ሰሞኑን በሙስሊሙ ማኅበረሰብና በመለስ ዜናዊ የሙት መንፈስ በሚታዘዘው የወያኔው ሥውር (abstract) መንግሥት መካከል የጦፈ ግጭት እንዳለ ይወራል፡፡ ይህም የሚደመጠው ድረገጾቻችንን ጨምሮ ኢሣትን ከመሳሰሉ ከሀገር ውጪ ከሚገኙ የዜና ማዕከላት እንጂ በሀገር ቤቱ የወያኔ የውሸት ወፍጮማ ሁሉም ሰላም እንደሆነ ነው ሰርክ እየተደሰኮረ ያለው፡፡
ይህ ሃይማኖትን ተመርኩዞ የተቀሰቀሰ ግጭት ወዴት ሊያመራ እንደሚችል መጨረሻው ወደፊት የሚታይ ሆኖ በተለይ ስለእስልምናና ክርስትና ሃይማኖቶች (በኢትዮጵያ) ትንሽ ነገር መናገር እፈልጋለሁ፡፡ ግጭቱ የሃይማኖት ሳይሆን የመብት ረገጣ የወለደው የአትንኩኝ ባይነት ትግል መሆኑን አምናለሁ፡፡ ወያኔ ዜጎችንና ጦርነትን በቆረጣ መግጠሙ ዛሬ የጀመረው አይደለም፡፡ ጠላቶቹ ተቆጥረው አያልቁም፤ የሚገጥምበት ሥልት ግን በተራና በቆረጣ ነው፡፡ ይህን የተበላ ዕቁብ ሕዝበ ክርስቲያንና ሕዝበ ሙስሊም ካልነቃበት ራሱ ያልቅበታል፡፡ ወያኔ ተንኮለኛ ነው፡፡ ሃይማኖት የለውም፡፡ ሃይማኖት አለን የሚሉ ወገኖችን ግን እርስ በርስ ሊያባላቸው የአንዱ ዕንባ አባሽ መስሎ አንዱን ከሌላው ሊያጋጭ ይሞክራል፡፡ ሞኝ ካገኘ ይሳካለታል፡፡ ከተነቃበት ግን ራሱ ያልቅለታል፡፡ ይህን ነው ሁሉም ሕዝብ መረዳት ያለበት፡፡ በየተራ ማለቅ ነው የሚጠቅመው ወይንስ ተባብሮ የጋራ ጠላትን ልኩን እንዲያውቅና መብትን መርገጥን እንዲያቆም ማድረግ? ምርጫው የምዕመናን ነው፡፡
እንደደራሲ ሰርቫንቴስ የምናብ ፍጡር እንደዶን ኪሾት የሚመሰለው ወያኔ ይህን ሙስሊሞችን ጥያቄ በቀላሉ ሊመልሰው ሲችል ተፈጥሮው ከሁሉም ነገሮች ጋር(ሕይወት ካለውም ከሌለውም ጋር) የመጋጨት እንጂ ሰላምን የመፍጠር ባለመሆኑ ይሄውና የራሱን መቃብር እየቆፈረ ይገኛል፡፡ ወያኔ ሰዓት ስንት እንደሆነ እንኳ ቢጠየቅ – እንደተቋም – “ሰዓት መጠየቅ እንደአካሄድ ትክክል ሞሆን አለሞሆኑ አነጋጋሪነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ነገር ግን ማን ነው ሰዓት ጠያቂው? የግንቦት ሰባት አባል ነው ወይንስ የመድረክ? ለምን ዓላማ? ሰዓት ጠያቂው ሰዓት መጠየቅ ከሽብርተኝነት ጋር ቁርኝት ሊኖረው እንደሚችል ያልተገነዘበበት ምኽኒያቱ ምንድነው? ሰዓት የተጠየቀው ለሽብር የሚጠመድን የ‹ሠ› ሰዓት ፈንጂ ለማስተካከል አለሞሆኑ እስኪረጋገጥ ሰዓት ጠያቂውና ዘመድ ወዳጆቹ በቁጥጥር ሥር ውለው ከተጣራ በኋላ ሰዓቱ ሊነገረውም ላይነገረውም ይችላል…” ሊል ይችላል – ሰዓት መጠየቅም በወያኔ ቤት ቁም ነገር ሆኖ፡፡ ስለዚህ ወያኔን ምንም ነገር መጠየቅ በሽብርተኝነት ሊያስጠረጥር፣ ሊያስከስስና በታዛዥ ዳኞች – በሰው መሰል የወያኔ ሮቦት ዳኞች – ዕድሜ ይፍታህ ወይም የስቅላት ሞት ሊያስበይን የሚችል አደገኛ ወንጀል ነው፤ ‹ራበኝ አጉርሱኝ፣ ጠማኝ አጠጡኝ፣ ታረዝኩ አልብሱኝ፣ ዘቀዘቀኝ አንተርሱኝ፣ መንገድ አሳዩኝ …› በወያኔ በአሸባሪነት ሊያስጠረጥሩ የሚችሉ ‹ወንጀሎች› ናቸው፤ ይህ ዓይነት ዕንቆቅልሽ ፍጡር ለግማሽ ምዕተ ዓመት በሕይወት መኖሩ በራሱ በርግጥም ያስደንቃል – በድንቃ ድንቅ ታሪኮች መዝገብም ሊሠፍር ይገባዋል፡፡ ወያኔ እኮ በማሰብህም የሚከስህ የመጀመሪያው የዓለማችን ጉድ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ሀገራቸው ደግሞ በነጻነት መናገር እንደቅንጦት የሚቆጠር ሆኖ እንዲሁ ማሰብም መብላት መጠጣትም የማይቻልባት የመጀመሪያዋ ሀገር ናት – ለኢ-ወያኔያዉያን ነው ታዲያ፡፡ ኢ-ወያኔነት ደግሞ በእውነተኛ ኢትዮጵያዊነት የሚያገኙት የሚከብድ ሸክም እንጂ በዘርና በሃይማኖት ተፈጥሯዊና የግል ጉዳዮች የሚወሰንና ለተመረጡ ብቻ የሚሰጥ ምንዳ አይደለም፡፡ ከዚህ አኳያ ሙስሊሙም፣ ክርስቲያኑም፣ አማራውም፣ ኦሮሞውም፣ አደብ ካልገዛና የወቅቱን በረከተ መርገም ከአሌታዊው(ዘረኛ) ሥርዓት ተለጥፌ ከርሴን አልሞላም ብሎ ከቆረጠ ትግሬውም ጭምር ከዚህ ወያኔያዊ የጭካኔ በትር አያመልጡም – አብዮት ልጆቿን የመብላቷ መዝሙር በደርግ ዘመን ብቻ ተቀንቅኖ አልቀረም፡፡ ወያኔን ያልመሰለና ያልሆነ አሣር ይደርስበታል፡፡ በምንም ሁኔታ ተከፋፍሎ መገኘት ለወያኔው ዱላ ይበልጥ ምቹ መሆን ነው፡፡ አለመተባበር መሰባበርን እንደሚያስከትል ዶክተር መረራ አስቀድመው አስታውቀዋል- ለሚገባው፡፡ ግን ግን አፍዝ አደንግዟን ማን ወንድ ይፍታት! ለነገሩ ከላይ የመጣው ከላይ ካሉት ፍትሃቱን ጀምሯልና ዋናው መታገስ ነው – ‹እናያለን ገና› ብሏል አቀንቃኙ፡፡ በጊዜ የተመለሰ ብቻ ይድናል፡፡
