታተሙን ሰሞኑን ተሰምቷል፡፡ ከቀደምት መጽሃፍቅዱስ ትርጉሞች መካከል በዋንኛነት የሚጠቀሰው የንጉሥ ጀምስ ዕትምን በመተካት የንግሥት ጀምስ ዕትም በማለት የወጣው ይኸው መጽሐፍ በመጽሐፍቅዱስ ላይ ስለ ግብረሰዶማውያን የተጠቀሰውን የፍርሃቻና የተዛባ አጻጻፍ በተከላከለ መልኩ የተጻፈ መሆኑን ያስረዳል፡፡
ደራሲው፡ እግዚአብሔር ተባባሪው ደግሞ ክርስቶስ በማለት በውስጥ ገጹ ላይ ያሰፈረውን ይህንን መጽሐፍ ማን እንዳዘጋጀው የተሰጠ ምንም ዓይነት መረጃ የለም፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሽያጭ ላይ የሚገኝ ሲሆን በርካታ አስተያየት ሰጪዎችም የተለያዩ የሃይማኖት መጽሐፎች በተለይም ቁርዓን እንደዚህ ባለ መልኩ ለግብረሰዶማውያን እንዲታተም ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
“ስታሊንን እወደዋለሁ” 
ሰሞኑን የቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት መሪ የነበሩት ጆሴፍ ስታሊን 133ኛ የልደት በዓል በተከበረ ጊዜ በጆርጂያና በሩሲያ የሚገኙ ደጋፊዎቻቸው በዓሉን በሃዘን – መሪያቸውን በማጣታቸው – በኩራት – እንደ ስታሊን ዓይነት ወደዚህ ምድር በመወለዱ – አክብረውታል፡፡
“ስታሊንን እወደዋለሁ” የሚሉት በበዓሉ ላይ የተገኙት ደጋፊ ሲናገሩ “የ12 ዓመት ልጅ ሆኜ ሳለሁ አያቴ ስታሊን ሞቶ እንዴት አምርራ ስታለቅስ እንደነበረ አስታውሳለሁ” ብለዋል፡፡ በሩሲያ በተከበረው በዓል ላይ በኮሙኒስት ፓርቲው መሪ ጌናዲ ዡጋኖቭ የሚመሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎች የስታሊን መቃብር በሚገኝበት ቀዩ አደባባይ አበባ አኑረዋል፡፡ የስታሊን ተቃዋሚ የሆኑ በተለይም በዩክሬይን የሚኖሩም በዓሉን ተቃውሞ በማሰማት አሳልፈዋል፡፡
“በወንድሙ ጦስ ተገደለ”
የአሳድን አገዛዝ ለመጣል እየተዋጉ ያሉትና የምዕራባውያን ቀጥተኛ ድጋፍ ያላቸው የሶሪያ አማጺያን ሰሞኑን የፈጸሙት ግድያ በአሰቃቂነቱ ተጠቃሽ ሆኗል፡፡ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆነውን ግለሰብ ታፍኖ ከተወሰደ በኋላ አማጺያኑ አንገቱን ቆርጠው የቀረውን አካሉን ለውሾች መስጠታቸውን ታውቋል፡፡
በታክሲ ሥራ የሚተዳደረው የ38 ዓመቱ ግለሰብ ወንድም አማጺያኑን በመንቀፍ የውንብድና ሥራ እየሰሩ መሆናቸውን ከተናገረ በኋላ በወንድሙ ጦስ ታፍኖ መወሰዱን ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁት መነኩሴይት ተናግረዋል፡፡ የቅዱስ ያዕቆብ ገዳም መነኩሴ የሆኑት እናት በድርጊቱ እስላማዊ አክራሪዎችን የኮነኑ ሲሆን ምዕራባውያን እንዲህ ያለው አሰቃቂ ድርጊት በአገራቸው እንዲፈጸም ለአማጺያኑ መሣሪያ በማቀበል መደገፋቸውን አጥብቀው ኮንነዋል፡፡ በቶሎ ካልተቋጨ ወደፊት ወደ ሃይማኖታዊ ጦርነት ሊሸጋገር እንደሚችል የከረረ ሃሳብ እየተሰጠበት ያለውና ሁለት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት የቀሩት የሶሪያ ጦርነት እስካሁን ከ44ሺህ በላይ ዜጎችን ህይወት ቀጥፏል፡፡
ጥይት መከላከያ ለልጆች
በቅርቡ በአሜሪካ በት/ቤት ተኩስ ተከፍቶ 20ሕጻናት ተማሪዎች ከተገደሉ በኋላ በኮሎምቢያ የሚገኝ የጥይት መከላከያ ጃኬት አምራች ድርጅት ለልጆች የሚሆን ልብስ ማዘጋጀቱን ገለጸ፡፡
ከማንኛውም ዓይነት የሽጉጥና አውቶማቲክ ጠብመንጃ ጥይት የሚከላከለውና ቀለል ያለ ክብደት ያለው ጃኬት የልጆችን ቀልብ እንዲስብ በተለያዩ ቀለማት እንደሚሠራ ኩባንያው አስታውቋል፡፡ ዋጋው 500ዶላር ከሆነው ከዚህ ጃኬት በተጨማሪ ኩባንያው ጥይት የሚከላከል የልጆች ደብተር መያዣ ቦርሳም እንዳዘጋጀ ገልጾዋል፡፡
ኤሌክትሮኒክ ሲጋራ አያዋጣም
የሲጋራ ሱስን ለመተው ይረዳል እየተባለ በስፋት የሚሸጠው የኤሌክትሮኒክ ሲጋራ ማጨስ ለማቆም እንደማይረዳ ተሰማ፡፡ የጣሊያን ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው በዚሁ መግለጫ መሠረት ኒኮቲን ያለው በመሆኑ ጉዳቱ እንደመደበኛው ሲጋራ ሲሆን አጫሾችን ሲጋራ ለማቆም የሚያደርገው አስተዋጽዖ እንደሌለ አስታውቋል፡፡
በሲጋራ ማጨስ ማቆምን አስመልክቶ ምክር የሚሰጡ እንደሚሉት ኒኮቲንን ከሰውነት በማስወገድ በአጠቃላይ ሲጋራ ማጨስ ማቆም አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንደሆን ይናገራሉ፡፡ ሰዎች ይህንን ውሳኔ ሲያደርጉ የተለያዩ ስሜቶች የሚፈራረቁባቸው ቢሆንም አስቸጋሪ የሆኑት ስሜቶች ከ24 እስከ 72ሰዓታት ባሉት ጊዜያት ውስጥ እንደሚጠፉ እንዲሁም በአካል ላይ የሚከሰቱት ችግሮች ደግሞ ከአራት ሳምንታት ባልበለጠ ጊዜ ፈጽሞ እንደሚወገዱ ሳይንሳዊ መረጃዎችን በመጥቀስ አስተያየት ይሰጣሉ፡፡
የሳምንቱምርጥፎቶ
ምስሉን ያገኘነው ከፌስቡክ ነው፡፡ “ልማቱ እንዴት ነው?” ብሎ ለሚጠይቅ ብዙ ከማለት ይህንን “ልማታዊ ፎቶ” “ከሶማሊያውያን የሚበልጡ ኢትዮጵያዊያን ተሰደዋል” በሚል ርዕስ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን ያወጣውን ዘገባ አጣቅሰን ከጻፍነው “ደጋፊ ዜና” ጋር ማቅረብ ጥሩ መልስ ሊሆን ይችላል፡፡
ዘገባውን ለማጠናቀር በየጽሁፉ ከጠቀስናቸው ምንጮች በተጨማሪ ሌሎችንም የሚዲያ ውጤቶች መጠቀማችንን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ ከዜናዎቹ ማነስ አኳያ በየጸሁፉለመግለጽ ባለመቻላችን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ የማን ነው? የእኛ ነው ወይስ?


(ከመልዕክተ ተዋሕዶ – ዘሮኪ)፦ እንግዲህ ላለፉት 20 ዓመታት ከችግራችን ጋር ተወልዶ፥ ያደገው መንግሥት ፥ አቋሙን በግልጽ አሳውቆናል።  “ነገ ልትዳሪ ነው ሲሏት፥ ካልታዘልኩ አላምንም” እንዳለችው ሙሽራ መሆኑ ይብቃን፥ እርማችንን እናውጣ። ስለ ነገ እናስብ፥ ስለ ቤተ ክርስቲያን እናስብ፥ ስለ አባቶቻችን እናስብ። የግዴታ ማክሰኞን መጠበቅ ያለብን አይመስለኝም። ቅዱስ ሲኖዶስ በመጪው ማክሰኞ  በሚያደርገው ስብሰባ ላይ፥ ካስታወሰን መልዕክታችንን መነጋገር ያለብን፥ ዛሬንና ነገ ብቻ ነው። የመንግሥትን አቋም ባይገርመንም የሚጠበቅ ስለሆነ ሰምተነዋል። የቅዱስ ሲኖዶስ ግን ማክሰኞ ይለይለታል። ቅዱስ ሲኖዶስ የማነው ወይ የኛ የኦርቶዶክስያዊያኑ ነው! አለበለዚያ፥ ተጠሪነቱ በቀጥታ ለመንግሥት ነው። እንደኔ እንደኔ  የቅዱስ ሲኖዶስም ቢሆን፥ ግልጽ ይመስለኛል።  ይህንን ለመረዳት፥ ወደ ፊት ሁለት ቀን ጠብቆ ማየት ሳይሆን፥ ወደ ኋላ ብዙ ዓመታትን ማስታወስ ይበቃል። ያለፉትን ሁለት ሶስት ሳምንታት ብቻ እንኳን ስርመረምሩ፥ እውነታው ቅዱስ ሲኖዶስ ከመንግሥት ፍላጎት ውጪ አንድ ቀን እንኳን በነጻ አስተሳሰቡ ውሎ ማደር እንዳልቻለ ግልጽ ነው። ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ የቅዱስ ሲኖዶስ አካሄድን ነቅፈው፥ መሆን ያለበትን ተናግረው ውለው ሳያድሩ የደኅንነት ክፍሉ ኃላፊ “ንቡረ ዕድ” ኤልያስ አብርሃ ዝም ነው አሰኟቸው። በግዴታም ፈረሙ። ነገ ወደ አገር መግቢያ የላችሁም ተባሉ። ተስማሙም። ይህ በቂ አይመስላችሁምን? ጠብቀን እንስማው፥ ካላችሁ ግን ፥ ታገሱ።
 የተዋሕዶ ልጆች፥ ዛሬ ቅዱስ አትናቴዎስ፥ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ፥ ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ፥ በአካል የሉም። ማን እነሱን ይሁን? ቡዙ የምንወዳቸው፥ የምናደንቃቸው ብጹአን ሊቃነ አልነበሩምን እንዴ? የት ሄዱ? ቢያንስ ካሉን ሊቃነ ጳጳሳት አንዳቸውስ !! እንኳን፥ ስለፍቅርና የቤተ ክርስቲያን አንድነት፥ በአደባባይ መናገር ይፍሩ? የተዋሕዶ ልጆች፥ ስለ አንቀጽ 39፣ ወይም ስለ ኢትዮጵያ አንድነት፥ ስለ ኑሮ ውድነትና ስራ አጥነት፣ወይም ዘረኝነት እኮ አይደለም ጥያቄው! ያንን ያነሳ እማ መድረሻም የለውም። ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት መናገር ብቻ!! በግልጽ ቤተ ክርስቲያን አንድ ትሁን ማለት፤ ከፓትርያርክ ምርጫ በፊት ዕርቀ ሰላም ይውረድ ማለት፤ የፈረሰው ይስተካከል፥ የጠመመው ይቅና፥ ብሎ መናገር፥ መመስከር አስፈርቷቸዋል። በእናንተ ፍርሀት የተነሳ፥ ነገ መሥዋዕትነት ሊከፍሉ የተዘጋጁ፥ የተዋሕዶ ልጆች ያሣፍሯችኋል። ዛሬ እናንተ ለቤተክርስቲያናችሁ ብትቆሙ፥ ነገ ከእናንተ ጋር ቆመን ዋጋ ብንከፍል ያምርብን ነበር። ግና፥ ይህ የሚሆን አይመስለኝም።
 ከዚህ በኋላ መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያለን ሁሉ፥በየሰበካችን ነገ በዚህ ጉዳይ ላይ መወያየት ይጠበቅብናል። ምን ብናደርግ ይሻላል? የሚሰሙ ብፁዓን አባቶች አሉ ብሎ የሚያምን በስልክም፣ በኢሜልም እንዲሁም በአካል ተገኝቶ ያስረዳ። ሌላው፥ መላው ሰባክያነ ወንጌል፣ መምህራን ነገ ይህንን ጉዳይ አንስታችሁ ምን ማድረግ እንደሚሻል፥ ተወያዩ። መምህራኑ ዝም ካሉ ደግሞ፥ ምእመናን ጠይቁ፥ መብታችሁ ነው። በየኤምባሲውና የመንግሥትና የቤተ ክርስቲያን ተወካዮች ባሉበት፥ አቤቱታችሁን አሰሙ። ሰላማዊ ሰልፎች ከቤተ ክህነቱ ቢሮ ጀምሮ እስከ ሊቃነ ጳጳሳቱ መኖሪያ ድረስ፥ ይደረጉ። ማኅበረ ቅዱሳንም ሆነ ሌሎች መንፈሳውያን ማኅበራት ከቤተ ክህነቱ ጋር ያላችሁ ግንኙነት እንዳይበላሽ በመሥጋት መደረግ የሚገባውን ሳትዘገዩ ዛሬ አድርጉት! ያለበለዚያ የእናንተም አስፈላጊነት አጠያያቂ ይሆናል። ትምህርተ ወንጌልን ማዳረስ፣ ገዳማትን ማጠናከር፣ አረጋውያንን መርዳት፣ መምህራንን በሚያስፈልጋቸው መርዳት የሚቻለው ቤተ ክርስቲያን ሕልውናዋ ተጠብቆ፥ አንድነቷ ተከብሮ ሲገኝ ብቻ ነው። አድር ባይነት በታሪክ ያስወቅሳል። ያስፈርድማል።
 ለምርጫ ራሳችሁን ያዘጋጃችሁት አባቶቻችን ልብ ግዙ። እነ ብፁዕ አቡነ ማትያስ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ እነ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ወዘተ የቤተ ክርስቲያንን ችግር ከውስጥም ከውጭም ሆናችሁ አይታችሁታል። ይህ ኃላፊ ወቅት አያታላችሁ። ነገ ይቆይ እንጂ፥ በኦርቶዶክሳውያን መሥዋዕትነት፣ይነጋል።
 በዚህ አጋጣሚ፥ ሊቀ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዓለማየሁ፣ መልአከ መንክራት ቀሲስ አንዱዓለም፣ ዲያቆን አንዱዓለም፣ ቀሲስ ፋሲል ወዘተ ከገለልተኛው ወገንና በውጭው ዓለም የሚገኙትን አባቶች፥ የወከሉትን በአጠቃላይ፥ በመላው የሰላምና አንድነት ኮሜቴ ስም፥ ላደረጉት ታሪክ የማይረሳው፥ ቤተ ክርስቲያን የማትረሳው ትልቅ አርአያነት ያለው ሥራ እግዚአብሔር አምላክ በሰማያት ዋጋችሁን ይክፈላችሁ እላለሁ።
 ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የተመሠቃቀለውን የፖለቲካ ውጥንቅጣችንና ነፃነታችን።


