FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Saturday, December 22, 2012

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአንድነት ልዩ አስተባባሪ ኮሚቴ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ሊያደርግ ነው


በታምሩ ጽጌ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ልዩ አስተባባሪ ኮሚቴ በአገሪቱ ወቅታዊ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ታህሳስ 14 ቀን 2005 ዓ.ም. ውይይት እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአንድነት ልዩ አስተባባሪ ኮሚቴ የውይይቱን መድረክ ያዘጋጀው ከአንድነት ድርጅት ቋሚ ኮሚቴ ጋር በመተባበር መሆኑን፣ የአንድነት ሊቀ መንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ተናግረዋል፡፡
ለውይይቱ መነሻ ሐሳብ የሚሆን “በወቅታዊ የአገሪቱ ፖለቲካ ላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና” በሚል ርዕስ ጽሑፍ በአንድ ታዋቂ ምሁር እንደሚቀርብ ዶ/ር ነጋሶ ገልጸዋል፡፡ ስማቸውን ለመግለጽ ግን ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ በውውይቱ ላይ በመላው አገሪቱ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራንና ተማሪዎች እንደሚሳተፉና ታዋቂ የፖለቲካ ሰዎችም እንደሚገኙ ሊቀመንበሩ ጠቁመዋል፡፡
ሌላው ዶክተር ነጋሶ ያስረዱት፣ ከአንድ ዓመት በላይ የአንድነት የሕዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበሩት አንጋፋውና አዛውንቱ ዶ/ር ኃይሉ አርዓያ በሌላ ወጣት የፓርቲው አባል መተካታቸውን ነው፡፡ ዶ/ር ኃይሉ ለእረፍት ወደ አሜሪካ በተጓዙበት ወቅት ባደረጉት የሕክምና ምርመራ እረፍት እንደሚያስፈልጋቸው ስለተነገራቸውና በሕመም ምክንያት ከኃላፊነታቸው በፈቃደኝነት መልቀቅ እንደሚፈልጉ ለፓርቲው ባመለከቱት መሠረት በሌላ ሰው መተካታቸውን ዶ/ር ነጋሶ ገልጸዋል፡፡
በፓርቲው የሥራ አስፈጻሚ አባላትን የሚመለምለውና ለምክር ቤቱ በማቅረብ የሚያፀድቀው ሊቀ መንበሩ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ነጋሶ፣ እሳቸውም ወጣት፣ ትኩስ ኃይልና በሳል ነው ያሉዋቸውን አቶ ዳንኤል ተፈራን አቅርበው ምክር ቤቱ ይሁንታ እንደሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም አቶ ዳንኤል ከታህሳስ 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ የሥራ አስፈጻሚ አባልና የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ሆነው መሰየማቸውን አስታውቀዋል፡፡
አቶ ዳንኤል የተሾሙበትን ኃላፊነት አቶ ስዬ አብርሃ ይዘውት የነበረ ቢሆንም፣ ለትምህርት ወደ አሜሪካ ሲሄዱ በሽብርተኝነት ወንጀል ዕድሜ ልክ ተቀጥተው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ አንዱዓለም አራጌ ተረክበው ነበር፡፡ አቶ አንዱዓለም ሲታሰሩ ደግሞ ዶ/ር ኃይሉ አርዓያ ተሹመው ሲሠሩ መቆየታቸው ታውቋል፡፡ አቶ ስዬ አስፈቅደው ስለሄዱና አሜሪካ አንዳንድ የሚጨርሷቸው ጉዳዮች ስላሏቸው በጨረሱ ጊዜ መመለስ እንደሚችሉ ዶ/ር ነጋሶ አስታውቀዋል፡፡

No comments:

Post a Comment