ይህ በእንዲህ እያለ ነው እንግዲህ ሙስሊሞች መብታችን ይከበር ሲሉ ክርስቲያኑ ፀጥ ረጭ ብሎ የሚታየው፡፡ ሁለቱም መታረዳቸው የማይቀር በጎች ናቸው – የገናና የፋሲካ በጎች፡፡ ነገር ግን የፋሲካው አንድ ሦስት ወሮች ያህል ዕድሜ ስላሉት እየታረደ ባለው የገናው በግ ይስቃል ይባላል – በምሳሌያዊ አነጋገሩ፡፡ ለነገሩ በግ ባኣኣ ይላል እንጂ አይስቅም፡፡ እኛም ክርስቲያን ነን የምንል ወገኖች እየሳቅን ሳይሆን ባኣኣ ባንልም ዕርዱ እንደማይቀርልን ተገንዝበን በማጉረምረም ላይ የምንገኝ የወያኔ ጭዳዎች ነን፡፡ ዝምታ ድጋፍን ሳይሆን በአብዛኛው ተቃውሞን እንደሚጠቁም መገንዘብ ተገቢ ነውና የቁርጡ ሲመጣ ሙስሊሞች አጋዥ የለንም ብለው እንዳይሰጉ ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡ ይልቁናም ሁለቱም ሃይማኖቶች መጠንቀቅ የሚገባቸው በውስጣቸው የሚገኙ የሁለት ጫፍ አክራሪዎችን ነው – ትልቁ መጥፎ ነገር ዘመድ መስሎ የሚቀርብ ጠላት ነው፡፡
የአክራሪነትምንጭ ደግሞ የተወሳሰበ ነው – ያንተ ‹አክራሪ›ና የኔ ‹አክራሪ› የኛ አለመሆናቸውን ምናልባትም ከጋራ ጠላታችን የተላኩና በውስጣችን የሠረጉ ምንደኞች መሆናቸውን የምናውቅበት መንገድ ለሰላምና ለብዙኃን ድምጽ አንገዛም ያሉ እንደሆነ ነው፤ ‹አጭበርባሪ አይተኛኝም› ያለችዋን የሴተኛ አዳሪዋን ምሳሌ መቀበል ከብዙ ጉዳት ይሠውራልና ጠንቀቅ እንበል ጎበዝ፡፡
አክራሪነት በየትኛውም ሁኔታ ጎጂና አፍራሽ ነው፡፡ አክራሪ ክርስቲያን ይጠንቀቅ፤ አክራሪ እስላምም ይጠንቀቅ፡፡ አለበለዚያ ያከረሩት ነገር ሲበጠስ ከነአክራሪው ነው ገደል የሚከተው፡፡ አክርሮ ዘወር የማይባልባቸው ሁኔታዎች አሉ፡፡ ሁልጊዜ ጌትነት የለም፡፡ … ወያኔን ስለምናውቅ በሌሎች መጨፍጨፍ የምንደሰት ጤናማ ዜጎች በመካከላችን አንኖርም፡፡ ግን የወያኔ ፕሮፓጋንዳና ለዘመናት የተረጨብን ፍርሀትን የሚያነግሥ የሀሰት ቱሪናፋ እንዲሁም ከደርግ ጀምሮ የወረደብን የልጆቻችንን ሬሣ ሳይቀር ከመንግሥት የመግዛት አረመኔያዊ ድርጊት ሰንገው ይዘውን አንዳችን የአንዳችንን መከፋት ተከትሎ ብቻም ሳይሆን እኛ ራሳችን እየተገረፍንም ቢሆን ላለመጮህና ተቃውሞኣችንን ላለማሰማት የማልን እንመስላለን፡፡ እንጂ ይህ ወቅት ሃይማኖትና ብሔር ሳንል ሁላችን በህብረት ‹ሆ› ብለን በመውጣት ይህን አናቱ ተቆርጦ የተጣለ የቀትር እባብ ወያኔ ቆራርጠን የምንጥልበት ዘመን ነበር፡፡ መቆራረጥ ሲባል ሥጋዊ ትርጉም ሳይሆን መንፈሳዊ ፍቺን እንዲይዝልኝ እወዳለሁ፡፡ መቆራረጥ ክፉ ሃሳብን ነው – አካልን አይደለም፡፡ አካል ቢቆረጥ አካልን ይተካል፡፡ ክፉ አስተሳሰብ ከተቆረጠና ከተወገደ ግን የወደፊቱ ትውልድ ከመሰል ዕኩይ ፍልስፍናና ጠማማ አስተሳሰብ ይድናል፡፡ መቆራረጥ የሚለያየንንና የሚከፋፍለንን የወያኔን የዘውገኛነት ልክፍት ነው፤ መቆራረጥ ሀገርንና ሕዝብን ለከፋ ችግር የሚዳርግ የወንድሞቻችንንና የእህቶቻችንን የሆድ አምላኪነት የአስተሳሰብ ደዌ ነው፡፡