አንዱ ዓለም ተፈራ
በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የወያኔን ቡድን ከሥልጣን ለማውረድ የሚደረገው ትግል አሁንም ቀጥሏል። ይህ ትግል አንድነት የለውም። ይህ ትግል አንድ ማዕከል የለውም። ይህ ትግል አንድ መሪ የለውም። ያለንበትን መርምረን ወደፊት እንዴት እንደምንሄድ መወያየት አለብን። ለዚህ ይረዳ ዘንድ፤ በኔ በኩል መደረግ አለባቸው የምላቸውን እጠቁማለሁ። ይቺ ሀገር ያንቺም፣ ያንተም፣ የነሱም፣ የኛም የሁላችን የኢትዮጵያዊያን ሀገር ናት። ስለሆነም ሁላችንም ለወደፊቷ እኩል ባለጉዳዮች ነን። ማንም የነገዋን ሀገራችን እድል ሲወስን፤ እኛ የበይ ተመልካች መሆን አይገባንም። “ከወያኔ የተሻለ እስከመጣ ድረስ እኔ ምን ቸገረኝ!” ብለን ለሌሎች ጉዳዩን የምንተወው ሊሆንም አይገባም። አዎ የሚሻል ይኖራል። ያባሰም አለ። የሚሻለውም ሆነ የባሰው ሲመጣ የራሱን አጀንዳ ይዞ ስለሆነ የሚመጣው፤ እኛም ሆነ የሀገራችን ጉዳይ በሌሎች አጀንዳ ይያዛል ብለን ማለም የዋህነት ነው። ማንኛውም ድርጅት የራሱን አጀንዳ አራማጅ መሆኑ፤ የፖለቲካ ድርጅት የሕልውና መሠረታዊ ሀ ሁ ነው። ታጋዮች ሆነው ጦራቸውን የማይቀስሩትም ቢሆኑ፤ ሀገራቸውን ነፃ ሊያወጣ የተነሣ ድርጅትን መመርመርና ማወቅ ግዴታ አለባቸው።
ወያኔን የሚቃወሙ በየመልኩና በየቦታው መኖራቸው ግልፅ ነው። እነኚህ ድርጅቶች በሙሉ፤ እያንዳንዳቸው የተነሱበትና አንዱ ከሌላው የሚለይበት፤ የየራሳቸው አጀንዳ አሉዋቸው። አንድ ሀገራዊ አጀንዳ ቢኖራቸውና ሁሉም እኩል ለሀገራቸው የተነሱ ቢሆኑ ኖሮ፤ በተለያየ ወቅትና በተለያይ ቦታ ቢፈጠሩም፤ በመሰባሰብ አንድ ድርጅት ብቻ በመሠረቱ ነበር። ስለዚህ የተለያየ አጀንዳ እንዳላቸው መቀበሉ ግዴታ ነው። የተለያየ አጀንዳ ስላላቸው ደግሞ፤ የተለያየ ውጤትን ፈላጊ መሆናቸው የተጠበቀ ነው። ልዩነታቸው በጥቃቅን ጉዳዮች ከሆነ፤ በተወሰነ ደረጃ እነኚህን ልዩነቶች አጣጥመው፤ መሠረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመስማማት፤ አንድ ግንባር ፈጥረው፤ ትግሉን በኅብረት ያካሂዱ ነበር። ይህ እስካሁን አልተደረገም። ለወደፊቱ አይደረግም የሚል ተስፋ አስቆራጭ እምነት የለኝም። ለወደፊቱ ያለኝ ምኞት ከፍ ያለ ነው። በአሁኑ ጊዜ የጠራ ብርሃን አይታየኝም። ሆኖም እኔ ይኼን አቋም ብይዝም፤ ሌሎች ይኼን ይቀበላሉ ማለት አልችልም።
ባሁኑ ሰዓት ትግሉ ወደፊት እንዳይገፋ የሚፈታተኑት ጥቂት ጉዳዮች አሉ። እኒህ መሠረታዊ የእምነትና የአመለካካት ጉዳዮች ናቸው። እኒህ የእምነትና የአመለካከት ጉዳዮች ደግሞ፤ ለመቀራረብና ጉልበት ያለው ኃይል ለማሰባሰብ አስቸጋሪ እንቅፋት ሆነውብናል። ታዲያ ብዙዎች ያልተሰባሰቡበትና የጠራ የአመለካከት አንድነት ያልተፈጠረበት ትግል፤ አድሮ መበታተንን ያስከትላል። ይኼን ደግሞ ላለፉት አርባና ሃምሳ ዓመታት ታሪካችን አስታቅፈን፤ ባዲስ ምዕራፍ ወደፊት መሄድ አለብን።
ባሁን ሰዓት የወያኔ ቡድን በሚያካሂደው ወያኔያዊ ግዛታዊ አስተዳደር፤ ሀገራችን ብዙ ችግሮች ገጥመዋታል። በወያኔ እስር ቤቶች የታጎሩት ኢትዮጵያዊያን፣ የተዛባዉ አስተዳደራዊ ልማት፣ የሠራዊቱ አወቃቀርና የሥልጣን አመዳደብ፣ የብሔር ብሔሮች ጥያቄ፣ የነፃ አውጭዎች ጋጋታ፣ የውጭ መሬት ተቀራማጮች እውነታ፣ የደንበሩ መሠጠት፣ የኤርትራ ጉዳይ፣ የወያኔ ሥልጣናትና ከሕዝብ የዘረፉት ንብረት፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ የተባረሩት አማራዎችና የተገደሉባቸው ዘመዶቻቸው፣ በዓለም የተበተነው ስደተኛ ኢትዮጵያዊና ሀገራዊ ጥማቱ፣ ወያኔ በመሸጥ ላይ ያለው የሕፃናት ዓለም አቀፋዊ ብተና፣ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚሰቃዩት እህቶቻችን፣ ወዘተ. . . ለእነዚህ ጥያቄዎች የምንሠጣቸው መልሶች፤ ያስተባብሩናል ወይንም ያለያዩናል። ከዚህ ተነስተን ደግሞ፤ ጠንካራ ድርጅት ሊመሠረት የሚቻልበትን መንገድ በኅብረት እናበጃለን።
አንድ ነገር ግልፅ ነው። የወያኔው ቡድን በምንም መንገድ ሥልጣን ለቆና በሕዝብ ድምፅ ተገዝቶ ሀገራችንን በሰላም ወደ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ይመራታል ብሎ የሚያልም፤ ከንቅልፉ ያልነቃ ነውና መቀስቀስ አለበት። ይህን በአሁን ሰዓት ያልተገነዘበ ኢትዮጵያዊ አለ ብሎ መቀበል ያስቸግረኛል። ከወያኔ የራቁ መስለው የሚንቀሳቀሱ የግል ጥቅማቸው ከሀገራቸው ሕልውና የበለጠባቸው አስመሳዮች በርግጥ ሊቀላምዱ ይችላሉ። ከዚህ በተረፈ ግን፤ ሁላችንም ወያኔ ካልተገፋ አይወድቅም በሚለው ብንስማማም፤ እንዴት በሚለው ላይ ውይይት አላደረግንበትም። ታዲያ አንድ ወገን ኃላፊነቱን ጨብጦ፤ እርምጃ ለመውሰድ ቢነሣ፤ ይህ ጉዳይ የሁላችንንም ነገ ወሳኝ ስለሆነ ያገባኛል ማለት አለብን። አንድ ሠራዊት ተመሠረተ ሲባል፤ ማን መሠረተው? አጀንዳው ምንድን ነው? እቅዱ ምንድን ነው? ብለን መጠየቅ ግዴታችን ነው። እንዲያው ቀድሟልና እንከተለው ወይንም እንደግፈው ማለቱ የዋህነት ነው። ወያኔን እናውድም የሚለው ባዶ ቃል ብቻ የትም አያስኬድም። የሃምሳ ዓመታት የትግል ትምህርታችንን ገደል አንክተተው። ሕዝብን ነፃ አውጥቶ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የሚመሠርት ሠራዊት፤ ከሀገራዊ ውይይቱ የመነጨ ይሆናል። ሕዝብን ነፃ አውጥቶ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የሚመሠርት ሠራዊት፤ በሕዝባዊና ሀገራዊ ሁሉን አቀፍ ድርጅት ይመራል። በግትርነትና በምኞት ሀገር አቀፍ ትግል አይካሄድም።
ይኼን ትግል አንዳንዶች የትግሬዎችና የቀሪዎቹ ኢትዮጵያዊያን ጠብ አድርገው ያዩታል። ሌሎች ደግሞ የነፃ አውጪዎችና የሀገር ወዳዶች አድርገው ያዩታል። ቀሪዎች ደግሞ ከውጭ ሀገር ባነበቡትና ባገኙት ተመክሮዎች አጣብቀው ትርጉም ሊሠጡት ይፈልጋሉ። የተወሰነው ክፍል ደግሞ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባርና የኢትዮጵያዊያን የጨቋኝና ተጨቋኝ አድርገው ያቀርቡታል። ከሀገራችን የምጣኔ ሀብት ሥምሪትም አንፃር የሚመለከቱትና፤ የሀገራችን ሀብት በአንድ ቡድን ተጠፍርቆ መያዙና ለመመዝበሪያ መንገዱ የሆነውንም ሥልጣን ጨምድደው መያዛቸው ያስቆጣቸው አሉ። ወያኔ የሠጣቸውን ተቀብለው ሌላም ይገባናል፤ አንሦናል ባዮችም አሉ። ጥያቄው፤ የጠመንጃ አንሽዎቹ መሠረት የት ላይ ነው የወደቀው? ነው።
እጃችንን አጣጥፈን እንቀመጥ የሚሉ ካሉ የተሣሣቱ ናቸው። ለመፍትሔው፤ ሕዝብ፣ ሕዝብ ስልም፤ ሕዝቡ እንደሚነሳ፤ እምነት ስላለኝ ነው። አንዳንዶቻችን ታዲያ ሕዝቡ ለምን አይነሳም? የምንል አለን። እስኪ ረጋ ብለን ራሳችንን እንጠይቅ! ማነው ከመካከላችን በሕዝቡ መካከል ገብቶ፣ ችግራቸውን አብሮ ተካፍሎ፣ ከሕዝቡ ጋር ሆኖ መፍትሔ ምንድን ነው? የሚለውን ከሕዝቡ ተምሮ፤ ቅመሙን ይዞልን የመጣ? ይኼ አዎ! ድካምን ይጠይቃል። ታዲያ የሕዝብ ትግል ማለት፤ አድካሚ፣ ትዕግሥትን አስጨራሽና ሕዝቡ ማዕከል የሆነበት ማለት አይደለም እንዴ? ወይንስ ነፃ አጭዎቹ ከውጭ እስክንመጣለት ሕዝቡ እየጠበቀን ነው የሚለውን፤ እኛ አቡክተን እኛው ጋግረን ያስቀመጥነውን እንጀራ እየበላን ነው?
“የጦር ቡድን ተመስርቶ አንድ ከተማ ቢይዝ፤ ወታደሩ ተገልብጦ ወደኛ ይመጣል” የሚል ዜማ ይሰማል። ከተኛንበት እንንቃ። ትግሉን እንደጋቢ ከላይ ላይ ደርበን እንሂድ ቢባል፤ ሲሞቅና ሲበርድ የሚለበስና የሚጣል የውጭ አካል ይሆናል። ትግሉ የሚሳካው፤ ትግሉን ሕይወት ብለው ሲይዙትና ከሰውነት አዋኅደው፤ ትግሉን ሲሆኑት ነው። በአንድ ነፃ አውጪ ድርጅት ጠመንጃ ነፃነት የሚመጣበትን መንገድ ሳስበው፤ ሰውነቴ ይጨማደዳል። በዚህ የነፃ አውጪ ድርጅት መሪዎች አዳራሽ ነው የምንንፈላሠሠው ወይንስ ይህ የነፃ አውጪ ድርጅት ነፃ እንዲወጣ “በሚታገልለት” ሕዝብ እውነታ? የሚለው ከፊቴ ይደቀናል።
በዚህ ጽሑፍ ጥቂት የውይይት ነጥቦችን አንስቻለሁ።
ሀ)   መነሻዬ፤ መታገያ መርኀችን ምንድን ነው? እንወያይበት።
ለዚህ ጥያቄ የምንሠጠው መልስ ወሳኝ ነው። ይህ ትግል የእኔ፣ ያንተ ወይንም ያንቺ የግል ትግል አይደለም። ይህ ትግል የኢትዮጵያዊያን በአንድነት ትግል ነው። ኢትዮጵያዊያን ደግሞ ከወያኔ ጋር በሀገራቸው በትንንቅንቅ ላይ ነው ያሉት። እኛም ሀገራዊ ውይይቶች አድርገን፤ ከሞላ ጎደል ሁላችንን የሚያስማማ መታገያ አንድ መርኅ ላይ እንድረስ እላለሁ። ይህ አሁን የለንም። ድቅድቁን የሀገራችን የፖለቲካ ጨለማ እኔ ብቻ ነኝ ትክክለኛ፣ ለሀገሪቱ እኔ አውቃለሁ ወይንም የምላችሁን ስሙ የማዛችሁን ሥሩ የሚለው ቅኝት፤ ቢያንስ በኛ ደረጃ አልፎበታል። ተማክረን እናደርገው። ሀገራዊ ውይይት ይቅደም። ሀገርን ሰብስቦ ውይይት ይደረግ የሚል ብዥታ የለኝም። ከሞላ ጎደል ግን፤ በዬተገኘው መድረክ፤ ግልፅ መውጣት ያለባቸውን ሀገራዊ ጉዳዮች ማኘክና ማላመጥ አለብን። መልሱ በሁላችንም ዘንድ አንድ ይሁንና እንነሳ።
ለ)   ቀጥሎ፤ የኢትዮጵያዊያንን ትግል ማን ይምራው? እንወቅ።
በመሪነትና በታጋይነት ማዕከለኛውን ቦታ መያዝ ያለበት፤ ሕዝቡ ነው። የማያዳግም ሀገራዊ ነፃነት የሚያመጣና ሕዝቡን የሚያስነሣ ድርጅት ሕዝባዊ ነው። አንድ ወገንተኛ ሳይሆን አብዛኛውን ያቀፈ ነው። አብዛኛውን ያቀፍ ድርጅት ደግሞ፤ ማዕከላዊ ለሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች፤ አብዛኞችን ያካተተ መልስ በግልፅ ያስቀምጣል። ሀገር ቤት ያለውን እውነታ ያላካተተ፣ ሀገር ቤት ያለውን ታጋይ ያላስቀደመና በዚያ ያልተመራ ድርጅት፤ ጉልቻን ከመቀያየር የተለዬ የሚያመጣው ፋይዳ የለም። እኔ፤ ሀገር ቤት ውስጥ፤ ከወያኔ ጋር እየተጋፈጠ ያለው ወጣት፤ በሀገሪቱ ውስጥ ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ተመሥርቶ፤ የአሁን ትግሉን የሚመራ ድርጅት ውስጥ ውስጡን ይፈጥራል የሚል እምነት አለኝ። አሁን አለ የሚል እምነት የለኝም።
ሐ) ሌላው፤ የትጥቅ ትግሉን የተመለከተ ጉዳይ ነው። እንመርምረው።
ከገጠር ወደ ከተማ ወይንስ በከተማ ውስጥ የሚለው ጥያቄ መልስ አልተሠጠውም። ዓለም አቀፉ የፖለቲካ ሀቅና የሀገራችን የፖለቲካ እውነታ፤ የተወሰኑ የታጠቁ ታጋዮች ከገጠር ተነስተው እንደወያኔ እየበረሩ አዲስ አበባ የሚገቡበት ክፍት ክስተት የትናንት ሆኗል። በኔ ግምት፤ ትግሉ ሕዝቡ ባለበትና በከተማ ውስጥ ነው። ትክክለኛ ድርጅት ከተመሠረተ፤ ባጭር ጊዜ ውስጥ የወያኔ ቡድን ይቀበራል። ሕዝቡን በያለበት የሚያስነሣ ድርጅት አጭር ትግል ነው የሚኖረው። ይህ የታጠቀ ቡድን አስፈላጊነትን ያጎላዋል እንጂ አላስፈላጊ አያደርገውም። የዚህን የታጠቀ ቡድን መልክ፣ ይዘት፣ አወቃቀር፤ አካሂያድና ሚና መሪ ድርጅቱ በቦታው፣ በሰዓቱና በሂደቱ ይወስነዋል።
ከዝግጅት ክፍሉ፡- አቶ አንዱ ዓለም ተፈራ እንደዜጋ ያላቸውን ሃሳብ በጽሁፍ እንደገለጹ ሁሉ ያገባኛል የምንል ወገኖች ደግሞ በተመሳሳይ መልኩ ሃሳባችንን (የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ) በግለሰብ ላይ ሳይሆን በጉዳዩ ላይ ብቻ በማድረግ ውይይቱን ማዳበር ይቻላል፡፡ እኛ እንደሚዲያ ሁሉንም እንደምናስተናግድ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ለትግሉ የችሎታችንን ያህል ጠጠር በመወረዉር ከአገር አቀፍ ንግግር ወደ አገር አቀፍ ተግባር መሸጋገር


