FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Tuesday, December 25, 2012

የኢትዮ ኤርትራ ዲፕሎማቶች ኒዮርክ ላይ የቃላት ጦርነት ገጠሙ


Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8  ሰዓት በ1340 ኤ.ኤም  የአየር ሞገድ ያዳምጡ። በስልክ ለማዳመጥ  610-214-0200 አክሰስ ቁጥር 729369#
የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ታህሳስ 14 ቀን 2005 ፕሮግራም
<…ከሶማሊያ ወደብ ወደ የመን ለመሻገር የሞከሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በአንዳንድ ህገ ወጥ አሻጋሪዎች ሆን ተብለው ባህር ውስጥ እንዲሰጥሙ የሚደረገው በተደጋጋሚ ነው።ሚዲያዎች ግን ለጉዳዩ ትኩረት አልሰጡትም።…> ጋዜጠኛና ደራሲ ዳንኤል ገዛኸኝ ሰሞኑን ወደ የመን በጀልባ ለመሻገር የሞከሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በአሻጋሪዎቻቸው ባህር ላይ እንዲሰጥሙ የተደረገበትን አሳዛኝ ክስተት በተመለከተ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ ሙሉውን ቃለ  ቃለ መጠይቅ  ያዳምጡ
<<…ይሔ መንግስት ዘላለማዊ አይደለም። …ቤተ ክርስቲያኑዋ ቀጣይ ናት።ቀጣኢ የሆነውን የቤተ ክርስቲያኑዋን ታሪክ ጊዜያዊ ከሆነው ነገር ጋራ አብሮ መጓዝ አስፈላጊ አይደለም።አባቶች ትክክለኛ አባት የሚሆኑትና የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያከብራቸው ለቤተ ክርስቲያኑዋ ዓላማ ሲቆሙ ነው።….>> ብጹዕ አቡነ  ዮሴፍ የኔቫዳ፣የሀይዳሆና የአሪዞና ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ ም/ዋና ጸሐፊ የአዲስ አበባው ሲኖዶስ አንዳንድ አባላት የሕዝበ ክርስቲያኑን ጥያቄ ወደ ጎን በማድረግ በጥድፊያ ጳጳስ ለመሾም የሚያደርጉትን እርምጃ እንዲያቆሙ ከጠየቁበት (ከህብር ጋር ያደረጉትንሙሉውን ቃለ መጠይቅ ያዳም )
ዜናዎቻችን
የኢትዮ ኤርትራ ዲፕሎማቶች ኒዮርክ ላይ የቃላት ጦርነት ገጠሙ
አላሙዲ ያልሰሩበት መሬት ከአዲስ አበባ ይወሰዳል መባልን ተከትሎ ሰሞኑን ባለስልጣናት ቢሮ ጎራ ብለው ነበር
በህቡ ያሉት የሙስሊሙ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴ መሪዎች ለትግሉ ይጠቅማል ያሉትን ግምገማ ማጠናቀቃቸውን ገለጹ
የታሰሩት የሕዝብ ተመራጭ መሪዎች በቃሊት ሆን ተብሎ ከአእምሮ በሽተኛ ጋር እንዲተኙ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
በትጥቅና በሰው ሀይል የተደራጀ የግንቦት ሰባት ሕዝባዊ መመስረቱን ይፋ አደረገ
ከሶማሊያ ወደ የመን በጀልባ ሊሻገሩ የሞከሩ ኢትዮጵያውያንና ሶማሊያውያን ስደተኞች በአሻጋሪዎቻቸው ወደ ባህር መጣላቸው ተነገረ
ሰሞኑን 138 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በታንዛኒያና በማላዊ ታስረዋል
 እና ሌሎችም ዜናዎች አሉን
 በአሜሪካ የህጻናቱን እልቂት ያስከተለውን ግድያና ተከትሎት  የመጣውን የመሳሪያ ላይ ገደብ ይደረግ ሰፊ ክርክር ላይ ትንታኔ
ከአቶ ተመስገን ዘውዴ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ የውጭ ግንኙነት ሀላፊና የመድረክ የአመራር አባል ጋር የተደረገ ሁለተኛ ክፍል ቃለ መጠይቅ ይዘናል  https://soundcloud.com/user39134184/hiber-radio-122312
maledatimes.com

No comments:

Post a Comment