በኢትዮጵያ እስልምናና ክርስትና በሰላም ኖረዋል፡፡ የሃይማኖቶች በሰላምና በፍቅር የመኖር አርአያ ኢትዮጵያ ናት፡፡ በአንዳንድ ወቅቶች በዚህ ወያ በዚያ ሃይማኖት ተከታይ ምክንያት አንዱ በሌላው ላይ የሚያደርስውን ጉዳት ከታሪክ ማኅደር ማስታወስ ይቻላል ፤ ግን የግጭትን ታሪክ እያስታወሱ የሻረ ቁስልን ከማንቆርና ቂም በቀልን ከማጫር ይልቅ ያሳለፍናቸውን የፍቅርና የደስታ፣ የመተሳሰብና የመተዛዘን ገጽታዎችን እያወሱ ተንኮለኞች ከቀደዱልን የጥፋት ቦይ መውጣት ነው የሚበጀን፡፡ አንድ መታወቅ ያለበት ነገር አለ፡፡ የአንድን ሰው ወይም የአንድን ማኅበረሰብ ሃይማኖታዊና ዘውጋዊ ማንነት በተመለከተ በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ ንጹሕ ዘርና ንጹሕ ሃይማኖት የሚባል ነገር በጭራሽ የለም፡፡ በዘመናት የአብሮነት ሕይወት ምክንያት ሁሉም ተባዝቆ ተባዝቆ ተቀላቅሏል፤ አንዱን ከሌላው ለመለየት በሚያስቸግር ሁኔታ ተዋህዷል – የኔን ብነግራችሁ ትገረማላችሁ፡፡ አንድ ወቅት የአፋሩ መንፈሳዊና አስተዳደራዊ አባት አሊሚራህ እንዲህ አደረጉ አሉ፡- ሁሉም ሰው በዬሽብራሩ ወተት እንዲያመጣ አደረጉ፡፡ ሁሉም ያመጣውን ወተት ወደ አንድ ትልቅ ማጋቢያ እንዲገለብጥ አዘዙ፡፡ በኋላም ሁሉም ሰው ከዚያ የወተት ጋን ውስጥ የራሱን ወተት እየለዬ ባመጣበት ሽብራር መልሶ እንዲወስድ አስታወቁ፡፡ ሰው ሁሉ በአግራሞት ተጨንቆ “እንዴ! እንዴት ይታወቃል? ተደበላልቆ የለም እንዴ አባታችን?” ብሎ ይጠይቃቸዋል፡፡ ያም ብልሁ የሀገር አባት “የኢትዮጵያ ሕዝብም እንደዚህ ነው! ሁላችንም ስለተዋሃድን አንዳችንን ከአንዳችን ለመነጠል አይቻልም” በማለት ሕዝባቸውን በጉልበትና በዐዋጅ ከጋጋታ ሳይሆን በጥበብ አስተማሩ፡፡ የኢትዮጵያን ባንዴራ እንኳን አፋሮች ግመሎቻቸው እንደሚያውቋት የመሰከሩትም ያን ጊዜ ነው፡፡

ዶክተር ብርሀኑ በትናንቱ ቃለ መጠይቅ (እንዴት ያለ ግሩም ቃለ መጠይቅ ነበር!) እንዳለው ከሞላ ጎደል በሁላችንም ቤት እስልምናና ክርስትና አሉ – እንዲያውም ከነዚህም በላይ፡፡ የሃይማኖት ውርርሱ በጋብቻ ወይም በትውልድ ሐረግ ከአባት እናት የተወረሰ ወይም በማወቅና በይሁንታ ከአንዱ ወደ ሌላኛው በመዛወር የተገኘ ሊሆን ይችላል፡፡ በየትም ይምጣ ዋናው ነገር ግን የሃይማኖት ጉዳይ የግል እንጂ የሀገር አይደለም፡፡ ሁሌ እንደሚባለው ሀገር የጋራ ናት፡፡ ሃይማኖት ግን የግል ነው፡፡