በሀብተጊዮርጊስ ለገሰ – ኖርዌይ ኦስሎ
Ginbot 7 Popular Force - GPF formed“ሁሉም የሚችለዉን ያህል ጠጠር  ይወርዉር” ይህ መልዕክት የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሀይል ምስረታን በተመለከተ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከእሳት ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ወቅት ያስተላለፉት ነዉ:: በእርግጥ የኢሳት ቴሌቪዥን የጋዜጠኛ ሲሳይ ዓላማ ህዝባዊ ሀይሉን በተመለከተ በተለያዩ  ግለሰቦች ለሚነሱት ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ነበር::
የህዝባዊ ሀይሉ መሪ ማነዉ? ህዝባዊ ሀይሉ የየትኛዉ ድርጅት ወታደራዊ ክንፍ ነዉ? የዉጊያዉን እንቅስቃሴ የሚያደርገዉ የት አካባቢ ነዉ? የሚሉና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ከአንዳንድ ግለሰቦች የሚነሱ ቢሆንም የወታደራዊ ስትራቴጂ ጥያቄዎች በመሆናቸዉ ወቅታዊ ጥያቄዎች አይደሉም፣ ከዶ/ር ብርሀኑም አገላለጽ የምንረዳዉ ወቅታዊ ጥያቄ መሆን ያለበት የህዝባዊ ሀይሉ ዓላማ ምንድነዉ? ትግሉን  ያነጣጠረዉ በማን ላይ ነዉ? የሚሉት ናቸዉ፣ ፣ከመልስም አንጻር መረጋገጥ ያለበት ወያኔ ላይ ያተኮረ ትግል በማድረግ ዘረኛዉን መንግስት በማስወገድ ሉአላዊነቷ የተከበረ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መመስረት ነዉ::
በመንደርደሪያነት የተጠቀምኩት የዶ/ር ብርሃኑ መልዕክት አንድ ዓረፍተ ነገር ቢመስልም በዉስጡ ያዘላቸዉ ሀሳቦች ግን ብዙ ናቸዉ፣ ፣ይህ መልዕክት ዓላማን መሰረት ያደረገ ትግል እንድናደርግ የሚያሳስበን ነዉ:: ትግላችን ከአንድ ብሄር በተዉጣጣ ቡድን የተጫነብንን የዉስጥ የቅኝ አገዛዝ ለማስወገድ የሚደረግ የነጻነት ትግል በመሆኑ ያለንን መለስተኛ የሀሳብ ልዩነታችንን ነጻ ከወጣን በሗላ በእኩልነት የምንዳኝበትን ስርዐት ፈጥረን ለኢትዮጵያ ህዝብ ማቅረብ ያለብን መሆኑን የሚጠቁም መልክት ነዉ::
ቅኝ አገዛዝ(colonialism) በ19ኛዉና በ20ኛዉ ክፍለ ዘመን  የዉጭ ሀይሎች በተለይ አዉሮፓዉያን የሌላን ሀገር ህዝብ በማግለልና የፖለቲካ የበላይነትን በመቆጣጠር ለእናት ሀገራቸዉ የሌላን ሀገር ሀብት መመዝበር ላይ ያተኮረ ፖሊሲ ያራመዱበትን የሚገልጽ ቃል ነዉ:: በቅርጹ ከቅኝ አገዛዝና ከእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ( Colonialism and Neo-colomialism) የተለየዉና በይዘት አንድ የሆነዉ የዘመኑ የዉስጥ ቅኝ አገዛዝ ( Internal colonialism) በጥልቀት መታየት እንዳለበት በተለያዩ ምሁራን እየተገለጸ ይገኛል::
ባሬራ (Barera) የተባሉት ምሁር የዉስጥ ቅኝ አገዛዝን ሲገልጹ ”Internal colonialism is a structured relationship of domination and subordination which are defined along ethnic or racial lines where the relation is established or maintained the interests of all or part of the dominant group in which the dominant and the subordinate populations intermingle.” ይላሉ::
በተጠናከረ መዋቅርና በረቀቀ ስልት  በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ ሀብት ከአንድ ዘር የተዉጣጣዉን ቡድን ኪስ እያሳበጠና እያደለበ ስናይ፣ የመከላከያና የደህንነት ሀይሉ ከአንድ ዘር በተዉጣጣ ቡድን ፈላጭና ቆራጭነትን ሲገለጽ፣ የፖለቲካ ሀይሉ በአንድ ዘር የበላይነት ሲመራ፣ ቢሮክራሲዉ በአንድ ዘር ተተብትቦ ሰራተኛዉን መግቢያና መዉጪያ ሲያሳጣዉ ስናይ የባሬራ (Barera) የዉስጥ ቅኝ አገዛዝ(Internal colonialism) አገላለጽ የሀገራችን የዘረኛዉ መንግስት መገለጫ መሆኑን ሳንጠራጠር እንድንቀበል ያስገድደናል::
ቅኝ አገዛዝና ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ የማይለያዩ ሀሳቦች ናቸዉ:: የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ አንድ ሀይል ሌላዉን ትልቅ ሀይል በትንንሽ ክፍሎች በታትኖ እነዚህን ትንንሽ ሀይሎች አንድ በአንድ የመቆጣጠር ስልት ነዉ:: በእርግጥ ትልቁን ሀይል ትንንሽ ቦታዎች መከፋፈል ከባድ በመሆኑ አሸናፊዉ ክፍል ፖለቲካዉን፣ ሚሊታሪና ደህንነቱን፣ እንዲሁም ኢኮኖሚ ዘርፉን መጨበጥና የህዝብ አንድነት እንዳይፈጠር መከላከል የህልዉናዉ መሰረት ነዉ:: በመሆኑም የከፋፍለህ ግዛ መሪዎች በጎሳዎች፣ በብሔሮችና በአጠቃላይ በሕዝቡ መካከል የእርስ በርስ ጥላቻ መርዝ መርጨትና ማራገብ (encouraging blood feuds) የየዕለት ተግባራቸዉ ነዉ;; ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የእያንዳንዱን ጎሳና ብሔረሰብ ስስ ብልትና ደካማ ጎን አጥንቶ ማጋጨትና ማጣላትን ይጠይቃል;;በአገራችንም በትልልቆቹ ብሔረሰቦች በአማራና በኦሮሞ እንዲሁም በተለያዩ ጎሳዎች መካከል የተፈጠረዉ የመረረ ጥላቻና በጠላትነት እንዲተያዩ የማድርግ ሴራ በወያኔ ተግባራዊ የተደረገ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ዉጤት ነዉ::
ይህ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ በዓለማችን በሰፊዉ ስራ ላይ ዉሏል ሮማዎችና እነግሊዞች ግዛታቸዉን ለማስፋትና ለመቆጣጠር ጎሳዎችን እርስ በርስ በማጋጨት ፖሊሲዉን ለሀብት ምዝበራ ተጠቅመዉበታል እንግሊዞች ህንድን፣ አንግሎ ኖርማን አየርላነድን ለመቆጣጠር የተጠቀሙበት ዘዴ ነዉ:: በአገራችንም ኢጣሊያን በአምስት ዓመት ቆይታዉ አገሪቷን በቋንቋ ከፋፍሎ ለመግዛት ያደረገዉ ሙከራ የሚረሳ አይደለም::
በመሆኑም ለ21 ዓመታት የተዘራዉ የጎሰኝነት ወይም የዘረኝነት መርዝ ለነጻነት የሚደረገዉን ትግል ዉስበስብና ከባድ ያደርገዋል;;እዚህ ላይ ተጨምሮ የመቃወም ትርጉምና የተቃዋሚዎች ስራ እርስ በርስ በመብላላት ላይ የተመሰረተ ከሆነ ትግሉን ከማዳከምና የስርአቱን ዕድሜ ከማራዘም ዉጭ የሚፈየደዉ እንደሌሌ በቃለምልልሱ ላይ በጉልህ መገለጹ አግባብ ነዉ;; ሁሉም የአቅሙን ያህል፣ የችሎታዉን ያህል ለትግሉ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ ሲቀርብ ከልባችን ዲሞክራሲያዊ ለዉጥ በኢትዮጵያ እንዲመጣ እንደምንፈልግና እንደማንፈልግ የሚለይበት በመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላቶች በጉልህ ተለይተዉ የሚታወቁበት ወቅት ላይ የደረስን መሆኑን ከመልዕክታቸዉ መረዳት ይቻላል::
የኢትዮጵያ ሕዝብ በአሁኑ ወቅት አስከፊ የሆነ ጭቆና ስር ወድቋል የአንድ አገር ምሶሶዎች ተደርገዉ የሚታዩት ኢኮኖሚ፣ ቢሮክራሲ፣መከላከያ፣ ደህንነትና ፖሊስ ከአንድ ብሔር በተዉጣጣ ቡድን እጅ የተያዘ በመሆኑ አብዛኛዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የበይ ተመልካች  የሆነበት ወቅት ላይ ደርሰናል:: በኢሳት ቴሌቪዥን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በቡድን አሳይመንት መስራት ጥያቄ እንደሚያስከትል መግለጻቸዉ የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚጠቁም ነዉ፡፡ የልቅ-ግብረስጋ ግንኙነት(pornography) ድህረገጾች እየተለቀቁ ስለ አገራችን ችግሮች መረጃ ልናገኝባቸዉ  የምንችልባቸዉን ድህረገጾች ይዘጉበናል በማለት ተማሪዎቹ አሰደምመዉናል:: ይህን ሰምቶ ምን አገባኝ ብሎ መቀመጥ ከህሊና ወቀሳ አያድነንም::
መረጃን ማራቅ፣ ያለመተማመን ስሜት በእያንዳንዱ ግለሰብ ዉስጥ እንዲፈጠር ማድረግ፣ የርስ በርሰ ጠላትነት ስሜት መፍጠር፣ ሁሉም በአይነቁራኛ እንዲተያይ ማድረግ የዘረኛዉ መንግስት የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ማጠናከሪያ ዘዴዎች ናቸዉ::
ስለዚህ ይህን ፀረ ሕዝብ የሆነ ከፋፋይ ዘረኛ ቡድን ለማስወገድ በሚደረገዉ ትግል ለመሳትፍ አምርረዉ የተነሱት አገራዊ አጀንዳ ያላቸዉ እንደ ግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሀይልና የመሳሰሉ ድርጅቶች ሙሉ ድጋፍ ሊሰጣቸዉ ይገባል:: በተለይ ህዝባዊ ሀይሉ ሀገራዊ አጀንዳ ካላቸዉ ከሌሎች በጎሳ/በብሔር ከተደራጁት ጋር ተባብሮ ለመታገል መወሰኑ በአንዳንድ ግለሰቦች የሚነሳዉን ስጋት ከማስወገዱም በላይ ድሉን የሚያፋጥነዉ በመሆኑ የሚደገፍ አቋም ነዉ::
በአጠቃላይ ከጠባቂነት ተላቀን የእያንዳንዳችን ሀላፊነት መሆኑን በመረዳት ሁላችንም ለትግሉ የችሎታችንን ያህል ጠጠር በመወረዉር ከአገር አቀፍ ንግግር  ወደ አገር አቀፍ ተግባር  መሸጋገር እንዳለብን የሚጠቁም መለልዕክት የተላለፈ ስለሆነ በአዎንታ መቀበል ይኖርብናል::
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች !!!
ፀሐፊዉን ለማግኘት ከፈለጉ - tgiorgis2005@yahoo.com

