FREE ALL POLITICAL PRISONERS

FREE ALL POLITICAL PRISONERS
FREE ALL POLITICAL PRISONERS

Friday, December 28, 2012

በሰሜን ሸዋ ነጋዴዎች ስብሰባዎችን ረግጠው ወጡ


ታህሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ከታህሳስ 17-18 በተጠራ ስብሰባ ላይ የተገኙ ነጋዴዎች ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸው ታውቋል።
ስብሰባውን ከ6 ወረዳዎች የተውጣጡ ነጋዴዎች የተሳተፉበት ሲሆን፣ መንግስት በአግልግሎት ክፍያ፣ በግብርና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ እንደሚያወያይ ጥሪ አስተላልፎ እንደነበር ነጋዴዎች ገልጸዋል።
ይሁን እንጅ ባለስልጣናቱ አጀንዳውን በመሰረዝ የትራንስፎርሜሽን እቅዱን እንዴት ተግባራዊ እናድርግ የሚል አጀንዳ ይዘው በመምጣታቸው ነጋዴዎች በሙሉ ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸው ታውቋል።
ነጋዴዎች በመጀመሪያ ” የእኛን ችግር ተረዱልን፣ መንግስት ከህዝብ ችግር ይልቅ የራሱን አጀንዳ አያስቀድም” በሚል ውዝግብ መነሳቱንና ስምምነት ላይ ለመድረስ ባለመቻሉ ነጋዴዎች ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል።
ስብሰባውን ረግጠው ከወጡት መካከል የካራቆሬ ከተማ ነጋዴዎች፣ የአጣየ ከተማ ነጋዴዎች እና የአንጾኪያ ከተማ ነጋዴዎች ይገኙበታል።
ኢሳት በአማራ ክልል ተመሳሳይ ስብሰባዎች መካሄዳቸውን፣ ነጋዴዎችም በስብሰባው ምንም መፍትሄ ሳያገኙ መቅረታቸውን ከተለያዩ አካባቢዎች ከደረሱት ዜና ለማወቅ ተችሎአል።

No comments:

Post a Comment