በአንድ ቤት ውስጥ አምስትም አስርም ሃይማኖት ሊኖር ይችላል፡፡ በአንድ ቤት ውስጥ ግን አምስትም አስርም ሀገር ሊኖር አይችልም፡፡ ስለዚህ የማይቀላቀልን ነገር ማቀላቀል ለብንም፡፡ ቅድሚያ መስጠት ላለብን ቅድሚያውን እንስጥ፡፡ ዋናው ነገር ሃይማኖትም ሆነ የራሳችን ኅልውና ሊኖረን የሚችለው በቅድሚያ ሀገር ስትኖረን ነው፡፡ ሀገር ሊኖረን የሚችለው ደግሞ የግልና የቡድን ነጻነታችንን የሚያከብር ቢቻል በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ራሳችን የምንመርጠው ባይቻል እንኳን የልብ ትርታችንን የሚያዳምጥ ከእኛው የወጣ እኛኑ የመሰለ ሀገርና ዜጋ የማይሸጥ እንደመለስ ያለ ወፍዘራሽ የርግማን ውጤት ሳይሆን ሀገር በቀል የሆነ መሪ ሲኖረን ነው – እንደኃይለማርያምም የራሱን ማንነት ለመናኛ ጥቅም ያልለወጠ - እንደኤሳውም በምሥር ብኩርናውን ያልሸጠ፡፡ ዴሞክራሲ እዬዬም ሲዳላ ነው እንዲሉ ነው፡፡ ቀድሞ የመቀመጫዬን ብላለች ዝንጀሮ፡፡ አሁን እኮ ብዙዎቻችን ጨካኙን መንግሥቱ ኃይለ ማርያምን ሳይቀር እየናፈቅን ነው – አትታዘቡኝ እኔ መንግሥቱን መናፈቅ ከጀመርኩ ቢያንስ ሰባት ዓመት አልፎኛል፡፡ መንግሥቱ እኮ ሥልጣኑን አትይበት እንጂ ከመሬት ተነስቶ የ‹ዐይንህን ቀለም› እያየ ሞትና እሥራት ርሀብና ሥቃይ አያዝብህም ነበር – እንዴ፣ መንጌ እኮ በጭካኔው ካባ ሥር የነበረው የሀገር ፍቅርና የሕዝብ ወገናዊነት እንዲህ በቀላሉ የሚታይ አልነበረም፤ ሰውን መጥላትም ሆነ ማፍቀር በፈርጅ በፈርጁ እንጂ ሕጻኑን ከነታጠበበት ቆሻሻ ውኃ መድፋት ተገቢ አይመስለኝም(አንድ የኦሮምኛ አባባል ትዝ አለኝ፡- ‹አህያ እረዱ ቢሉን አህያ አረድን፣ አይጠቅማችሁም ቢሉን ጠራርገን ጣልን፣ እንዴ – ይጠቅማችሁ ነበር እኮ ቢሉንና ሄደን ብንፈልገው አጣነው› ይላል ይህ ቆንጆ ብሂል፡፡ አሁን መንጌን የት እናግኘው?(አቤት – ብዙ ሰው ሲንጫጫብኝ ታየኝ!)፡፡ ሰው የሚመሰገነው አንድም ሲሞት አንድምሲለይ የሚባለው አውነት ነው፡፡ የራሳችንን ጨካኝ እንደዋዛ ሸኝተን አሁን የሰው ዘመሚትና ተምች አንበጣና የዓሣማ ግሪሣ በላያችን ላይ አነገሥን፡፡ ሰበቡ እኛ አይደለንም፤ ደግሞም እኛው ነን፡፡ የዘመን ዕንቆቅልሽ፡፡