ዶክተር ሽፈራው ተክለማሪያም አክራሪነትን ለመዋጋት በሚል ከ 18 አመት በታች ያሉ ታዳጊዎች ቁርዐን ትምህርት እንዳይሰጥ አዘዙ


ዶክተር ሽፈራው ተክለማሪያም ከ18 አመት በታች የሆኑ ህፃናቶች የዲንና የአረብኛ ትምህርት እንዳይሰጣቸው የሚል ሃሳብ ማንሳታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሮባቸዋል፡፡
መጅሊስ በፍትህ ሬዲዮ ለተለቀቀው ዜና የማስተባባያ መግልጫ በኢቲቪ ሊያወጣ ነው፡፡
ዶክተር ሽፈራው ተክለማሪያም አክራሪነትን ለመዋጋት በሚል ከ 18 አመት በታች ያሉ ታዳጊዎች ቁርዐንና የዲን ትምህርት እንዳይሰጥ የተናገሩትን ተከትሎ በፍትህ ሬዲዮ መዘገቧ ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም በአወሊያ ኮሌጅ ከዚህ በፊት ይሰጡ የነበሩት የአረበኛና የዲን ትምህርት እንዲቆሙ መደረጉንም እንዲሁ መዘገባችን ይታወቃል፡፡ ሆኖም እነኚህ እውነቶች ለህዝብ ከተጋለጡ በኋላ መንግስትና የመንግስት ሹመኞቹ የመጅሊስ አመራሮች ድንጋጤ ውስጥ ገብተዋል፡፡ ይህን ተከትሎ በመንግስት ትእዛዝ መጅሊሱ የአወሊያ ትምህርት ቤት ለሃይልስኩል ተማሪዎች ብቻ የአረብኛ ትምህርት እንዲሰጥ ትእዛዝ ተሰጥቷል፡፡ ትናትና የአወሊያ ትምህርት ቤት አስተዳደር የአረብኛ መምህራንን አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት “መንግስት የአረብኛ ትምህርት እንዲሰጥ ፈቅዷል፣ ከዚህ በኋላ እናንተ መምህራኖች ትምህርቱን ለመስጠት በደንብ መዘጋጀት አለባችሁ ፡፡ ተማሪዎችን በአረብኛ ትምህርት ዘርፍና በመልካም ባህሪ የማብቃት ትልቅ ሃላፊነት ይጠብቃችኋል፡፡ ኦቨርታይም ጭምር በመስራት ይህን ማሳካት አለባችሁ” የሚል መመሪያ በስብሰባው ወቅት ለመምህራኖቹ ተላልፏል፡፡ ታዛቢዎች እንደሚሉት ግን የዲንና የአረብኛ ትምህርቱ በአወሊያ ኮሌጅ እንዳይሰጥ ተከልክሎና ተማሪዎቹ ተበትነው እያለ ፣ዜናዎችን ለማስተባበል ሲባል ብቻ የዲኑ ትምህርት ቆሞና የአረብኛ ትምህርት ተለይቶ በአወሊያ ሀይስኩል እንዲሰጥ መታዘዙ ተቀባይነት እንደሌለው እየተናገሩ ነው፡፡ እንደውም ይህ ሁሉ የሚያመለክተው መጅሊሱ በመንግስት ቀጥተኛ ትእዛዝ እንደሚሰራ አመላካች ነው ሲሉ ታዛቢዎች ተናግረዋል፡፡
በ…ሌላ በኩልም ዶክተር ሽፈራው ተክለማሪያም ከ18 አመት በታች የሆኑ ህፃናቶች የዲንና የአረብኛ ትምህርት እንዳይሰጣቸው የሚል ሃሳብ ማንሳታቸውን ተከትሎ በፍትህ ሬዲዮ ሳምንታዊ ዜና እወጃ ላይ ከተነገረ በኋላ ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሮባቸዋል፡፡ የአዲስ አበባ የመጅሊስ ፕሬዚደንት ከሳምንት በፊት በአንድ ስብሰባ ላይ “ዶክተር ሽፈራው እንደቀልድ አክራሪነትን ለመቀነስ በስብሰባ ላይ ከ18 አመት በታች ያሉትን ህፃናቶች የዲንና አረብኛ ትምህርት እንዳይሰጥ ይደረግ ይሆን? ብለው እንደቀልድ የተናገሩትን ጠቅላላ የስብሰባውን ሪፖርት ወስደው ለፍትህ ሬዲዮ ሰጡት ” በማለት በብስጭት ሲናገሩም እንደነበር ምንጮች አጋልጠዋል፡፡ አሁን ደግሞ በጉዳዩ ዙሪያ በመንግስትና በህገወጡ መጅሊስ መካከል ምክክር ከተደረገ በኋላ ከ18 አመት በታች ያሉ ህፃናቶች የቁርዐንና የዲን ትምህርት እንዳይማሩ ሊከለከል ነው እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ ሃሰት ነው ብሎ መጅሊሱ መግለጫ እንዲሰጥ ታዟል፡፡ በዚህ መሰረት መንግስት ትላንት ማክሰኞ 16 -4-2005 የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዝን ጋዜጠኞችን ወደ ህገወጦቹ መጅሊስ ቢሮ ልኮላቸው ኢንተርቪው ማድረጋቸውም ታውቋል፡፡ ህዝቡም ይህን ቀድሞ ተረድቶ እንደከዚህ ቀደሙ የመንግስትንና የመጅሊሱን ግዜያዊ ተራ ፕሮፖጋንዳ ቀድሞ እንዲያውቅና ለመግለጫውም ቦታ እንዳይሰጠውና ተቀባይነት እንደማይኖረውም ከወዲሁ እንዲያውቁት ማድረግ አለብን ፡፡ፍትህ ሪዲዮም በዚህ አጋጣሚ የምታስተላልፈው መልዕክት፤ የመንግስት ባለስልጣናት በየስብሰባው አዳራሽ አፋቸውን ያለገደብ እየከፈቱ ህዝብን የበለጠ ከማስቆጣት እና ማስተባበያ ለማውጣት ከመንደፋደፍ ይልቅ መፍትሄው የህዝበ ሙስሊሙን መሰረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ነው ትላለች፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ሙስሊም!
source: http://minilik-salsawi.blogspot.no/

ESAT Daliy News-Amsterdam Dec. 31 2012 Ethiopia


በደሴ መስጊዶች በሀይል እየተነጠቁ ነው


ታህሳስ  ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የተለያዩ የመንግስት አካላት ከፖሊስ ጋር በመተባባር በደሴ የሚገኙ መስጊዶችን ቁልፎች አዳዳስ ለተመረጡት የመጅሊስ አመራሮች እንዲያስረክቡ ማድረጋቸው  ታውቋል።
በዛሬው እለት በከተማ የሚገኙ ዋና ዋና መስጊዶች ቁልፎች ለአዳዲሶቹ የመጅሊስ ተመራጮች እንዲረከቡዋቸው ተደርጓል።
በተመሳሳይ ዜናም የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን በሙስሊም መሪዎች ቤት ውስጥ ሆን ብሎ በማስቀመጥ  ቪዲዮ እየተሰራ መሆኑንና ቪዲዮውም አመራሮችን ለመክሰስ እንደማስረጃ እንደሚቀርብ ታውቋል።
በመንግስት እና በሙስሊም ኢትዮጵያውያን መካከል ያለው ውዝግብ አንድ አመት ሊደፍን አንድ ወር እድሜ ብቻ ቢቀረውም መንግስት አብዛኛውን ሙስሊም የሚያስቆጣ እርምጃ ከመወሰድ ባሻገር ችግሩን ለመፍታት ሙከራ ሲያደርግ አይታይም።

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰሙ


ታህሳስ  ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ተማሪዎቹ ባለፈው አርብ ምሽት በጀመሩት ተቃውሞ የመማሪያ ክፍሎች መስኮቶች መሰባበራቸውን ለማወቅ ተችሎአል።
አርብ ምሽትና ቅዳሜ የፌደራል ፖሊስ አባላት ዩኒቨርስቲውን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ተማሪዎች ግቢውን ለቀው የወጡ ሲሆን ገሚሶቹ በቤተክርስቲያኖች ውስጥ ተጠልለው እንደነበር ታውቋል።
ተማሪዎቹ ተቃውሞአቸውን ያሰሙት አዲሱን የውጤት አሰጣጥ ፖሊሲ በመቃወም እንዲሁም መሰረታዊ የሆኑ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ስላልተሟሉላቸው ነው። በግቢው ውስጥ 2 ሺ ተማሪዎች ያሉ ሲሆን፣ ከፍተኛ የሆነ የውሀና የመጸዳጃ እጥረት አለ። አብዛኞቹ ተማሪዎች የሀይላንድ ውሀ እየገዙ እንደሚጠቀሙና በየጫካው ለመጸዳዳት እንደተገደዱ ታውቋል።
ዩኒቨርስቲው አንድ ቤተመጽሀፍት ብቻ ያለው ሲሆን፣ በቂ መጽሀፎችም እንደሌሉት ተማሪዎች ይናገራሉ። 95 በመቶና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች ብቻ “ኤ” እንዲያገኙ የሚያስገድደው አዲሱ መመሪያ ተማሪዎችን አስቆጥቶ ወደ አደባባይ እንዳስወጣቸው ታውቋል።
ከ300 በላይ ተማሪዎች በዚህ ሁኔታ አንማርም በማለት ዩኒቨርስቲውን ጥለው ወደ ቤተሰቦቻቸው የተመለሱ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ በትናንትናው እለት ከዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት በተገባላቸው ቃል መሰረት ወደ ግቢያቸው መመለሳቸው ታውቋል። ይሁን እንጅ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ትምህርት አለመጀመራቸው ታውቋል።
ከሳምንት በፊት አዲሱን የውጤት አሰጣጥ መመሪያ በመቃወም  የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተቃውሞ ለማሰማት ውስጥ ለውስጥ መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ መንግስት መመሪያውን ተግባራዊ እንዳማያደርገው ቃል በመግባቱ እንቅስቃሴው ሊቆም እንደቻለ ታውቋል።
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ በቦረና ዞን እንደሚገኝ ይታወቃል።

የጎንደር ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ዲን ተማሪዋን አስገድደው ደፈሩ


ታህሳስ  ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የተማሪዎች ዲን የሆኑት አቶ ናትናኤል ህዳር 27 ቀን 2005 ዓ.ም የሚያስተምሯትን ተማሪ ስልክ በመደወል ከምሽቱ 1፡30 ገዳማ ቢሯቸው ድረስ ካስጠሩ በኋላ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንደፈጸሙባት ከጎንደር ያገኘነው ዜና ያስረዳል።
የተደፈረችው ተማሪ በግሏ ጥረት ወደ ዩኒቨርስቲው ሆስፒታል በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና ምርመራ ያደረገች ሲሆን የምርመራው ውጤትም ተማሪዋ የአስገድዶ መደፈር ሰላባ መሆኗን የሚያረጋግጥ ነው።
ተማሪዋን አስገድደው የደፈሩት ግለሰብ ያላቸውን የኃላፊነት ቦታ እንዲሁም የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራር የሆኑ ወዳጆቻቸውን በመጠቀም የምርመራ ውጤቱን ማስረጃ ከዩኒቨርስቲ ሆስፒታሉ ደብዛውን ለማጥፋት ቢሞክሩም ተጠቂዋ የህክምና ምርመራ ውጤቷን አስቀድማ በመውሰዷ ሳይሳካላቸው ቀርቷል።
የተጠቃችው ተማሪ የህክምና ውጤቱን ማስረጃ በመያዝ ታህሳስ 12 ቀን 2005 ዓ.ም ለጎንደር ከተማ አስተዳደር 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ያመለከተች ቢሆንም ፖሊስ መረጃውን ተቀብሎ ምንም አይነት እርምጃ ሳይወስድ የቆየ ሲሆን የተጠቂዋ ተማሪ ቤተሰቦችና አንዳንድ መምህራን ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት እና ጫና ታህሳስ 20 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ገዳማ ተጠርጣሪው አቶ ናትናኤል በፖሊስ ተይዘው እንዲታሰሩ ተደርጓል።
ይህ ከሆነም በኋላ የ6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ፖሊስ አባላት ከጎንደር ዩኒቨርስቲ የአስተዳደር ም/ፕሬዝዳንት ከሆኑት አቶ ሰለሞን አብርሃ ጋር በመሆን ወንጀሉን ለማድበስበስ እና ተጠቂዋ ተማሪን በተደጋጋሚ ስልክ እየደወሉና እየተገናኙ ጫና በመፍጠር ልጅቷ ክሷን እንድታቆምና ነገሩን በእርቅ አሳበው የወንጀሉን ዱካ ለማጥፋት እየተሯሯጡ ይገኛሉ።
የልጅቷን ሁኔታ በቅርበት የሚከታተሉ ግለሰቦችም ደፍረዋል የተባሉት ግለሰብ ያላቸውን ፖለቲካዊ ተሳትፎ እና መንግስታዊ ስልጣን ተጠቅመው ወንጀሉን በቀላሉ እንዲጠፋ ሊያስደርጉ ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል።
አስገድደው ደፍረዋል ተብለው የተጠረጠሩት የተማሪዎች ዲን የሆኑት አቶ ናትናኤል ልጅና ሚስት ያላቸው ሲሆን ወደ ጎንደር ዩኒቨርስቲ ከመግባታቸው በፊት በደቡብ ጎንደር ዞን ውስጥ በወረዳ ካቢኔነት አገልግለዋል።
ለገዢው ፓርቲ ባላቸው ታማኝነትና አገልጋይነት በቀላሉ የዩኒቨርስቲ መምህር መሆን የቻሉ ሲሆን ግለሰቡ ለገዢው ፓርቲ በዩኒቨርስቲው ውስጥ በሚሰሩት የፖለቲካ ስራ ያለ ትምህርት ዝግጅታቸው እና ያለ ብቃታቸው የተማሪዎች ዲን መሆን ችለዋል።
በጎንደር ዩኒቨርስቲ ውስጥ በዩኒቨርስቲው አመራሮች የሚፈጸመው ሙስና ከልክ እያለፈ መምጣቱን የግቢው ሰራተኞች ይናገራሉ።

በአማራ ክልል 500 ፖሊሶች ስራቸውን ለቀቁ / የአረና ፓርቲ ጽህፈት ቤት በዶዘር ፈረሰ


ታህሳስ  ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው በክልሉ በአንድ አመት ውስጥ ብቻ 500 ፖሊሶች ስራቸውን ለቀዋል። ፖሊሶች ስራቸውን መልቀቃቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በአንድ ስብሰባ ላይ አምነዋል።
ፖሊሶች ስራቸውን የለቀቁት በአስተዳደር ጫና እና ከስራቸው ጋር የማይጣጣም እና የኑሮ ውድነቱን ለማቋቋም የማያስችል ክፍያ ስለማይከፈላቸው መሆኑን ይገልጻሉ።
በክልሉ ውስጥ የሚታየው የኑሮ ውድነት ፖሊሶችን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የመንግስት ሰራተኞችን እያስመረረ መምጣቱን ለኢሳት የሚደርሱት መረጃዎች ያመለክታሉ። በዚህ የኑሮ ውድነት ላይ ለአባይ ግድብ ማሰሪያና ለትራንስፎርሜሽን እቅዱ ማሳኪያ በሚል ሰራተኞች መዋጮ እንዲከፍሉ መገደዳቸው ኑሮአቸውን የከፋ እንዲሆን እንዳደረገው ሰራተኞች ይገልጻሉ።



የአረና ፓርቲ ጽህፈት ቤት በዶዘር ፈረሰ 
ታህሳስ  ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በሁመራ የሚገኘው የፓርቲው ጽህፈት ቤት በዶዘር እንዲፈርስ ከተደረገ በሁዋላ የድርጅቱ ጽህፈት ቤትም ተዘርፎአል። በተመሳሳይ መንገድም የድርጅቱ አባል የሆኑት የአቶ ገብረእግዚ ናዩ ቤት ያለምንም ማስጠንቀቂያ እንዲፈርስ ተደርጓል።
በተንቤን የድርጅቱ አባል የሆኑት አቶ ጸጋየም መታሰራቸው ታውቋል። በአቶ ገብሩ አስራት በሚመራው አረና ፓርቲ ላይ የትግራይ ክልል ባለስልጣናት የሚወስዱት እርምጃ እየከፋ መምጣቱን መዘገባችን ይታወሳል።

የተቃዋሚ 33 የፓለቲካ ድርጅቶች ያቋቋሙት ጊዚያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን ሊከሰው መሆኑን አስታወቀ


ታህሳስ  ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- የምርጫ  ቦርድ ከፍተኛ ሀላፊ የኢህአዴግ አባል ሆነው ለክልል ምክር ቤት አባልነት ምርጫ መወዳደራቸውንም አጋልጧል::
ጊዜያዊ ኮሚቴው ለምርጫ ቦርድ ባቀረበው 18 ጥያቄዎች ማስረጃ ያላቸውን ይፋ ያደረገ ሲሆን ምርጫ ቦርድን ለፓርላማ አፈጉባኤ እንደሚከስ አስታውቋል::
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በአስተባባሪ ኮሚቴው የቀረቡት 18 ጥያቄዎች ማስረጃ የላቸውም ብሎ ጥያቄዎቹን ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ ነው ወሳኝ ያላቸው ማስረጃዎች ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች ኮሚቴው ይፋ ያደረገው:፡
ምርጫ ቦርድ በተቃዋሚዎች የቀረቡትን ቅሬታዎች ለወር ያህል ከገመገምኩ በኋላ ሰጠሁ ያለው ምላሽ አሳፋሪና ነገ በህዝብ ዘንድ የሚያስወቅስ መሆኑን ያመለከተው ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማስረጃ እንድናቀርብ ሳይጠይቀንና ሳያነጋግረን ውሳኔውን በመንግስት ሚዲያ ማወጁ አሳዝኖናል ብለዋል::
የጊዚያዊ አስተባባሪ ኮሚቴው አባልና የቦርድ አመራር አቶ ገብሩ ገብረማሪያም ከጋዜጠኞች ምን ማስረጃ አላችሁ ተብለው ለቀረበ ጥያቄ ለሁሉም በቂ ማስረጃ አለን በማለት የምርጫ ቦርድ  የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሬት ዳይሪክተር ወ/ሮ የሺ ፍቃደ የኢህአዴግ አባል ሆነው ለምርጫ የተወዳደሩበት ማስረጃ አቅርበዋል::
የክልል ም/ቤት አባላት ምርጫ ጣቢያ የድምጽ ቆጠራ ውጤት መተማመኜ በሚለውና የምርጫ የምርጫ ቦርድ አርማ ባለበት በዚህ ሰነድ የእጩ ተወዳዳሪዋ የወ/ሮ የሺ ፍቃደ ስም የሚገኝበት፡ በብአዴን ፓርቲ በንብ ምልክት ፡ እየታዩ ያመጡት የድምጽ ብዛትና ደረጃቸው የሰፈረበት ፡ ለአማራ ክልል ምክር ቤት የደብረ ብርሀን እጩ ተወዳዳሪ ሆነው መቅረባቸውን ያሳያል::
የጊዜያዊ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አስራት ጣሴ አንድም ማስረጃ የሌለው ጥያቄ አላቀረብንም ፡ ካሉ በኋላ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኢህአዴግ ጉዳይ አስፈጸሚ በመሆኑና ሊያነጋግረንም ፡ ማስረጃ እንድናቀርብ ሳይጠይቀንም ጥያቄያችሁን ውድቅ አድርጌያለሁ ማለቱ እንዳሳዘናቸው ገልጠዋል::

ሽምግልናውን ሲያካሒድ ከነበሩ አስታራቂዎች የቤተክርስትያን አባቶች መካከል አንደኛው ከኢትዮጲያ ሲባረሩ ሁለተኛው የደረሱበት አይታወቅም


ታህሳስ  ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባዎቹ ተደራዳሪ አባቶች ባለፈው ሳምንት ያወጡት መግለጫ ተገደው የፈረሙበት መሆኑም ተገለጸ።በቅርቡ በዳካስ ቴክሳስ የተካሄደውን ሶስተኛ ዙር በሎስአንጀለሰ ካሊፎርንያ ለማካሔድ ቀጠሮ ይዘው ከተነሱት አባቶች አንደኛው የሆኑት ብጹነ አቡነ ገሪማ በገጠማቸው የጤና ችግር አሁንም በዮኤስ ኣሜሪካ አንደሚገኙ ለማወቅ ተችሉአል።ቅዳሜ ታህሳስ 20/2005 ኣሜሪካ የደረሱት ሊቀ ካህናት ኃይለሰላሴ አለማየው ታግደው መባረራቸውን ለሾይስ ኦፍ ኣሜሪካ የአማርኛ አገልግሎት አረጋግጠዋል::
ከርሳቸው ጋር አብረው የተጎዙት ሌላው የሽምግልና ቡድን አባል ዲያቆን አንዱአለም ዳግማዊ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ የታወቀ ነገር የለም ፡ ሊቀካህን ሀ/ስላሴ ከእስር ተርፈው የተባረሩት የአሜሪካ ዜጋ በመሆናቸው እንደሆነም ተመልክቷል::
ይህ በእንዲህ እንዳለም ከአዲስ አበባ ተወክለው በድርድሩ ተሳታፊ የነበሩት አባቶች ታህሳስ 13/2005 በአስታራቂ ኮሚቴው ላይ ያወጡትን መግለጫ ተገደው መፈረማቸውን ደጀሰላም ዘግቧል:: አባቶቹ ኤምባሲ መጠራታቸውን መዘገባችን ይታወሳል::
ከደጀሰላም ዘገባ መረዳት እንደተቻለው አባቶቹ የተጠሩት አስታራቂውን ቡድን በሚያወግዘው መግለጫ ላይ ፊርማቸውን እንዲያሳርፉ ነው::
ይህንን በማቀነባበር አቢይ ሚና የተጫወቱት የልኡኩ ቡድን አባል ንቡረእድ ኤሊያስ አብርሀ መሆናቸውም በዘገባው ተመልክቷል::
በሌላም በኩል የሀገር ቤቱ ልኡክ አባል ብፁእ ዶ/ር አቡነ ገሪማ በደረሰባቸው የጤና ችግር በአሜሪካ ህክምና በመከታተል ላይ ናቸው::
አቡነ ገሪማ በገጠማቸው የጤና ችግር ምእመናን ለህክምና መዋጮ እያሰባሰቡ ይገኛሉ::

Sunday, December 30, 2012

ሰበር ዜና `ከአሜሪካን የሚመጣው ሲኖዶስ መፈንቅለ መንግስት ሊያደርግ እንጂ ቤተክርስቲያን ሊመራ አይደለም!!` በረከት ስምኦን

ሰበር ዜና

`ከአሜሪካን የሚመጣው ሲኖዶስ መፈንቅለ መንግስት ሊያደርግ እንጂ ቤተክርስቲያን ሊመራ አይደለም!!` በረከት ስምኦን

የወያኔው የህዝብ ግንኙነት ሰው ወይም ራሳቸዉን ምኒስትር ብለው የሚያስጠሩት አቶ በረከት ስምኦን ዛሬ ማምሻውን የኦርቶዶክስ ቤ/ክ አስመልክቶ ከወዳጆቻቸው ጋር ባደረጉት ዉይይት ቤተ ክርስቲያኒትዋን በመከፋፈል የጽንፈኛ ዲያስፖራዎችን ፖለቲካዊ አላማ በማንገብ አገር ቤት ከገቡ በሁዋላ ሽብር በመንዛት መንግስትን እና ህዝብን ለማጋጨት የተሸረበ ሴራ ነው ብለዋል:ሲሉ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ገለጡ::
የአሜሪካው ሲኖዶስ ነኝ የሚለው የፖለቲካ ቡድን በኢትዮጵያ ዉስጥ መረጋጋት እንዲኖር የሚሰራ እና ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉን የተረጋጋ መንግስት ለመገልበጥ የተዘጋጀ ቡድን ነው ሲሉ ወቅሰዋል::

አቶ በረከት እንዳሉት የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈልገው ሰላም እና ዲሞክራሲ በልማት አዋህዶ ማደግ እንጂ በበርገር የጠገቡ ጳጳሳትን አይደለም ብለው ተወያይ ወዳጆቻችውን  ፈገግ አሰኝተዋል:: እንደ አቶ በረከት አባባል ለእርቀ ሰላም ከመጡት ሰዎቻቸው አንደኛው (ሃይለስላሴ አለማየሁ) ከተቃዋሚ መሪዎች ጋር በተለያየ ጊዜ በመንግስት ደህንነቶች በመታየቱ ይህን ጉዳይ ከአቡነ ናትናኤል ጋር ተወያይተንበት ከምታስሩት ከሃገር እንዲወጣ አድርጉት ..አለም አቀፍ ተቃውሞው እንዳይበረታ ...የሚል ነገር ስለነገሩን ከሃገር አባረነዋል ሲሉ አቶ በረከት ተንፍሰዋል:እንደ ምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች::

አቶ በረከት የሙስሊሞች እንቅስቃሴ በተመለከተ በቁጥጥር ስር ለማዋል እየተሰራ መሆኑን ገልጠው አንዳንድ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ዲፕሎማቶች ይረዱዋቸዋል እንዲሁም ወደ ፖለቲካ ሽብር ለመቀየር እየለፉ ነው ሲሉ የሚለፉትን ሰዎች ስም ከመጥቀስ ተቆጥበዋል...የሚረዱትንም እንዲሁ...ዲያስፖራው ጽንፈኝነትን ለማስፋፋት እየሮጠ እንደሆን ሳያወሩ አላለፉም::