እስላምና ክርስቲያን አንድ ነን አንድ አይደለንም ቅብጥርሶ የሚለው ክርክር ለተመቸው ነው፡፡ እኛ እሾህ ላይ ቆመን፣ የሲዖል እሳት ላይ ተቀምጠን የምንገኝ ዜጎች በመሆናችን ቢያንስ በአንድ የሥቃይ ቋት ውስጥ ገብቶ እንደሚወቀጥ የጋራ ዕጣ ተቋዳሽ ራሳችንን በመቁጠር በተናጠል ላለማለቅ በጋራ የጋራ ጠላታችን ላይ እንነሳ እላለሁ፡፡ ወያኔ የዘራብንን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ከቁብ አንጣፈው፡፡ መጀመሪያ ሀገር ትኑረን፤ ሀገር እንዲኖረን በማድረጉ ሂደት ጎን ለጎን የዴሞክራሲያዊ መንግሥት ምሥረታ በሚመለከታቸው የሀገሪቱ ልሂቃን ይሠራ፡፡ ከእንግዲህ ወዲያ ቀጣፊና አጭበርባሪ ወደሥልጣን የማይመጣበት አስተማማኝ የሕግ መደላድል በሀገራችን እንዲፈጠር ሁሉም ወገን ከዘርና ከሃይማኖት ግላዊ ጉዳዮች ተቆጥቦ በጋራ የኅልውና ማስጠበቂያ አውታሮች ላይ ይረባረብ፡፡ ታማኝ በየነን ጆሮ እንስጠው፡፡ ዛሬ ጧት ያዳመጥኩት የዛሬ ዓመቱ ንግግሩ አንጀቴን ነው የበላው፡፡ ለመቃወም ሲባል የተፈጠረ ሰው ካልሆነ በስተቀር ያን ንግግሩን መቼም የሚቃወም ሰው የሚኖር አይመስለኝም፡፡ ስለዚህ ድል ማለት አንዱት ትቶ ሌላውን አንስቶ ነውና ግላዊ ጉዳዮችን ወደጎን እየተውን አንድ በሚያደርጉን ነገሮች ብቻ እንሰባሰብ፡፡ ያን ባናደርግ ተጎጂዎቹ እኛ ስንሆን ተጠቃሚዎቹ የጋራ ጠላቶቻችን ወያኔና መሰል የሀገር ውስጥና የሀገር ውጪ ጠላቶቻችን ናቸው፡፡ ጨው የሚጣፍጠው በጨውነቱ እስከቆዬ ድረስ ነው፡፡ ጨው ድንጋይ ነበር፤ ድንጋይም ጨው ነበር፡፡ ምርጫው የጨውና የድንጋይ ነው፡፡ ይህን ነባራዊ እውነት ዕንወቅ – ወቅቱን ጠብቆ ጨውም ጨው ድንጋይም ድንጋይ ይሆናሉ፡፡ የጭንቅላት ሥጋ መብሰሉ ለማይቀረው እሳት ይፈጃል ይባላል፤ የኢትዮጵያ ጠላቶችም መቸ(ሸ)ነፋቸው ለማይቀረው ብዙ ‹ትግስት›ን እየጨረሱብንና ውድመትን እስያከተሉብን ተቸገርን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን ይባርክ!አላሁዋክበር! (እግዚአብሔር ታላቅ ይሁን!(ነው!(?))
እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን ይባርክ!አላሁዋክበር! (እግዚአብሔር ታላቅ ይሁን!(ነው!(?))
ይድረስ ለእስልምናና ክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች
ይሄይስ አእምሮ(yiheyisaemro@gmail.com)
No comments:
Post a Comment