አሕባሽ የተባለዉን ነገር አንስተው ይህ የሃይማኖት ሴክት /ሃራጥቃ / ነው ያሉት አቶ በረከት በህገ መንግስቱ መሰረት መስራት ይችላል ሆኖም ዘይቤው ሽብርተኛ አይደለም እንደለላው ብለዋል::
አቶ በረከት ይህን ሁላ ሲያወሩ የተቀዳላቸው ሻይ በርዶ ነበር::እንደ ምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች ዘገባ::

ESAT WAZA ENA KUMENRGER 29-Dec. 2012


ብሶት የወለደኝ እያለ የሚመጻደቀው ወያኔ ብሶተኞችን እየፈለፈለ ነው


በአገራችን ውስጥ የነበረው ብልሹ አስተዳደር በፈጠረው ኢፍትሃዊነት ብሶት አርግዞ ለድል ያበቃውን ጠመንጃ እንደመዘዘ በኩራት የሚደሰኩረው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ፡ የመንግሥት ሥልጣንን የሙጥኝ በማለት በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ባለው ሰቆቃ ተማርረው በተራቸው ብሶት አርግዘው ጠመንጃ ለማንሳት የሚገደዱ ሃይሎችን በየቀኑ እየፈለፈለ መሆኑ በተግባር እየታየ ነው።
ወያኔ የድጋፍ መሠረቴ ነው ከሚለው የትግራይ ክልል ውስጥ የወጣው “የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት” ወይም ዴሚት በሚል ምህጻረ ቃል ከሚጠራውና በርካታ የትግራይ ወጣቶችን ማሰባሰብ ከቻለ ድርጅት ጀምሮ “በአገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የብሄር እኩልነት ካባ አከናንቤያችኃለሁ” ብሎ ወያኔ ከሚመጻደቅባቸው ህዝቦች አብራክ የወጡ የኦሮሞ፣ የኦጋዴን፣ የቤነሻንጉል፣ የጋምቤላ፣ የአፋርና የደቡብ ህዝቦች የዚህን ዘረኛ ሥርዓት እብሪትና ጥጋብ አስተንፍሰው የተዋረደውን ክብራቸውን ለማስመለስ መሳሪያ አንስተው መፋለም ከጀመሩ ውለው አድረዋል።
በወያኔ የዘር ፖለቲካ ከማለዳው ጀምሮ የጥቃት ሰለባ የሆነውና እንደ ባዕድ ወራሪ በሰላም ከየሚኖርባቸው ክልሎች ታድኖ የሚባረረው አማራም “በዘር መደራጀት ከጥቃት የሚያድን” ከሆነ በሚል ቁጭት ተደራጅቶ የትጥቅ ትግሉን ጎራ መቀላቀሉን አስታዉቋል። በብሄር እኩልነት ስም በየክልሉ ለተሾሙ ምስለኔዎች በታኮነት የተመደቡ ዘረኞች በህዝባችን ስም እየማሉና እየተገዘቱ የሚያደርሱት ግፍ አስመርሯቸው ጠመንጃ ካነሱ ከነዚህ የብሄር ድርጅቶች በተጨማሪ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ላለፉት 12 አመታት ከወያኔ ጋር የሽምቅ ውጊያ እያካሄደ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባርም የተፈጠረው ወያኔ በህዝባችንና በአገራችን ላይ በሚፈጽማቸው ወንጀሎች ብሶት ባረገዙ ዜጎች መሆኑን የማያውቅ ኢትዮጵያዊ የለም።
ሰሞኑን ደግሞ የወያኔን ዘረኛና አምባገነናዊ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ በትጥቅ ትግል ለማስወገድ በአገር ወዳድና ለህዝብ ተቆርቋሪ በሆኑ ዜጎች ስብስብ፤ ወጣቶችና፣ ምሁራን የተሞላ ድርጅት ማቋቋሙን ለህዝብ ይፋ ያደረገው “የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል” ካሰራጨው መግለጫ መረዳት እንደተቻለው፤ ወያኔ ድርድርና እርቅ የማይገባው፣ ትዕግስትን እንደፍራቻ፣ አርቆ አሳቢነትን ደግሞ እንደ ሞኝነት የሚቆጥር በዚህም ስሌት ሕዝብን ለዘላላም እየረገጠና እየዘረፈ ለመግዛት ቆርጦ የተነሳ እኩይ ኃይል በመሆኑ ወያኔን ሊገባው በሚችል ብቸኛ ቋንቋ በማነጋገር የአገዛዝ ዕድሜውን ለማሳጠር ቆርጦ ብረት ያነሳ ሃይል ተፈጥሯል።
ግንቦት7 የፍትህ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ሲያስጠነቅቅ እንደኖረው ፋሽስት ጣሊያን ሞክራ ባልተሳካላት የመንገድና የህንጻ ግንባታዎች ተደልሎ ወይም ከግማሽ በላይ የሆነውን ህዝባችንን ለረሃብ በዳረገ ወያኔ ግን ልማትና እድገት ብሎ በሚጠራው ለውጥ ተታልሎ ክብሩንና ነጻነቱን አሳልፎ በመስጠት እስከወዲያኛው ለወያኔ ባሪያ ሆኖ ለመገዛት የተዘጋጀ ህዝብ የለም ብሎ ያምናል።
ወያኔ ጥጋብ በወለደው እብሪቱ በማንአለብኝነት የህዝብን መብትና ነጻነት ረግጦ በአፈና ሥልጣን ላይ ለመቆየት የሚወስዳቸውን እርምጃዎች አለኝታየ በሚላቸው የፖሊስ፣ የደህንነትና ወታደራዊ ኃይሎች እስከ መጨረሻው አጠናክር ለመቀጠል የሚችል አድርጎ ያስባል። በዚህም ምክንያት እስካፍንጫው ባስታጠቀው ወታደር ብዛትና በነዋሪው ቁጥር ልክ ህዝብ መሃል ባሰማራው ሰላዮች የተገነባው የፍርሃት ግምብ የሚናድም መስሎ አይታየውም። ሃቁ ግን በግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የተሰባሰቡ ወጣቶችም ሆኑ ወያኔን በአራቱም የአገራችን ማዕዘናት ለመግጠም ጠመንጃ ያነሱ ሃይሎች ወያኔ ህዝባችንን ሊያስፈራራ የሚችልበትን ሁሉ በጣጥሰው ለመውጣት ምንም ችግር የሌለባቸው መሆኑን ነው።
ንቅናቄያችን ግንቦት 7 ወያኔ ገንብቻለሁ ብሎ የሚኮፈስበትን የፍርሃት ግምብ ደርምሰው ለነጻነታቸው ሲሉ ውድ የህይወት ዋጋ ለመክፈል በግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ዙሪያ መሰባሰባቸውን ይፋ ያደረጉ ወጣቶች የተነሱለትን ክቡር አላማ ያደንቃል። በዚህም ምክንያት ለነጻነቱ ቀናኢ ለሆነው ህዝባችን ያቀረቡትን የትግል ጥሪ ወቅታዊነት ሁሉም እንዲረዳው የበኩሉን አሰተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

ESAT Tikuret Dr. Birhanu Nega December 2012 Ethiopia


ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫ ቦርድ ላይ ሚስጥራዊ ያሉዋቸውን ሰነዶች ይፋ አደረጉ


የቦርዱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የኢሕአዴግ ዕጩ ሆነው የተወዳደሩበትን ሰነድ አቀረቡ
- የምርጫ አስፈጻሚዎች ለኢሕአዴግ የአባልነት መዋጮ የከፈሉበት ሰነድ አለን ይላሉ
- አንድ ለአምስት አደረጃጀት ለምርጫ ቅስቀሳ እየዋለ ነው በማለት ኮነኑ
በየማነ ናግሽ
መድረክንና መኢአድን ጨምሮ ዋነኛ ተቃዋሚዎች የተሰባሰቡበት 33 የፖለቲካ ፓርቲዎች ያቋቋሙት ጊዜያዊ ኮሚቴ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ለፓርላማው አፈ ጉባዔ ክስ እንደመሠረቱበት ገልጸው፣ አገኘናቸው ያሉዋቸውን አንዳንድ ሚስጥራዊ ሰነዶች ይፋ አደረጉ፡፡
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ግንባር (መድረክ) ጽሕፈት ቤት የፓርቲዎቹ ጊዜያዊ ኮሚቴ ባለፈው ሐሙስ ለአገር ውስጥና ለውጭ ጋዜጠኞች በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ አንዳንድ ሚስጥራዊ ያላቸውን ሾልከው የወጡ ሰነዶችን ይፋ በማድረግ፣ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባለፈው ሳምንት ለቅሬታቸው ማስረጃ የላቸውም ማለቱን አስተባብለዋል፡፡
“የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ላቀረብናቸው 18 ጥያቄዎች የሰጠው ምላሽ ቦርዱ የገዥው ፓርቲ ወገንተኛና ጉዳይ አስፈጻሚ ለመሆኑ ማረጋገጫ ነው፤” በሚል ርዕሰ ጊዜያዊ ኮሚቴው ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ቀጣዩ ምርጫ ፍትሐዊ እንዲሆን እንነጋገርበት በሚል ለቦርዱ 18 የቅሬታ ጥያቄዎችን ቢያቀርብም፣ “አንዳቸውም በማስረጃ የተደገፉ አይደለም” በሚል በተሰጣቸው ምላሽ ውድቅ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
ምርጫ ቦርድ በተቃዋሚ ፓርቲዎች የቀረበለትን ቅሬታ ለአንድ ወር ያህል ከገመገምኩ በኋላ በሚል የሰጠው ምላሽ አሳፋሪና ነገ በሕዝብ የሚያስጠይቅ ነው ያሉ ሲሆን፣ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ሳይጠይቃቸውና ተወካዮቻቸውን ሳያነጋግር ውሳኔውን ያሳወቃቸው ለመንግሥት መገናኛ ብዙኃን መግለጫ በሰጠበት ወቅት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በምርጫ ቦርድ ምላሽና በምላሽ አሰጣጡ አግባብነት የተበሳጨው የ33 ፓርቲዎች ጊዜያዊ ኮሚቴ፣ ቦርዱን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በፓርላማ አፈ ጉባዔው ላይ ክስ እንደመሠረተበት አስታውቋል፡፡ በሌላ በኩል ማስረጃ ያላቸውን ለጋዜጠኞች ይፋ አድርጓል፡፡ “በታሪክም በኢትዮጵያ ሕዝብ ፊትም የሚያስተዛዝብና የሚያስጠይቅ ነው፤” ባለበት በዚሁ መግለጫ፣ “ለመሆኑ መቼ መድረኩ ተከፍቶ ተወያይተን? ማስረጃ ለማቅረብ ተጠይቀን ማቅረብ አለመቻላችን ታየና ነው እንዲህ ሊባል የተቻለው?” በማለት በጥያቄ ለተነሳው ጉዳይ የኮሚቴው አባላት ምላሽ የሰጡት ማስረጃ ያሉትን በማቅረብ ነበር፡፡
የኮሚቴው ዋና ጸሐፊ አቶ ግርማ በቀለ መግለጫውን አንብበው ከጨረሱ በኋላ፣ “ማስረጃችሁ ምንድን ነው? ምን አዲስ ነገር ይዛችኋል?” በሚል ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ቀድመው ምላሽ የሰጡት የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አስራት ጣሴ፣ “አንድም ማስረጃ የሌለው ቅሬታ አላቀረብንም፡፡ ቦርዱ ግን የኢሕአዴግ ጉዳይ አስፈጻሚ ሆኗል፡፡ ፈጽሞ አላነጋገረንም፤ ማስረጃ እንድናቀርብም አልጠየቀንም፤” ብለዋል፡፡
የኮሚቴው አባልና የመድረክ አመራር አባል አቶ ገብሩ ገብረማርያም በበኩላቸው፣ ለእያንዳንዱ ቅሬታ ማስረጃ መያዛቸውን ያረጋገጡት፣ የቦርዱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ የሺ ፈቃደ በተለያዩ ሚዲያዎች እንደ ኢሕአዴግ ሆነው ሲከራከሩዋቸው ቆይተው አሁን የኢሕአዴግ አባል የሆኑበት ማስረጃ መገኘቱን በማሳወቅ ነበር፡፡
“በወይዘሮ የሺ ላይ ግላዊ ጥላቻ ኖሮን አይደለም፡፡ ነገር ግን የኢሕአዴግ አባላት ሥራ አስፈጻሚ የሆኑበት ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ሆኖ ምርጫ ማከናወን አይችልም፤” ብለዋል፡፡ በኃላፊዋ ላይ ለምን እንዳተኮሩ ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፣ ማስረጃውን ይዘዋል የተባሉት የኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ አቶ ወንድማገኝ ደነቀ ንግግራቸውን የጀመሩት በእጃቸው አንድ ሰነድ ከፍ አድርገው በማመልከት ነበር፡፡ በ1997 ዓ.ም. በተካሄደው አገራዊ ምርጫ “የክልል ምክር ቤት አባላት የምርጫ ጣቢያ የድምፅ ቆጠራ ውጤት መተማመኛ” በሚል የምርጫ ቦርድ ዓርማ ያለበት ሰነድ የዕጩ ተወዳዳሪዋ የወይዘሮዋ የሺ ፈቃደ ስም የሚገኝበት፣ በብአዴን ፓርቲ በንብ ምልክት ያገኙት የድምፅ ብዛትና ደረጃቸው የሰፈረበትና ለአማራ ክልል ምክር ቤት የደብረ ብርሃን ዕጩ ተወዳዳሪ ሆነው መቅረባቸውን የሚያሳይ ነው፡፡
ወይዘሮ የሺ በቀረበው ማስረጃ ላይ አስተያየት እንዲሰጡን ጠይቀናቸው፣ “ይህ ማስረጃ ለምርጫ ቦርድ አልቀረበም፡፡ የምሠራው ለቦርዱ ነው፡፡ ቦርዱ ይህ ማስረጃ ቀርቦለት ጥያቄ ሲያቀርብልኝ ብቻ ምላሽ የምሰጥበት ይሆናል፤” በማለት የቀረበው ማስረጃ እውነተኛ ነው አይደለም ሳይሉ ለጥያቄው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡
ሌላ የኮሚቴው አባል አቶ ለገሠ ላንቃም የሲዳማ ዓርነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ተወካይ ሲሆኑ፣ በርካታ ማስረጃዎችን ማቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል በደቡብ ክልል የቦርባ ምርጫ ክልል ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሲሠሩ የቆዩት አቶ ዮሐንስ አብርሃም የተባሉ ግለሰብ፣ የደኢሕዴን (ኢሕአዴግ) አባልነት መዋጮ የከፈሉበት ሰነድ ይገኝበታል፡፡ ብዙዎቹ ምርጫ አስፈጻሚዎች የፓርቲ አባላት መሆናቸውን ማሳያ ነው በማለት ነበር ያቀረቡት፡፡ ሌሎች ማስረጃዎች እንዳሏቸው በመጠቆም ጭምር፡፡ በምርጫ 2002 የነበረው ሁኔታ ምንም አለመቀየሩንና በተመሳሳይ መንገድ እየተካሄደ መሆኑን የገለጹት አቶ ለገሠ፣ በተለይ “በወቅቱ የአርቤጎና ወረዳ ምርጫ ሥራን ለማሳካት የወጣ አጭር ማስፈጸሚያ ቼክ ሊስት” በሚለው ሰነድ፣ የክልሉ ገዥው ፓርቲ ከወረዳ ማዕከል እስከ ቀበሌ የሚሠሩ ተግባራትን ያካተተ ነው፡፡ “ለልማት የፈጠርነውን የልማት ሠራዊት ወደ ምርጫ ተግባር አንድ ለአምስት በማዟዟር” በሚል የአንድ ሳምንት አደረጃጀት እንዴት ለቅስቀሳና ለምርጫ እንደሚውል፣ የሴቶችና የወጣቶችን የቀበሌ አደረጃጀቶች እንዴት መጠቀም እንደሚቻል፣ ትምህርት ቤቶችንና የሃይማኖት ተቋማት እንዴት ማንቀሳቀስ እንደሚቻል የሚያብራራ ጽሑፍም አሳይተዋል፡፡ ይኼው ሰነድ ፓርቲውን ሳያወላውል የሚመርጠውን “A” አቋሙ ተለይቶ ያልታወቀውን “B” በማለት፣ ፈጽሞ የለየለትን ተቃዋሚ ደግሞ “C” እንደሰጠ ገልጸው፣ ወደ “A” ለማምጣት ጠንካራ ሥራ መሥራት እንደሚያስፈልግ ያመለክታል ካሉ በኋላ፣ የማይመርጡትን ምን እንደሚሠሩ “በዓይነ ቁራኛ” የቅርብ ክትትል ማድረግ ይጠይቃል በማለት አስረድተዋል፡፡
ሌሎች አባላትም ባለፈው ምርጫ ቤታቸው የተቃጠለባቸውን፣ ተገደሉ ያሉዋቸውን ሰዎችና ለእስር የተዳረጉትን ስም እየጠቀሱ ያቀረቡ ሲሆን፣ ይኼም እስካሁን በግልጽ እየተሠራበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
“መንግሥት አንድ ፓርቲ አንድ አገር ብሎ ያውጅና ቁርጣችንን እንወቅ፤” ያሉት አቶ ገብሩ ገብረማርያም፣ “ጥያቄያችን ከ80 ሚሊዮን ሕዝብ ውስጥ ኢሕአዴጋዊያን ያልሆኑ ለምርጫ ቦርድ ይሥሩ የሚል ነው፤” በማለት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይኼንን የተበላሸ የምርጫ ሥርዓትና አምባገነንነት በመቃወም ከጐናቸው እንዲቆም ጠይቀዋል፡፡
ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎቹ ያቀረቧቸው አቤቱታዎችም ሆኑ ቅሬታዎች በማስረጃ ያልተደገፉና ብዙዎችም በ2002 ምርጫ ማግስት በፍርድ ቤት ሳይቀር መልስ የተሰጠባቸው ናቸው ይላል፡፡ ቦርዱ አሁንም የቀረቡለትን ቅሬታዎች በዝርዝር ካየ በኋላ ማጣራቱን ገልጾ፣ ፓርቲዎቹ አላነጋገረንም የሚሉት ተቀባይነት የሌለው ነው ብሏል፡፡
ቦርዱ ሁሉንም ፓርቲዎች እኩል እያገለገለ እንደሚገኝ አስረድቶ፣ የሚተዳደርባቸው ደንቦችና መመርያዎች በፓርቲዎች ተሳትፎ የወጡ በመሆናቸው ወገንተኛ አድርጎ ማቅረብ ትክክል አይደለም በማለት አስረድቷል፡፡ ምርጫ ቦርድ ከማንም ፓርቲ ጋር የመወገን ዓላማ እንደሌለውና ሕጉም እንደማይፈቅድለት እየተናገረ ነው፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት “ምርጫ ለመድረክ ግንባርነት ዕውቅና ሰጠ” በሚል ርዕስ በወጣው ዜና “… መድረክን የፖለቲካ አጀንዳውንና የገንዘብ አቅሙን በመገምገም ብቁ ሆኖ በመገኘቱ ያቀረበው ጥያቄ በቦርዱ ተቀባይነት ማግኘቱን ወይዘሮ የሺ ገልጸዋል፤” የሚለው ዓረፍተ ነገር ከቦርዱ ሥልጣንና ኃላፊነት ውጪ በመሆኑ በዚህ መሠረት ተስተካክሎ እንዲነበብ እንጠይቃለን፡፡
http://www.ethiopianreporter.com/news/293-news/9048-2012-12-29-11-06-05.html

ፓርላማው የአቶ ጁነዲን ሳዶን ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ ነው


በዮሐንስ አንበርብር
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) በቅርቡ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርነታቸው የተነሱትን የአቶ ጁነዲን ሳዶ ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ መሆኑን ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገለጹ፡፡
የምክር ቤቱ አባል የሆኑ ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አቶ ጁነዲን በፓርላማ የሥነ ሥርዓት ደንብ መሠረት ሊጠየቁበት የሚችል የሕግ ጉዳይ ሊኖር ስለሚችል፣ በምክር ቤት አባልነታቸው ያገኙትን ያለመከሰስ መብት ምክር ቤቱ እንዲያነሳ የሚጠይቅ ደብዳቤ በመንግሥት ቀርቧል፡፡ ጥያቄው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ ወይም በፍትሕ ሚኒስትሩ አቶ ብርሃን ኃይሉ በኩል መቅረብ ያለበት መሆኑን የምክር ቤቱ ደንብ ያዛል የሚሉት እነዚሁ ምንጮች፣ ጥያቄው በየትኛው አካል መቅረቡን ለመረዳት እንዳልቻሉ አስረድተዋል፡፡
ባለፈው ሐሙስ የዓመቱን ዘጠነኛ ስብሰባውን ያካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአምስት አጀንዳዎች ላይ ለመወያየት ፕሮግራም ይዞ የነበረ ቢሆንም፣ በአራቱ ላይ ብቻ ተወያይቶ የቀረውን ላልተወሰነ ጊዜ አስተላልፎታል፡፡
የስምንተኛ መደበኛ ስብሰባውን ቃለ ጉባዔ፣ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረትን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅ፣ እንዲሁም ሁለት የተለያዩ ዓለም አቀፍ የብድርና የትብብር ስምምነቶችን ማፅደቅ በዕለቱ የተወያየባቸውና ውሳኔ ያሳለፈባቸው አጀንዳዎች ናቸው፡፡ በአምስተኛ አጀንዳነት ተይዞ የነበረው “የአንድ የምክር ቤት አባልን የሕግ ከለላ ስለማንሳት የቀረበ የውሳኔ ሐሳብን መርምሮ ማፅደቅ” የሚል ቢሆንም፣ የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ ይህንን አጀንዳ በቀጣይ ስብሰባ ለመመልከት ላልተወሰነ ጊዜ አስተላልፈውታል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት ለጉባዔው የሚቀርቡ አጀንዳዎችን ቀደም ብለው በማወቅ በጉዳዩ ላይ የሚቀርቡ ሰነዶች ካሉ ደግሞ ሰነዶቹ ከውይይቱ ሦስት ቀናት በፊት እንዲደርሳቸው የምክር ቤቱ የአሠራር ደንብ ቢደነግግም፣ የሕግ ከለላን ስለማንሳት ቀርቦ ስለነበረው አጀንዳ የቀረበላቸው ምንም ዓይነት ሰነድ እንደሌለ ምንጮች ተናግረዋል፡፡
የሕግ ከለላው እንዲነሳ ጥያቄ የቀረበበት የምክር ቤት አባል ማንነት በይፋ ባይገለጽም፣ ይፋዊ ባልሆነ መንገድ የአቶ ጁነዲን ሳዶ ጉዳይ መሆኑን እንደተረዱ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
አቶ ጁነዲን ሳዶ በአሁኑ ወቅት በሽብር ተግባር ተጠርጥረው በእስር ላይ ከሚገኙት ባለቤታቸው ወ/ሮ ሐቢባ መሐመድ ጋር በተያያዘ፣ በድርጅታቸው ኦሕዴድ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ተገምግመው ከፓርቲው ከፍተኛ አመራርነት ወደ ተራ አባልነት ዝቅ መደረጋቸው ይታወሳል፡፡
በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በፓርላማ በፀደቀላቸው የሚኒስትሮች ሹመት ደግሞ ከሲቪል ሚኒስትርነታቸው መነሳታቸውን ሪፖርተር ዘግቧል፡፡
SOURCE: http://www.ethiopianreporter.com/

ESAT Kignit Aleweledim tewelede Kignit 29 December 2012 Part 2


Saturday, December 29, 2012

ሰበር ዜና፡ 6ኛውን ፓትርያርክ ለማስመረጥ ለተሾሙት ሰዎች ከሲኖዶስ የተጻፈላቸው ምስጢራዊ ደብዳቤ እጃችን ገባ




(ዘ-ሐበሻ) የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ታኅሣሥ 6 ቀን በዋለው ጉባኤው ለስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ ከሦስት ያላነሱ ከአምስት ያልበለጡ ዕጩ ሊቃነ ጳጳሳት ለውድድር እንዲቀርቡ ወስኗል፤ አስመራጭ ኮሚቴም ተመርጧል ስትል ዘ-ሐበሻ መዘገቧ ይታወሳል። ሆኖም ግን አዲስ አበባ ያለው ሲኖዶስ እንዲህ ያለ ውሳኔ አለመወሰኑን አስተባብሎ ነበር።አሁን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው ከሲኖዶስ የወጣና ለፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴዎች የተጻፈው ደብዳቤ ግን ማን ውሸታም እንደሆነ የሚያጋልጥ ነው ተብሏል። ግን እንዴት ይህ ሁሉ የኦርቶዶክስ ምዕመንን መዋሸት አስፈለገ? ምስጢራዊው ደብዳቤን አይታችሁ ፍረዱ።Holy-sinod
Holy-sinod-1

መንግሥት ለዕርቁ ጉዳይ የሄዱትን ሊቀ ካህናት ኀ/ሥላሴ ዓለማየሁን አስሮ ወደ አሜሪካ ላካቸው


የኢትዮጵያ መንግሥት ዓላማውን ግልጽ አድርጓል፤ እኛው አውቀናል
by Deje Selam on Saturday, December 29, 2012 
የመንግሥት ደጋፊ የጡመራ መድረኮች “አስታራቂ ኮሚቴው” ላይ ዘምተዋል፤
ከጳጳሳቱ መካከል የዕርቁ እንቅፋት የሆኑት አባቶች በግልጽ ታውቀዋል፤ ስማቸውን ከማውጣታችን በፊት አሁንም ሐሳባቸውን ይቀይሩ እንደሆነ እንጠብቃቸዋለን፤
ጉዳዩን ያቀነባበሩት የአዲስ አበባው ልዑክ አባል የሆኑት ን/ዕድ ኤልያስ አብርሃ ናቸው ተብሏል፤
የአዲስ አበባው ልዑክ አባቶች ዲሲ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ከተጠሩ በኋላ ተገደው እንዲፈርሙ ተደርገዋል፤
(ደጀ ሰላም ታኅሣሥ 20/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 29/2012)፦ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ አልገባኹም በሚል ሰሞኑን መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ መንግሥት ለዕርቁ ጉዳይ ከቅ/ሲኖዶስ ጋር ለመነጋገር ወደ አዲስ አበባ የሄዱትን የሰላምና አንድነት ጉባኤውን አባል ሊቀ ካህናት ኀ/ሥላሴ ዓለማየሁን አስሮ ወደ አሜሪካ ከላካቸው ወዲህ ለዕርቁ ያለው የተስፋ ደጅ መዘጋቱ እሙን ሆኗል። መንግሥት የዕርቁ ድርድር ለይስሙላ እንጂ “ከምር” እንዲሆን አልፈለገም ነበር። ነገሩ ከምር ሲሆን ግን “የጭቃ ጅራፉን” መምዘዝ ይዟል። ለዲፕሎማሲ ይጠቅመኛል ብሎ የፈቀደው ዕርቅ መሳካት ሲጀምር ከዲፕሎማሲው ከማገኘው ትርፍ በሩን መዝጋት ይሻለኛል ያለ መስሏል። የራሱን ፓርቲ አባል በፓትርያርክነት ለማስቀመጥ በጠራራ ፀሐይ ወረራውን ቀጥሏል።
በተያያዘ ዜና አስታራቂ ጉባኤው አውግዘው መግለጫ እንዲሰጡ የተገደዱት የአዲስ አበባው ልዑክ አባላት ሐሳባቸውን በግድ እንዲቀይሩ የተገደዱት ወደ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ከተጠሩ በኋላ መሆኑ ሲታወቅ ደብዳቤውን ያዘጋጁት ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ ከኤምባሲው ሰዎች ጋር በመሆን እንደሆነ ምንጮቻችን ገልጸዋል። ሦስቱ ብፁዓን አባቶች ደብዳቤውን ያለውድ በግድ እንዲፈርሙ ሲገደዱ ሐሳባቸውን ላለመቀየር ያንገራገሩት ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ በብዙ ማግባባት ፊርማቸውን እንዲያኖሩ ተደርገዋል ተብሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ መግለጫው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ኢላማ የተደረገው አስታራቂ ጉባኤ በመንግሥት ደጋፊ የግል ጦማሪዎች ሳይቀር በመወገዝ ላይ ይገኛል። “መጀመሪያውኑም ገለልተኛ አልነበረም” የተባለው አስታራቂው ቡድን ከመ-አርዮስ የታየበት ምክንያት ዕርቁን ከግብ ለማድረስ በመቃረቡ ነው።
ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን።

ESAT Daily News Amsterdam 29 December 2012 Ethiopia


በቡሬ ግንባር የሚገኙ እና በግጭቱ ተሳትፈዋል የተባሉ ወታደሮች መሳሪያቸውን እንዲያስረክቡ ታዘዙ


ታህሳስ  ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢሳት ወታደራዊ ምንጮች እንደገለጹት ባለፈው ማክሰኞ ሌሊት በሰራዊቱ መካከል የተፈጠረውን የእርስ በርስ ግጭት ተከትሎ በርካታ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ከሆኑ በሁዋላ ባለፈው ሀሙስ ከመቀሌ እስከ አፍዴራ የተንቀሳቀሱ ወታደራዊ አዛዦች በግጭቱ የተሳተፉት ሁሉ ትጥቃቸውን እንዲፈቱ ማድረጋቸው ታውቋል። በእለቱ ከፍተኛ ግምገማ መካሄዱንም ለማወቅ ተችሎአል።
በአሁኑ ሰአት አንጻራዊ ሰላም መስፈሩን በአካባቢው የሚኖሩ የአፋር ተወላጆች ለኢሳት ገልጸዋል።
በቡሬ ግንባር በሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል ማንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ማክሰኞ ሌሊት የእርስ በርስ ግጭት ተፈጥሮ እንደነበርና ቁጥሩ ከ12 እሰከ 40 የሚደርስ የሰራዊት አባላት መሞታቸውን መዘገባችን ይታወሳል። 15 ወታደሮች በማንዳ ሆስፒታል የሞቱ ሲሆን፣ 12ቱ ደግሞ በሞትና በህይወት መካከል እንደነበሩ መዘገባችን ይታወቃል። በጽኑ የቆሰሉ አዛዦችም ወደ መቀሌ ሆስፒታል ተወስደዋል።
የግጭቱን መንስኤ እስካሁን በትክክል ለማወቅ አልተቻለም። በአካባቢው የተመደቡ የሰራዊት አባላትን ለማናገር ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም ሊሳካልን አልቻለም። በቡሬ ግንባር አካባቢ የሞባይል ስልክ ኔትወርክ ለማግኘት አስቸጋሪ መሆኑን መረጃውን ያደረሱን ምንጮች ገልጸዋል።
ማንዳ ከቡሬ ግንባር 21 ኪሎሜትር የሚርቅ ሲሆን፣ ግጭቱ በትክክል የተነሰባት ቦታ አሊ ፉኑ ዳባ እየተባለ በሚጠራው የጎሳ መሪ ስም በተሰየመ አሊ ፉኒ አካባቢ ነው።

በኢሳት እርዳታ ሳጅን ሽታየ ወርቁ ራሱን ከማጥፋት ተቆጠበ


ታህሳስ  ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከሁለት ቀናት በፊት በደቡብ ክልል በዳዉሮ ዞን በሎማ ወረዳ ገሣ ከተማ ላይ ይደረግ በነበረዉና የሎማ ዲሣ ህዝብ የአዲስ ወረዳ አግባብነት ስብሰባ ላይ የግል አስያየቱን የሰጠዉ የፖሊስ ባልደረባ ሳጅን ሽታየ ወርቁ እራሱን ከምግብ እና ከውሀ ለ24 ሰዓታት ከልክሎ በወጣበት ዛፍ ላይ ራሱን ከማጥፋቱ በፊት ከኢሳት ጋር ተገናኝቶ አላማውን ለህዝብ ይፋ ለማድረግ በመፈለጉ የኢሳት ባልደረቦች በስልክ አግኝተው ራሱን እንዳያጠፋ በመምከራቸው፣ ከድርጊቱ ታቅቦ በፖሊስ ታጅቦ ወደ እስር ቤት ተጉዟል።
ሣጅን ሽታዬ ወርቁ ሺበሺ ከሁለት ቀናት በፊት “ወረዳ አያስፈልግም ካላችሁ ለምን ድሮ ለሲዳማ 9 ለወላይታ 5 እያለችሁ ሸንሽናችሁ ሰጣችሁ በማለት” በስብሰባ ላይ በሰጠዉ አስተያየት ምክንያት በዕለቱ ለስብሳበ የወጡ የወረዳዉ የመንግሥት ሠራተኞች የእርሱን ሀሳብ በመደገፍ ስብሰባዉን አቋርጠዉ በመዉጣታቸዉ ምክንያት ከትላንቱ ስብሰባ የወረዳዉ ፖሊስ አባላት በሙሉ እንዳይገቡ መከልከላቸዉን መግለጻችን ይታወሳል፡፡
ሳጅን ሽታየ በእለቱ ያጋጠመውን ድርጊት በዝርዝር አስረድቷል ።
ሳጅን ሽታየ ራሱን ለማጥፋት የወሰነው በእርሱ እና በቤተሰቡ ላይ የደረሰበት በደል ከሚችለው በላይ ሆኖበት መሆኑን ለኢሳት ተናግሯል ምናልባት ህይወትህን ብታጠፋ መንግስት የአእምሮ በሽተኛ ነህ ሊልህ ይችላልና አእምሮ በሽተኛ ነህ ወይ ተብሎ ለቀረበት ጥያቄ፣ ሙሉ ጤነኛ ሆኖማ ስራውን ችግሩ እስከተፈጠረበት ድረስ ሲሰራ እንደነበር ገልጿል፡፡
የኢሳት ባልደረቦች ሳጅን ሽታየ ራሱን እንዳያጠፋ ለረጅም ሰአት ምክር የለገሱት ሲሆን፣ በመጨረሻም እጁን ለፖሊስ በመስጠት ወደ ዞኑ እስርቤት ተወስዷል።
ረዳት ሣጅን ሽታዬ ወርቁ ሎማ ዲሣ አካባቢ የዲሣን ወረዳ ጥያቄ የሚያንቀሳቅሱ ሦስት ግለሰቦችን እንዲያስር ከዳዉሮ ዞን የፖለቲካ ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ሽመልስ ታምራት መመሪያ ተሰጥቶት ያለ ጥፋት ሰዉ አይታሰርም በማለቱም በዞኑ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ዘንድ ቅሬታ እንደተያዘበት ታውቋል።
የዲሣን ወረዳ ጥያቄ ያንቀሳቅሳሉና መታሰር አለባቸዉ ተብለዉ ከዞኑ ፖለቲካ ሀላፊ ከአቶ ሽመልስ ትዕዛዝ ከተላለፈባቸዉ ግለሰቦች መካከል አቶ አባቴ አሰፋ ፤ አቶ መስፍን ማሞ ፤ እና አቶ ደስታ ቶልባ ይገኙበታል።
በዳዉሮ ዞን የወረዳና ተያያዥ የመብት ጉዳዮች ገፈፋ ጋር በተያያዘ ከመምህር የኔሰዉ ገብሬ ራሱን በቤኒዚን ከማጋየት በኋላ ዓመት ባልተቆጠረ ጊዜ ዉስጥ ከ6 ያላነሱ ሰዎች ራሳቸውን በዛፍ ላይ በመስቀል እና ከገደል ላይ በመወርወር ሞተዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት መተማ ወረዳ አለንጌ በተባለ ቦታ ጥቃት ፈፀመ / የባለራእይ ወጣቶች ማህበር አባላት ጉባኤ እንዳናካሂድ ተከለከልን አሉ


የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት መተማ ወረዳ አለንጌ በተባለ ቦታ ጥቃት ፈፀመ
ታህሳስ  ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ታህሳስ 18 ቀን 2005.ዓ.ም በመተማ ወረዳ ልዩ ስሙ አለንጌ በተባለው አካባቢ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በተካሄደው ውጊያ 8 የጠላት ወታደሮችን ገድሎ 11 በማቁሰል ከፍተኛ የህይወትና የንብረት ኪሳራ ማድረሱን ግንባሩ ገልጿል።
ግንባሩ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን መማረኩንም ገልጿል።
መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ የሰጠው መልስ የለም። ዜናውንም ከገለልተኛ ወገን ለማረጋገጥ አልተቻለም።


የባለራእይ ወጣቶች ማህበር አባላት ጉባኤ እንዳናካሂድ ተከለከልን አሉ
ታህሳስ  ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ብርሀኑ ተግባረእድ እና ምክትል ሊቀመንበሩ ወጣት ሚካኤል አለማየሁ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ጉባኤያቸውን ለማዘጋጀት አዳራሽ ፍለጋ ቢንከራተቱም የጸጥታ  ሀይሎች በሚያደርሱባቸው ተጽእኖ ለመከራየት አልቻሉም።
ወጣቶቹ በመጪው እሁድ ጉባኤ ለማካሄድ የተከራዩትን አዳራሽ፣ የጸጥታ ሀይሎች ባሳረፉት ጫና ሆቴሉ ፈቃደኝነቱን እንደሰረዘባቸው ገልጸዋል።
ሀሳባችንን በነጻነት መግለጽ አልቻልንም የሚሉት ወጣቶቹ፣ ለማን አቤት እንደሚባልም ግራ እንደገባቸው ገልጸዋል
ከወጣቶቹ ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቃለምልልስ በትኩረት ዝግጅታችን መከታተል ትችላለችሁ።

በቡሬ ግንባር የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰራዊት እርስ በርሱ ተዋጋ


ታህሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጡት በቡሬ ግንባር በሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት  አባላት መካከል ማንዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ማክሰኞ ሌሊት የተጀመረው የእርስ በርስ ጦርነት እስከ እኩለ ቀን ዘልቆ እንደነበርና አሁንም ውጥረቱ እንዳለ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።
የእርስ በርስ ጦርነቱ እንደተጀመረ የአካባቢው ነዋሪ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት ጀመሩ በሚል ቀየውን ለቆ የተንቀሳቀሰ ሲሆን፣ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት በሄሊኮፕተር እየተንቀሳቀሱ ጦርነቱን ለማስቆም ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ምንጮቻችን ገልጸዋል።
40 ወታደሮች መሞታቸውን እንዲሁም ከ39 በላይ ደግሞ መቁሰላቸውን ከማንዳ ሆስፒታል የተገኘ መረጃ ያመለካተ ሲሆን፣ ሆስፒታል ሳይደረሱ የሞቱ፣ ወደ መቀሌ ሆስፒታል በሄሊኮፕተር የተወሰዱ ወታደራዊ አዛዦች መኖራቸውንም ለማወቅ ተችሎአል።
ዘግይቶ በደረሰን ዜና ደግሞ 15 ወታደሮች ወዲያውኑ መሞታቸውን ፣ 12ቱ ደግሞ ለሞት ሲያጣጥሩ በአይናቸው ማየታቸውን አንድ ስማቸውም ድምጻቸውም እንዳይተላለፍ የጠየቁ በሆስፒታሉ ውስጥ የሚሰሩ ነርስ ተናግረዋል።
የግጭቱን መንስኤ በትክክል ለማወቅ አልተቻለም። አንዳንድ ወገኖች ግጭቱ በህወሀት ወታደራዊ ባለስልጣናት መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የተነሳ ነው ሲሉ ሌሎች ወገኖች ደግሞ በህወሀት ደጋፊ ወታደሮችና በተቀረው ሰራዊት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ነው ይላሉ።  ኢሳት የግጭቱን ትክክለኛ ምንጭ ለማወቅ ጥረት እያደረገ ነው።
ማንዳ ከቡሬ ግንባር 21 ኪሎሜትር የሚርቅ ሲሆን፣ ግጭቱ በትክክል የተነሰባት ቦታ አሊ ፉኑ ዳባ እየተባለ በሚጠራው የጎሳ መሪ ስም በተሰየመ አሊ ፉኒ አካባቢ ነው። ግጭቱ በዚሁ ስፍራ ይጀመር እንጅ ወደ አራት አጎራባች አካባቢዎች ተሰራጭቶ እንደነበር ምንጮች አመልክተዋል።
ከትናንት በስቲያ እና ትናንት ውጥረቱ እንደነበር ለማወቅ የተቻለ ሲሆን፣ ምናልባትም ግጭቱ እንደገና ሊያገረሽ ይችላል በሚል ስጋት የአካባቢው ሰዎች ቀያቸውን እየለቀቁ ነው።
የቡሬ ግንባር ዋና እዝ መቀሌ የሚገኝ ሲሆን፣ በሰሜን እዝ አዛዥ ጄነራል ሳእረ መኮንን እንደሚመራ ይታወቃል።
ቡሬ ግንባር የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከባድመ ቀጥሎ ሀይሉን በብዛት ያሰማራበት ቦታ መሆኑ ይታወቃል። ኢሳት በቅርቡ በሰሜን ግንባር የተመደበን አንድ የመከላከያ ሰራዊት አባል በማናገር በሰራዊቱ ውስጥ ያለውን ችግር መዘገቡ  ይታወሳል።
በሌላ ዜና ደግሞ በአካባቢው ለሚንቀሳቀሰው የአፋር ጋድሌ ሚሊሺያ ሀይል ወጣቶችን ትመለምላላችሁ የተባሉ የሚሊሺያው ወታዳራዊ አዛዥ የሆኑት የኮሎኔል ሙሀመድ አህመድ 4 የቅርብ ዘመዶች ተይዘው ታስረዋል። በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት መንገሱንና መንግስትም ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ በርካታ ወታደሮችን ማስፈሩን መዘገባችን ይታወሳል።